የካቲት 23 ቀን 2007 ዓ.ም.
በዘማች አዩኔ /ከሆሳዕና ማእከል/
የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ወርኃዊ በዓል ለማክበር ምእመናን በቤተ ክርስቲያን ተገኝተው የቅዳሴ ሥነ-ሥርዓት እንደተጠናቀቀ እና ቡራኬ ተቀብለው ወደየቤታቸው በተመለሱ በ20 ደቂቃ ውስጥ ካህናት እና ዲያቆናት ገና በደጀ ሰላም እያሉ ከቤተ መቅደሱ ውስጥ ቃጠሎው እንደጀመረም ተናግረዋል፡፡ በወቅቱ ሁሉም የቤተ ክርስቲያኗ በሮች ከውጭ ተቆልፈው ስለነበር ቁልፎቹን በቅርበት ለማግኘት ስላልተቻለ እሳቱን ቶሎ በቁጥጥር ለማዋል አልተቻለም፡፡ በዚህም ምክንያት በውስጥ የነበሩት ንዋያተ ቅድሳት ሙሉ ለሙሉ ወድመዋል፡፡ የደብሩ ካህናትና ዲያቆናት የቤተ ክርስቲያኗን በር ሰብረው በመግባት በዕለቱ ቅደሴ የተቀደሰበትን ታቦት አፈር በማልባስ ከእሳቱ ለመከላከል ተችሏል፡፡ ከተመሠረተች ከአንድ መቶ ዓመት በላይ ያስቆጠረችው ቤተ ክርስቲያን በቃጠሎው ሙሉ በሙሉ ብትወድምም በቤተ መቅደስ ውስጥ የነበሩት ታቦታት ምንም ዓይነት ጉዳት ሳይደርስባቸው በእግዚአብሔር ቸርነት ተርፈዋል፡፡ ከቃጠሎው የተረፉት ታቦታት እሳቱ ከጠፋ ከሦስት ሰዓታት በኋላ በካህናት፣ በዲያቆናት እና ምዕመናን ታጅበው ለጊዜው ወደተዘጋጀላቸው ማረፊያ ገብተዋል፡፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሀድያ እና ስልጤ ሀገረ ስብከት የሆሳዕና ደብረ ገነት ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን የተመሠረተችው በ1901 ዓ.ም ሲሆን፤ አካባቢው በሌሎች የእምነት ድርጅቶችና እና በ ኢ-አማንያን የተከበበ በመሆኑ ምእመናን በሃይማኖት በምግባር ጸንተው እንዲኖሩ በደብሩ በተለያዩ ጊዜያት ጉባኤ በማዘጋጀት የተጠናከረ የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ሲሰጥበት የቆየ ቦታ ነው፡፡ |
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ መሠረት የሚቀርቡ መንፈሳዊ ትምህርቶች ፤መረጃዎች እና የመሳሰሉት የሚስተናገዱበት ገጽ ነው
2015 ማርች 4, ረቡዕ
የሆሳዕና ደብረ ገነት ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ተቃጠለች
ደንበኛ ይሁኑ ለ፡
ልጥፎች (Atom)
በአውሮጳ የካህናት አንድነት ማኅበር ሊቋቋም መሆኑ ታወቀ በ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከመላዋ አውሮጳ የተውጣጡ ካህናት፡” የ...

-
በ ዲ.ዮርዳኖስ አበበ (ናታኒም ጡመራዊ መጽሔት ሐምሌ 4 ) እንኳን ለአባቶቻችን ቅዱሳን 12ቱ ደቂቀ ነቢያት ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ +"+ +" 12ቱ ቅዱሳን ደቂቀ ነቢያት &quo...
-
ጾመ ፍልሰታ የእመቤታችን ዕረፍት Written By Hulubante Abebe on Tuesday, August 5, 2014 | 1:02 PM መ/ር ሳሙኤል ተስፋዬ ...
-
እምየዋ ! እምየ አድማሱ ጀምበሬ። ምነው በዕድሜ ደርሰን ዐይንዎን አይተን ድምፅዎን ሰምተን በነበር። ዛሬማ ቸልታችንን ዕድሜ ይንሳው እና ኹሉን ነገር ችላ ብለን ለነአባ ...