2013 ዲሴምበር 11, ረቡዕ

“ይቅርታ አድርጉልን ?” :- የቤተ ክህነቱ ተቋማዊ ድቀት ምስክሮች ስልተ ነገር(በጽጌ ማርያም)

December 10, 2013 at 10:16am
በቅርቡ የበጋሻው  ደሳለኝ እና የያሬድ አደመ ቀኖናዊ ያልሆነ የ“ይቅርታ አድርጉልን ?”እግረ ጉዞ ለብዙዎች የመነጋገሪያ ጉዳይ ሆኗል፡፡የ“ይቅርታ አድርጉልን ?”ሒደትም የመጀመሪያ እንጂ የመጨረሻ እንደማይሆንም በራሳቸው “ይቅርታ አድርጉልን ?”በሚሉት እና ከቤተ ክርስቲያን አውጥተው “እምነ ጽዮን ”የስደተኞች ማኀበር በሚል በፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ መስመርነት በሐዋሳ ከአደራጆት ቡድናቸው ጋር መከፋፈላቸውም ገላጭ እሆነ ነው፡፡ይህ ቀኖናዊ አግባቦችን  አላሟላም የሚባለው የ“ይቅርታ አድርጉልን ?”እግረ ጉዞ   ያስከተለው መለስተኛ ውዝግብ በልጆቹ ብቻ አልተወሰነም፡፡ደዌው ተዛምቶ እውነተኛ የቤተ ክርስቲያን ልጆችንም አምሶ ነበር፡፡አሁንም ቢሆን ( በመሠረቱ )የጉዳዬን ማዕከላዊ ጭብጥ እና መነሻ አድበስብሶ የሚያልፍ ከመሆን የታደገው ያገኘ አይመስልም፡፡
“ይቅርታ አድርጉልን ?”እግረ ጉዞ ላይ የሚነሡትን ክርክሮች ወይም አሳቦች በሁለት ከፍሎ ማየት ይቻላል፡፡አንደኛው በይቅርታ በራሱ ተፈጥሯዊ ምንነትና ትርጉም ላይ ያነጣጠረ ነው፡፡ይቅርታ ምንድ ነው? ውግዘት ምንድ ነው? በቤተ ክርስቲያን ትምህርት፣በቀኖና ድንጋጌዎችና ትውፊትስ ያለው ቦታ ምንድ ነው? የማዉገዝ ምክንያቶች ምንድ ናቸው? መናፍቃን የሚወገዙት እንዴት ነው? እንዴትስ ይመለሳሉ?የሚሉትን ጥቄዎች በመመለስ ላይ የሚሽከረከሩ ናቸው፡፡ይህ ክርክር ዕውቀት ሰጪነቱ እንደተጠበቀ ሆኖ በግልብ ምሁራዊነት(pseudo intellectualism)የተጣበበ መሆኑንም መደበቅ አይቻልም፡፡በዚህም ምክንያት ከስልት አኳያ ዕውቀት ሰጪነቱ ጎጂ ባይሆንም በቀጥታ“ይቅርታ አድርጉልን ?”የሚሉትን ልጆች  ወይም የሐዋሳውን አፈንጋጭ ስብስብ በአድራሻ ገላጭ አይደለም፡፡ሁለተኛው በ”ይቅርታ አድርጉልን”ባዬቹ ትእምርታዊ(symbolic) ትርጉም ላይ ያነጣጠረ ነው፡፡ይህ ምልክታ በአብዛኛው ‹ውጫዊ› በተለይም ፖለትካዊ፣ ክልላዊነትና ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ዘውጌነት የሚጫነው ነው፡፡የ”ይቅርታ አድርጉልን”ን ውዝግብ ከጥቅስ እና ከቀኖና ክርክር ለጥጦ በመመልክት አገራዊ እና ምዕመን ዐቀፍ ገጽታ ለመስጠት

2013 ዲሴምበር 9, ሰኞ



    የካህናት ሥልጠና ለቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ ለውጥ ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው ተገለጠ

                                                                                                     

                                                           ምስካበ ቅዱሳን አቡነ ኪሮስ ቤተ ክርስቲያን 
              ካህናቱ በሥልጠና ላይ
                          የካህናት ሥልጠና ለቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ ለውጥ ከፍተኛ ድርሻ 

  በሰሜን ሸዋ ሰላሌ ሀገረ ስብከት በሚገኘው በለገጣፎ ምስካበ ቅዱሳን አቡነ ኪሮስ  ቤተ ክርስቲያን የሚገኙ ካህናትና ዲያቆናት ለሁለት ቀናት የቆየ ሥልጠና ተከታለዋል ፡፡ሥልጠናው  መንፈሳዊ አገልግሎትና  ትምህርተ ኖሎት  ሲሆን  የካህናት  አገልግሎት መንፈሳዊ  ከመሆኑ የተነሳ ሕዝበ ክርስቲያኑን  በመንፈሳዊ ሕይወታቸው ከፍተኛ  ለውጥ ማምጣት ይችሉ ዘንድ  ስልጠናው አስፈላጊ መሆኑን ተጠቁሟል ፡፡ በተለይ ካህናት ከንስሓ ልጆቻቸው ጋር ያለው  ግንኙነት እንዴትና በምን መልኩ መሆን እንዳለበትና ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት መስጠት ይችሉ ዘንድ ትምህርተ ኖሎት መሰልጠን አስፈላጊ መሆኑ ተገልጦአል  ሥለጠናው የተዘጋጀው በደብሩ ስብከተ ወንጌል አስተባባሪነት ሲሆን ሰበካ ጉባኤውም ይሁንታውን መለገሱ ታውቆአል ፡፡ በሥልጠና ላይ የተሳተፉት ካህናትና ዲያቆናት መምህራንም ሥልጠናው ወደፊትም ቢቀጥል ጥሩ ነው ካሉ በኋላ ሥልጠናው ከደብሩ አስተዳደር /ከላይ መጀመር እንዳለበት አበክረው ጠቁመዋል የቤተ ክርስቲያን ትልቁ ችግር ከላይ በከፍተኛ አስተዳደር ላይ የተቀመጡ የደብሩም  አስተዳደር ስልጠና እንደሚያስፈልገው በአጽንኦት ተናግረዋል አያይዘውም የደብሩን ስብከተ ወንጌልን እናመሰግናለን ብለዋል ፡፡የደብሩ ስብከተ ወንጌል ወደፊትም ከካህናቱ ጋር በመሆን የንስሓ ልጆቻቸውን  ለማስተማር ሁኔታዎችን እያመቻቸ መሆኑም ተገልጦአል ፡፡ ደብሩ እጅግ በጣም ሰፊ መሬት ያለው ሲሆን ጠንካራ አስተዳደር ህዝብንና ካህናትን ያማከለ ዘመኑን የዋጀ አስተዳደር እንደሚያስፈልግም በተደጋጋሚ ተጠቁሞአል  ዘመኑ ዝም ተብሎ የሚተኛበት ዘመን አይደለም ያሉት ካህናቱ ተደጋጋሚ ሥልጠናዎች ያስፈልጉናል ብለዋል ፡፡ ጻድቁ አቡነ ኪሮስ ልጅ የሌላቸውን ልጅ ያገኙ ዘንድ የሚያስችል ቃልኪዳን የተሰጣቸው መሆኑ የሚታወቅ በመሆናቸው ብዙ ምእመናን እየተሳሉ /ገድላቸውን በመሸከም በአዓመቱ ልጅ ተሸክመው እቦታው ድረስ ይሄዳሉ  በዚህ ምክንያት በጣም ብዙ ሕዝብ የሚጎበኘው ታላቅ ቦታ በመሆኑ የተቀላጠፈ ጠንካራ አስተዳደር የሰለጠኑ ካህናት ስለሚያስፈልግ  ስልጠናው መዘጋጀቱን የደብሩ ስብከተ ወንጌል ክፍሉ ገልጦአል ወደፊትም ተጠናክሮም ይቀጥላልም ተብሎአል::


                                  የደብሩ ሰባክያነ ወንጌል ሊቀ ጠበብት ገረመው እና መምህር ቀለመወርቅ




2013 ዲሴምበር 5, ሐሙስ

               

ሰበር ዜና – የመስቀል ደመራ ክብረ በዓል የመጀመሪያው የኢትዮጵያ የዓለም መንፈሳዊ ቅርስ ኾኖ በዩኔስኮ ተመዘገበ

(ሪፖርተር፤ ኅዳር ፳፮ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም.)

ኄኖክ ያሬድ
Meskel Demera Celebration at Meskel Squareየኢትዮጵያው የመስቀል ክብረ በዓል በዓለም ቅርስነት መመዝገቡን ዩኔስኮ አስታወቀ፡፡ ዩኔስኮ የመስቀል ክብረ በዓልን (Commemoration feast of the finding of the True Holy Cross of Christ) በዓለም ቅርስነት መመዝገቡን ኅዳር 25 ቀን ይፋ ያደረገው፣ በኢንታንጀብል (መንፈሳዊ) ባህላዊ ቅርሶች ጥበቃና ክብካቤ ላይ የሚሠራው ኮሚቴው ስምንተኛውን ጉባኤ እያካሄደባት ካለው የአዘርባጃኗ ባኩ ከተማ ነው፡፡
ስለ ቅርሱ የመረመረው ኮሚቴ ባቀረበው ውሳኔ ሐሳብ ላይ እንደተመለከተው፣የመስቀል ክብረ በዓል የኢትዮጵያን ሃይማኖታዊና ባህላዊ ትውፊቶችን የያዘ፣ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ መምጣቱና በአገሪቱ ማኅበራዊ አንድነትንና የርስ በርስ ትስስርን፣ ብዝኃነትንም የሚያንጸባርቅ፣ በበርካታ ብሔረሰቦች ባህሎች መካከል ትስስርን የፈጠረ በመኾኑ ዓለም አቀፍ መስፈርቱን አሟልቷል ብሎታል፡፡

2013 ዲሴምበር 3, ማክሰኞ



                                                                   ሀገረ ማርያም

ሀገረማርያም ከተማ  

ከአዲስ አበባ 467 ኪሎ ሜትር ነው፡፡በደቡብ ክልላዊ ምንግስት ቦረና ዞን ውስጥ የምትገኝ የወረዳ ከተማ ናት ሀገረ ማርያም የመጀመሪያ  ስሟ ኩኩ ትባላለች  በኋላ ደግሞ ሀገረ ማርያም ስትባል ቆይታ  አሁን ደግሞ ቡሌ ሆራ እየተባለች ትጠራለች  በቅርቡ በከተማዋ ዳር ላይ የመንግስት ዩኒቨርስቲ ( ቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ/ ተቋቁሟል ፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ቤተ ክርስቲያኒቷ ከሰጠችው ከፍተኛ አደራ ውስጥ ዋናው በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የሚማሩትን የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ተከታዮች ተማሪዎችን  ሥርዓተ ትምህርት ቀርጾ በማስተማር ሃይማኖታቸውን  አጽንተው ይዘው ቤተ ክርስቲያናቸውን ፤ ሀገራቸውን  የሚጠቅሙ መልካም ዜጋ ማፍራት  ተቀዳሚ ተግባሩ ነው፡፡ እኔም ይህንኑ ለመተግበር  ዕለተ ሰኞ በ23/3/2006  ወደ ሀገረ ማርያም ተጉዤ ለ7 ቀናት ያህል ከተማሪዎች ጋር ለመቆየት  ደረስን ሀገረ ማርያም  አንድ ትልቅ የቤተ ክርስቲያን አባት አግኝቼ ጠየቅኳቸው ሀገረ ማርያም ለምን ተባለች? ብዬ እሳቸውም መለሰው ቀድሞ ኩኩ ትባል ነበር በአንድ ዘመን በአካባቢው ትልቅ ጥፋት ያጠፋ ሰው የሚቀጣው በስቅላት ነበርና ሰውዬውን ሲሰቅሉት ገመዱ እየተበጠሰ አስቸገረ ያቀን ደግሞ የእመቤታችን ዕለት ነበረን እመቤታችን ናት ያዳነችው ቦታውንም ከዛሬ ጀምሮ ሀገረ ማርያም ይባል ብለው ተስማሙና ሀገረ ማርያም ተባለች በማለት ነገሩኝ በከተማውም ዕድሜዋ 98 ዓመታት ያስቆጠረች የእመቤታችን  ቤተ ክርስቲያን አለች  ቤተ ክርስቲያኗ ጥንታዊት ናትና በጣም ሰፊ ቦታዎችን  ይዛለች  ከሁሉም የሚያስደስተው  ከk1 እስከ 8ኛ ክፍል ድረስ የሚያስተምር  ቅድስት ማርያም አጸደ ሕጻናትና  1ኛ  ደረጃ ት/ቤ/ት ተከፍቶ  1268 ያህል ተማሪዎችን በማስተማር ላይ ይገናል  በከተማውም ካሉት የግልም ሆነ የመንግስት ት/ቤ/ቶች ተቀዳሚ ተመራጭ መሆኑ የተመሰከረት ይህ የቅድስት ማርያም ት/ቤ/ት ነው ፡፡ በ1980 ዎቹ አጋማሽ የተቋቋመው ይህ ት/ቤ/ት  በደብሩ ሰበካ ጉባኤና በቦርድ አባላት የኋሊትና የፊት በመጎተት ስለሚመራ እድገቱ እዚያው ነው ይላሉ  አንዳንድ ምእመናን  ት/ቤ/ቱ የሚያስከፍለው በጣም አነስተኛ ነው ከሌሎች አንጻር ሲታይ 85.00 የኢት ብር ብቻ  ምክንያቱም ይላሉ የት/ቤ/ቱ መምህራን  የቤተ ክረስቲያናችን ዋና ዓላማ  ገንዘብ ሳይሆን ሰው ማትረፍ ነው  ከ300 በላይ ሕጻናትም በአጸደ ሕጻናቱ  ይማራሉ ፡፡ወላጅ አልባ ተማሪዎችን፤ ተወሰኑ የካህናት ልጆችን ፤ ካህናቱን ቸምሮ በነጻ  እንደሚያስተምርም  የት/ቤ/ቱ ርዕሰ መምህር መ/ር አቢዩ አየለ   በሥርዓተ ትምህርት ጥራት ከዲላ ኒቨርስቲ  የተመረቀውና ልዩ ልዩ ተያያዥ ስልጠናዎችን  የወሰደና ፍላጉት ያለው ነው ርእሰ መምህሩ  ወደፊትም 9ኛ ክፍል ለመቀጠል ዕቅዱ እንዳላቸውም ነግሮኛል ፡፡ የመጻህፍትና ሌሎች  ትምህርት መርጃ መሳርያዎች እጥረት  እንደገጠማቸውና እርዳታ እንደሚፈለጉም እንዲሁ  ፍላጎታችን ብዙ ነው የአቅም ችግር ነው እንጂ ያሉት መላከ ሰላም አባ ኃይለ ገብርኤል  የሀገረ ማርያም ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም  ቤተክርስቲያን  አስተዳደሪ ናቸው  በ5 ብር ክፍያ በጥቂት ጥካራ የቤተ ክርስቲያን ልጆች የአይስኩል መምህራን  ሀሳብ የተጀመረውን ይህንን ት/ቤ/ት በማተናከር በመርዳት በባለሞያ ብቻ እንዲመራ  የትምህርት መርጃ ቁሳቁሶችን በማገዝ  የባለሙያ ድጋፍም እንደሚያስፈልገው ርእሰ መምህሩ አሳስቦአል ፡፡ ት/ቤ/ቱ እስከ አሁን ድረስ ከካህናትም ሌሎችንም ወጣቶች ለከፍተኛ ውጤት  ያበቃ ሲሆን  ወደፊትም አተናክሮ  እንደሚቀጥል ርእሰ መምህሩ ተናግሮአል ፡፡
          
የት/ቤ/ቱ                                            
                                                                                                                                                     
                                                                                    
                                                                                     የት/ቤ/ቱ ርእሰ መምህር                                         
የደብሩ አስተዳዳሪ መላከ ሰላም አባ ኀ/ገብርኤል

                                   በአውሮጳ   የካህናት አንድነት ማኅበር ሊቋቋም መሆኑ ታወቀ በ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከመላዋ አውሮጳ   የተውጣጡ ካህናት፡” የ...