2014 ጃንዋሪ 4, ቅዳሜ

ሰበር - ዜና የመስቀል ደመራ በዓል በዓለም ቅርስነት በዩኔስኮ መመዝገቡን ተከትሎ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የእንኩዋን አደረሳችሁ በማለት ገለጸችቅዳሜ ታኅሳስ 26 2006 ዓ.ም በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ በተዘጋጀው መርሃ ግብር ላይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ እንደተናገሩት የመስቀል ደመራ በዓል በአለም ቅርስነት በመመዝገቡ እንኩዋን ደስ አለችሁ ካሉ በኋላ በቀጣይም የጥምቀት በዓል ፤ የቅዱስ ያሬድ ዜማ ፤ ቅኔ፤ እና የ መጻሕፍት ትርጓሜ  በአለም ቅርስነት እነዲመዘገቡ ማስተዋወቅ ና በትጋትና በጥራት መስራት አለብን ብለዋል ቅዱስ ፓትርያርኩ  ለዚህ ታላቅ ውጤት ለመብቃት በባሕልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የቅርስና ጥበቃ ባለስልጣናት ቢሮን ተወካይ፤ የአዲስ አበባን አድባራትና ገዳማትን አመስግነዋል በተዘጋጀው የእንኩን ደስ አላችሁ በዓል ላይ ብፁዐን ሊቃነ ጳጳሳት የአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች ፤ካህናት ምእመናን ተገኙ ሲሆን የገነተ ጽጌ ቅዱስ ዑራኤል ደብር ሊቃውንት ወረብ  አቅርበዋል፡፡ በተቸማሪም ደብሩ ለተገኙት ተሳታፊዎች  የቁርስ መስተንግዶ አቅርቦአል፡፡

                                   በአውሮጳ   የካህናት አንድነት ማኅበር ሊቋቋም መሆኑ ታወቀ በ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከመላዋ አውሮጳ   የተውጣጡ ካህናት፡” የ...