2014 ኤፕሪል 8, ማክሰኞ

ኒቆዲሞስ

 

 

ምስባክ

መዝ.16: 3 "ሐወጽከኒ ሌሊተ ወፈተንኮ ለልብየ፡፡
 አመከርከኒወአተረክበ ዓመፃ በላዕሌየ፡፡
 ከመ ኢይንብብ አፉየ ግብረ እጓለ እመሕያው፡፡"

ትርጉም፦ 
በሌሊትም ጐበኘኸኝ፤ ልቤንም ፈተንኸው÷ፈተንኸኝ÷ 
ዐመፅምአልተገኘብኝም የሰውን ሥራ አፌ እንዳይናገር÷
ስለ ከንፈሮችህ ቃል ጭንቅ የሆኑ መንገዶችን ጠበቅሁ


ኒቆዲሞስ ዮሃ ፫፤፪ 

                 
ከፈሪሳዊያን ወገን የሆነ የአይሁድ አለቃ የሆነ ኒቆዲሞስ የሚባል አንድ ሰው በሌሊት ወደ ጌታ እየሄደ ይማር ነበር ኒቆዲሞስ ከቀኑ ክፍለ ጊዜ ይልቅ የሌሊቱን ጊዜ ለትምህርት ለምን መረጠ ?
         

           . ኒቆዲሞስ መምህር ስለነበር ስማር ሰዎች ቢያዩኝ ውዳሴ ከንቱ መምህር መባል ይቀርብኛል ብሎ ነው እኛስ ዛሬ የዘላለም ህይወት የሚሰጠንን ቅዱስ ቃል ብትህትና መማር ሲገባን ለምድራዊ ክብር ብለን በቀን ጊዜያችን መማር ያልቻልን ስንቶቻችን ነን ስለዚህ ቀን ጊዜአችንን በአግባቡ ልንጠቀምበት ይገባል
 ‹ ማንም ሊሰራ የማይችልባት ሌሊት ትመጣለችናዮሃ ፱፤፬

 .ኒቆዲሞስ የአይሁድ መምህር ስለነበር እንዳያዩት ፈርቶ ሌሊት እየመጣ ይማር ነበር እኛስ ዛሬ ልባችን የተረዳውን እውነት በግልጥ እንዳንፈጽም በፍራቻ በይሉኝታ የምንሰውር ስንቶቻችን ነን
 ‹
ፍጹምፍቅር ፍርሃት የለውም ፍርሃት ቅጣት አለውና፩ዮሃ ፬፤፲፰   ፍርሃትን አስወግደን ለእውነት ልንቆም ይገባል::


    ኒቆዲሞስ ከቀን ልብ ይልቅ የሌሊት ልብ የተካተተ ስለሆነ በሙሉ ልቡ በማስተዋል ለመማር ስለፈለገ ከቀኑ ክፍለ ጊዜ ይልቅ የማታውን መረጠ ዛሬስ ስንቶቻችን ነን ቅዱስ ቃሉን በማስተዋል ከልብ ሆነን የምንማር የሰማነው ቅዱስ ቃል በህይወታችን ፍሬ እንዲያፈራ ቅዱስ ቃሉን ከልብ ሆነን በማስተዋል ልንሰማ ይገባናል ቃሉን ሰምቶ የሚያስተውል ልብ መልካም መሬት ተብ
በመልካም መሬት የተዘራውም ይህ ቃሉን ሰምቶ የሚያስተውል ነውማቴ ፲፫፡፳፫

    አንዳንዶቻችን ጸሎት እያደረግን እንኳን አንደበታችን የእግዚአብሄርን ቃል ይነዳል ልባችን ሌላ ቦታ ይንጎዳጎዳል በማህበር ጸሎትም አብረን እየጸልይን በመሃል ሳይን አውት አርገን ልክ ሲፈጸም አለቀ እንዴ ብለን ሳይን ኢን የምናደርግ አንጠፋም
       

      ሌሊት ጨለማ ነው ብርሃን የለም ይህም የኃጢአት ምሳሌ ነው ኒቆዲሞስ በሌሊት መምጣቱ በኃጢአት እንዳለ ንስሃ እንደሚፈግ ያስረዳናል ዛሬስ ስንቶቻችን ነን ቅዱስ ቃሉን ስንሰማ በተአምኖ ኃጢአት በንስሃ ውስጥ ሆነን የምንሰማ ያለንስሃ የምንሰማው ቃል በህይወታችን ፍሬ የማፍራት እድሉ ጠባብ ነው ምክንያቱም በንስሃ ከልባችን ያልጸዱት ክፉ ምኞቶች እንደ እሾህ ሆነው ያንቁታልና
ሌላውም በእሾህ መካከል ወደቀ እሾህም ወጣና አነቀውማቴ፲፫፤፰  ተብሎ የተጻፈው ለዚህ ነው
          

   ሌሊት የቆየው ኪዳን ወይም የብሉይ ኪዳን ምሳሌ ነው ኒቆዲሞስም እኔ ምሁረ ኦሪት እንጂ ምሁረ ወንጌል አይደለሁም ወንጌልን ካንተ እማር ዘንድ ያስፈልገኛል ሲል በሌሊት ይመጣ ነበር ብሉያት ከሓዲሳት ጋር ተዋህደው ሲተረጎሙ ሰሙና ወርቁ ተጣምሮ የሕይወት ትምህርት ያስገኛል አንዳንዶች ዛሬ ብሉያት ጭራሽ አያስፈልጉም ሲሉ ይደመጣሉ ነገር ግን እንደ ኒቆዲሞስ ሁለቱን ኪዳናት አዋህዶ መጓዝ ትክክለኛው መንገድ ነው ለዚህም ነው ጌታ ሲያስተምርእውነት እላችኋለው ሰማይና ምድረስኪያልፍ ድረስ ከህግ አንዲት የውጣ ወይም አንዲት ነጥብ አታልፍምማቴ፭፤፲፰ በማለት አበክሮ የተናገረው ኒቆዲሞስ ምንም እንኳን የቀኑ ክፍለ ጊዜ ባይመቸውም በሌሊቱ ሰአት ለመማር እኛም ከሱ ተምረን ከልብ ካለቀሱ እንባ አይጠፋምና ምንም ስራ ቢበዛብን ለቅዱስ ቃሉ ጊዜ አይጠፋምና ህይወት ለሚገኝበት ትምህርት ጊዜ ልንሰት ይገባል።

2014 ኤፕሪል 1, ማክሰኞ

የዐቢይ ጾም ስድስተኛ ሰንበት ገብርሔር

Thursday, March 27, 20140 comments

የዐቢይ ጾም ስድስተኛ ሰንበት ገብር ሔር (ቸር አገልጋይ) የተሰኘው ሲሆን ይህንን ስያሜ ያገኘበትም ምክንያት ከዋዜማው ጀምሮ የሚዘመረው ጾመ ድጓ ‹‹ገብር ሔር ወገብር ምእመን ገብር ዘአስመሮ ለእግዚኡ፤ ጌታውን ያስደሰተው አገልጋይ ታማኝና ቸር አገልጋይ ነው፡፡  ገብርሔር በጎ አገልጋይ ማለት ሲሆን የስያሜውን መነሻ የምናገኘው በዕለቱ ሥርዓተ ቅዳሴ ከሚነበበው የወንጌል ክፍል ማቴ.25-14-30 ነው፡፡


ምስባክ     መዝ. 39÷8 
"ከመ እንግር ፈቃደከ መከርኩ አምላኪየ፡፡ 
ወሕግከኒ በማዕከለ ከርሥየ፡፡
 ዜኖኩ ጽድቀከ በማኅበር ዐቢይ፡፡"

ትርጉም፦ አምላኬ ሆይ፥ ፈቃድህን ለማድረግ መከርሁ፥
 ሕግህም በልቤ ውስጥ ነው።
 በታላቅ ጉባኤ ጽድቅህን አወራሁ።

ወንጌል
ማቴ. 25÷14-30 “መንገድ እንደሚሄድ÷ አገልጋዮቹንም ጠርቶ ሊያተርፉበት ገንዘቡን እንደ ሰጣቸው ሰው እንዲሁ ይሆናልና፤ ለእያንዳንዱ እንደ ችሎታው ለአንዱ አምስት÷ ለአንዱ ሁለት÷ ለአንዱም አንድ ሰጠና ወዲያውኑ ሄደ፡፡ ያ አምስት መክሊት የተቀበለውም ሄደ፤ ነግዶም ሌላ አምስት መክሊት አተረፈ፡፡ እንዲሁም ሁለት የተቀበለው ሌላ ሁለት አተረፈ፡፡ አንድ መክሊት የተቀበለው ግን ሄዶ ምድርን ቈፈረና የጌታዉን ወርቅ ቀበረ፡፡ ከብዙ ጊዜም በኋላ የእነዚያ አገልጋዮች ጌታ ተመልሶ ተቈጣጠራቸው፡፡ አምስት መክሊት የተቀበለውም ቀረበና፡- አቤቱ አምስት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ እነሆ ሌላ አምስት አተረፍሁ ብሎ አምስት መክሊት አስረከበ፡፡ ጌታውም፡- መልካም÷ አንተ የታመንህ በጎ አገልጋይ በጥቂት የታመንህ ስለ ሆንህ በብዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው፡፡ ሁለት መክሊት የተቀበለውም መጥቶ፡- አቤቱ÷ ሁለት መክሊትን ሰጥተኸኝ አልነበረምን? እነሆ ሌላ ሁለት መክሊትን አተረፈሁ አለ፡፡ ጌታውም፡- መልካም÷ አንተ የታመንህ በጎ አገልጋይ በጥቂቱ የታመንህ ስለ ሆንህ በብዙ አሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው፡፡ አንድ መክሊት የተቀበለውም መጣና እንዲህ አለ፡- አቤቱ÷ አንተ ካልዘራህበት የምታጭድ÷ ካልበተንህበትም የምትሰበስብ ጨካኝ ሰው እንደ ሆንህ አውቃለሁ፤ ስለ ፈራሁም ሄድሁና መክሊትህን በምድር ውስጥ ቀበርሁ፤ እንግዲህ እነሆ÷ መክሊትህ፡፡ ጌታውም መልሶ አለው፡- አንተ ክፉና ሰነፍ አገልጋይ÷ እኔ ካልዘራሁበት የማጭድ÷ ካልበተንሁበትም የምሰበስብ ጨካኝ ሰው እንደ ሆንሁ ታውቃለህን? ገንዘቤን ለለዋጮች መስጠት በተገባህ ነበር፤ እኔም ራሴ መጥቼ ገንዘቤን ከትርፉ ጋር በወሰድሁ ነበር፡፡
 ከዚያ የቆሙትንም እንዲህ አላቸው፤ ይህን መክሊት ከእርሱ ተቀብላችሁ ዐሥር መክሊት ላለው ስጡት፡፡ ላለው ሁሉ ይሰጡታልና፤ ይጨምሩለታልም፤ ለሌለው ግን ያንኑ ያለውን ይወስዱበታል፡፡ ክፉውን አገልጋይ ግን÷ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ወዳለበት በውጭ ወደ አለ ጨለማ አውጡት፡፡


ዲያቆን (ምንባብ) 
2ኛ ጢሞ.2÷1-15 ልጄ ሆይ÷ አንተም በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ በርታ፡፡ በብዙ ምስክሮች ፊት ከእኔ የሰማኸውን ትምህርት ለሌሎች ሊያስተምሩ ለሚችሉ ለታመኑ ሰዎች እርሱን አስተምራቸው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደሚያገለግል በጎ አርበኛ ሆነህ መከራ ተቀበል፡፡ ወደ ሰልፍ የሚሄድ÷ አለቃውን ደስ ያሰኝ ዘንድ ነው እንጂ የዚህን ዓለም ኑሮ አያስብምና፡፡ የሚታገልም ቢሆን እንደ ሕጉ ካልታገለ አክሊልን አያገኝም፡፡ የሚደክም አራሽም አስቀድሞ ፍሬውን ሊያገኝ ግድ ነው፡፡ ያልሁህን አስተውል፤ እግዚአብሔርም በሁሉ ነገር ጥበብን ይስጥህ፡፡
 በወንጌል እንደምሰብከው÷ ከሙታን ተለይቶ የተነሣውን ከዳዊት ዘር የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን አስበው፡፡ ስለ እርሱም እንደ ወንጀለኛ አስክታሰር ድረስ መከራ እቀበላለሁ፤ የእግዚአብሔር ቃል ግን አይታሰርም፡፡ ስለዚህ እነርሱ ደግሞ በኢየሱስ ክርስቶስ ያለውን ሕይወትና የዘለዓለም ክብር በሰማያት ያገኙ ዘንድ÷ ስለ ተመረጡት ሰዎች በሁሉ ነገር እታገሣለሁ፡፡ ነገሩ እውነት ነው፤ ከእርሱ ጋር ከሞትን ከእርሱ ጋር ደግሞ በሕይወት እንኖራለን፡፡ ብንታገሥም ከእርሱ ጋር ደግሞ እንነግሣለን፤ ብንክደው ግን እርሱም ይክደናል፡፡ ባናምነውም እርሱ የታመነ ሆኖ ይኖራል፤ ራሱን መካድ አይቻለውምና፡፡
እንግዲህ ይህን አሳስባቸው፤ በቃልም እንዳይጣሉ÷ በእግዚአብሔር ፊት ምከራቸው፤ ይህ ምንም የማይጠቅም÷ የሚሰሙትንም የሚያፈርስ ነውና፡፡የእግዚአብሔርን ቃል በእውነት አቃንቶ ሲያስተምር እንደማያፍር ሰራተኛ ሆነህ ፣ራስህን የተመረጠ አድርገህ  ለእግዚአብሔር ታቀርብ ዘንድ ትጋ።  

ንፍቅ ዲያቆን (ምንባብ)

 1ኛ ጴጥ.5÷1-11 እንግዲህ እኔ ከእነርሱ ጋር ሽማግሌ÷ የክርስቶስም መከራ ምስክር÷ ደግሞም ሊገለጥ ካለው ክብር ተካፋይ የሆንሁ በመካከላቸው ያሉትን ሽማግለዎችን እማልዳቸዋለሁ፡፡ በእናንተ ዘንድ ያሉትን የእግዚአብሔርን መንጋዎች ጠብቁ፤ ስትጠብቁአቸውም እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በውድ እንጂ በግድ አይሁን፤ በበጎ ፈቃድ እንጂ መጥፎውን ረብ በመመኘትም አይሁን፡፡ ለመንጋዉ ምሳሌ ሁኑ እንጂ ሕዝቡን በኀይል አትግዙ፡፡ የእረኞችም አለቃ በተገለጠ ጊዜ የማይጠፋውን የክብር አክሊል ትቀበላላችሁ፡፡ እንዲሁ እናንተ ጐልማሶች ሆይ÷ ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም ትሕትናን ልበሷት፤ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ያዋርዳልና፤ ራሳቸውን ዝቅ የሚያደርጉትን ግን ያከብራቸዋል፡፡
እንግዲህ በጐበኛችሁ ጊዜ ከፍ ከፍ ያደርጋችሁ ዘንድ ከጸናችው ከእግዚአብሔር ክንድ በታች ራሳችሁን አዋርዱ፡፡ እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት፡፡ እንግዲህ ዐዋቂዎች ሁኑ፤ ትጉም፤ ጠላታችሁ ጋኔን የሚውጠውን ፈልጎ÷ እንደሚያገሳ አንበሳ ይዞራልና፡፡ እርሱንም በእምነት ጸንታችሁ ተቃወሙት፤ እንዲህም ያለ መከራ በዓለም በአሉ ወንድሞቻችሁ ሁሉ እንደሚፈጸም ዕወቁ፤ ፍቅርንም አጽንታችሁ ያዙአት፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ዘለዓለም ክብሩ የጠራችሁ የጸጋ ሁሉ አምላክ ለጥቂት ጊዜ መከራን ከተቀበላችሁ በኋላ ፍጹማን ያደርጋችኋል፤ ያጸናችኋል፤ ልባሞችም ያደርጋችኋል፡፡ለእርሱ ክብርና ኅይል እስከ ዘለአለም ይሁን፤አሜን።
ንፍቅ ቄስ (ምንባብ)
የሐዋ.1÷6-8 እነርሱም ተሰብስበው ሳሉ÷ "ጌታ ሆይ÷ በዚህ ወራት ለእስራኤል ልጆች መንግሥትን ትመልሳለህን?” ብለው ጠየቁት፡፡ እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸው÷ “አብ በገዛ ሥልጣኑ የወሰነውን ቀኑንና ዘመኑን ልታውቁ አልተፈቀደላችሁም፡፡ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኅይልን ትቀበላላችሁ፤በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ሁሉ፣በሰማሪያና እስከ ምድር ዳርቻ ድረስም ምስክሮቸ ትሆኑኛላችሁ።"

ቅዳሴ
ዘባስልዮስ

የብፁዕ አቡነ ቶማስ ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ


አትም ኢሜይል
 መጋቢት 17 ቀን 2006 ዓ.ም.

abuna tomas
የቀድሞ ስማቸው አባ መዘምር ተገኝ የአሁኑ ብፁዕ አቡነ ቶማስ ጥር 14 ቀን 1932 ዓ.ም ጎጃም ደጋ ዳሞት ዝቋላ አርባዕቱ እንስሳ ተወለዱ፡፡ መሠረታዊ የቤተ ክርስቲያን ትምህርትን በሚገባ ከተማሩ በኋላ ጸዋትወ ዜማን ከመሪጌታ አንዱዓለምና መሪጌታ ካሣ ይልማ ፣ ቅኔ ከመሪጌታ ፈንቴ /ዋሸራ/፣ መጻሕፍተ ሐዲሳትን ከመሪጌታ ብርሃኑ ወልደ ሥላሴ ፣ መጻሕፍተ ሊቃውንትን ከመሪጌታ ቢረሳ ደስታ ተምረዋል፡፡ በዘመናዊ ትምህርትም እስከ 6ኛ ክፍል ፣ የእንግሊዝኛን ቋንቋ በግላቸው የተማሩና የመኪና ጽሕፈት /type writing/ የሚያውቁ ነበሩ፡፡ ብፁዕ አቡነ ቶማስ ዲቁና ከአቡነ ማርቆስ፣ ቅስና ከአቡነ ባልዮስ፣ ቁምስና ከብፁዕ አቡነ ተክለሃይማኖት ተቀብለዋል፡፡

abuna tomas 2በደብረ ሊባኖስ ገዳም መጻሕፍተ ሊቃውንትን ረዘም ላለ ጊዜ አስተምረዋል፡፡ በገዳሙ የሠራተኞች ቅርንጫፍ ማኅበር ሲቋቋምም የመጀመሪያው ሊቀ መንበር በመሆን አገልግለዋል፡፡ ከዚያም ወደ አዲስ አበባ ተዛውረው በጎፋ መካነ ሕያዋን ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል በአስተዳዳሪነትና መጻሕፍተ ሓዲሳትንና ሊቃውንትን በማስተማር የሚጠበቅባቸውን ተልእኮ ተወጥተዋል፡፡ ጥር 14 ቀን 1972 ዓ.ም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖት ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ አንብሮተ ዕድ ተሹመው ሰፊ አገልግሎት ሲሰጡ ቆይተዋል፡፡ ከዚያም ወደ አዲስ አበባ በመመለስ የታእካ ነገሥት በዓታ ለማርያምና መንበረ መንግሥት ግቢ ገብርኤል ገዳም የበላይ ጠባቂ ሆነው አገልግለዋል፡፡

ብፁዕነታቸው ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ የምእራብ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በመሆን ሲያገለግሉ ቆይተው፤ ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው መጋቢት 16 ቀን 2006 ዓ.ም መንበረ ጵጵስናቸው በሚገኝበት በፍኖተ ሠላም ከተማ ዐርፈዋል፡፡ ሥርዓተ ቀብራቸውም በዚያው በፍኖተ ሰላም እንደሚፈጸም ይጠበቃል፡፡

የአባታችንን ነፍስ በአብርሃምና በይስሐቅ እቅፍ ያኑረልን፡፡

2014 ማርች 27, ሐሙስ

የተዋሕዶው መዶሻ ጳጳስ አባ ቶማስ


 

ብፁዕ አቡነ ቶማስየምዕራብ ጎጃም(ፍኖተ ሰላም) ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
Abayneh Kassie's photo.
ከዲ/ን አባይነህ ካሴ
                                                                                            የተዋሕዶው መዶሻ ጳጳስ አባ ቶማስ
ረዘም ላሉ ጊዜያት በቅርበት ከማውቃቸው ብጹዓን አበው መካከል ሊቀ ጳጳስ አቡነ ቶማስ አንዱ ናቸው፡፡ ዜና ዕረፍታቸውን ስሰማ እጅግ አዘንሁ፡፡
- የተመሰከረላቸው ሊቅ
- ፊት ለፊት ዞሮ / ማማት የሌለባቸው/
- ጥቡዕ / በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተከሰተውን ርካሽ አስተዳደር በድፍረት የተቃወሙ እና የታገሉ/
- ቀናኢ
- ተሐድሶን ከቤተ ክርስቲያን ነቅሎ ለመጣል ያለ ማሰለስ የተጋደሉ ብርቱ
- እምነታቸውን በብርዕ ያደመቁ
- አባቶቻቸውን መስለው የኖሩ …ታላቅ አባት
አንድ ሊቅ ሲሞት አንድ ታላቅ ቤተ መጻሕፍት እንደተቃጠለ ይቆጠራል እንዲሉ እንዲህ እንዲህ እያሉ እየተሰናበቱን ሄዱ፡፡ እንኪያስ ምን ይበጀን ይሆን

በረከታቸው ይድረሰን እንጂ ሌላ ምን ይባላል፡፡
                 


የተዋሕዶው መዶሻ ጳጳስ አባ ቶማየተዋሕዶው መዶሻ ጳጳስ አባ ቶማስ
ረዘም ላሉ ጊዜያት በቅርበት ከማውቃቸው ብጹዓን አበው መካከል ሊቀ ጳጳስ አቡነ ቶማስ አንዱ
የተዋሕዶው መዶሻ ጳጳስ አባ ቶማስ
ረዘም ላሉ ጊዜያት በቅርበት ከማውቃቸው ብጹዓን አበው መካከል ሊቀ ጳጳስ አቡነ ቶማስ አንዱ ናቸው፡፡ ዜና ዕረፍታቸውን ስሰማ እጅግ አዘንሁ፡፡
- የተመሰከረላቸው ሊቅ
- ፊት ለፊት ዞሮ / ማማት የሌለባቸው/
- ጥቡዕ / በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተከሰተውን ርካሽ አስተዳደር በድፍረት የተቃወሙ እና የታገሉ/
- ቀናኢ
- ተሐድሶን ከቤተ ክርስቲያን ነቅሎ ለመጣል ያለ ማሰለስ የተጋደሉ ብርቱ
- እምነታቸውን በብርዕ ያደመቁ
- አባቶቻቸውን መስለው የኖሩ …ታላቅ አባት
አንድ ሊቅ ሲሞት አንድ ታላቅ ቤተ መጻሕፍት እንደተቃጠለ ይቆጠራል እንዲሉ እንዲህ እንዲህ እያሉ እየተሰናበቱን ሄዱ፡፡ እንኪያስ ምን ይበጀን ይሆን

በረከታቸው ይድረሰን እንጂ ሌላ ምን ይባላል፡፡
ናቸው፡፡ ዜና ዕረፍታቸውን ስሰማ እጅግ አዘንሁ፡፡
- የተመሰከረላቸው ሊቅ
- ፊት ለፊት ዞሮ / ማማት የሌለባቸው/
- ጥቡዕ / በቤተ ክርስቲያን
 

                                   በአውሮጳ   የካህናት አንድነት ማኅበር ሊቋቋም መሆኑ ታወቀ በ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከመላዋ አውሮጳ   የተውጣጡ ካህናት፡” የ...