ሚያዝያ 15 ቀን 2007 ዓ.ም.
በሰሜን ሊቢያ ሜድትራንያን ባሕር ዳርቻ በእምነታቸው ምክንያት በግፍ ከተገደሉ ኢትዮጵያውያን መካከል ቂርቆስ ቤተ ክርስቲያን አካባቢ ከሚገኙ የሰማዕታት ወላጆች ጋር የማኅበረ ቅዱሳን አመራርና አባላት ሐዘናቸውን እየተካፈሉ ነው፡፡
መርሐ ግብሩ በማኅበሩ መዘምራን ሰማዕታቱን የሚያስብ መዝሙር የቀረበ ሲሆን፤ መዝሙር 118፡ 129 ላይ ምስክሮችህ ድንቆች ናቸው፣ ስለዚህ ነፍሴ ፈለገቻቸው በሚል ርእስ ሰባኬ ወንጌል ዲያቆን ብርሃኑ አድማስ ትምህርት ሰጥተዋል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ጸሎተ ምሕላ የተካሄደ ሲሆን ከሰማዕታቱ በረከት ለመሳተፍ የእራት ማብላት ሥነ ሥርዓት በማኅበሩ አስተባባሪነት በቦታው ተካሔዷል፡፡ ራሱን እስላማዊ መንግሥት ብሎ የሚጠራው አይ ኤስ አሸባሪ ቡድን በአሰቃቂ ሁኔታ ከገደላቸው ኢትዮጵያውያን መካከል እስከ አሁን አምስቱ የቂርቆስ አካባቢ ክርስቲያኖች ሆነው ተገኘተዋል፡፡ |
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ መሠረት የሚቀርቡ መንፈሳዊ ትምህርቶች ፤መረጃዎች እና የመሳሰሉት የሚስተናገዱበት ገጽ ነው
2015 ኤፕሪል 24, ዓርብ
ማኅበረ ቅዱሳን በሊቢያ የተሰዉ ሰማዕታት ቤተሰቦችን በማጽናናት ላይ ይገኛል
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የተሰጠ መግለጫ
April 23, 2015 1 Comment
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤ አሜን
‹‹ርትዕት ሃይማኖቶሙ ለቅዱሳን አበዊነ = የአባቶቻችን ሃይማኖት የቀናች ናት››
ራሱን እስላማዊ መንግሥት (አይ ኤስ አይ ኤስ) እያለ የሚጠራው የጨካኝ አረመኔዎች ስብስብ፣ በግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ላይ ያካሔደው ዘግናኝ ግድያ ሳይበቃው ይህን እኩይ ድርጊቱን በልዩ ልዩ ምክንያት ከአገር ተሰድደው በሊቢያ በነበሩ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምእመናን ላይ ፈጽሟል፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ‹‹ሃይማኖቱን ገልጦ የማይናገር በክብር የተገለጠ አይኾንም››/ሃይ.አበ. 63÷41/ እንዳለው ‹‹ሃይማኖታችንን አንክድም፤ ማዕተባችንን አንበጥስም›› ባሉ የቤተ ክርስቲያን ልጆች ላይ ኢሰብአዊነት በተሞላበት ግፍ አንገታቸውን በሰይፍ በመቅላት እና ጭንቅላታቸውን በጥይት በመበታተክ በጭካኔ አገዳደል ገድሏቸዋል፡፡
ይህ ቡድን ከጨካኝ እና አረመኔ የግድያ ድርጊቱ አንጻር የአባላቱን ሰብአዊ ፍጥረት አጠራጣሪ የሚያደርገው ነው፡፡ እጆቻቸው በደም የተሞሉ ናቸው፡፡ ቅዱስ ዳዊት፣ ‹‹የሰውን ደም ለማፍሰስ እግራቸው ፈጣን ነው፤ በመንገዳቸው ኃሣር መከራ አለ፤ የፍቅርን መንገድ አያውቋትም፤ በልቡናቸው እግዚአብሔርን መፍራት የለም፤›› እንዳለው ነው፡፡ መዝ. 13(14)÷1-4፡፡
ስለኾነም በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ሥር የምንገኝ ሰንበት ት/ቤቶች፡-
- በየትኛውም ቦታ እና ጊዜ ክርስትናን በማስገደድ እና በመቀሰጥ ለመለወጥ የሚደረገውን ዘመቻ እና እንቅስቃሴ በጥብቅ እንቃወማለን፡፡
- ራሱን አይ ኤስ አይ ኤስ ብሎ የሚጠራውን ቡድን ድርጊት በጥብቅ እናወግዛለን፡፡
- በዚኹ ቡድን እና በቡድኑ የአሸባሪነት ድርጊት ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ያወጣቸውን የአቋም መግለጫዎች በሙሉ እንቀበላለን፤ በአፈጻጸሙም እንታዘዛለን፡፡
- በደቡብ አፍሪቃ በዜጎች እና ሌሎችም ወገኖች ላይ የሚፈጸመውን ጥላቻ እና ዘረኝነት የወለደው ግድያ እና ዘረፋ በጥብቅ እናወግዛለን፡፡
- በአዲስ አበባ ያሉ ሰንበት ት/ቤቶች ኹሉ መርሐ ግብር በማውጣት በየቤተሰቦቻቸው ቤት በመገኘት ሐዘንተኞችን የሚያጽናኑ ይኾናሉ፡፡
ወደፊትም ኹኔታውን እየተከታተልን የሚጠበቅብንን ድርሻ ለመወጣት ዝግጁ መኾናችንን እየገለጽን ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን፣ በተጋድሎ ላለፉት ወንድሞቻችን ደግሞ ዕረፍተ መንግሥተ ሰማያትን ልዑል እግዚአብሔር እንዲሰጥልን እንለምናለን፡፡
ልዑል እግዚአብሔር በሃይማኖታችን ያጽናን፤ ለዓለሙም ሰላም ይስጥልን፤ አሜን፡፡
የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት
የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት
ደንበኛ ይሁኑ ለ፡
ልጥፎች (Atom)
በአውሮጳ የካህናት አንድነት ማኅበር ሊቋቋም መሆኑ ታወቀ በ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከመላዋ አውሮጳ የተውጣጡ ካህናት፡” የ...

-
በ ዲ.ዮርዳኖስ አበበ (ናታኒም ጡመራዊ መጽሔት ሐምሌ 4 ) እንኳን ለአባቶቻችን ቅዱሳን 12ቱ ደቂቀ ነቢያት ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ +"+ +" 12ቱ ቅዱሳን ደቂቀ ነቢያት &quo...
-
ጾመ ፍልሰታ የእመቤታችን ዕረፍት Written By Hulubante Abebe on Tuesday, August 5, 2014 | 1:02 PM መ/ር ሳሙኤል ተስፋዬ ...
-
እምየዋ ! እምየ አድማሱ ጀምበሬ። ምነው በዕድሜ ደርሰን ዐይንዎን አይተን ድምፅዎን ሰምተን በነበር። ዛሬማ ቸልታችንን ዕድሜ ይንሳው እና ኹሉን ነገር ችላ ብለን ለነአባ ...