ሐሙስ 20 ፌብሩዋሪ 2014

ል ረገድ ከፍተኛ ተስፋ የተጣለባቸውና በቋሚ ሲኖዶሱ ላይ ርክክብ የተካሔደባቸው የመዋቅር የአደረጃጀት የአሠራር ጥናት ሰነዶች ብዛት ዐሥራ ሦስት ሲኾን ከአንድ ሺሕ ገጽ ያላነሰ ጠቅላላ ብዛት ያላቸው እንደኾኑ ከቋሚ ሲኖዶሱ ርክክብ አንድ ቀን አስቀድሞ በሀ/ስብከቱ ጽ/ቤት በተካሔደ መርሐ ግብር ላይ ተገልጧል፡፡ His Grace Abune Estifanos with the 12 documentsየጥናት ሰነዶቹም የአደረጃጀትና የመዋቅር ጥናትና መመሪያ፣ የአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ደረጃ መስፈርት ጥናትና መመሪያ፣ የአገልግሎት መደቦች የሥራ ዝርዝር ሰነድ፣ የተፈላጊ ችሎታ መመሪያና የሰው ኃይል ትመና ሰነድ፣ የደመወዝ ስኬል ጥናት ሰነድ፣ የአገልጋዮች ማስተዳደርያ፣ የፋይናንስ፣ የልማት ሥራዎች፣ የግዥ፣ ሽያጭና ንብረት አስተዳደር፣ የዕቅድ ዝግጅት፣ ሪፖርትና ግምገማ፣ የኦዲትና ኢንስፔክሽን ፖሊሲዎችና ዝርዝር የአፈጻጸም መመሪያዎች እንዲኹም የሥልጠና ማእከልና የአረጋውያንና የሕፃናት መርጃ ማእከል ፕሮጀክት ጥናት ሰነድ እንደኾኑ ተዝርዝሯል፡፡ የጥቅምት ቅ/ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ለጥናቱ በሰጠው ይኹንታና በሰጠው አቅጣጫ መሠረት የጥናት ሰነዱ ለርክክብ ከመቅረቡ አስቀድሞ÷ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የመምሪያና ድርጅት ሓላፊዎችን ጨምሮ የሀገረ ስብከቱ የዋና ክፍል ሓላፊዎች፣ የክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጆች፣ የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪዎች፣ የሀገረ ስብከቱ ማኅበረ ካህናት፣ ማኅበረ ምእመናንና የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች እንደተወያዩበት ተገልጦአል፡፡ በውይይት የተነሡት ሐሳቦች በአግባቡ ተመዝግበውና ተገምግመው በእያንዳንዱ የመዋቅርና የአሠራር መመሪያ ውስጥ እንዲካተቱ መደረጉን የባለሞያ ቡድኑ ሰብሳቢ አቶ ታደሰ አሰፋ ያስረዱ ሲኾን ለ14 ቀናት በጥናቱ ላይ በተካሔደው ውይይት 96 በመቶ ተቀባይነት እንዳገኘ ማረጋገጣቸውን ተናግረዋል፡፡ ‹‹ጥናቱን እንድናደርግ የተሰጠን ዕድል ታሪካዊ ነው፤›› ያሉት አቶ ታደሰ፣ ችግር ፈቺ እንደኾነ ለሚያምኑበት የጥናት ሰነድ ዝግጅት መሳካት አስተዋፅኦ አድርገዋል ያሏቸውን ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ የሀገረ ስብከቱን ሓላፊዎችና አገልጋዮች እንዲኹም የለውጥ እንቅስቃሴውን ያስጀመሩትንና ከጅምሩ እስከ ፍጻሜው በኹሉ ነገር አልተለዩም ያሏቸውን ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስን አመስግነዋል፤ የቤተ ክርስቲያኒቱ የበላይ አካል የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ እንደወሰነውም በካህናት፣ ምእመናንና የሰንበት ት/ቤቶች ወጣቶች አስተያየት ዳብሮ የቀረበው የጥናት ሰነዱ በቋሚ ሲኖዶሱ ጸድቆ ወደ ተግባር ይገባ ዘንድ አደራ ብለዋል፡፡ በተያያዘ ዜና፣ በትውፊታዊውና ጥንታዊው የቤተ ክርስቲያኒቱ የትምህርት ማእከላት በኾኑት አብያተ ጉባኤያት ወንበር ተክለው የሚያስተምሩ የአብነት መምህራን ዋነኛ የጤና ችግር ከዐይን እክል ጋር የተያያዘ መኾኑን ሰንደቅ የደረሰው መረጃ ጠቁሟል፡፡ An Accomplished Scholars of the Ethiopain Orthodox Tewahido Church Traditional Schools አባ ሰረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል የውስጥና የውጭ ተባባሪዎቻቸውን አሰልፈው በፓትርያርኩ ደብዳቤ ያሳገዱት የሦስተኛው ዙር ሀገር አቀፍ የአብነት መምህራን ጉባኤ ተሳታፊ የምስክር ሊቃውንት በማኅበረ ቅዱሳን የዋናው ማእከል ጽ/ቤት በራፍ ማኅበረ ቅዱሳን ለሦስተኛ ጊዜ ባዘጋጀውና በፓትርያርኩ ደብዳቤ እንደታገደ በተገለጸው የአብነት መምህራን ሀገር አቀፍ ጉባኤ ላይ ለመገኘት ከኹሉም አህጉረ ስብከት ተውጣጥተው ወደ አዲስ አበባ ከመጡት 202 የምስክር መምህራን መካከል ለ170ዎቹ ተሳታፊዎች የጤና ምርመራ መደረጉን መረጃው ያመለክታል፡፡ W.ro Alemtsehay Meseret, Deputy Board Chair of Kidusat Mekanat Limat ena Mahiberawi Agelgilot ወ/ሮ ዓለም ፀሐይ መሠረት የማኅበረ ቅዱሳን ቅዱሳት መካናት ልማትና ማኅበራዊ አገልግሎት ዋና ክፍል ምክትል የቦርድ ሰብሳቢ የንዋያተ ቅድሳት ምርት ከቤተ ክርስቲያናችን የገቢ ማስገኛ ዘዴዎች በአማራጭነት ሊካተት ይችላል፡፡ ንዋያተ ቅድሳት በቅድስት ቤተ ክርስቲያን በቅዳሴና በልዩ ልዩ መንፈሳዊ አገልግሎቶች የምትጠቀምባቸውን ግብአቶች ያጠቃልላል፡፡ እነዚህ ግብዓቶች ቤተ ክርስቲያን ካላት መንፈሳዊ አገልግሎት÷ ቅዳሴ፣ ክርስትና፣ ተክሊልና ፍትሐት ስፋት እንዲኹም የምእመናኑና የአብያተ ክርስቲያኑ ብዛት ከግምት ስናስገባው ከፍተኛ ምርትንና ሽያጭን ይጠይቃል፡፡ ምርቱና ሽያጩ ለቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች የገቢ ምንጭ ለመፍጠር ብቻ ሳይኾን የአመራረቱን ትውፊትና ሥርዐት ለመጠበቅ፣ ከከተማ ውጭ ያሉትን ገዳማትና አድባራት የንዋያተ ቅድሳት እጥረት ለመቀነስ በከፍተኛ ኹኔታ ያግዛል፡፡ ለዚኽ ገለጻ ተብሎ በተሰበሰበው መረጃ መሠረት፣ በአኹኑ ሰዓት ንዋያተ ቅድሳት በገበያ ላይ ለሽያጭ የሚቀርቡት 95% ከቤተ ክርስቲያን ጋራ ምንም ግንኙነት በሌላቸው ለትርፍ በተቋቋሙ ወይም በሚሠሩ የግል አቅራቢዎች ወይም አምራቾች ነው፡፡ ለምሳሌ ያህል፡- 95 በመቶ የጧፍ ምርት በአብዛኛው ከመርካቶ የግል አቅራቢዎች የሚቀርብ ነው፡፡ ምእመናን በአነስተኛ ግምት በዓመት ወደ 93 ሚልዮን ብር ለጧፍ ግዥ ያወጣሉ፡፡ ከ93 ሚልዮን ብር ሽያጭ 20 ሚልዮን ብር ትርፍ ይገኛል ተብሎ ሊሰላ ይችላል፡፡ ይህ ትውፊቱን ጠብቆ በቤተ ክርስቲያን ካህናት ተመርቶ ቢኾን ኖሮ የካህናቱም ገቢ በዚኹ መጠን ያድግ ነበር፡፡ የጧፍ ምርት፡- የሰው ኃይል፣ የፈትል ክር፣ ሰም ወይም ዋክስ በአካባቢ በሚሠራ ቴክኖሎጂ በመጠነኛ ዋጋ የሚዘጋጅ ነገር ግን ኹሌም ገበያ ያለው ምርት ነው፡፡ የተለየም ሞያ የማይጠይቅ ሥራ ነው፡፡ በመቶ ሺሕ የሚቆጠሩ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ካህናት፣ የካህናት ሚስቶች በቀላሉ ሥልጠና ቢሰጣቸው ኑሯቸውን ሊያሻሽሉ ይችላሉ፡፡ ጧፍ በቤተ ክርስቲያን ካለመመረቱ የተነሣ በአኹኑ ሰዓት አምራቾች የሚጠቀሙበት የሰም ዋጋ ውድ ከመኾኑ ጋራ ተያይዞ ትውፊቱን ለመጠበቅ የሚያስችል ምክንያት ስለሌላቸው በአብዛኛው ሻማና ሞራ እንዲኹም ልዩ ልዩ ኬሚካሎች በመጠቀም ጣፉን በማምረት ላይ ናቸው፡፡ ይህም ከጧፉ ጢስ ጋራ በተያያዘ ካህናትን ለጤና ችግር እየዳረጋቸው ይገኛል፡፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ማኅበረ ቅዱሳን የልማት ተቋማት የጧፍ ማምረቻ ማሽን ፈብርኮ በየዓመቱም 250‚000 ጧፍ ከሰም ያመርታል፡፡ ምርቱን ለማምረት ለሚፈልጉ አብያተ ክርስቲያናት የማሽን ሥራና ሥልጠና ይሰጣል፡፡ /የምጣኔ ሀብትና የሕዝብ ጤና አጠባበቅ ባለሞያዋ ወ/ሮ ዓለም ፀሐይ በ፴፪ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ዓመታዊ ስብሰባ ላይ ‹‹በቤተ ክርስቲያን ልዩ ልዩ አነስተኛ የገቢ ማስገኛ ዘዴዎችን ተግባራዊ ስለማድረግ›› በሚል ርእስ ካቀረቡት ጥናታዊ ጽሑፍ የተወሰደ/


 

 

                                   በአውሮጳ   የካህናት አንድነት ማኅበር ሊቋቋም መሆኑ ታወቀ በ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከመላዋ አውሮጳ   የተውጣጡ ካህናት፡” የ...