2015 ኦገስት 25, ማክሰኞ

ሁለተኛው ስደትና መፍትሔው

                                                                 በርሊን ደብረ ገነት አማኑኤል  ቤ/ክ በቅርቡ የተገዛ
                            
                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                           ሰዎች  ከአንዱ ሀገር ወደ ሌላው ሀገር በስደት መዘዋወሩ በጎላ በተረዳ
ይታወቃል ። ይሁን እንጂ ታዲያ የሚያሳዝነው ስደቱን እጥፍ የሚያደርገው የመንፈሳዊ አገልግሎት ፤የማኅሌቱ፤ የቅዳሴው ፤ የስብከተ ወንጌሉ እና የመሳሰለው መንፈሳዊ አገልግሎት  መተግበሪያ / መገልገያ ቤተክርስቲያን  አለመኖሩ ነው ። ምንም እንኩዋን በአውሮጳ /ፓ የሉተራውያን የካቶሊካወያን አቢያተ እምነታት  በሙሉ የተዘጉ እና የእምነቱ ተከታዮች ሁሉን ነገር ትተውታል ። እጅግ በሚያስደንቅ ጥበብ የታንጹ አቢያተ እምነቶቻቸው በጣም ያሳዝናሉ ። ጥቂት የሚሆኑ የእምነቱ ተከታዮች አረጋወያን በቻ እሁድ ረፋድ ላይ ይገኛሉ ። በስደት የሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን መእመናን በየአካባቢያችው ይህንኑ ቤተ እምነት አስፈቅደው  ይገለግሉበታል  አንዳንዶቹም አቅሙ ያላቸው  ውርሃዊ ክፍያ በመክፈል ይክራዩታል። ይህንን ማድረግ ያልቻሉ ግን እሁድ ጠዋት ሲከፈት ገብተው ቶሎ ቶሎ  ብለው ቅዳሴውን ቀድሰው ንዋዬ ቅዱሳቱን ይዘው ይወጣሉ ። ነሐሴ ኪዳነ ምሕረት የእመቤታችንን በዓለ ዕርገት  ለማክበር  ከሐምቡርግ  ፍራንክፈርት አቅራቢያ ወደ ምትገኝ ሐመረ ኖህ ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን  ተጓዝን  በዓሉ የተከበረው ነሓሴ 17 ነበረ   ቅዳሴው  በብፁዕ አቡነ ሙሴ የደቡብ መዕራብና ምሥራቅ አውሮጳ/ፓ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳሳት ኢየተመራ እያለ ሰዓት ደረሰ ቶሎ ታቦቱ ወጥቶ ቶሎ መግባት አለበት ስለተባለ ቶሎ ቶሎ  ታቦተ ድንግል ማርያም  ቶሎ ቶል ተብሎ ወጥቶ ቶሎ ተመልሶአል ወዲያውኑ ምንጣፉን መጋረጃውን  የመሳሰሉትን ንዋዬ ቅዱሳቱን ሰብስቦ መሮጥ ነው ።ይህኛውስ ስደት መፍትሔው ምንድንነው?
                               ብቸኛው አማራጭ የሉተራውያንን አቢያተ ክርስቲያናትን መግዛት  

ይህንን ለማድረግ የሚያስፈልገው አንደኛ ስለቤተ ክርስቲያን ጉዳይ በሚገባ የተረዳ በእምነቱ ጠንካራ የሆነ ምእመን፤ ማለትም መሰረታዊ  የሃይማኖታችንን ትምህርት በሚገባ የተገነዘበ  ለወደፊቱ ለልጆቹ በትኩረት የሚያስብ ያይማኖታዊ ዕቅድ ያለውና ምእመናኑን በማስተማር፤ በማስተባበር  ጥሩ ምሳሌ የሚሆን የሕዝቡን መሰረታዊ ችግር ተረድቶ መፍትሔ የሚፈልግ  አስተዳዳሪ  ካለ በቀላሉ መግዛት ይቻላል ። ለዚህ ጥሩ ምሳሌ መላከ ገነት ቆሞስ አባ ብርሃነ መስቀል የበርሊን ደብረ ገነት አማኑኤል ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ  ከፍተኛ እንቅስቃሴ የሕዝቡ ተሳትፎ  ያመጣው ውጤት  በበርሊን ደረጃውን የጠበቀ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን መግዛታችው ትልቅ የምሥራች ነው ። መላክ ገነት አባ ብርሃን መስቀልን ምስጋና ይገባቸዋል ። የሙኒክ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል  ቤተ ከርስቲያን የመግዝት እንቅስቃሴም በመፋጠን ላይ ይገኛል። የሀገረ ስብከቱም ሊቀ ጳጳስ አቡነ ሙሴ ከሀገረ ሰብከቱ  ሠራተኞች ፤ የአድባራት አስተዳዳሪዎች በማኅበረ ቅዱሳን አውሮጳ/ፓ ማዕከል ፤ ምእመናንን በማስተባበር ውጤታማ ሥራ በመሥራት ላይ ይገኛሉ።
ይሁን እንጂ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ  ለዚህ ሁሉ ጅምር በጎ አገልግሎት በተለይ በአውሮጳ/ፓ እንቅፋት  እየሆነ የመጣው እንፈውሳለን ፤ እናጠምቃለን  ባሕታውያን ነን የሚሉ ገለሰቦች  ለበጎ ነገር በአንድነት ተባብሮ ያገለግል ይገለገል የነበረውን  ዳግመኛ እንዳይስማማ አድርገው በመከፋፈል ላይ መገኘታቸውና ሕዝቡም ያለ ማስተዋል መከተሉ ትልቅ ችግር ሆኖ ይታያል ፡፤ ከዚህ በተረፈ ግን የራሳችንን ቤተ ክርስቲያን የመግዛቱን ነገር በትኩረት መመልከት ይገባል ። እግዚአብሔር ይርዳን ።

 ማስገንዘቢያ ሁለቱ የሉተራን ቤተ እምነት ናቸው

2015 ኦገስት 24, ሰኞ

ሀገሬን ከሀገሬ ውጪ አገኘኋት

          ሐምቡርግ ዩኒቨርስቲ
አንድ ሰው
  ከሀገር ሲወጣ ያየውን ሁሉ ከሀገሩ ጋር በማወዳደር  ይህን ሀገሬ ቢኖራት እያሉ መመኘት ልማድ ነው ። እኔም በተለያዩ የኣውሮጳ/ፓ ሀገራት ለአገልግሎት ስዘዋወር እንዲሁ መመኘቴ አልቀረም ይሁን እንጂ ግን ሀገሬን ከሀገሬ ውጪ አገኘኋት  ያልኩበት ነገሩ እንዲህ ነው ። ዐርብ ጠዋት   ከጀርመን ዋና ከተማ በርሊን  ተነስተን ከመላከ ገነት ቆሞስ አባ ብርሃነ መስቀል  የበርሊን ደብረ ገነት አማኑኤል ቤተ ክርስቲያንና የሐምቡርግ ደብረ መድኃኒት ኪዳነምሕረት አብያተ ክርስቲያናት  አስተዳዳሪ ጋር ነሐሴ 1የእመቤታችንን በዓለ ዕርገት ለማክበር ወደ ሐምቡርግ ከተማ አመራን  ዕድሜ ለቤተክርስቲያን ልጆች ተቀበሉን   እንደሰማችሁ /እንዳያችሁት  ሐምቡርግ ሲነሳ የሐምቡርግ ዩኒቨርስቲ መነሳቱ አይቀሬ ነው ። እኔም ከታላቁ ሊቅ መጋቤ ስብሐት ተክሌ ሲራክ  ጋር በመሆን ሐምቡርግ ዩኒቨርስቲን መጎብኘት ጀመርን  ዕድሜና ጤንነት ለዶ/ር ጌቴ ገላዬ  በጀርመን ሐምቡርግ ዩኒቨርስቲ የአማርኛ ቛንቛ ሥነ ጽሑፍ እና የአፍሪቃ ሥነ ቃል መምህር ናቸው በተለይ ስለገራችን ባህልና  ቛንቛዎች  ጉዳይ  እያነሱ  ብዙ ሥራ ባለመሰራቱ እየተቃጠሉ  ይኖራሉ።  በቁጭት ቃላት እያብራሩ  የአፍሪቃና  የኢትዮጵያ ቛንቛዎች እና ባህል ጥናት ክፍ  ል ጀምረን  ጉብኝታችንን ቀጠልን  ምን ልበላችሁ! የሀገራችንን ቛንቛ  ባህል  ከፍተኛ ትኩረትና ክብር ተሰጥቶ  በዚሁ ክፍል የሚማሩ ሩሲያውያንና የሌሎች ሀገሮች ዜጎች ፈረንጆች  በኢትዮጵያ ቛንቛዎችና ባህል  እንዲሁም በቅዱሳን ገድላት ላይ ጥናት ሲያደርጉ  የግዕዝ  መዝገበ ቃላት  ጥናት  ሲያደርጉ  በየቢሮአቸው የኢትዮጵያ ባህልና ገዳማትን የሚገልጡ ፎቶዎችን  በመለጠፍ  አማርኛ ቛንቛ ሲናገሩ  ስመለከት ሀገሬን ከሀገሬ ወጪ አገኘኋት  አልኩ አለመታደል ሆኖ እኛ  ለሃይማኖታችን ለባህላችን  የኛ ለምንናቸው ሁሉ ትኩረት አለመስጠታችን  ሀገራችን ከሀገራችን ውጪ ትገኛለች።  ሀገር ማለት ሃይማኖት  ከነሥርዓቱ ፤የሕዝቡ ባህልና አለባበስ በዓላትና አከባበራቸው  ወዘተ ....  ማለት ነው እነዚህ ከተሰደዱ  ሀገሪቷ ከሀገር ወጣች ያስብላልና ።ይቆየን
ከሐምቡርግ  ጀርመን                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                  እነዚህን ፎቶዎችን  ተመልከቱ
                                                                               
                                                           የግዕዝ ጥናት ፕሮጀክት







2015 ኦገስት 5, ረቡዕ

በእንተ ሙኒክ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያንና ሊቀ ብርሃናት ቆሞስ አባ ገብረ ሕይወት ፍስሐ [ጀርመን ]


ምእመናን  ከአንዱ ሀገር ወደ  ሌላው ሀገር በተለያየ ምክንያት  መሰደዳቸው አይቀሬ  ነው:: ታዲያ ሲሰደዱ በሄዱበት  ሀገር  ሁሉ ቤተክርስቲያን ያስፈልጋቸዋል :: ምንም አያጠያይቅም  የተመቻቹ  ሁኔታዎችም  አሉ :: ቤተክርስቲያን መግዛት ይቻላል :; ምናልባት የሀገረ ስብከቶች   ወጥ የሆነ መዋቅር አለመኖር  የምእመናኑ  አንድ ሐሳብ አለመሆን  ወዘተ  ችግሮች  ውጤታማ  የሆነ መንፈሳዊ አገልግሎት ለመስጠት  ችግሮች ይታያሉ :: የህዝቡ መንፈሳዊ  ተነሳሽንት  ግን ይበል የሚያሰኝ ነው :: በተለይ አንዳንድ  አድባራት ቤተክርስቲያን ለመግዛት  የሚያደርጉት እንቅስቃሴ  በጣም ግሩም ነው :;ለዛሬ የማካፍላችሁ  ስለሙኒክ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል  ቤተክርስቲያን ነው  [ጀርመን ] ሙኒክ /ሙንሽን  ማለት  የመነኮሳት  ከተማ  ማለት ነው :: ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አለ  በዚያ የሚኖሩ ምእመናን በጣም  ጠንካሮች  ናቸው :: “ጓደኛህን ንገረኝና ማንነትህን  ልንገርህ”  እንደተባለው  የሕዝቡ  ጥንካሬ  የቤተክርስቲያን  ግዥ እንቅስቃሴውን  ልነግራችሁ  አልችልም;;  ምስጢሩ  ደግሞ ልንገራችሁ ?  ; የሊቀ ብርሃናት ቆሞስ  አባ ገብረ ሕይወት ፍስሐ  ከፍተኛ  እንቅስቃሴ  ውጤት ነዋ !
ሊቀ ብርሃናት  ቆሞስ አባ ገብረ ሕይወት ፍስሐ   በጀርመን  የሙኒክ  ደብረ ብሥራት  ቅዱስ  ገብርኤል ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ  ናቸው:: ሀገር ቤት /  ኢትዮጵያ አዲስ አበባ  ኢያሉ  በተለያዩ  አድባራት  በአስተዳዳሪነት  ለረጅም ጊዜያት  አገልግለዋል::

ሊቀ ብርሃናት አባ ገብረ ሕይወት  የቅዳሴ መምህር  ናቸው  አቋቋም አዋቂ ማኅሌታዊ ናቸው  ከሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ  መንፈሳዊ ኮሌጅ  በዲፕሎማ  ; ከቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ  የመጀመሪያ ድግሪ አግኝተዋል ሙኒክ ከሚገኘው  ሉድቪግ ማክስሚልያንስ  ዩኒቨርሲቲ  የጀርመንኛ  ቋን ቋ  ሰርተፍኬት ተቀብለዋል አሁንም በመማር ላይ ይገኛሉ :: ሲቀድሱ ማኅሌት ሲቆሙ  ሲያስተምሩ  ሕዝቡን  ለበጎ ነገር  ሲያስተባብሩ  በተለይ ቤተክርስቲያን ለመግዛት  በሚያደርጉት የማስተባበር  የማስተዳድር  ልዩ ስጦታቸ  በሀገር ቤትም ሆነ በዚሁ በጀርመን በሀገረ ስብከቱም  ሆነ በሕዝቡ ዘንድ የተመሰከረላቸው ናቸው አስቀዳሹ ሁሉ ሳይቀር መልክዐ ውዳሴውን  በሚገባ አሰልጥነዋል  ለድቁናም የበቁ ደቀመዛሙርትም  አፍርተዋል 
በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ሊቀብርሃናት ሊቀብርሃናት  ደከመኝ ሰለቸኝ ማለት አያውቁም :: ታዲያ እንዲህ ያሉ አባቶች ከአገልግሎት  ፍላጎት እስክ  ብቃት  .ከብቃት እስከ ውጤታማንት  የተዋጣላቸው አባቶቻች  ጥቂቶች  ቢሆኑም  ምእመናኑ እንደነዚህ  ያሉ አባቶችን  ከጎናቸው በመቆም  አብሮ ማገልገል ይገባል :: በሙኒክ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል  ቤተክርስቲያንን  ለመግዛት  እየተደረገ  ያለው እንቅስቃሴ  በጣም የሚበረታታ  ነው :: 

                                   በአውሮጳ   የካህናት አንድነት ማኅበር ሊቋቋም መሆኑ ታወቀ በ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከመላዋ አውሮጳ   የተውጣጡ ካህናት፡” የ...