2017 ሴፕቴምበር 24, እሑድ

የመስቀል ደመራ በዓል በሄልሲንኪ ለሁለተኛ ጊዜ በደማቅ ሁኔታ ሊከበር መሆኑን  አዘጋጅ ኮሚቴው አስታወቀ።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት  በፊንላንድ ሄልሲንኪ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ለሁለተኛ ጊዜ የመስቀል ደመራ በዓል  በአደባባይ እንደሚከበር ተገለጠ ። ምንም እንኳን እንደ ሀገር ቤት እንደ ሚፈለገው ሃይማኖታዊ ሥርዓትን ለመፈጸም የሀገሪቱ ሁኔታ ባያመችም እንደ ነባራዊ ሁኔታው የመስቀል ደመራ በዓልን በአደባባይ ማክበር የተጀመረው ባለፈው ዓመት መሆኑ ይታወቃል ።በዘንድሮውም ዓመት የመስቀል ደመራ በዓል አዘጋጅ ኮሚቴ እንዳስታወቀው ከባለፈው በተሻለ መልኩ ከፍተኛ እንቅስቃሴ ኢየተደረገ መሆኑ ኮሚቴው አስታውቋል ። በመስቀል ደመራ በዓል በእንግድነት ከተለያዩ ቤተ እምነቶች የሃይማኖት መሪዎች የከተማው ከንቲባ ጽ/ቤት  የከተማው አስተዳደር ከፍተኛ የመንግሥት ሓላፊዎች የባሕል ሙዝዬሞች ፤ መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት ሓላፊዎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና በፊንላንድ በተለያዩ ከተሞች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ምእመናን እንደሚገኙ ይጠበቃል።  

                                   በአውሮጳ   የካህናት አንድነት ማኅበር ሊቋቋም መሆኑ ታወቀ በ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከመላዋ አውሮጳ   የተውጣጡ ካህናት፡” የ...