ሰበር ዜና – የመስቀል ደመራ ክብረ በዓል የመጀመሪያው የኢትዮጵያ የዓለም መንፈሳዊ ቅርስ ኾኖ በዩኔስኮ ተመዘገበ
(ሪፖርተር፤ ኅዳር ፳፮ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም.)
ኄኖክ ያሬድ
ስለ ቅርሱ የመረመረው ኮሚቴ ባቀረበው ውሳኔ ሐሳብ ላይ እንደተመለከተው፣የመስቀል ክብረ በዓል የኢትዮጵያን ሃይማኖታዊና ባህላዊ ትውፊቶችን የያዘ፣ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ መምጣቱና በአገሪቱ ማኅበራዊ አንድነትንና የርስ በርስ ትስስርን፣ ብዝኃነትንም የሚያንጸባርቅ፣ በበርካታ ብሔረሰቦች ባህሎች መካከል ትስስርን የፈጠረ በመኾኑ ዓለም አቀፍ መስፈርቱን አሟልቷል ብሎታል፡፡