2015 ኦክቶበር 29, ሐሙስ

ሰበር ዜና – አጥማቂ ነኝ ባዩ ግርማ ወንድሙ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ዋለ(ኤፍ ቢ ሲ፤ አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 17 ቀን 2008 ዓ.ም.)
girma wondimu
የአዲስ አበባ ፖሊስ፣ አጥማቂ ነኝ ባዩን ግርማ ወንድሙን በቁጥጥር ሥር አዋለ።
የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ምንጮች፣ አጥማቂ ነኝ ባዩን ግርማ ዛሬ በፖሊስ በቁጥጥር ሥር ውሎ ምርመራ እየተደረገበት መኾኑን ተናግረዋል።
አጥማቂ ነኝ ባዩ ግርማ፣ በማጥመቅ እፈውሳለኹ በሚል በተለያዩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን ሕገ ወጥ ሀብት ሲያካብት እና በርካታ ምእመናንን ለተለያዩ ችግሮች ሲዳርግ ቆይቷል፡፡
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያነገጋረው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት፣ አጥማቂ ነኝ ባዩ ግርማ ዕውቅና እና ፈቃድ በይፋ የተነፈገው ሕገ ወጥ እንደኾነ አረጋግጧል።
የፋና ምንጮች፣ አጥማቂ ነኝ ባዩ ግርማ በፈውስ አገልግሎት ስም የማጭበርበር ወንጀል ሳይጠረጠር እንዳልቀረ ነው የተናገሩት።

                                   በአውሮጳ   የካህናት አንድነት ማኅበር ሊቋቋም መሆኑ ታወቀ በ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከመላዋ አውሮጳ   የተውጣጡ ካህናት፡” የ...