2013 ኦክቶበር 14, ሰኞ


፴፪ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ዓመታዊ ስብሰባ ተጀመረ

His Holiness Abune Mathias on the 32nd SGGA
ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ የአጠቃላይ ጉባኤው ርእሰ መንበር
  • የቃለ ዐዋዲው ድንጋጌ በፍርድ ቤቶች ያለው ተቀባይነት ማነስ ያስከተለው ችግር፣ ልዩ እምነት ያላቸው አንዳንድ የመንግሥት ባለሥልጣናት በቤተ ክርስቲያን ላይ የሚያደርሱት ሕገ መንግሥቱን የጣሰ ተጽዕኖ፣ ወደ ዐረብ አገሮች እየሔዱ እምነታቸውን ወደ እስልምና የሚለውጡ ኦርቶዶክሳውያን ቁጥር መበራከትና ከእኒህም የካህናት ሚስቶች መኖራቸው፤ የአብነት ት/ቤቶች ህልውና ቀጣይነትና በተለይም የመጻሕፍተ ሊቃውንት ጉባኤያት በብዛት መታጠፍ፤ የመንፈሳዊ ኮሌጆች አስተዳደር፣ የደቀ መዛሙርቱ ምልመላና ምደባ፤ በጠረፋማ አህጉረ ስብከት የአብያተ ክርስቲያን መራራቅ፣ በበጀትና በካህናት እጥረት ለችግራቸው ቶሎ መድረስ አለመቻልና የብዙዎቹ መዘጋት፣ በሰሜን ጎንደርና ቦረና አህጉረ ስብከት የአስተዳደር ችግራቸው ያልተፈታላቸው አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን የአህጉረ ስብከቱን 20 በመቶ ፈሰስ አንከፍልም ማለታቸው፣ ባልታወቁ ሰዎች የአብያተ ክርስቲያን መቃጠል፣ የቤተ ክርስቲያን ይዞታዎች (ዐደባባዮች፣ መካነ መቃብሮች፣ የልማት ቦታዎች) መደፈርና ወደ ግል የማዞር ችግር ጉባኤውን እያወያየ ነ፡፡
  • ‹‹የቤተ ክርስቲያን ቀዳሚ ሀብቶች ምእመናን ናቸው፡፡ ብዙ ገቢ ማፍራታችን እሰየኹ ሊባል የሚገባው ቢኾንም ምእመናንን በማብዛት በኩል የተሠራው ሥራ አመርቂ አይደለም፤ የሰበካ ጉባኤያት ዋናው ትኩረት ከገንዘብ ይልቅ በገንዘብ ባለቤቶች ምእመናን ላይ መኾን ይኖርበታል፡፡›› /የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ/
Abune Mathewos presenting annual report
ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ አቡነ ማቴዎስ የ፳፻፭ በጀት ዓመት አጠቓላይ ሪፖርት ሲያቀርቡ
  • ኀምሳ አህጉረ ስብከት በ፳፻፭ ዓ.ም. ከገቢያቸው ለጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ፈሰስ ያደረጉት 35 በመቶ ከ89 ሚልዮን ብር በላይ ደርሷል፤ ከእዚህ ውስጥ 55‚256‚651 ብሩ የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ለመንበረ ፓትርያርኩ ያስገባው ነው፡፡ ኀምሳው አህጉረ ስብከት በበጀት ዘመኑ ለመንበረ ፓትርያርኩ ፈሰስ ያደረጉት የአጠቃላይ ገቢያቸው 35 በመቶ ፈሰስ ከ፳፻፬ ዓ.ም የፈሰስ መጠን ጋራ ሲነጻጸር የታየው ጭማሪ 27‚273‚309 ያህል ነው፡፡ የፈሰሱ መጨመር አጠቃላይ የገቢ ዕድገትን ቢያሳይም የመንበረ ፓትርያርኩ የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ የሒሳብ አሠራሩን ትክክለኛነት የሚያረጋግጥበት ስምሪትና በጀት የለውም
  • ‹‹በደቡብ ሱዳን አምስት ያህል አብያተ ክርስቲያን ተተክለው አገልግሎት እየሰጡ ከጋምቤላ ሀ/ስብከት ጋራ እየተዳደሩ ነው›› በሚል በብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ ተካትቶ የቀረበው የሀ/ስብከቱ ሪፖርት ፍጹም ሐሰት ኾኖ መገኘቱ አንዳንድ አህጉረ ስብከት ረጃዎች በጥንቃቄ መታየት እንደሚገባው ያመላከተ ኾኗ
    Participants of the 32nd SGGA03
    የመ/ፓ/አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ፴፪ኛው ዓመታዊ ስብሰባ ተሳታፊዎች
  • ፴፪ው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ዓመታዊ ስብሰባ ተሳታፊዎች አቀባበል፣ በአዳራሽ ዝግጅትና መስተንግዶ፣ በጉባኤ ሰነዶች አደረጃጀትጥናታዊ ጽሑፎችና የቡድን ውይይቶች መርሐ ግብሮች ይዘቱ መሻሻል ታይቶበታል፤ ይኹንና ለአንገብጋቢ ጉዳዮች ትኩረትና ሰፊ ጊዜ ሰጥቶ ከመወያየት ይልቅ ሪፖርቶችን ለማዳመጥ የተመደበው ሰዓት የዓመታዊ ስብሰባውን አብዛኛውን ጊዜ የሚወስድ መኾኑ ይታያ፡፡ ለስብሰባው ብር 652‚000 ወጪ ይደረጋል፡፡
    Participating archbishops of the 32nd Sebeka Gubae General assembly
    የአጠቃላይ ጉባኤው ዓመታዊ ስብሰባ ተሳታፊ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በከፊል
  • ሊቃነ ጳጳሳትን ጨምሮ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የመምሪያዎችና ድርጅቶች ሓላፊዎች፣ ከኀምሳ በላይ የአህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆች፣ የካህናት፣ ምእመናን፣ ሰንበት ት/ቤት ወጣቶችና የስብከተ ወንጌል ተወካዮች፣ የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት 160 ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎችና የሰበካ ጉባኤ ምክትል ሊቃነ መናብርት በአጠቃላይ ከ900 በላይ ተሰብሳቢዎች ተሳታፊዎች ናቸው፡፡
የዜናው ዝርዝር ይቀጥላል

2013 ኦክቶበር 12, ቅዳሜ


ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ዐረፉ፤ የቀብር ሥነ ሥርዐቱ ነገ በኢየሩሳሌም ይፈጸማል

  • በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ከሠላሳ ዓመታት በላይ አገልግለዋል
  • ‹‹በጌቴ ሰማኔ፣ በጎልጎታ፣ በዴር አብርሃም ሁሉ ሰፊ ይዞታ እንዳለን በታሪክ ሰፍሯል፡፡ ግብር ለመገበር አቅም ስላነሰን ዴር አብርሃምን ግሪኮች ወሰዱብን፤ ቤተ ልሔም ያለውን ርስታችንን አርመኖች ወስደውታል፤ በዚያ ላይ ያለንን መረጃ በሙሉ ቀደም ሲል አርመንና ግብጾች ወስደው አጥፍተውታል፡፡››
  • ‹‹ግብጾች በጣም ነው የሚከራከሩት፡፡ በዴር ሡልጣን ጉዳይ ግብጾች ያቋቋሙት ትልቅ ኮሚቴ አላቸው፡፡ ኢትዮጵያውያንም የእኛ ነው ካልን ዴር ሡልጣን ከእጃችን አይወጣም፡፡ ለዚህ ቦታ መርጃ የሚኾን አንዳንድ ፕሮጀክት መዘርጋት አስፈላጊ ኾኖ ሲገኝ ምእመናን እጃችኹን መዘርጋት ያስፈልጋል፡፡ ዴር ሡልጣን አለን ማለቱ ብቻውን በቂ አይኾንም፡፡››
  • ‹‹ሕዝቡ ከገዳሙ ጎን ቆሞ፣ ገዳሞቻችን እንደ ሌሎቹ በልጽገው ፈጣሪ እንዲያሳየኝ ጸሎቴ ነው፡፡ የዴር ሡልጣን ክርክር ፍጻሜ አግኝቶ፣ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን መብቷ እስከ ኾነ ድረስ የኢትዮጵያ ምእመናን ለዴር ሡልጣን መርጃ እንዲኾን አስቦ እንደ ግብጾች አንድ ድርጅት አቋቁሞ ለዚያ ሒሳብ ተከፍቶ እንዳየው እመኛለኹ፡፡›› /ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ በ፲፱፻፺፮ ዓ.ም. ለጋዜጠኞች የተናገሩት/
His Grace Abune Heryakos
ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ
(ከ1923 – 2006 ዓ.ም.)
በመጻሕፍተ ሐዲሳት መምህርነታቸው፣ በጸሎትና የተባሕትዎ ሕይወታቸውና መፃዕያትን በሚናገሩበት ሀብተ ትንቢታቸው የሚታወቁት አረጋዊው ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ፣ መስከረም ፳፭ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ዐርፈዋል፡፡ የቀብር ሥነ ሥርዐታቸው ነገ፣ ጥቅምት ፪ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ከ፲፱፻፷፬ ዓ.ም. ጀምሮ ከሠላሳ ዓመታት በላይ ባገለገሉበትና በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ገዳማት አንዱ በኾነው በአልዓዛር ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ይፈጸማል፡፡
በቆየባቸው ሕመምና በዕርግና ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ባረፉት በብፁዕነታቸው የቀብር ሥነ ሥርዐት ላይ ለመገኘት የሰሜን ምዕራብ ሸዋ – ሰላሌ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ፣ የባሌ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስና የወቅቱ የቋሚ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ ወደ ስፍራው ማምራታቸው ታውቋል፡፡
በፊት ስማቸው አባ ላእከ ማርያም ዐሥራት በኋላ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ተብለው ለማዕርገ ጵጵስና የበቁት በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማትን የተመለከቱ ጉዳዮች እንዲያስፈጽሙ በ፲፱፻፹፭ ዓ.ም. ከማኅበረ መነኰሳቱ ተልከው ወደ ኢትዮጵያ በሄዱበት አጋጣሚ ነው፡፡ በወቅቱ ከብፁዕነታቸው ጋራ በአጠቃላይ ሦስት ኤጲስ ቆጶሳት ተሹመዋል፤ እነርሱም በቀደምት የኢየሩሳሌም ተሳላሚዎች መንገድ ወደ ኢየሩሳሌም የተጓዙትና በ፳፻፫ ዓ.ም. ያረፉት በገዳማቱ የሊቀ ጳጳሱ ረዳት ብፁዕ አቡነ አብሳዲ እንዲሁም የደቡብ አሜሪካው ብፁዕ አቡነ ታዴዎስ ናቸው፡፡
ከ፲፱፻፷፬ – ፲፱፻፸ ዓ.ም. በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ሊቀ ጳጳስ ከነበሩት ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ ካልዕ ጋራ አብረው ወደ ኢየሩሳሌም የተጓዙት ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ በኤጲስ ቆጶስነት ከተሾሙ በኋላ ወደ ኬንያና ጅቡቲ አምርተው ለአምስት ዓመታት አገልግለዋል፡፡ ከአምስት ዓመት በኋላ ከኬንያና ጅቡቲ ተመልሰው የአፋር ሀ/ስብከት ጳጳስ ኾነዋል፡፡ ከተወሰኑ ዓመታት ቆይታ በኋላ ለሕክምና ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሰው እስከ ኅልፈታቸው ድረስ ከኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ገዳማት አንዱ በኾነው በአልዓዛር ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም ኖረዋል፡፡
በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም በነበራቸው ከ35 ዓመታት በላይ ቆይታ ስለ ቅድስናና የታሪክ ይዞታችን ተጠያቂ ከነበሩት አባቶች አንዱ የኾኑት ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ፣ ቤተ ልሔም ላይ የነበረው ይዞታችን ከግለሰቦች እጅ ተገዝቶ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን እጅ ሲገባ ታላቅ አስተዋፅኦ አበርክተዋል፤ መጋቢም ኾነው አገልግለዋል፡፡
አረጋዊው ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የተወለዱት በ፲፱፻፳፫ ዓ.ም. በደብረ ሊባኖስ አካባቢ ነው፡፡ በልጅነታቸው በተወለዱበት ስፍራ የቃል ትምህርት፣ ንባብ፣ ግብረ ዲቁና ተምረዋል፡፡ ከዚያም ወደ ጎጃም በመሻገር የቅኔ ትምህርታቸውን በሚገባ ተከታትለዋል፡፡ የቅኔ ትምህርታቸውን የተከታተሉት ደግሞ አማራ ሳይንት ወደሚባለው ስፍራ ወርደው ነው፡፡ እኒህን ትምህርቶች ከተከታተሉ በኋላ ለጊዜው አቁመው ደቡብ ወሎ ሀ/ስብከት ወደሚገኘው የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ገዳም ገብተዋል፡፡ በዚያም በረድእነት አባቶችን ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡
በዚሁ ገዳም እያሉ አንድ ወቅት የገዳሙ አበ ምኔትና ሌሎች መነኰሳት ያልተገባቡበት ጉዳይ ስለነበር አለመግባባቱን ለመፍታት መነኰሳቱን ተከትለው ወደ ደሴ ይሄዳሉ፡፡ መፍትሔ ባለማግኘቱ ጉዳዩን ለጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ለማቅረብ አሁንም መነኮሳቱን ተከትለው አዲስ አበባ ይደርሳሉ፡፡ በዚያው መንፈሳዊ ትምህርታቸውን ለመቀጠል ወደ ሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ገብተው መጻሕፍተ ነቢያትን ተመርዋል፡፡ ወደ መ/ር ገብረ ማርያም መርሻ ተዛውረው መጻሕፍተ ሐዲሳትን አጥንተዋል፡፡
በሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ከ፲፱፻፶ – ፶፯ ዓ.ም ከቆዩ በኋላ ወደ ታዕካ ነገሥት በኣታ ለማርያም ገዳም ሄደው አለቃ ሞገስ ከተባሉ መምህር ዘንድ ከመጻሕፍተ ሊቃውንት መካከል ቄርሎስንና ዮሐንስ አፈ ወርቅን ተምረዋል፡፡ ሌሎችንም የሊቃውንት መጻሕፍት በጉባኤ ቤት እየተገኙ ሲሰሙ ቆይተዋል፡፡ በመጨረሻም በዚሁ ገዳም የሐዲሳት መምህር እንዲኾኑ ተመርጠው ሐዲሳትን በማስተማር በርካታ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንን አፍርተዋል፡፡
*          *          *

‹‹ሕዝቡ ከገዳሙ[ዴር ሡልጣን] ጎን ቆሞ ገዳሞቻችን እንደ ሌሎቹ በልጽገው ፈጣሪ እንዲያሳየኝ ጸሎቴ ነው››
/ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ በ፲፱፻፺፭ ዓ.ም. ለስምዐ ጽድቅ ጋዜጠኛ ከተናገሩት/

ስምዐ ጽድቅ፡- ብፁዕ አባታችን እስኪ ስለ ኢየሩሳሌም ገዳማት የሚያውቁትን ያጫውቱኝ?
ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ፡- ታሪኩን እንኳ ከሌሎች አባቶች መስማቱ ይሻላል፡፡ እኔ ግን ስለ ገዳማቱ ችግር ላጫውትኽ እችላለኹ፡፡ ገዳሙ ባለፈው ከሐምሌ ወር ጀምሮ እስከ ጥቅምት ድረስ ብዙ ችግር ደርሶበታል፡፡ መነኰሳት ተደብድበዋል፡፡ በአንድ ግብጻዊ መነኩሴ ምክንያት አባቶች ተንገላትተዋል፡፡ ይህ መነኩሴ እኛ ገዳም ውስጥ ብዙ ዓመት ኖሯል፡፡ ዘንድሮ ግን ሌላ ታሪክ ይዞ አየኹ፡፡ አባቶችን አስደበደበ፡፡
ስምዐ ጽድቅ፡- እኛ ራሳችን ቦታ ስለሰጠነው አይመስልዎትም?
ብፁዕነታቸው፡- ልክ ነኽ፣ እንደዚያ ነው፡፡ በእኛ ገዳም እኮ ብዙ ጊዜ ቆይቷል፡፡ እንዲያውም ሲቸግረው መጠጊያ የኾነው የእኛ ገዳም ነው፡፡ አንድ ወቅት ኢራቅ እስራኤልን ልትመታ ሮኬት የወረወረች ጊዜ የእርሱ ወገኖች አባረውት ከእኛ መነኮሳት ጋራ ነው ሲመገብ የከረመው፡፡ ከእኛ ገዳም እንደ አንድ አባል ኾኖ ብዙ ስንረዳው ቆይተናል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን አሁን ያሉት የግብጽ ጳጳስ ምን ተስፋ እንደሰጡት አላውቅም፣ አድርጎት የማያውቀውን ማድረግ ጀመረ፡፡
ከመኖርያ ቤቱ እየወጣ ወደ ራሳቸው ወደ ግብጻውያን ወደ ራሳቸው ገዳም ይሄዳል፡፡ ከዚያ ትንሽ ይቆይና ሦስት አራት ፖሊሶች አጅበውት መጥቶ እኛ ገዳም ወንበሩን ዘርግቶ ይቀመጣል፡፡ ግማሽ ሰዓት ያህል ይቀመጥና ደግሞ ተነሥቶ ወንበሩን አሸክሞ ወደ ቤቱ ይገባል፡፡ እነርሱ በእኛ ገዳም ሊሠሩት ያሰቡት አንድ ነገር እንዳለ ያስታውቃል፡፡ አንዳንድ ሰዎች ጉዳዩን እንደ ቀላል አይተነዋል፡፡ ቀላል ግን አይደለም፡፡
አሁን ለምሳሌ እኛ የቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አለን፡፡ እዚያ ለሰኔና ለኅዳር ሚካኤል በዓል በምናከብርበት ወቅት ብዙ ሕዝብ ይመጣል፡፡ ቦታ ስለሚጠብ ከግቢ ውጭ ወጥተው ለማስቀደስ ይገደዳሉ፡፡ ግብጻውያን ግን አይፈቅዱላቸውም፡፡ ሊቀ ጳጳሱ አባ ዳንኤል ይባላል፡፡ እርሱ ወጥቶ ያባርራቸዋል፡፡ ለአንድ ሰዓት እንኳ ማስቀደስ እንዳንችል ያደርጋሉ፡፡ ቦታው ላይ ቆመው ካስቀደሱ፣ ነገ ይዞታችን ነው ብለው ይከራከሩናል ብለው በመፍራት ተጠራጣሪ ስለኾኑ አያስቀርቡንም፡፡ የእኛ ግን ምን እንደኾነ ስሜቱን አላውቅም፣ በገዳማችን እየተመላለሰበት ሲፈልግ ወንበሩን ዘርግቶ እየተቀመጠ ይኖራል፡፡
የሚገርመው ወንበሩን ዘርግቶ ከመቀመጥ አልፎ ወደ እኛ ገዳም ሲገቡ ‹‹የግብጽ ገዳም ነው›› እያለ ያስተዋውቃል፡፡ መነኩሴው ምን ዓላማ እንዳለው አንዳንድ ሰዎች የተረዱት አይመስለኝም፡፡
ስምዐ ጽድቅ፡- ግንኮ ያ ሁሉ ርስታችን ተወስዶ ዛሬ በዚህች በተረፈችን ቦታ ላይ መከራችንን ማየታችን የሚገርም ይመስለኛል፡፡
ብፁዕነታቸው፡- ታሪካችን የጥንት ኾኖ ዛሬ በዚህ ኹኔታ መገኘታችንን ስናየው ያስብላል፡፡ አንድ ዝኤብ ብልናኢ የተባለ ደራሲ በጻፈው መጽሐፍ የእኛ ይዞታ የት የት እንዳለ ገልጾአል፡፡ እርሱ እንዲያውም በጌቴ ሰማኔ፣ በጎልጎታ፣ በዴር አብርሃም ሁሉ ሰፊ ቦታ እንዳለን በታሪክ አስፍሮታል፡፡ ዴር አብርሃም የተባለው ቦታ የኢትዮጵያውያን ነበር፡፡ ግብር መገበር አቅቷቸው ግሪኮች ወስደውባቸዋል ብሎ ጽፏል፡፡ መጽሐፉ ከቤቴ አለ፡፡ ይኸም ኾኖ ግን ቦታውን በዘመን ብዛት የእነርሱ ይዞታ ስላደረጉት የእኛ ነው ለማለት ያስቸግራል፡፡
ቤተ ልሔም ያለውን ርስታችንን አርመኖች ወስደውታል፡፡ በዚያ ላይ ያለንን መረጃ በሙሉ ቀደም ሲል አርመንና ግብፆች ወስደው አጥፍተውታል፡፡ በኋላ ግን በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ የነበሩት (ከ1944 – 1957 ዓ.ም.) ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ ደጃች መሸሻ የሰበሰቡትን መረጃና የቀረውንም ራሳቸው አሰባስበው ክሥ በመመሥረት የተያዙብንን ገዳማት በከፊል ወደ እኛ እንዲመለስ አድርገዋል፡፡
ስምዐ ጽድቅ፡- በቤተ ልሔም ያለንን ይዞታ ያገኘነው በእርስዎ አማካይነት መኾኑን መነኰሳቱ ነግረውኛል፡፡
ብፁዕነታቸው፡- ቤተ ልሔም እኔ መጋቢ ኾኜ በጊዜው የነበሩ ሊቀ ጳጳስ ወደ ኢትዮጵያ ሄደው ስለነበር አልነበሩም፡፡ ለጊዜው ባለቤት የነበረው ዐረቡ በድንገት ተነሥቶ ቦታውን ካልገዛኽ ለሌላ እሸጠዋለኹ ስላሉኝ እኔ ለማኅበሩ ነገርኩና እንግዛ ብለን ተመካከርን፡፡ እንዳልኩኽ ሊቀ ጳጳሱ ኢትዮጵያ ስለነበሩ ለእርሳቸው ደውዬ፣ ቦታውን ሰውዬውን አሁን ካልገዛችኹን ልሸጠው ነው ስላለ በዚያ ላይ የሚሸጠው መሬት ከልዑል ራስ ካሳ ቦታ ጋራ አዋሳኝ ስለኾነ ወደፊት ምናልባት ደግሞ እነርሱ በበጎ አድራጎት መሬታቸውን ቢሰጡን ተያይዞ አንድ አቋም ያለው ትልቅ ቤተ ክርስቲያን መሥራት ይቻላልና እንግዛው አልኋቸው፡፡ እንዲያው ግዙት አሉ፡፡ ያን ጊዜ እኔ ገዳማቱ መጋቤ ነበርኩኝ፡፡ አሁን የሚቀደስባትንና ታች መነኰሳቱ የሚኖሩበትን በእኔ መጋቢነት ተገዛ፡፡ የወዲህኛው ፎቁ ግን በኋላ በብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ ነው የተገዛው፡፡
ስምዐ ጽድቅ፡- ብፁዕ አባታችን፣ በእስራኤል ከሚነገሩት ቋንቋዎች ምን ያህሉን ያውቃሉ?
ብፁዕነታቸው፡- ዕብራይስጥ እችላለኹ፤ ዐረብኛም እንደው ለራሴ እሞካክራለኹ፡፡ በተለይ ዕብራይስጡን እጽፋለኹ፤ አነባለኹኝ፤ በእርሱ ምንም ችግር የለብኝም፤ መጽሐፉም አለኝ፤ መጽሐፍ ቅዱስም አለኝ፤ የዕብራይስጥ ትርጓሜውም አለኝ፡፡ እርሱን በጊዜው እመለከታለኹኝ፡፡
ስምዐ ጽድቅ፡- ታዲያ ዕብራውያን በራሳቸው ቋንቋ የጻፉት የኢትዮጵያ ገዳማትን የተመለከተ ማስረጃ አላገኙም?
ብፁዕነታቸው፡- ሳነብ የእኛ ይዞታ ለመኾኑ የሚያስረዳ ጽሑፍ አግኝቻለኹ፡፡ ብዙ በዕብራይስጥ እንዲያውም ዝኤብ ብልናኢ የሚባለው አንድ አራት መጻሕፍት አሉት፡፡ አንደኛው አሌፍ፣ ሁለተኛው ቤት፣ ሦስተኛው ጊሜል፣ አራተኛው ዳሌት ይባላሉ፡፡ የጌቴ ሰማኔውን ቦታችንን በካርታ ጭምር አውጥቶታል፡፡ ከእመቤታችን መቃብር አጠገብ ነው፡፡
ስምዐ ጽድቅ፡- እርስዎ መጻሕፍት ማንበብ እንደሚወዱ ይነገራል፡፡
ብፁዕነታቸው፡- እዚያ አዲስ አበባ ሳለኹ ብዙ ጊዜ የማሳልፈው ሐይቅ ነበር፡፡ አዲስ አበባ ቤተ መዘክር እንዲያው ሥራ በማይኖረኝ ቀን ስመለከት ነበር የምውለው፡፡ ትምህርት በማስተምርበት ጊዜ የክረምት ሲዘጋ ሐይቅ ሄጄ ከርሜ ስመለከት ውዬ ወይም ደግሞ ጠቃሚውን በማስታወሻ እየያዝኁ እመጣለኹ፡፡ ማስታወሻዬን እንደው ዝም ብዬ አዲስ አበባ ጥዬው ነው ያለ፡፡ ሌላው ግን ከዚህ ይዤ ልምጣ፣ ያኔ ኬንያ ልጣለው፣ ሌባ ይውሰደው እንጃ ብዙ ነበረ፣ ጠፋብኝ፡፡
ስምዐ ጽድቅ፡- ዕብራይስጡንና ግእዙን መጽሐፍ ቅዱስ አገናዝበውታል?
ብፁዕነትዎ፡- እዚህ ማስታወሻ እየያዝኁ ዕብራይስጡን አነባለኹ፡፡ ለነገሩ የቦታውን ይዞታ የሚጠቁሙ ካልኾኑ በስተቀር ሌላው በመጽሐፍ ቅዱስ የሚገኘው ንባቡ ግን የእነርሱ ሊቃውንት የተረጎሙት ነው፡፡ ጥሩ ነው፡፡ የእኛ ቤተ ክርስቲያን ከምትተረጉመው ጋራ ግን አይሄድም፡፡ የሚተረጉሙት መጻሕፍተ ብሉያትን ነው፤ እርሱንም ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ፣ ለእመቤታችን ሰጥተን የምንተረጉመውን በመጽሐፈ ነቢያት በሌሎችም ያሉትን በሌላ ምስጢር ስለሚተረጉሙት ብዙም አልከታተለውም፡፡
አንድ ያየኹት ትልቅ ነገር፣ አንድምታው ላይ አንድም እያልን የምንተረጉመውን ትርጓሜ እገሌ ተረጎመው አንልም፡፡ እንደው ዝም ብለን አንድም ብለን ትርጓሜ ብቻ ነው፡፡ እነርሱ ግን በዚህ ዘመን የተወለደ፣ በዚህ ዘመን ከእገሌ የተማረ፣ ይህን ያህል ዘመን ቆይቶ ይህን ትርጓሜ ተረጎመ ብለው ስሙንም አገሩንም ሳይቀር እየጠቀሱ ያሰፍሩታል፡፡ በእኛ ቤተ ክርስቲያን የእነርሱን የሚመስል ትርጓሜ አለ – ትርጓሜ ወንጌል ይባላል፡፡ ግእዙ በግእዝ ነው የሚተረጎመው፡፡ በአማርኛ አይደለም፣ ግእዝ በግእዝ ነው፡፡ እርሱ ዓመተ ምሕረት ባይጠቅስም ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ቄርሎስ፣ ሳዊሮስ እንዲህ ይሄን ተረጎሙት ይላል፡፡ ሌላው ግን አንድም ብሎ ተርጉሞ ይሄዳል እንጂ እገሌ ነው አይልም፡፡
ስምዐ ጽድቅ፡- ብፁዕ አባታችን፣ እርሰዎ የሚኖሩት በአልዓዛር የኢትዮጵያ ገዳም ነው፡፡ እስኪ ስለ ገዳሙ ታሪክ ይንገሩኝ፡፡
ብፁዕነታቸው፡- አልዓዛር በአሁኑ ጊዜ ከተማ ኾኗል፡፡ በፊት ግን መንደርም አልነበረበትም፡፡ በመጀመሪያ ቦታው የተገዛው በብፁዕ አቡነ ፊልጶስ በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ነው፡፡ ለመቃብር ቦታ ብለው ራቅ አድርገው ነው የገዙት፤ መንደር አልነበረውም፡፡ የገዙበትን ዋጋውን የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ እንዲከፍሉ ጠየቋቸው፤ ንጉሡም ጥያቄውን ተቀብለው ገንዘቡን ሰጧቸው፡፡ በዚህ የተነሣ ገዳሙ በንጉሡ በዐፄ ኃይለ ሥላሴ የተገዛ መኾኑን የሚያመለክት ጽሑፍ በድንጋይ ተቀርጾ ቦታው ላይ እንዲቀመጥ ተደርጓል፡፡
በወቅቱ ምድረ በዳ ነበር፤ ሰውም ምንም አልነበረም፡፡ በኋላ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ ተሹመው መጡ፡፡ እርሳቸው ቤተ ክርስቲያንም ሠሩ፡፡ አሁን ከዚያ እርሳቸው ቤት ከሠሩ በኋላ መነኰሳት ተለይተው አያውቁም፡፡ እኔም አባ ገብረ ማርያም ኮንታ የሚባሉ አሉ፣ ከእርሳቸው ጋራ አንድ ትንሽ ጎጆ በግላችን መቁነናችንን አጠራቅመን ሠርተን አሁን እዚያ ነው የምንኖር፡፡ በአጠቃላይ በገዳሙ ሁለት ሦስት ነበርን፡፡ አሁን ደግሞ አንድ አራት ኾነናል፡፡ ብዙም ሰው አይኖርበትም፡፡
ስምዐ ጽድቅ፡- እስራኤልና ፍልስጤኤም ሁለት መንግሥት ከኾኑ ቦታው ወደ ማንኛው የሚኾን ይመስልዎታል?
ብፁዕነታቸው፡- አሁን ወደ ማን ክፍል እንደሚኾን አላወቅንም፡፡ ግን ከአጠገቡ መአሌ አዱሚሞ የሚባል ሰፊ ቦታ እስራኤሎች ብዙ ሕዝብ አስፍረውበታል፡፡ ወደ 30 ሺሕ ሰው ይመስለኛል የሰፈረው፡፡ በጣም ጥሩ ቦታ ነው፡፡ ግን ድሮም እዚያ ቤተ ክርስቲያን የተሠራበት ቦታ ነበር፤ እርሱን ለቱሪስት ክፍት አድርገውት ቱሪስት ያየዋል፡፡ ቀድሞ ቤተ ክርስቲያን የነበረበት ፍራሹ ይታያል፡፡ የእኛ ግን እላይ ነው፡፡ የአልዓዛር ቤት ከነበረው ትንሽ ገንጠል ብሎ ወደ ውስጥ ገባ ያለ ነው፡፡
ስምዐ ጽድቅ፡- አልዓዛር በሚገኘው ገዳማችን ችግር ገጥሟችኹ አያውቅም?
ብፁዕነታቸው፡- በጣም ያጋጥመናል፡፡ አሁን አሁን በቅርቡ እንኳ ዐረቦቹ ድንጋይ ይወረውሩብን ነበር፡፡ አሁን ግን አንድ የዐረብ ተወላጅ የሚኾን ዘበኛ ቀጥረን እርሱ ከገባ ጸጥ ብሏል፡፡ ድንጋይ አይወረውሩም፡፡ ግድግዳው ላይ ግን ይለቀልቃሉ፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በረድ ብሏል፡፡ ሰውዬውም ደኅና ልጅ ነው፤ ይጠብቃል፡፡
ስምዐ ጽድቅ፡- ገዳሙ በምንድን ነው የሚተዳደረው?
ብፁዕነታቸው፡- ለቦታው ጠባቂዎች ብለው ቦታ እየገዙ፣ ቤት እየሠሩ የሰጡን አሉ፡፡ በዚያ በምናገኘው ኪራይ ነው መነኰሳቱ የምንተዳደር፡፡ በርግጥ ቀድሞ ከኢትዮጵያ ገንዘብ ይላክ ነበር፡፡ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ጊዜ በየሦስት ወሩ 3000 ዶላር ይልኩልን ነበር፡፡ ከዚያም አዲስ አበባ ላይ ደግሞ ቤት ነበረን፡፡ እርሱን እንተወው፣ አሁን የለም፡፡ እዚህ ባለው ገንዘብ ነው አሁን የምንተዳደር፡፡
ስምዐ ጽድቅ፡- በሕይወት ዘመንዎ እንዲኾን የሚፈልጉትን ነገር ቢነግሩንና ብናጠናቅቅ?
ብፁዕነታቸው፡- የዴር ሡልጣን ክርክር ፍጻሜ አግኝቶ፣ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን መብቷ እስከ ኾነ ድረስ የኢትዮጵያ ምእመናን ለዴር ሡልጣን መርጃ እንዲኾን አስቦ እንደ ግብጾች አንድ ድርጅት አቋቁሞ ለዚያ ሒሳብ ተከፍቶ እንዳየው እመኛለኹ፡፡
ግብጾች አሁን ካየን ጳጳሱ ብቻውን ምን አቅም አለው? ክርስቲያኖች ምእመናኑ ናቸው የሚሟገቱለት፡፡ በዴር ሡልጣን ጉዳይ የግብጽ ክርስቲያኖች ያቋቋሙት ትልቅ ኮሚቴ አላቸው፡፡ ግብጽ ውስጥ መጅልስ የሚሉት ትልቅ ድርጅት አለ፡፡ አሜሪካም እንደዚሁ ድርጅት አቋቁመዋል፡፡ እነርሱ በጣም ነው የሚከራከሩት፡፡ ኢትዮጵያውያንም የእኛ ነው ካልን ዴር ሡልጣን ከእጃችን አይወጣም፡፡ ለዚህ ቦታ መርጃ የሚኾን አንዳንድ ፕሮጀክት መዘርጋት አስፈላጊ ኾኖ ሲገኝ ምእመናን እጃችኹን መዘርጋት ያስፈልጋል፡፡ ዴር ሡልጣን አለን ማለቱ ብቻውን በቂ አይኾንም፡፡ ጥንት መነኰሳቱ ናቸው በእግራቸው መጥተው ዴር ሡልጣንና ዮርዳኖስን የያዙት፡፡ በኋላ የተነሡ አባቶችም እነ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብም ሌሎችም እነ ዐፄ ዮሐንስም በቃላት ከምንገልጸው በላይ ደክመውበታል፤ እነ ዐፄ ምኒልክም ረድተዋል፡፡ እንደውም ዐፄ ምኒልክም ሙግትም ክሥ ተመሥርቶ ብዙ ክርክር አድርገዋል፡፡
ግን ይሄ ሁሉ ኃይል ለውጤት የሚበቃው፣ ርስታችን ለሁልጊዜ በእጃችን የሚቆየው ምእመናን ሲኖሩበት ነውና ምእመናኑ ለዚህ ቦታ መቆም አለባቸው፡፡ ስለዚህ ሕዝቡ ከገዳሙ ጎን ቆሞ፣ ገዳሞቻችን እንደ ሌሎቹ በልጽገው ፈጣሪ እንዲያሳየኝ ጸሎቴ ነው፡፡
ምንጭ፡- ስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ፣፲ኛ ዓመት ቁጥር ፲፪/ ቅጽ ፲ ቁጥር ፹፬/ መስከረም ፲፱፻፺፮ ዓ.ም
About these ads

2013 ኦክቶበር 10, ሐሙስ

ሰንበት ት/ቤቱ የካህናት  ሥልጠና አዘጋጀ
   በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በደብረ ከዋክብት አቡነ አረጋዊና ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ  ደብር የካህናት ሥልጠና ተዘጋጀ
የደብሩ ሰንበት ት/ቤት ያዘጋጀው ይህ ሥልጠና ከመስከረም 20-28  /2006  ዓ.ም ነው ፡፡ በሥልጠናውም ትምህርተ  ኖሎት ፤ ሥርዓተ ቤተክረስቲያን 
  ክርሥቲያናዊ ሥነ ምግባር ፤ የግጭት አፈታት ዘዴ እና ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ጉዳይች  በሥልጠናው ተካተዋል  የደብሩ ሰንበት ት/ቤት  በተለይ ለካህናቱ ስልጠና ማዘጋጀቱ የቤተክርስቲያንን አገልግሎት በተቀላጠፈ መልኩ ለመፈጸም ይረዳናል ያሉት ሠልጣኞች ካህናት ሥልጠናው ወደፊትም መቀጠል እንዳለበት ተቁመዋል፡፡ በተለይ አሁን ያለውን ትውልድ በሚገባ ለማገልገልና ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት ለሕዝበ ክርስቲያኑ ለማድረስ ይቻል ዘንደ የካህናት ሥልጠና በተጠናከረ መልኩ መቀጠል እንደሚያስፈልግ የደብሩ ሰንበት ት/ቤት ጠቁሞአል ፤በየደብሩ ይህ ተሞክሮ መቀጠል እንዳለበትም  የተጠቆመ ሲሆን ሌሎችም ባለድርሻ አካላት በሚችሉት ሁሉ ተሳታፊ እንዲሆኑ  ሰንበት ት/ቤቱ ጥሪ አቅርቧል፡፡  በሰንበት ት/ቤቱ  የሚያገለግሉ ወጣቶች በየመሥሪያ ቤቱ የሚሰሩ ዲያቆናት ሌሎቹንም በማስተባበር ሥልጠናው የተዘጋጀ መሆኑ ታውቋአል፡፡   

ሰንበት ት/ቤቱ የካህናት  ሥልጠና አዘጋጀ
   በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በደብረ ከዋክብት አቡነ አረጋዊና ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ  ደብር የካህናት ሥልጠና ተዘጋጀ
የደብሩ ሰንበት ት/ቤት ያዘጋጀው ይህ ሥልጠና ከመስከረም 20-28  /2006  ዓ.ም ነው ፡፡ በሥልጠናውም ትምህርተ  ኖሎት ፤ ሥርዓተ ቤተክረስቲያን 
  ክርሥቲያናዊ ሥነ ምግባር ፤ የግጭት አፈታት ዘዴ እና ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ጉዳይች  በሥልጠናው ተካተዋል  የደብሩ ሰንበት ት/ቤት  በተለይ ለካህናቱ ስልጠና ማዘጋጀቱ የቤተክርስቲያንን አገልግሎት በተቀላጠፈ መልኩ ለመፈጸም ይረዳናል ያሉት ሠልጣኞች ካህናት ሥልጠናው ወደፊትም መቀጠል እንዳለበት ተቁመዋል፡፡ በተለይ አሁን ያለውን ትውልድ በሚገባ ለማገልገልና ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት ለሕዝበ ክርስቲያኑ ለማድረስ ይቻል ዘንደ የካህናት ሥልጠና በተጠናከረ መልኩ መቀጠል እንደሚያስፈልግ የደብሩ ሰንበት ት/ቤት ጠቁሞአል ፤በየደብሩ ይህ ተሞክሮ መቀጠል እንዳለበትም  የተጠቆመ ሲሆን ሌሎችም ባለድርሻ አካላት በሚችሉት ሁሉ ተሳታፊ እንዲሆኑ  ሰንበት ት/ቤቱ ጥሪ አቅርቧል፡፡  በሰንበት ት/ቤቱ  የሚያገለግሉ ወጣቶች በየመሥሪያ ቤቱ የሚሰሩ ዲያቆናት ሌሎቹንም በማስተባበር ሥልጠናው የተዘጋጀ መሆኑ ታውቋአል፡፡   

ሰንበት ት/ቤቱ የካህናት  ሥልጠና አዘጋጀ
   በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በደብረ ከዋክብት አቡነ አረጋዊና ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ  ደብር የካህናት ሥልጠና ተዘጋጀ
የደብሩ ሰንበት ት/ቤት ያዘጋጀው ይህ ሥልጠና ከመስከረም 20-28  /2006  ዓ.ም ነው ፡፡ በሥልጠናውም ትምህርተ  ኖሎት ፤ ሥርዓተ ቤተክረስቲያን 
  ክርሥቲያናዊ ሥነ ምግባር ፤ የግጭት አፈታት ዘዴ እና ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ጉዳይች  በሥልጠናው ተካተዋል  የደብሩ ሰንበት ት/ቤት  በተለይ ለካህናቱ ስልጠና ማዘጋጀቱ የቤተክርስቲያንን አገልግሎት በተቀላጠፈ መልኩ ለመፈጸም ይረዳናል ያሉት ሠልጣኞች ካህናት ሥልጠናው ወደፊትም መቀጠል እንዳለበት ተቁመዋል፡፡ በተለይ አሁን ያለውን ትውልድ በሚገባ ለማገልገልና ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት ለሕዝበ ክርስቲያኑ ለማድረስ ይቻል ዘንደ የካህናት ሥልጠና በተጠናከረ መልኩ መቀጠል እንደሚያስፈልግ የደብሩ ሰንበት ት/ቤት ጠቁሞአል ፤በየደብሩ ይህ ተሞክሮ መቀጠል እንዳለበትም  የተጠቆመ ሲሆን ሌሎችም ባለድርሻ አካላት በሚችሉት ሁሉ ተሳታፊ እንዲሆኑ  ሰንበት ት/ቤቱ ጥሪ አቅርቧል፡፡  በሰንበት ት/ቤቱ  የሚያገለግሉ ወጣቶች በየመሥሪያ ቤቱ የሚሰሩ ዲያቆናት ሌሎቹንም በማስተባበር ሥልጠናው የተዘጋጀ መሆኑ ታውቋአል፡፡   



          ሰንበት ት/ቤቱ የካህናት  ሥልጠና አዘጋጀ
   በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በደብረ ከዋክብት አቡነ አረጋዊና ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ  ደብር የካህናት ሥልጠና ተዘጋጀ
የደብሩ ሰንበት ት/ቤት ያዘጋጀው ይህ ሥልጠና ከመስከረም 20-28  /2006  ዓ.ም ነው ፡፡ በሥልጠናውም ትምህርተ  ኖሎት ፤ ሥርዓተ ቤተክረስቲያን 
  ክርሥቲያናዊ ሥነ ምግባር ፤ የግጭት አፈታት ዘዴ እና ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ጉዳይች  በሥልጠናው ተካተዋል  የደብሩ ሰንበት ት/ቤት  በተለይ ለካህናቱ ስልጠና ማዘጋጀቱ የቤተክርስቲያንን አገልግሎት በተቀላጠፈ መልኩ ለመፈጸም ይረዳናል ያሉት ሠልጣኞች ካህናት ሥልጠናው ወደፊትም መቀጠል እንዳለበት ተቁመዋል፡፡ በተለይ አሁን ያለውን ትውልድ በሚገባ ለማገልገልና ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት ለሕዝበ ክርስቲያኑ ለማድረስ ይቻል ዘንደ የካህናት ሥልጠና በተጠናከረ መልኩ መቀጠል እንደሚያስፈልግ የደብሩ ሰንበት ት/ቤት ጠቁሞአል ፤በየደብሩ ይህ ተሞክሮ መቀጠል እንዳለበትም  የተጠቆመ ሲሆን ሌሎችም ባለድርሻ አካላት በሚችሉት ሁሉ ተሳታፊ እንዲሆኑ  ሰንበት ት/ቤቱ ጥሪ አቅርቧል፡፡  በሰንበት ት/ቤቱ  የሚያገለግሉ ወጣቶች በየመሥሪያ ቤቱ የሚሰሩ ዲያቆናት ሌሎቹንም በማስተባበር ሥልጠናው የተዘጋጀ መሆኑ ታውቋአል፡፡   

2013 ኦክቶበር 5, ቅዳሜ


ቀጣዩ የኢሕአዴግ ዒላማ ማኅበረ ቅዱሳን ይኾን?

FACT Weekily Magazine cover story
(ፋክት መጽሔት፤ ቁጥር 14 መስከረም ፳፻፮ ዓ.ም.)
ተመስገን ደሳለኝ
የኢሕአዴግ ታጋዮች የመንግሥት ‹‹ጠንካራ ይዞታ›› የሚባሉ ከተሞችን ሳይቀር መቆጣጠር ችለዋል፤ ወደ አዲስ አበባም የሚያደርጉት ግሥጋሴም ፕሬዝዳንት መንግሥቱ ኃይለ ማርያምን ሳይቀር ዕንቅልፍ ነስቷል፡፡ በአንዳች ተኣምር ግሥጋሴውን መግታት ካልቻሉ በጥቂት ወራት ውስጥ ሁሉም ነገር ታሪክ እንደሚኾን በማወቃቸው መላ በማፈላለጉ ላይ ተጠምደዋል፡፡ በዚህን ጊዜ ነበር(የሐሳቡ አመንጪ ተለይቶ ባይታወቅም)፣ ‹‹ለዩኒቨርስቲ ተማሪዎች አጭር ሥልጠና ሰጥቶ ከሀገሪቱ ሠራዊት ጎን ማሰለፍና የ‹ወንበዴውን ጦር› ማድረሻ ማሳጣት›› የሚለው ሐሳብ እንደ መፍትሔ የተወሰደው፡፡
እናም መንግሥቱ ራሳቸው ተማሪዎቹን በዩኒቨርስቲ አዳራሽ ሰብስበው እንዲህ ሲሉ አፋጠጧቸው፡- ‹‹እነርሱ (ኢሕአዴግና ሻዕቢያን ማለታቸው ነው) ለእኵይ ዓላማቸው ከእረኛ እስከ ምሁር ሲያሰልፉ እናንተ ምንድን ነው የምትሠሩት? በሰላማዊ ሰልፍና በስብሰባ ብቻ መቃወም ወይስ ወንበዴዎቹ እንዳደረጉት ከአብዮታዊ ሠራዊታችነ ጎን ቆማችኹ የአገሪቱን ህልውና ታስከብራላችኹ?››
ይህን ጊዜም አስቀድሞ በተሰጣቸው መመሪያ ከተማሪው ጋራ ተመሳስለው በአዳራሹ የተገኙት የደኅንነት ሠራተኞችና የኢሠፓ ካድሬዎች ‹‹ዘምተን ከጠላት ጋራ መፋለም እንፈልጋለን›› ብለው በስሜትና በወኔ እየተናገሩ በሠሩት ‹ድራማ› ተማሪው ትምህርት አቋርጦ እንዲዘምት ተወሰነ፤ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲም ተዘጋ፤ ተማሪዎቹም ለወታደራዊ ሥልጠና ደቡብ ኢትዮጵያ ወደሚገኘው ብላቴ የአየር ወለድ ማሠልጠኛ ከተቱ፡፡
ከመላው ዘማቾች ዐሥራ ሁለት የሚኾኑ ተማሪዎች ተሰባስበው ሲያበቁ በየቀኑ ካምፓቸው አቅራቢያ ወደሚገኘው ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በመሄድ ከመዐቱ ይታደጋቸው ዘንድ ፈጣሪያቸውን በጸሎት መማጠን የሕይወታቸው አካል አደረጉት፤ ከቀናት በኋላም በአንዱ ዕለት አንድም ለመታሰቢያና ለበረከት. ሁለትም ስብስቡ ሳይበተን ወደፊት እንዲቀጥል በሚል ዕሳቤ ‹‹ማኅበረ ሚካኤል›› ብለው የሠየሙትን የጽዋ ማኅበር መሠረቱ፡፡ . . . ይኹንና ከመካከላቸው አንዳቸውም እንኳ በ፲፱፻፸፯ ዓ.ም በፓዌ መተከል ዞን የተደረገውን የመልሶ ማቋቋም ሠፈራ ፕሮግራም እንዲያመቻቹ በዘመቱ ተማሪዎች ከተመሠረተውና ከተለያዩ የጽዋ ማኅበራት ጋራ በመዋሐድ የዛሬውን ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን›› እንደሚፈጥሩ መገመት የሚችሉበት የነቢይነት ጸጋ አልነበራቸውም፤ የኾነው ግን እንዲያ ነበር፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን
የ‹‹ማኅበረ ሚካኤል›› መሥራቾች ከተማሪ ጓደኞቻቸው ጋራ ‹‹ይለያል ዘንድሮ የወንበዴ ኑሮ››ን እየዘመሩ የገቡበት ወታደራዊ ሥልጠና ተጠናቅቆ ወደ ጦር ሜዳ ከመግባታቸው በፊት ዐማፅያኑ አሸንፈው የመንግሥት ለውጥ በመደረጉ ሥልጠናቸውን ሳይጨርሱ ወደየመጡበት ተመለሱ፡፡ ኾኖም ለውጡ በተካሄደ በዓመቱ እነርሱን ጨምሮ በአምላካቸው፣ በጻድቃን፣ በሰማዕታትና በመላእክታት ስም የተመሠረቱ[ከአቡነ ጎርጎርዮስ ዘንድ ሲማሩ የቆዩ] የተለያዩ ማኅበራት ተሰባስበው ወደ አንድ እንዲመጡ መደረጉ ሊጠቀስ የሚገባ ልዩነት ባይፈጥርም ስያሜው ግን ብርቱ ክርክር አሥነሳ፤ አቡነ ገብርኤልም ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን ብዬዋለኹ›› ብለው ውጥረቱን አረገቡት፡፡ ዕለቱም[ልደቱን የሚቆጥርበት] ግንቦት ፪ ቀን ፲፱፻፹፬ ዓ.ም. እንደነበር ተጽፏል፡፡
ዓላማው ምንድን ነው?
ማኅበረ ቅዱሳን ሲመሠረት ዓላማዬ ብሎ የተነሣበት መሠረታዊ ጉዳይ በተለያየ ጊዜ ለኅትመት ባበቃቸው ድርሳናቱ ተገልጧል፡፡ እርሱም፡- ትምህርተ ሃይማኖት፣ ሥርዐተ እምነት፣ ክርስቲያናዊ ትውፊትና ታሪክ ተጠብቀው ለትውልድ እንዲተላለፉ ማስቻል ነው፡፡
ማኅበሩ ከመሰሎቹ የተለየ ጥንካሬ እንዲኖረው ያስቻለው ዓላማውን ከግብ ለማድረስ በዋናነት በሀገሪቱ የተለያዩ ዩኒቨርስቲዎችና ኮሌጆች የሚማሩ ተማሪዎችን አባል ማድረጉ ላይ ተግቶ መሥራቱ ነው፡፡ ዛሬም ድረስ መስፈርቱ እያገለገለ እንደኾነ ይታወቃል፤ ይህ ኹኔታም ይመስለኛል አንዳንድ ጸሐፍት ማኅበሩን ‹‹ቤተ ክርስቲያኗ በዩኒቨርስቲዎች ያላት እጅ›› እንዲሉት ያስገደዳቸው፡፡
የኾነው ኾኖ ማኅበሩ በምሥረታው ማግሥት በሃይማኖቱ የመጨረሻውን ሥልጣን በያዘው ቅዱስ ሲኖዶስ ዕውቅና ተሰጥቶት በጠቅላይ ቤተ ክህነት የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ ሥር እንዲኾን ተደረገ፡፡ በ፲፱፻፹፭ ዓ.ም. ደግሞ መተዳደርያ ደንቡን አጸደቀ፡፡
የግጭት ጅማሬ
. . . አንዳንድ የኢሕአዴግ አመራሮች በብላቴ ከተመሠረተው ‹‹ማኅበረ ሚካኤል›› ጋራ በማያያዝ የማኅበሩን መሪዎች አልፎ አልፎ ‹‹ተረፈ ደርግ›› እና ‹‹መአሕድ›› እያሉ ከማሸማቀቅ ባለፈ ብዙም ጫና አያደርጉባቸውም ነበር፡፡ ዛሬ ማኅበሩን በመንግሥት ጥቁር መዝገብ በቁጥር አንድ ጠላትነት እንዲሰፍር ካደረጉት ልዩነቶች(ያለመግባባቶች) መካከል ዋናዎቹን በአዲስ መሥመር እጠቅሳለሁ፡፡
ኢሕአዴግ የአገሪቱን ምሥረታ ከዐፄ ምኒልክ ዘመን የሚጀምር የመቶ ዓመት ማድረጉ ማኅበሩ ዓላማዬ ከሚለው ‹‹ታሪክን ጠብቆ ለትውልድ ማስተላለፍ›› ጋራ መታረቅ አለመቻሉ ያስከተለው ውጥረት የመጀመሪያው ነው፡፡ ማኅበሩ ‹‹የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ታሪክ 2000 ዓመት ወደኋላ ሄዶ ማስላቱ ብቻውን፣ ‹‹አንዲት ኢትዮጵያን በመፍጠር ስም ምኒልክና ተከታዮቹ ያስፈኑትን ጭቆና በጠመንጃ ለማስወገድ በረሓ ገባን›› ከሚሉት የህወሓት መሥራቾች ጋራ ሊያጋጨው መቻሉ የሚጠበቅ ነበር፡፡ ጉዳዩን ከለጠጥነው ደግሞ ‹‹ማኅበሩን በ1980ዎቹ አጋማሽ እንደ ስጋት ይመለከተው የነበረውን ‹የሸዋ ፊውዳል› ወደ ሥልጣን ለማምጣት ያደፈጠ ተቃናቃኝ አድርጎ ፈርጆት ነበር›› ወደሚል ጠርዝ ሊገፋን ይችላል፡፡ በነገራችን ላይ፣ በፖሊቲካው መንገድ ለሹመት የበቁት አቡነ ጳውሎስም እስከ ኅልፈታቸው ድረስ ማኅበሩ በሸዋ ተወላጅ ጳጳስ ሊተካቸው የሚያሤር ይመስላቸው እንደነበር ይነገራል፡፡
በጥቅሉ በኢሕአዴግና በማኅበረ ቅዱሳን መካከል የርእዮተ ዓለም (በብሔር እና በኢትዮጵያዊነት ላይ የተመሠረተ) ልዩነት መኖሩ ላለመግባባቱ መነሾ ነው፡፡
ሌላው የቅራኔአቸው መንሥኤ፣ በወርኃ ሚያዝያ ፲፱፻፺፫ ዓ.ም ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያምና ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ጋራ ሰብአዊ መብትንና አስተዳደራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት ባደረጉ ማግሥት፣ በዋናው ግቢ ከተቀሰቀሰው ተቃውሞ ጋራ የሚያያዘው ኹነት ነው፡፡ በወቅቱ ተማሪዎቹ በሰላማዊ መንገድ ላቀረቡት ጥያቄ የጸጥታ አስከባሪዎች የኃይል ምላሽ መስጠታቸው ጉዳዩን ከቁጥጥር ውጭ አደረገው፡፡ ድብደባውና ማሠቃየቱ ከአቅም በላይ የኾነባቸው የተወሰኑ ተማሪዎችም ከመንበረ ፓትርያርኩ በአጥር ወደሚለየው ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ሸሽተው ይገባሉ፡፡ በአካባቢው የነበሩ የጸጥታ ሠራተኞችም የግቢውን በር ይቆልፋሉ፤ ተማሪዎቹንም በኃይል አስወጥተው ደብድበው አሰሯቸው፤ ድርጊቱንም ማኅበረ ቅዱሳን በስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ የቤተ ክርስቲያኗን ለሸሸ መጠለያነት ታሪክ አጣቅሶ አጠንክሮ መቃወሙ ከመንግሥት ጋራ በዐደባባይ ቅራኔ ውስጥ ከተተው፡፡
ሌላው ቅራኔአቸውን ያጦዘው ክሥተት ደግሞ በአቶ ተፈራ ዋልዋ በ፲፱፻፺፰ ዓ.ም ወርኃ ጥቅምት ‹‹መንግሥትና አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› በሚል ርእስ ለዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ሥልጠና በተሰጠበት ወቅት ኦርቶዶክስን ‹‹የነፍጠኞች ምሽግ››፣ ጥምቀቱንም ‹‹በውኃ መንቦጫረቅ›› ብሎ ማጣጣሉ ሲኖዶሱን ግድ ባይሰጠውም፣ ማኅበረ ቅዱሳንን አስቆጥቶ መልስ እንዲሰጥ ያደረገበት ኩነት መፈጠሩ ነበር፡፡
የመዋቅሩ ስፋትና የውጥረቶቹ ጡዘት
የማይቆጣጠረውን የተደራጀ ኃይል አጥብቆ ለሚፈራው ኢሕአዴግ፣ የማኅበሩ መዋቅር እየሰፋ መሄድ ስጋት ላይ ጥሎታል፡፡ አባላቱ የዩኒቨርስቲ ወይም ኮሌጅ ምሩቃን መኾናቸው ከገጠር እስከ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ ድረስ የራሱ ሰዎች እንዲኖሩት አድርጓል፡፡ የአገዛዙም ጭንቀት ‹‹ይህ ኃይል አንድ ቀን በተቃውሞ ፖሊቲካ ሊጠለፍ ይችላል›› የሚል ነው፡፡ ይህንንም የሚያረጋግጠው አቶ ኣባይ ፀሃየ መስከረም ፲፪ ቀን ፳፻፪ ዓ.ም. የማኅበሩን አመራር በሲኖዶስ ጽ/ቤት ባነጋገረበት ወቅት ‹‹ኢሕአዴግ ገለልተኛ የሚባል ነገር አይገባውም›› የሚል መኾኑን ስናስታውስ ነው፡፡
. . .በኢሕአዴግና በቅንጅት መካከል በድኅረ ምርጫ – 97 የተፈጠረውን አለመግባባት ቤተ ክርስቲያኗ የቄሣርን ለቄሣር ብላ ለማንም ሳትወግን ዕርቅ እንዲፈጠር መሸምገል እንዳለባት ማኅበሩ በልሳኖቹ መወትወቱ የተገላቢጦሽ አገዛዙን አስኮረፈው፡፡ በአናቱም ከአማራ ክልል የተላከው ሪፖርት፣ ‹‹በገጠር ያሉ የማኅበሩ አባላት ለተቃዋሚዎች ቀስቅሰዋል›› ማለቱ ውጥረቱን አንሮታል፡፡
በሌላ በኩል መንግሥት ለሦስተኛ ጊዜ ባካሄደው የሕዝብ ቆጠራ ‹‹የ[ኦርቶዶክስ]ክርስቲያኑ ብዛት 33 ሚልዮን ነው›› ማለቱ፣ ‹‹45 ሚልዮን ነው [የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያን መረጃ በመጥቀስ ከሚለው ማኅበረ ቅዱሳን ጋራ አለመግባባት ውስጥ ከቶት እንደነበር ይታወሳል፡፡
የኢሕአዴግ ክሦች
ኢሕአዴግ በ፲፱፻፺፱ ዓ.ም በጅማ በሻሻ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ካህናትና ምእመናን ‹‹የእስልምና እምነት ተከታዮች ናቸው›› በተባሉ አንገታቸው በስለት ተቆርጦ መገደላቸውን የሚያሳየውን ፊልም በሲዲ አባዝቶ ያሰራጨውም ኾነ ከጭፍጨፋው ጀርባ የመንግሥት እጅ አለበት የሚል የስም ማጥፋት ዘመቻ የመራው ማኅበሩ ነው ብሎ ያምናል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ በአዲስ አበባ ‹‹ኢትዮጵያ የክርስቲያን ደሴት ናት››፣ በጎንደር ‹‹ጎዶልያስ›› (የእግዚአብሔር ጦር) የሚል ጽሑፍ የታተሙባቸው ቲሸርቶች አዘጋጅቶ ያሰራጨው ማኅበረ ቅዱሳን ነው ሲል ይከሳል፡፡ በነሐሴ ወር ፳፻፭ ዓ.ም በፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሽፈራው ተክለ ማርያም ስም ‹‹የአክራሪነት/ጽንፈኝነት ዝንባሌዎችና መፍትሔዎቻቸው›› በሚል ርእስ የተሰራጨው ሰነድ ክሡን፡- ‹‹ኢትዮጵያ የክርስቲያን ደሴት ነች፤ አንድ አገር አንድ ሃይማኖት ወዘተ ጉዳዮችን በማቅረብ በአንድ በኩል የሃይማኖት ብዝኃነትን የሚፃረር፣ በሌላ በኩል ደግሞ አገራችን የሃይማኖት ብዝኃነት መኾኗን የሚቃወም አካሄድ ነው፤›› ሲል ያጠናክረዋል፡፡
የኦቦይ ስብሃት ኩዴታ
በ፳፻፩ ዓ.ም ፓትርያርኩ አቡነ ጳውሎስ ከሲኖዶሱ ጠንካራ ተቃውሞ አጋጥሟቸው እንደነበር ይታወሳል፡፡ ይኹንና ከዚህ ንቅናቄ ጀርባ አቡነ ሳሙኤልና ሁለት የማኅበረ ቅዱሳን አባላትን የያዙት ኦቦይ ስብሃት ነጋ እንደነበሩበት ለጉዳዩ ቅርብ ከነበሩ ሰዎች አረጋግጫለኹ፡፡ አቦይ ስብሃት ‹‹አቡነ ጳውሎስ ለኢሕአዴግ ዕዳ ነው›› ብለው መደምደማቸው ለኩዴታ እንዳነሣሣቸው ይነገራል፡፡
. . .[በተቃውሞው] ውጤት ፓትርያርኩ አሸነፉ፡፡ ማኅበሩ የእንቅስቃሴው ተቃዋሚ መኾኑን የተረዱት አቦይ ስብሃት ነጋ ጥርስ እንደነከሱበት ይነገራል፡፡ በነገራችን ላይ፣ የአቦይ ዕቅድ ቢሳካ ኖሮ ተያይዘው የሚነሡ አለመግባባቶችን በመጠቀም ማኅበሩን መምታትንም የሚያካትት ነበር፡፡
የዋልድባ ጉዳይ
በመንግሥትና በማኅበረ ቅዱሳን መካከል የነበረውን አለመግባባት ወደላቀ ጠርዝ ያደረሰው በዋልድባ ገዳም አካባቢ ይቋቋማል የተባለው የስኳር ፋብሪካ ጉዳይ ነው፡፡ በገዳሙ የሚኖሩ ምእመናንን ጨምሮ በርካታ የእምነቱ ተከታዮች ያሰሙትን ተቃውሞ ችላ በማለት ወደ ሥራ ለመግባት በሞከረው መንግሥት ላይ የተነሣው ተቃውሞ ተጠናክሮ ቀጠለ፡፡ ይኹንና ሥርዐቱ ገዳሙ ላይ አልደርስም ብሎ ሲከራከር፣ ቤተ ክህነትም የማጣራት ሥራ መሥራቱን ገልጦ ‹‹ምንም ዐይነት ችግር የለም›› ብሎ ከመንግሥት ጎን ቆመ፡፡
ማኅበረ ቅዱሳን ጉዳዩን ቦታው ድረስ ሄዶ የሚያጣራ አምስት አባላት ያለው ቡድን ወደ ዋልድባ ላከ፡፡ ቡድኑ አጥንቶ ባቀረበው ሪፖርት፡- ‹‹16.6 ሄክታር መሬት ከገዳሙ ተወስዷል፤ ገዳሙን የውኃ መጥለቅለቅ ያሰጋዋል፤ . . .›› የሚል ሪፖርት ለመንግሥት አቅርቧል፡፡ በተቃራኒው ደግሞ የዶ/ር ሽፈራው ሰነድ የማኅበሩን ጥናት እንዲህ ሲል ኮንኖታል፡- ‹‹መንግሥት በሃይማኖታችን ጣልቃ ገብቷል በሚል ገሃድ ፍላጎትና ድብቅ አሠራር ካላቸው የውጭ ቡድኖች ጋራ በማበር ሰላምን አደጋ ውስጥ የማስገባት፣ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዐቱን በሃይማኖት ሽፋን ለመናድ ይንቀሳቀሳሉ፡፡ በቅርብ በነበረው የፓትርያርክ ምርጫና በዋልድባ ገዳም ዙሪያ የተፈጠረው ዝንባሌ የነዚህ ፍላጎቶች ማሳያ ነው፡፡››
የፓትርያርኩ ኅልፈት
በ፳፻፬ ዓ.ም መጨረሻ አቡነ ጳውሎስ ማለፋቸው ሌላ ፍጥጫን አስከትሏል፡፡ ማኅበሩ ስደተኛውን ፓትርያርክ አቡነ መርቆሬዎስን ከአሜሪካ አምጥቶ ወይም እንዳሻው የሚያሽከረክረውን ጳጳስ መንበሩ ላይ ለማስቀመጥ ምርጫው በሚፈልገው መንገድ እንዲጠናቀቅ በርትቶ እየሠራ ነው የሚለው ወቀሳ የመንግሥት ቁጣን የበዛ አድርጎታል፡፡ የጠቀሱት ሰነድም ውንጀላውን በገደምዳሜ ገልጾታል፡- ‹‹በእስልምናም ይኹን በክርስትና ሃይማኖቶች ሽፋን የሚደረገው የአክራሪነት/ጽንፈኝነት እንቅስቃሴ በዋናነት እየነጣጠረ የሚገኘው የተቋማቱን የበላይ አመራር ዕርከኖች መቆጣጠር ነው፡፡››
ናዳው እየመጣ ነው?
ባለፉት ሁለት ዓመታት የእስልምና እምነት ተከታዮች ‹‹መንግሥት በሃይማኖታችን ጣልቃ አይግባ›› በሚል የጀመሩትን ትግል ተከትሎ አገዛዙ ማኅበረ ቅዱሳንንም ደርቦ የመምታት ዕቅድ እንዳለው የሚጠቁሙ ምልክቶች ታይተዋል፡፡ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤትን በሚኒስትር ማዕርግ የሚመራው አቶ ሬድዋን ሑሴን፣ ‹‹መንግሥት ጉዳዩን በሰላም ቢጨርሰው የተሻለ ነው›› ሲሉ ምክር ለመለገሥ ለሞከሩ የምዕራብ አገሮች ዲፕሎማቶች፣ ‹‹የአወሊያን ቡድን በዚህ መልኩ ሳናበረክከው ቀርተን መጅሊሱን እንዲወስድ ብናደርግ፣ ነገ ደግሞ ማኅበረ ቅዱሳን ‹ሲኖዶሱን አምጡ› ቢለን ምን መለስ ይኖረናል?›› ሲል የሰጠው ምላሽ ይህንኑ የሚመለክት ነው፡፡
የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር መ/ቤት ባለፈው ዓመት ወርኃ የካቲት ‹‹ለሃይማኖት ተቋማት የተዘጋጀ›› ብሎ ያሰራጨው ሰነድ ማኅበረ ቅዱሳን እና መብታቸው እየጠየቁ ያሉ የእስልምና እምነት ተከታየች የጥቃቱ ዒላማ እንደኾኑ ያሳያል፡፡ ሂደቱን በመምራትም ኾነ በማስፈጸም ከፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር ጀርባ ኾኖ በዋናነት የሚሠራው የፀረ ሽብር ግብረ ኃይል እንደኾነ ይታወቃል፡፡ ዶ/ር ሽፈራው ተክለ ማርያም ‹‹የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የፖሊቲካ ርብርብ ሜዳ አይኾኑም፤ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችም ከማንኛውም ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴ ነጻ መኾን አለባቸው›› ያሉበት ዐውድ ‹‹በዩኒቨርስቲዎች የአካዳሚ ትምህርትን ተገን በማድረግ እምነትን ማስፋፋት አይቻልም›› በማለት ማኅበሩ እንደ ቀድሞው አባላቱን ለማስተማር የሚችልበትን ኹኔታ የሚያግድ ነው፡፡
በ፳፻፮ ዓ.ም በዩኒቨርስቲዎች ይተገበራል የሚባለው አለባበስንና አመጋገብን የሚመለከተው መመሪያም ራሱን የቻለ አደጋ አለው፡፡ እንዲሁም የሃይማኖት ማኅበራት ዓላማቸውን አሳውቀው እንዲመዘገቡ የሚያስገድደውን ሕግ በምክር ቤት ለማጸደቅ ዝግጅቱ ተጠናቋል፡፡ መዝጋቢው ክፍል ማኅበራቱን በፍርድ ቤት ከማስቀጣት እስከ ማፍረስ የሚያደርስ ሥልጣን እንደሚሰጠው ምንጮቼ መረጃ አድርሰውኛል፡፡ ይበልጥ የመንደነግጠው ደግሞ በዚህ መልክ ማኅበራቱን ከጠለፉ በኋላ ማንም ሰው ‹‹ቅዱስ ቃሉን›› ለመስበክ ፈቃድ ማግኘትን ግዴታ ለማድረግ መታቀዱን ስናነብ ነው፡-
‹‹የሰባክያን/ዳኢዎች ሚናን የበለጠ ለማጎልበትና የተጠያቂነት ሥርዐት ለመትከል እያንዳንዱ የሃይማኖት ተቋም የራሱን መምህራን የሚለይበትን የመታወቂያ ሥርዐት ሊያበጅና በዚህም የክትትል ሥራ እንዲሠሩ መደገፍ ይቻላል፡፡››
ሰነዱ ወደ መንፈሳዊ ኮሌጅ የሚገቡ ተማሪዎችንም መልምሎ የሲኖዶሱን፣ የማኅበረ ቅዱሳንን፣ የመጅሊስን. . .አመራርነት የመያዝ ዕቅድ እንዳለው በዘወርዋራ ይጠቁማል፡፡ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር በ፳፻፬ ዓ.ም ባዘጋጀው የሥልጠና ማንዋል ላይም ‹‹በኦርቶዶክስ ክርስትና መድረክ አክራሪው ኃይል ማኅበረ ቅዱሳን ነው›› ሲል መፈረጁ ይታወሳል፡፡ ከዚህ ጎን ለጎንም የማኅበረ ቅዱሳንን ግቢ ጉባኤ በማዳከም፣ ከሰንበት ት/ቤቶች፣ ከሰበካ ጉባኤና ከሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጆች ጋራ በማጋጨት፣ በካህናት በማስወገዝና በመሳሰሉት ተጠቅሞ ሊያፈርሰው እንደተዘጋጀ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
በጥቅሉ ሰነዱ ማኅበረ ቅዱሳንን ‹‹በሃይማኖት ሽፋን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት መንግሥታዊ ሃይማኖት መኾን ይገባዋል በሚል በአቋራጭ በአቋራጭ የፖለቲካ መሣርያ ለማድረግ የሚንቀሳቀስ›› ሲል ይኮንነዋል፡፡ ‹‹የአክራሪነትና ጽንፈኝነት ምንጩን ለማድረቅ እየተሠራ የሕግ የበላይነትን የማስከበር ሥራም ጎን ለጎን መፈጸም ያለበት ነው፤›› ሲል ጥቁምታ ይሰጣል፡፡
መፍትሔው ምንድን ነው?
ከላይ በጥቅሉ እንደጠቀስኩት የ22 ዓመታቱ ሂደት የሚያስረግጠው፣ የኢሕአዴግን ማንኛውም ዓለማዊም ኾነ ሃይማኖታዊ ተቋማት ነጻነት ያለማክበሩ ብቻ ሳይኾን ቀስ በቀስ ህልውናቸውን ለዘላለሙ ለማጥፋት በሙሉ ኃይሉ እየሠራ እንደኾነ ነው፡፡
. . . ማኅበሩ ዝምታውን በመግራት የራሱን ህልውና እጅግ በፍጥነት ለመታደግ መሞከር ይኖርበታል፡፡ ከሥርዐቱ የፖሊቲካ ዘዬ እንደተረዳነው ቀስ በቀስ እየተረዳነው በመጣው አፈና ላይ ማኅበሩ አንገቱን ቀብሮ፣ ጣልቃ ገብነቱን ቸል ብሎ የማንገራገሩ አካሄድ፣ በአንድ ክፉ ቀን በመጅሊሱ የተፈጸመው ታሪክ በራሱም ላይ መደገሙ አይቀሬ እንደኾነ ለመናገር ነቢይ መኾንን አይጠይቅም፡፡ የትምህርት ተቋማትን የረገጡ ከተሜ ወጣቶች በማኅበሩ ውስጥ መብዛታቸው የመውጫ መንገዱን በአመራሩ ላይ ይጥለዋል፤ ‹‹ለትላንት አናረፍድም፤ ለነገ አንዘገይም›› እንዲሉ የቤተ ክርስቲያኗ ሊቃውንት፡፡
ማስታወሻ፡- ጽሑፉ ከአንዳንድ መረጃውና ይዘቱ አንጻር መጠነኛ አርትዖት ተደርጎበት የቀረ

                                   በአውሮጳ   የካህናት አንድነት ማኅበር ሊቋቋም መሆኑ ታወቀ በ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከመላዋ አውሮጳ   የተውጣጡ ካህናት፡” የ...