2014 ማርች 14, ዓርብ

ዐቢይ ጾም አራተኛ ሳምንት "መጻጉዕ"

 


ይህ ሳምንት የዐቢይ ጾም አራተኛ ሳምንት እሁድ ነው። ስሙም መጻጉዕ ይባላል። በዚህ እለት ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ድውያንን ፈውሷል፥ ጎባጣዎችን አቅንቷል፣ እውራንን አብርቷል፣ አንካሶችንም አድኗል ለምፃሞችንም በመለኮታዊ ሃይሉ አንጽቷል። ቤተ ክርስቲያናችንም በዚህ ዕለት ስለ ጌታችነ ገቢረ ተዓምራትና ስለ ድውያን ፈውስ በሰፊው ታስተምራለች። በቅዳሴ ጊዜ ይህንኑ የሚያስረዱ የመፃሕፍት ክፍሎችም ይነበባሉ። እነሱንም እንደሚከተለው ማየት እንችላለን።
የመጀመሪያ ምንባብ የሐዋርያው የቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት ወደ ገላትያ ሰዎች
ምዕራፍ 
፩. በነጻነት ልንኖር ክርስቶስ ነጻነት አወጣን፤ እንግዲህ ጸንታችሁ ቁሙ እንደ ገናም በባርነት ቀንበርአትያዙ። ፪. እነሆ፥ እኔ ጳውሎስ እላችኋለሁ። ብትገረዙ ክርስቶስ ምንም አይጠቅማችሁም። ፫.ሕግንም ሁሉ እንዲፈጽም ግድ አለበት ብዬ ለሚገረዙት ሁሉ ለእያንዳንዶች ደግሜ እመሰክራለሁ።፬. በሕግ ልትጸድቁ የምትፈልጉ ከክርስቶስ ተለይታችሁ ከጸጋው ወድቃችኋል። ፭.  እኛ በመንፈስከእምነት የጽድቅን ተስፋ እንጠባበቃለንና። ፮. በክርስቶስ ኢየሱስ ሆኖ፥ በፍቅር የሚሠራ እምነትእንጂ መገረዝ ቢሆን ወይም አለመገረዝ አይጠቅምምና። ፯. በመልካም ትሮጡ ነበር፤ ለእውነትእንዳትታዘዙ ማን ከለከላችሁ?፰.  ይህ ማባበል ከሚጠራችሁ አልወጣም። ጥቂት እርሾ ሊጡን ሁሉያቦካል። ፱-፲. የተለየ ነገር ከቶ እንዳታስቡ እኔ በጌታ ስለ እናንተ ታምኜአለሁ፤ የሚያናውጣችሁ
ማንም ቢኖር ግን ፍርዱን ሊሸከም ነው። ፲፩. ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ እኔ ገና እስከ አሁንመገረዝን ብሰብክ እስከ አሁን ድረስ ለምን ያሳድዱኛልእንኪያስ የመስቀል ዕንቅፋት ተወግዶአል።፲፪. የሚያውኩአችሁ ይቆረጡ። ፲፫. ወንድሞች ሆይ፥ እናንተ ለአርነት ተጠርታችኋልና፤ ብቻአርነታችሁ ለሥጋ ምክንያትን አይስጥ፥ ነገር ግን በፍቅር እርስ በርሳችሁ እንደ ባሪያዎች ሁኑ። ፲፬. ሕግ ሁሉ በአንድ ቃል ይፈጸማልና፥
እርሱም። ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ የሚል ነው። ፲፭. ነገር ግን እርስ በርሳችሁ
ብትነካከሱ ብትበላሉ እርስ በርሳችሁ እንዳትጠፋፉ ተጠንቀቁ። ፲፮.  ነገር ግን እላለሁ፥ በመንፈስተመላለሱ፥ የሥጋንም ምኞት ከቶ አትፈጽሙ። ፲፯. ሥጋ በመንፈስ ላይ መንፈስም በሥጋ ላይይመኛልና፥ እነዚህም እርስ በርሳቸው ይቀዋወማሉ፤ ስለዚህም የምትወዱትን ልታደርጉ አትችሉም።፲፰.  በመንፈስ ብትመሩ ግን
ከሕግ በታች አይደላችሁም። ፲፱. የሥጋ ሥራም የተገለጠ ነው እርሱም ዝሙት፥ ርኵሰት፥ ፳.መዳራት፥ ጣዖትን ማምለክ፥ ምዋርት፥ ጥል፥ ክርክር፥ ቅንዓት፥ ቁጣ፥ አድመኛነት፥ ፳፩.  መለያየት፥መናፍቅነት፥ ምቀኝነት፥ መግደል፥ ስካር፥ ዘፋኝነት፥ ይህንም የሚመስል ነው። አስቀድሜምእንዳልሁ፥ እንደዚህ ያሉትን የሚያደርጉ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም። ፳፪. የመንፈስፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥
እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው።፳፫.  እንደዚህ ያሉትን የሚከለክል ሕግ የለም። ፳፬. የክርስቶስ ኢየሱስም የሆኑቱ ሥጋን ከክፉ መሻቱና ከምኞቱ ጋር ሰቀሉ። ፳፭. በመንፈስ ብንኖርበመንፈስ ደግሞ እንመላለስ። ፳፮. እርስ በርሳችን እየተነሣሣንና እየተቀናናን በከንቱ አንመካ።
ሁለተኛ ምንባብ የያዕቆብ መልእክት
ምዕራፍ 
፲፬. ከእናንተ የታመመ ማንም ቢኖር የቤተ ክርስቲያንን ሽምግሌዎች ወደ እርሱ ይጥራ፤ በጌታምስም እርሱን ዘይት ቀብተው ይጸልዩለት። ፲፭.  የእምነትም ጸሎት ድውዩን ያድናል ጌታምያስነሣዋል፤ ኃጢአትንም ሠርቶ እንደ ሆነ ይሰረይለታል። ፲፮. እርስ በርሳችሁ በኃጢአታችሁተናዘዙ። ትፈወሱም ዘንድ እያንዳንዱ ስለ ሌላው ይጸልይ፤ የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግኃይል ታደርጋለች። ፲፯. ኤልያስ እንደ እኛ የሆነ ሰው ነበረ፥ ዝናብም እንዳይዘንብ አጥብቆ ጸለየ፥በምድርም ላይ ሦስት ዓመት ከስድስት ወር አልዘነበም፤ ሁለተኛም ጸለየ፥ ፲፰. ሰማዩም ዝናብን ሰጠምድሪቱም ፍሬዋን አበቀለች። ፲፱. ወንድሞቼ ሆይ፥ ከእናንተ ማንም ከእውነት
ቢስት አንዱም ቢመልሰው፥ ፳. ኃጢአተኛን ከተሳሳተበት መንገድ የሚመልሰው ነፍሱን ከሞትእንዲያድን፥የኃጢአትንም ብዛት እንዲሸፍን ይወቅ።
ሦስተኛው ምንባብ የሐዋርያት ሥራ
ምዕራፍ 3
፩. ጴጥሮስና ዮሐንስም በጸሎት ጊዜ በዘጠኝ ሰዓት ወደ መቅደስ ይወጡ ነበር። ፪. ወደ መቅደስምከሚገቡት ምጽዋት ይለምን ዘንድ፥ ሰዎች ተሸክመው መልካም በሚሉአት በመቅደስ ደጅ በየቀኑያስቀምጡት የነበሩ ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ አንካሳ የሆነ አንድ ሰው ነበረ። ፫. እርሱም ጴጥሮስናዮሐንስ ወደ መቅደስ ሊገቡ እንዳላቸው ባየ ጊዜ፥ ምጽዋትን ለመናቸው። ፬. ጴጥሮስም ከዮሐንስ ጋርትኵር ብሎ ወደ እርሱ ተመልክቶ። ወደ እኛ
ተመልከት አለው። ፭. እርሱም አንድ ነገር ከእነርሱ እንዲቀበል ሲጠብቅ ወደ እነርሱ ተመለከተ።፮. ጴጥሮስ ግን። ብርና ወርቅ የለኝም፤ ይህን ያለኝን ግን እሰጥሃለሁ፤ በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስስም ተነሣና ተመላለስ አለው።
፯.  በቀኝ እጁም ይዞ አስነሣው፤ በዚያን ጊዜም እግሩና ቍርጭምጭምቱ ጸና፥ ፰. ወደ ላይ ዘሎምቆመ፥ ይመላለስም ጀመር፤ እየተመላለሰም እየዘለለም እግዚአብሔርንም እያመሰገነ ከእነርሱ ጋር ወደመቅደስ ገባ። 9 ሕዝቡም ሁሉ እግዚአብሔርን እያመሰገነ ሲመላለስ አዩት፤ ፲. መልካምምበሚሉአት በመቅደስ ደጅ ስለ ምጽዋት ተቀምጦ የነበረው እርሱ እንደ ሆነ አወቁት፤ በእርሱምከሆነው የተነሣ መደነቅና መገረም ሞላባቸው። ፲፩. እርሱም ጴጥሮስንና ዮሐንስን ይዞ ሳለ፥ ሕዝቡሁሉ እየተደነቁ የሰሎሞን ደጅ መመላለሻ በሚባለው አብረው ወደ እነርሱ
ሮጡ። ፲፪. ጴጥሮስም አይቶ ለሕዝቡ እንዲህ ሲል መለሰ። የእስራኤል ሰዎች ሆይ፥ በዚህ ስለ ምንትደነቃላችሁወይስ በገዛ ኃይላችን ወይስ እግዚአብሔርን በመፍራታችን ይህ ይመላለስ ዘንድእንዳደረግነው ስለ ምን ትኵር ብላችሁ ታዩናላችሁ?
የዕለቱ ምስባክ
እግዚአብሔር ይረድኦ ውስተ ዓራተ ሕማሙ
ወይመይጥ ሎቱ ኩሉ ምስካቤሁ እምደዌሁ
አንሰ እቤ እግዚኦ ተሣሃለኒ።         መዝ.፵፥፫
እግዚአብሔር በደዌው አልጋ ሳለ ይረዳዋል
መኝታውን ሁሉ በበሽታው ጊዜ ያነጥፍለታል
እኔስ አቤቱ ማረኝ።       መዝ.፵፥፫
የዕለቱ ወንጌል የዮሐንስ ወንጌል
ራፍ 5
፩. ከዚህ በኋላ የአይሁድ በዓል ነበረ፥ ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ። ፪. በኢየሩሳሌምም በበጎችበር አጠገብ በዕብራይስጥ ቤተ ሳይዳ የምትባል አንዲት መጠመቂያ ነበረች፤ አምስትም መመላለሻነበረባት። ፫. በእነዚህ ውስጥ የውኃውን መንቀሳቀስ እየጠበቁ በሽተኞችና ዕውሮች አንካሶችምሰውነታቸውም የሰለለ ብዙ ሕዝብ ይተኙ ነበር። ፬. አንዳንድ ጊዜ የጌታ መልአክ ወደመጠመቂያይቱ ወርዶ ውኃውን ያናውጥ ነበርና፤ እንግዲህ ከውኃው መናወጥ በኋላ በመጀመሪያ የገባከማናቸው ካለበት ደዌ ጤናማ ይሆን ነበር። ፭. በዚያም ከሠላሳ ስምንት ዓመት ጀምሮ የታመመአንድ ሰው ነበረ፤ ፮. ኢየሱስ ይህን ሰው ተኝቶ ባየ ጊዜ፥ እስከ አሁን ብዙ ዘመን እንዲሁ እንደ ነበረአውቆ። ልትድን ትወዳለህንአለው። ፯. ድውዩም። ጌታ ሆይ፥ ውኃው በተናወጠ ጊዜበመጠመቂያይቱ ውስጥ የሚያኖረኝ ሰው የለኝም ነገር ግን እኔ ስመጣ ሳለሁ ሌላው ቀድሞኝይወርዳል ብሎ መለሰለት። ፰. ኢየሱስ። ተነሣና አልጋህን ተሸክመህ ሂድ አለው። ፱. ወዲያውምሰውዬው ዳነ አልጋውንም ተሸክሞ ሄደ። ፲. ያም ቀን ሰንበት ነበረ። ስለዚህ አይሁድ የተፈወሰውንሰው። ሰንበት ነው አልጋህንም ልትሸከም አልተፈቀደልህም አሉት። ፲፩. እርሱ ግን። ያዳነኝ ሰው። አልጋህን ተሸክመህ ሂድ አለኝ ብሎ መለሰላቸው። ፲፪. እነርሱም። አልጋህን ተሸክመህ ሂድያለህ ሰው ማን ነውብለው ጠየቁት። ፲፫. ዳሩ ግን በዚያ ስፍራ ሕዝብ ሰለ ነበሩ ኢየሱስ ፈቀቅብሎ ነበርና የተፈወሰው ሰው ማን እንደ ሆነ አላወቀም። ፲፬.  ከዚህ በኋላ ኢየሱስ በመቅደስአገኘውና። እነሆ፥ ድነሃል፤ ከዚህ የሚብስ እንዳይደርስብህ ወደ ፊት ኃጢአት አትሥራ አለው። ፲፭.ሰውዬው ሄዶ ያዳነው ኢየሱስ እንደ ሆነ ለአይሁድ ነገረ። ፲፮. ስለዚህም በሰንበት ይህን ስላደረገአይሁድ ኢየሱስን ያሳድዱት ነበር ሊገድሉትም ይፈልጉ ነበር። ፲፯. ኢየሱስ ግን። አባቴ እስከ ዛሬይሠራል እኔም ደግሞ እሠራለሁ ብሎ መለሰላቸው። ፲፰. እንግዲህ ሰንበትን ስለ ሻረ ብቻአይደለም፥ ነገር ግን ደግሞ ራሱን ከእግዚአብሔር ጋር አስተካክሎ። እግዚአብሔር አባቴ ነው ስላለ፥ስለዚህ አይሁድ ሊገድሉት አብዝተው ይፈልጉት ነበር። ፲፱. ስለዚህ ኢየሱስ መለሰ እንዲህምአላቸው። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብ ሲያደርግ ያየውን ነው እንጂ ወልድ ከራሱ ሊያደርግምንም አይችልም፤  የሚያደርገውን ሁሉ ወልድ ደግሞ ይህን እንዲሁ ያደርጋልና። ፳. አብ ወልድንይወዳልና፥ የሚያደርገውንም ሁሉ ያሳየዋል፤ እናንተም ትደነቁ ዘንድ ከዚህ የሚበልጥ ሥራ ያሳየዋል።፳፩. አብ ሙታንን እንደሚያነሣ ሕይወትም እንደሚሰጣቸው፥ እንዲሁ ወልድ ደግሞ ለሚወዳቸውሕይወትን ይሰጣቸዋል።
፳፪-፳፫. ሰዎች ሁሉ አብን እንደሚያከብሩት ወልድን ያከብሩት ዘንድ፥ ፍርድን ሁሉ ለወልድሰጠው እንጂ አብ በአንድ ሰው ስንኳ አይፈርድም። ወልድን የማያከብር የላከውን አብንአያከብርም። ፳፬. እውነት እውነት
እላችኋለሁ፥ ቃሌን የሚሰማ የላከኝንም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፥ ከሞትም ወደ ሕይወትተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም። ፳፭. እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ሙታን የእግዚአብሔርንልጅ ድምፅ የሚሰሙበት ሰዓት ይመጣል እርሱም አሁን ነው፤ የሚሰሙትም በሕይወት ይኖራሉ።

                                   በአውሮጳ   የካህናት አንድነት ማኅበር ሊቋቋም መሆኑ ታወቀ በ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከመላዋ አውሮጳ   የተውጣጡ ካህናት፡” የ...