፡፡ ከ60 በላይ ማህበራት ተወካዮች
የተገኑበት መንፈሳዊ ጉዞ ወደ ርእሰ አድባራት ወገዳማት አዲስ ዓለም ገዳም መጋቢት 7 ቀን 2006 ዓ.ም ያደረገው ህብረቱ በፓትርያርኩ
ረዳት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ
አቅራቢነት ከቋሚ ሲኖዶስ እውቅናን አግኝቷል፡፡
ወጣቶቹ የሚታወቁት በተለይ በጥምቀት በዓል ለታቦታቱ ምንጣፍ በማንጠፍ አስፋልቱን በማጽዳት ቄጠማ በመጎዝጎዝ ከመታወቃቸውም በተጨማሪ የተሃድሶን እንቅስቃሴን በመግታት ረገድ ከፍተኛውን
ድርሻ የተወጡ ናቸው፡፡ እነዚህን ወጣቶች ማንም ሳያነሳሳቸው በራሳቸው ተነሳሽነት የተነሱ ስለሆነ መሰልቸትና ወደኋላ ማፈግፈግ የሚባል
ነገር አይታይባቸውም፡፡ የወጣቱን ከፍተኛ መንፈሳዊ እንቅስቃሴ የተመለከተችዋ ቤተ ክርስቲያናችንም ለወጣቶቹ እውቅና
ሰጥታለች፡፡ መጋቢት 7 በተደረገው መንፈሳዊ ጉዞ ላይ በአሁን ሰዓት
የተሃድሶ ፕሮቴስታንትን የውስጥ አርበኞችን
በቤተክርስቲያን
ላይ እያሴሩ ያለውን ድብቅና ግልጥ አጀንዳቸውን በተመለከተ መረጃ
የቀረበ ሲሆን ወጣቶቹም ከዚህ በፊት ለቅዱስ ሲኖዶስ የቀረበውና ጉዳያቸው በይደር የተያዘውን ጉዳይ ከፍጻሜ እንዲያደርስና አፋጣኝ
መልስ ለህዝበ ክርስቲያኑ እንዲሰጥ ጠይቀዋል፡፡ በተለይ በቅርቡ ጉዳያቸው በይደር የተያዘላቸው ግለሰቦች ሾልከው
ወደ ቤተክርስቲያን መግባታቸውን የገለጹት ወጣቶቹ ቤተክርስቲያናችንን አናስደፍርም፤ ነቅተን እንጠብቃለን ተሀድሶ አራማጆች
ግለሰቦችን ወደ ቤተክርስቲያን በማስገባት የሚሯሯጡትን አባቶችም
ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡም አሳስበዋል፡፡ ቤተክርስቲያን የሁላችንም ናት ያሉት ወጣቶቹ ጥቂት አባቶች የቅዱስ ሲኖዶሱን
/ምለዓተ ጉባኤ/ አጀንዳ ወደ ጎን በመተው የሚወሰነው ውሳኔ ትክክል
አለመሆኑን የገለጹት ወጣቶቹ ወደፊትም በየደብራችን
ቤተክርስቲያናችንን ነቅተን መጠበቅ አለብን በማለት ተስማምተዋል፡፡
ከ6000/ ከስድስት ሺህ በላይ አባላት ያሉት ህብረቱ ወደፊትም ከሰንበት ት/ቤቶች ከሰበካ ጉባኤ አባላት ከምእመናንና ከሌሎች ማህበራት ጋር
በጋራ መበሆን የተሀድሶ እንቅስቃሴ ከመሰረቱ ነቅሎ እንደሚጥልም አቅጣጫ
ያስቀመጠ ሲሆን ማንኛውም ተባባሪ አካላትም ከጎናችን እንዲቆም ሲሉ
ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስም ይህንኑ የወጣቱን መንፈሳዊ እንቅስቃሴ በመደገፍ ና ወጣቱን ሰብስቦ በማወያየት አባታዊ
ምክርና ትምህርት በመስጠት ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጀምሮ የአባትነት ድርሻቸውን በሚገባ እንዲወጡም አሳስበዋል፡፡
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ መሠረት የሚቀርቡ መንፈሳዊ ትምህርቶች ፤መረጃዎች እና የመሳሰሉት የሚስተናገዱበት ገጽ ነው
ደንበኛ ይሁኑ ለ፡
ልጥፎች (Atom)
በአውሮጳ የካህናት አንድነት ማኅበር ሊቋቋም መሆኑ ታወቀ በ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከመላዋ አውሮጳ የተውጣጡ ካህናት፡” የ...
-
June 1, 2015 ከሐራ ዘተዋሕዶ በሐዋርያዊት፣ ጥንታዊት እና ብሔራዊት ቤተ ክርስቲያናችን ህልውና እና ዕድገት ፊት ከተጋረጡትና አፋጣኝ እልባት ከ...
-
‹‹…ወንድማችንን እናውቃቸዋለን፤ በእውነቱ ለፌ ወለፌ የማይሉ ደረቅ ሊቅ ናቸው፤ በሃይማኖቱ ዘርፍ ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን፣ ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን አንዲቱም ነጥብ እንዳትዛባ...