2014 ጁን 28, ቅዳሜ

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም


 እንኩዋን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ
                                                                             
                 በ ዲ.ዮርዳኖስ አበበ
(ናታኒም ጡመራዊ መጽሔት ሰኔ 21 ትናንት ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሐዋርያት ወረደ: ፊልዽስዩስ በምትባል ሃገር በዼጥሮስ እጅ የመጀመሪያዋን ቤተ ክርስቲያን አነጸ ብለን ነበር:: በዚህች ዕለት ደግሞ አእላፍ መላዕክትን: ሰማያውያን ቅዱሳንን እና እናቱን ቅድስት ድንግል ማርያምን ይዟት ወረደ::

+ሐዋርያቱ አብዛኞቹ እዛው ሲጸልዩ አድረው ነበርና ጌታችን ከቅዳሴው በፊት 2 ነገሮችን አሳየ:-
-አስቀድሞ ቤተ ክርስቲያኗን በድንግል እናቱ ስም አክብሮ ሥርዓተ ቤተ ክርረስቲያንን አሳየ::
-ቀጥሎ ደግሞ ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ዼጥሮስን ከመካከል አቁሞ "አርሳይሮስ" ሲል ሾመው:: ይኼውም የዓለም ሁሉ ሊቀ ዻዻሳት (ፓትርያርክ) ማለት ነው:: በዚህ ጊዜ ቅዱሳን መላእክት "አክዮስ" እያሉ 3 ጊዜ አሰምተው ጮሁ:: አክዮስ ማለት በግዕዙ "ይደልዎ": በዐማርኛው ደግሞ "ይገባዋል: ያሥምርለት" እንደ ማለት ነው::

+ጌታችን ይሕን ከከወነ በሁዋላ ይቀድስ ዘንድ ጀመረ:: አማናዊት ማሕደሩን ድንግል ማርያምን መንበር አድርጎ: ቅዱስ ዼጥሮስ እንደ ተራዳኢ ካህን ቆሞ: ቅዱስ እስጢፋኖስ ሠራኢ ዲያቆን ሆኖ: ሐዋርያት ድንግልን ከበው: መላእክተ ብርሃን በክብራቸው ቁመው ጌታችን ቀድሶ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለወዳጆቹ አቀበለ::

2014 ጁን 26, ሐሙስ

የደብረ ሊባኖስ ገዳም አምስቱ ስያሜዎች




 ሰኔ 17 ቀን 2006 ዓ.ም.
የደብረ ሊባኖስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አንድነት ገዳም ገዳማዊ ሥርዓቱ እንደተጠበቀ ቢሆንም የጎርፍ አደጋ፤ የብዝኅ ሕይወት መመናመን፤ የሕገ ወጥ የመሬት ወረራና ሌሎችም ችግሮች እየተፈታተኑት ይገኛል፡፡ ይህንን ችግር ለመቅረፍና ዘላቂ መፍትሔ ለማምጣት በገዳሙና በማኅበረ ቅዱሳን ባለሙያዎች ፕሮጀክቶች ተቀርጸው ወደ ሥራ ተገብቷ



ፕሮጀክቶቹንም በተያዘላቸው እቅድ መሠረት ለማስፈጸም በጠቅላይ ቤተ ክህነት ስብከተ ወንጌል አዳራሽ ሠኔ 8 ቀን 2006 ዓ.ም. የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር ላይ ፕሮጀክቶቹንና ገዳሙን አስመልክቶ የተዘጋጀ መጽሔት ለምእመናን ተሰራጭቷል፡፡ ከመጽሔቱ ያገኘናቸውን ጥቂት መረጃዎች እናካፍላችሁ፡



Dedication of the Debre Libanos Church, November 18, 1962የደብረ ሊባኖስ አቡነ ተክለ ሃማኖት አንድነት ገዳም በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ከአዲስ አበባ ወደ ጎንደር- ጎጃም መውጫ በ104 ኪሎ ሜትር ርቀት፤ ወደ ምሥራቅ አቅጣጫ 4.5 ኪሎ ሜትር ተገንጥሎ የሚገኝ የአንድነት ገዳም ነው፡፡
ገዳሙ በጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት በ1296 ዓ.ም. የተቆረቆረ ሲሆን፤ 710 ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡ በገዳሙ አስተዳደር ሥር ከአቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን በተጨማሪ የቅዱስ አማኑኤል እና የቅዱስ ፊልጶስ አብያተ ክርስቲያናት ይገኛሉ፡፡

በገዳሙ ውስጥ የሚጎበኙ የተለያዩ የነገሥታት ሥጦታዎች፤ ቅዱሳት መጻሕፍት፤ ንዋየ ቅድሳት፤ የቅዱሳን አጽም፤ ፈውስ የሚገኝባቸው የጸበል ቦታዎችም ይገኛሉ፡፡

የደብረ ሊባኖስ ገዳም አምስቱ ስያሜዎችን ስንመለከት፡-

ምድረ ግራሪያ፡-
ግራሪያ የሚለውን ስያሜ የሰጠችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ ከወዳጇ ከጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ወደ ምድረ ግብጽ ስትሰደድ በኢትዮጵያ ውስጥ ከቆየችባቸው ቦታዎች አንዱ ይህ ቅዱስ ቦታ ነው፡፡ ለአንድ ሳምንት ቆይታ አድርጋ የቦታውን ስም ምድረ ግራሪያ ስትል ሰይማዋለች፡፡ ግራሪያ ማለት ኩሉ ይገርር ሎቱ፤ ሁሉ ይገዛላታል ማለት ነው፡፡ አንድም ግራር በቁሙ ለሁሉ ጥላ፤ መሰብሰቢያ እንደሆነ ደብረ ሊባኖስም የሁሉ ጥላ መሰብሰቢያ ነውና ምድረ ግራሪያ ተብሏል፡፡

2014 ጁን 10, ማክሰኞ

የ2006 ዓም የበጎ ሰው ሽልማት አሸናፊዎች ተሸለሙ



ከ120 ተጠቋሚ ኢትዮጵያውያን መካከል በበጎ ሰው ዳኞች የተመረጡት ሰባት ኢትዮጵያውያን ‹በጎ ሰዎች› ቅዳሜ ግንቦት 30 ቀን 2006 ዓም በኢሊሊ ሆቴል በተከናወነ ሥነ ሥርዓት ተሸለሙ፡፡

2014 ጁን 9, ሰኞ

አስቸኩዋይ ጥሪ ለምእመናን በሙሉ




የታላቁ የደብረ ሊባኖስ ገዳምን ለመርዳት  ገዳሙ ጥሪ አስተላለፈ ገዳሙ በአሁን ሰዓት በመሬት መንሸራተት ምክንያት  ከፍተኛ አደጋ እንደተጋረጠበት ተጠቅሶ ሰኔ 8 ቀን ከ7፡30 ጀምሮ በጠቅላይ ቤተ ክህነት የስብከተ ወንጌል አዳራሽ  ቅዱስ ፓትርያርኩ ብፁዓን  ሊቃነ ጳጳሳት እና ምእመናን  በሚገኙበት ፕሮግራም ላይ ስለሁኔታው ይገለጣልና ስለዚህ ስቸኩዋይ ጥሪ አስተላልፎአል

                                   በአውሮጳ   የካህናት አንድነት ማኅበር ሊቋቋም መሆኑ ታወቀ በ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከመላዋ አውሮጳ   የተውጣጡ ካህናት፡” የ...