ዓርብ 16 ኦክቶበር 2015

ለዘብተኛነት/ሊበራሊዝም/፡የክርስትና ዘመናዊው ጠላት



ግን በመጨረሻው ቀን የሚያስጨንቅ ዘመን እንዲመጣ ይህን ዕወቅ፣ ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወዱ ይሆናሉ፣

የአምልኮት መልክ አላቸው ኃይሉን ግን ክደዋል፡፡ 2ኛጢሞ. 3÷5

ለዘብተኛነት/ሊበራሊዝም/ በ18ኛው መክዘ መጨረሻ እና በ19ኛው መክዘ መጀመርያ ብቅ ያለ አስተሳሰብ ነው፡፡ ይህ አስተሳሰብ በፖለቲካው መስክ ግራ ዘመም አስተሳሰብ በመባል ይታወቃል፡፡ በደምሳሳው ልቅ በሆነ መብት እና ነጻነት የሚያምን፤ ነባር ባሕሎችን፣ ልምዶችን እና እምነቶችን በየጊዜው በመናድ ሰዎች ራሳቸውን አማልክት አድርገው እንዲያስቡ የሚያበረታታ አመለካከት ወይም ርእዮተ ዓለም ነው፡፡

ዛሬ በፖለቲካው መስክ ያለው ለዘብተኛነት ርእሰ ጉዳያችን አይደለም፡፡ የምንወያየው ስለ ለዘብተኛ/ሊበራል/ ክርስትና ነው፡፡

ሊበራል ክርስትና የግራ ዘመምን አስተሳሰብ በመያዝ በዚያው በ18ኛው መክዘ መጨረሻ እና በ19ኛው መክዘ መጀመርያ ብቅ ያለ አስተምህሮ ነው፡፡ ይህ አስተምሮ ፕሮቴስታንቲዝምን ሳይቀር አክራሪ /conservative/ ነው ብሎ የሚያምን እና በሃይማኖት ለሰው ልጅ ልቅ የሆነ መብት እና ነጻነት ሊሰጠው ይገባል በሚል የተነሣ ነው፡፡ በአሜሪካ እና በአውሮፓ አብዛኞቹ ፕሮቴስታንቶች እና ፓስተሮቻቸው በዚህ አመለካከት የሚመሩ ናቸው፡፡

ይህ አመለካከት የፕሮቴስታንቱን ዓለም ሃይማኖት አልባ ማድረጉ ሳያንሰው የካቶሊካውያንን እና የምሥራቅ እና የኦርየንታል አብያተ ክርስቲያናትን በር በማንኳኳት ላይ ይገኛል፡፡ በመገናኛ ብዙኃን እና በኤሌክትሮኒክስ ሚዲያው በየጊዜው ስለሚለፈፍ፣ ታላላቅ የሚባሉ ፖለቲከኞች እና የተከበሩ ሰዎች በየአጋጣሚው ስለሚያነሡት የሊበራል ክርስትና አስተሳሰብ እንደ ተስቦ በየሰው እየሠረፀ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ሊበራል ክርስትናን እንዲህ እና እንዲያ ነው ብሎ ከመበየን መገለጫዎቹን ማቅረቡ ይበልጥ ግልጽ ያደርገዋል፡፡

የሊበራል ክርስትና አመለካከት ዋና ዋና መገለጫዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል አይደለም ይላሉ

ሊበራል ክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስ በአንድ ወቅት የነበሩ ሰዎች ስለ እግዚአብሔር ምን እንደሚያምኑ የገለጡበት መጽሐፍ እንጂ የእግዚአብሔር ቃል አይደለም ብለው ያምናሉ፡፡ በመሆኑም ሊተች፣ ሊስተካከል፣ ሊታረም እና ሊቀየር የሚችል ጽሑፍ ነው ይላሉ፡፡ በዚህ አስተሳሰባቸው ምክንያትም ዛሬ ዛሬ ብዙዎቹ የፕሮቴስታንት አስተማሪዎች በትምህርታቸው ውስጥ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ማለት አልነበረበትም እያሉ ይተቻሉ፡፡ ወይም አንድ ሰው እንዳለው they want to re-write the bible፡፡ ሃይማኖታቸውም የግድ መጽሐፋዊ መሆን እንደሌለበት እና መጽሐፍ ቅዱስ የሃሳብ መነሻ ብቻ መሆን እንደሚችል ያስተምራሉ፡፡ በመሆኑም በየጊዜው አዳዲስ እና የተሻሻሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ቅጅዎች እንዲታተሙ ያበረታታሉ፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ ወጥ ትርጓሜ አያስፈልገውም ይላሉ

ሊበራሎች መጽሐፍ ቅዱስን ማንም ሰው እንደተመቸው እና እንደገባው መተርጎም ይችላል፡፡ አንድ ወጥ የሆነ እና «ትክክል ነው» ተብሎ ሊመሰከርለት የሚችል ትርጓሜ የለም ይላሉ፡፡ ይህም በሃይማኖት እና በአስተሳሰብ የተለያዩ ሚሊዮን ዓይነት የክርስትና ክፍልፋዮች እንዲፈጠሩ አድርጓል፡፡ ዶግማ እና ቀኖና የሚባል ነገር ስለሌላቸው ስለሚያመልኩት አምላክ እንኳንስ ሁሉም፣ በአንድ ጉባኤ የተገኙት እንኳን ተመሳሳይ እምነት የላቸውም፡፡ በማናቸውም ትምህርታቸውም ቢሆን የቀደሙ አበውን ትምህርት፣ ትርጓሜ እና ሐተታ አያካትቱም፡፡ ምናልባት መጽሐፍ ቅዱስን ይጠቅሱ ካልሆነ በቀር፡፡ የቅዱሳንን ሕይወትም አስረጂ አድርገው አይቆጥሩትም፡፡

በሃይማኖት ጉዞ ውስጥ አንድ ሊቋረጥ የማይገባው አንድነት «አሐተኔ» አለ፡፡ ይኸውም በአንድ ዘመን በሚኖሩ ክርስቲያኖች መካከል፣በአንድ ዘመን በሚኖሩ ወይንም በነበሩ ክርስቲያኖች እና ከእነርሱ በፊት በነበሩ ክርስቲያኖች መካከል፣እንዲሁም በአንድ ዘመን በሚኖሩ ወይንም በነበሩ ክርስቲያኖች እና ከእነርሱ በኋላ በሚመጡ ክርስቲያኖች መካከል የሃይማኖት አንድነት መኖሩ ነው፡፡ እኛ ከቀደሙ ክርስቲያኖች እና ወደፊት ከሚመጡ ክርስቲያኖች ጋር የሃይማኖት አንድነት ከሌለን «አንዲት ሃይማኖት፣ አንዲት ቤተ ክርስቲያን» ብለን መጥራት አንችልም፡፡

ሊበራሊዝም መጽሐፍ ቅዱስን እያንዳንዱ ሰው በራሱ መንገድ እንደፈለገ እንዲተረጉመው በመፍቀዱ የተነሣ በአንድ ዘመን በሚኖሩ ክርስቲያኖች መካከል የሃይማኖት አንድነት የለም፡፡ በአንድ ዘመን በሚኖሩ ክርስቲያኖች እና ከእነርሱ በፊት በነበሩ፣በኋላም በሚመጡ መካከል ያለውም አንድነት ፈርሷል፡፡

ትክክለኛም ሆነ የተሳሳተ ሃይማኖት የለም ይላሉ

ሊበራሎች «አንድ ሰው ትክክል ነው ብሎ እስካመነበት ድረስ ማንኛውም እምነት ትክክል ነው» ብለው ያስተምራሉ፡፡ ከኤፌሶን ምዕራፍ ሁለት «አንዲት እምነት» ከሚለው ትምህርት በተቃራኒ «የተሳሳተ ሃይማኖት የለም፤ ሁሉም ሃይማኖት እኩል እና ትክክል ነው፡፡ ልዩነቱ የሰዎች አስተሳሰብ ነው» ብለው ያስተምራሉ፡፡ በመሆኑም ልዩ ልዩ አመለካከት ያላቸው አማኞች በአንድ ጊዜ፣ በአንድ ቦታ ፣በጋራ ማምለክ ይችላሉ ብለው ያስባሉ፡፡

ይህ አስተሳሰባቸውም ሰዎች የራሳቸውን ፍልስፍና እንደ ሃይማኖት ትምህርት እየቆጠሩ በየጊዜው እንዲበታተኑ አድርጓቸዋል፡፡ ወደ ትክክለኛዋ መንገድ ከመመለስ ይልቅ ሁላችንም ትክክል ነን በሚል ፍልስፍና በስሕተቱ ጎዳና እንዲበረቱበት ረድቷቸዋል፡፡

የሚያስፈልገው ማኅበራዊ ወንጌል ብቻ ነው ይላሉ

የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ለማኅበራዊ ኑሮ፣ ለፍትሕ፣ ለዴሞክራሲ፣ ለሰብአዊ መብት እና ለእኩልነት መዳበር ከሚሰጠው ጥቅም አንጻር እንጂ በመሠረተ እምነት/ዶግማ/ ላይ ማተኮሩን ይቃወማሉ፡፡ ለስብከቱ ማራኪነት፣ አስደሳችነት እና ሳቢነት እንጂ ለትምህርቱ ትክክለኛነት አይጨነቁም፡፡ የነገረ ሃይማኖት ጉዳዮችን ማንሣት ሊለያየን ስለሚችል «ከዚህም ከዚያም ያልሆነ አቀራረብ» /neutral approach/ መጠቀም ያስፈልጋል ባዮች ናቸው፡፡ ትምህርታቸው መንፈሳዊ ሳይሆን ሥነ ልቦናዊ፣ ለማዳን ሳይሆን ለማስደሰት፣ እውነቱን ለመመስከር ሳይሆን ሰው እውነት የመሰለውን እንዲመርጥ ለማድረግ የታሰበ ነው፡፡ የዶግማ እና የቀኖና ትምህርት አይሰጡም፡፡

ዛሬ ዛሬ ይህ በሽታ እኛም ውስጥ ገብቶ ነው መሰለኝ ሰባክያን የተባልን ሰዎች ከዶግማ ትምህርት እየወጣን በስብከት ላይ ብቻ ወደማተኮር እየቃጣን ነው፡፡ በትምህርታችን ውስጥ እንኳን መሠረታዊ የሃይማኖት ትምህርትን በተገቢው መንገድ አናቀርብም፡፡ ምእመናንም ይህንኑ ለምደው መሠረታዊ ትምህርት ሲሰጥ እንደ ባከነ ጊዜ ይቆጥሩታል፡፡ በትምህርት አሰጣጣችንም ውስጥ የአበው ትምህርት፣ ትርጓሜ እና ሐተታ እየተረሳ፣ የቅዱሳንም ሕይወት በአስረጅነት መጠቀሱ እየቀረ ነው፡፡

ቤተ ክርስቲያን አልባ ክርስትናን ያስፋፋሉ

ሊበራል ክርስቲያኖች ቤተ ክርስቲያን ለድኅነት የግድ አስፈላጊ አይደለችም፡፡ ያለ ቤተ ክርስቲያን ክርስቲያን መሆን ይቻላል፤ ብለው ያምናሉ፡፡ አንድ ሰው ካመነ ክርስቲያን ለመሆን በቂው ነው፡፡ ስለዚህም ወደ ቤተ ክርስቲያን ሄዶ መጠመቅ፣ መቁ ረብ፣ መማር፣ መዘመር ወዘተ የግድ አያስፈልገውም ብለው ያስተምራሉ፡፡ ፕሮቴስታንቲዝም ሲጀመር «ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ከተራ ቤት እኩል ነው» ብሎ ተነሣ፣ ቀጥሎ ደግሞ ሊበራሎቹ «ያም ቢሆን አያስፈልግም» ብለው ደመደሙት፡፡ ውሻ በቀደደው አይደል ድሮስ ጅብ የሚገባው፡፡

በዚህ የተነሣም ብዙ ፕሮቴስታንቶች ወደ ቤተ ክርስቲያን አይሄዱም፣ አይሳተፉምም፡፡ ለምሳሌ በእንግሊዝ ሀገር 10% የሚሆኑ ክርስቲያኖች ብቻ ናቸው ቤተ ክርስቲያን እሑድ እሑድ የሚሄዱ፡፡ በስካንዴኒቪያን ሀገሮች ደግሞ ከ2 እስከ 3% ብቻ ይሄዳል፡፡ በአሜሪካ 60% ክርስቲያኖች ቤተ ክርስቲያን አይሄዱም፡፡ ከሚሄዱት ከ40% ብዙዎቹ ማኅበራዊ ጥቅማ ጥቅም ለማግኘት የሚሄዱ ናቸው፡፡ እንዲያውም በአሁኑ ዘመን ደግሞ «የኮምፒውተር ቤተ ክርስቲያን» online church የሚባል እየተከፈተ ነው፡፡ ስለዚህም በዳታ ቤዙ ላይ የኃጢአት ዝርዝር አለ፤ የሠሩትን ኃጢአት ከዳታ ቤዙ ውስጥ ገብተው ክሊክ ሲያደርጉ ቅጣቱን ይነግርዎታል፡፡

መዋቅር አልባ እምነትን ያስፋፋሉ

ሊበራሊዝም ማንኛውም ክርስቲያን በፈቀደው መንገድ እንዲያምን ስለሚያስተምር ማናቸውንም ዓይነት የሃይማኖት መዋቅሮች አይቀበልም፡፡ ሃይማኖታዊ መዋቅሮች ይኑሩ ከተባለም በዲሞክራሲያዊ መንገድ በሚመረጡ የቦርድ አባላት የሚመሩ እና ለብዙኃኑ ድምጽ ተገዥ የሆኑ መሆን አለባቸው ይላል፡፡ በዚህም የተነሣ የክህነትንም ሆነ የአስተዳደር እርከኖችን አይቀበልም፡፡ ጳጳሳት በካህናት ላይ፣ ካህናት በምእመናን ላይ ያላቸውን ሃይማኖታዊ ሥልጣን፣ እንዲሁም የቤተ ክርስቲያንን ሃይማኖታዊ እና አስተዳደራዊ ጉዳይ በመወሰን ረገድ ቅዱስ ሲኖዶስ ያለውን ሥልጣን አይቀበልም፡፡

በአሜሪካን ሀገር በ1960 እኤአ መሥመራውያን አብያተ ክርስቲያናት /main line protestants/ ከጠቅላላ ክርስቲያኑ 40% ይሸፍኑ ነበር፡፡ በ40 ዓመታት ውስጥ ግን በሊበራሎች ተነጥቀው ዛሬ 12% ብቻ ናቸው፡፡

ኑፋቄ የሚባል ነገር የለም ይላሉ

ሊበራሎች «የሁሉም ሰው ሃይማኖታዊ አመለካከት ትክክል ነው» ብለው ስለሚያምኑ ኑፋቄ የሚባል ነገር የለም ይላሉ፡፡ እንዲያውም ጥንት የተወገዙ መናፍቃን መብታቸው ተነክቷል ብለውም ያስባሉ፡፡ በቤተ ክርስቲያን ጉባኤያት የተለዩ የግኖስቲኮች መጻሕፍትን እንደ ገና ወደ ቤተ ክርስቲያን ለማስገባትም ይጥራሉ፡፡ መናፍቃንን በተመለከተ ምናልባት በዚያ ጊዜ የነበሩ አባቶች ተሳስተው ከሆነ ነገሩን እንደ ገና ማየት አለብን የሚል አመለካከት አላቸው፡፡ የበርናባስ ወንጌል፣ የይሁዳ ወንጌል፣ የማርያም መግደላዊት ወንጌል ወዘተ የተባሉና በግኖስቲኮች የተጻፉ የክህደት መጻሕፍት ዛሬ ዛሬ እንደ አዲስ ግኝት በመቸብቸብ ላይ ናቸው፡፡

መናፍቃንን መናፍቃን ማለተ ሰውን ማራቅ ነው፡፡ ስለ መናፍቃን ማውራት መለያየትን ማባባስ ነው፡፡ ስለ ራሳችን ብቻ እንናገር እንጂ ስለሌሎች አናንሣ፡፡ የሚሉት አመለካከቶች የልዩነቱን ድንበር አፍርሰው ክርስቲያኖች ስንዴውን እና እንክርዳዱን መለየት እንዳይችሉ የሚያደርጉ ናቸው፡፡

ለአዳዲስ አስተሳሰቦች ክፍት በር ይከፍታሉ

ሊበራሎች ለአዳዲስ አስተሳሰቦች በራችን ክፍት መሆን አለበት፣ አንድ ነገር አሳማኝ እስከሆነ ድረስ ልንቀበለው ይገባል ይላሉ፡፡ ዋናው ነገራቸው በቅዱሳት መጻሕፍት ትምህርት መሠረት ሳይሆን ምን ያህል ሕዝቡ ይቀበለዋል? በሚለው መሠረት ነው፡፡ በዚህ የተነሣም የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻን፣ የሴቶችን ክህነት፣ የእንስሳትን አባልነት ወዘተ በመቀበል ላይ ናቸው፡፡ የሊበራሎች አንዱ መሠረታዊ አስተሳሰብ ዘመኑን በቅዱሳት መጻሕፍት መዋጀት ሳይሆን ቅዱሳት መጻሕፍትን ለዘመኑ ማመቻቸት ነው፡፡ በዚህ የተነሣ ቤተ ክርስቲያን በቅዱሳት መጻሕፍት ቃል እና በአባቶች ትምህርት ሳይመረመሩ አዳዲስ አስተሳሰቦች እንዲሁ የሚገቡባት ቤት መሆን አለባት ይላሉ፡፡

ግዴለሽነትን ያስፋፋሉ

ሊበራሎች ለጾም፣ ለጸሎት፣ ለሥነ ምግባር እና ለባሕል ግዴለሾች ናቸው፡፡ ሥርዓታዊ እምነት አይመቻቸውም፡፡ አንድ ሰው ክርስቲያን ለመሆን ከማመን እና ከማወቅ በላይ አያስፈልገውም ስለሚሉ ሌላ ዓይነት ሥርዓተ አምልኮን እንዲፈጽም አይገደድም፡፡ ጋብቻን ማክበር፣ ከሱስ ነጻ መሆን፣ ንጽሕናን መጠበቅ፣ ድንግልናን ማክበር፣ ወዘተ የሰው በጎ ፈቃድ እንጂ የሃይማኖት ትምህርት ናቸው ብለው አይወስዷቸውም፡፡ ስለዚህም አማኞች ትክክለኛ ኑሮ እና የተሳሳተ ኑሮ፣ሥነ ምግባራዊ እና ኢሥነ ምግባራዊ የሚባለውን ለይተው እንዲያውቁ እና እንዲኖሩ አይነገራቸውም፡፡

ሊበራል ክርስትና ምን አመጣ?
               ይቀጥላል
                                                           

ረቡዕ 9 ሴፕቴምበር 2015

ወሪድዬ ብሄረ ሮሜ /ቅዱስ ያሬድ/

                                                                                ካታኮምፕ

ቅዱስ ጳውሎስ የተሠየፈበት
                                                                                                        ቅዱስ ጴጥሮስ   የታሰረበት
 


 ቅዱስ ጳውሎስ የታሠረበት

 የቅዱሳን የተጋድሎ አደባባይ  ፡ ሐዋርያት ስለ ሃይማኖታቸው  እውነትን  መስክረው አንገታቸውን  ለሠይፍ  የሰጡባት   የተሰቀሉባት  የቅዱሳን በአት  የጸሎት ዋሻቸው   የተዋሕዶ  ሃይማኖት  የኪነ ጥበብ  ምድር የነበረች  ዛሬም እንኳን  ያ ሁሉ የቅዱሳን የገድል ውጤት  የሚታይባት  የዓለም ጎብኚዎች  የሚተሙባት  ምድረ ሮሜን  በመንፈስ  ተመርቶ  በርቀት ተመልክቶ  ወደ ሮሜ  ወረድኩ ወርጄ  ስለቤተ ክርስቲያን  ተናገርኩ በማለት ቅዱስ ያሬድ  ተናገረ  እኔም “ በከመ ሰማዕነ ከማሁ ርኢነ “  እንደ ሰማን እንዲሁ ተመለከትን” ተብሎ እንደ ተጻፈ   ቅዱስ ጳውሎስ አንገቱን የተሰየፈበት ቅዱስ  ጴጥሮስ  ቁልቁል የተሰቀለበት የቅዱሳን በአት  የጸሎት ዋሻቸው “ ካታኮምፕ “ የወቅቱ ነገሥታት  ቅዱሳኑን  ከአንበሳ ጋር  ያታገሉበት  ቦታ  ምን አደከማችሁ የቅዱሳን  የተጋድሎ አደባባይ  ነበረች ሮማ  የዛሬውን አያድርገውና፤፤ ሰሞኑን እያየሁ ነበረ  የቱሪስቱ ሰልፍ  ለካ ! የትም ሀገር  ሰልፍ አይቀሬ ነው ዓይነቱ ይለያያል እንጂ  አልኩና ዕድሜና ጤንነት  ለወንድም በለጠ እና ለባለቤቱ ቤተልሔም  እየተመኘሁ ከእነሱ ጋር በመዘዋወር   በጽሁፍ ያነበብኩትን  በዓይኔ ተመለከትኩ  የሮማንንም ካቶሊክ  ላመሰግን ወደድኩ /ባቲካንን/ ለምንም ይሁን ለምን  በጥንቃቄ  ይዛ ታስጎበኛለች  እኛ ብንሆን እስከ ዛሬ  አንጠብቀውም  ይልቁንም የሚሸጠውን  እንሸጠው ነበረ  ። ሀገራችን ብዙ የቅዱሳን ቦታዎች  አሉ ግን በአግባቡ አልያዝናቸውም  የቅዱሳኑ ቦታ በሙሉ በሌሎች ተይዞ ሲታይ ያሳዝናል ፤፤ ጌታችን ቅዱስ ጳውሎስን  እንዲህ በማለት ወደ ሮሜ ልኮታል

“አስተርአዮ እግዚእነ ለጳውሎስ ወይቤሎ ተአመን  በከመ ኮንከኒ ሰማእትዬ  በኢየሩሳሌም ከማሁ ሀለውከ ትኩነኒ  ሰማእትዬ በሮሜሂ “   ሥራ 23. 11

ጳውሎስ ሆይ  በኢየሩሳሌም ስለ እኔ እንደ መሰከርህ  እንዲሁ በሮሜም ትመሰክርልኝ ዘንድ ይገባልና አይዞህ አለው ።

 ይህ የጌታችንን ጥሪ በደስታ የተቀበለው ቅዱስ ጳውሎስ   ሄዶ መከራን በመቀበሉ ዛሬ ሮማውያን  የሱን  የገድል ውጤት ኢያሳዩ /ኢያስጎበኙ ይኖራሉ ።

ለአንክሮ

Ø የባቲካን የቅዱሳኑን ቦታዎችን አክብራ ለቱሪስት ምቹ አድርጋ  መጠቀሟ

Ø ከተማዋ /ሮም ማለቴ ነው በሙሉ የጥንት ሃይማኖታዊ መልኳን  ሳትለውጥ መቀጠሏ

           ማሳሰቢያ

Ø  ኢትዮጵያውያን  በሮማ  ላላችሁ  ሁላችሁም በሮማ ከተማ ያለውን  ታሪካዊ የቅዱሳንን  ቦታዎች  ያላያሁ ትኖራላችሁና  እንድታዩት አሳስባለሁ።               በሮሜ ላላችሁ ሁሉ ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን ። ሮሜ . ፩ ፡ ፯

 

 የጉብኝት ሰልፍ


 

                                                                                                                                                                       


 




 

ቅዳሜ 5 ሴፕቴምበር 2015

የደቡብ ምሥራቅ እና ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት ፪ኛ ዙር ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔውን ትናንት ጀመረ



His_Grace_Abune_Mussie


 
ብፁዕ አቡነ ሙሴ
የደቡብ ደቡብ ምሥራቅና ምዕራብ አውሮፓ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
                                                                        

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን  የደቡብ ምሥራቅ እና ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት የ፪ኛ ዙር ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔውን ነሐሴ 29 /2007 ዓ ሞ  እንደሚጀምር  ታወቀ
በጀርመን  ፍራንክፈርት ለ፫ ቀናት በሚደረገው ጠቅላላ ጉባዔ ላይ በሀገረ ስብከቱ የሚገኙ ከ30 በላይ የሚሆኑ የአድባራት አስተዳዳሪዎች ፤  በማኅበረቅዱሳን የአውሮፓ ማእከል ተወካዮች  ምእመናን  እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ይሳተፋሉ . ጉባዔው ዓመታዊ የአድባራት  አገልግሎት  አፈጻጸም ሪፖርት እና የቀጣይ ዓመት ዕቅድ   ላይ የሚወያይ  ሲሆን  በገለልተኛ አቢያተክርስቲያናት ጉዳይም  ጠቅላላ ጉባዔው  አንድ ውሳኔ  እንደሚወስን ይጠበቃል  ጠቅላላ ጉባዔውን አስመልክቶ በፍራንክፈርት የሚገን አንድ ጋዜጣ እንደ ዘገበው  የከተማዋ ከንቲባ በተጋባዥነት በጉባዔው እንደ ሚገኙና የሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ የአቡነ ሙሴ  መንበረ ጵጵስና ለአገልግሎት ምቹ ይሆን ዘንድ ጠቅሶ  በከተማችን በንበረ ጵጵስና መኖሩ እድለኞች ያደርገናል ሲል ዘግቧ በመጨረሻም በሀገረ ስብከቱ ከፍተኛ የአገልግሎት አፈጻጸም ያገኙ አስተዳዳሪዎች በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሙሴ  ሽልማት እንደሚበረከትላቸው  ለማወቅ ተችሏል  በሊቀ ጳጳሱ አቡነ ሙሴ በማግባባት ላይ የተመሠረተ  መንፈሳዊ የማስተዳደር ጥበብ የተነሳ ሀገረ ስብከቱ ሰላማዊና አድባራቱ የራሳቸው ቤተ ክርስቲያን እንዲኖራቸው የሚደረገው እንቅስቃሴ ምስክር ነው  በቅርቡ የራሳቸው ቤተ ክርስቲያን ለመግዛት ዝግጅታቸውን ያጠናቀቁ የሙኒክ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤልን የሚጠቀሱ ሲሆን የበርሊን ደብረ ገነት አማኑኤል ቤተ ክርስቲያን ደግሞ የራሳቸውን ቤተ ክርስቲያን ገዝተዋል ሌሎቹም ከፍተኛ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ እንደሚገኙ የሀገረ ስብከቱ ያመለክታል





 

ማክሰኞ 25 ኦገስት 2015

ሁለተኛው ስደትና መፍትሔው

                                                                 በርሊን ደብረ ገነት አማኑኤል  ቤ/ክ በቅርቡ የተገዛ
                            
                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                           ሰዎች  ከአንዱ ሀገር ወደ ሌላው ሀገር በስደት መዘዋወሩ በጎላ በተረዳ
ይታወቃል ። ይሁን እንጂ ታዲያ የሚያሳዝነው ስደቱን እጥፍ የሚያደርገው የመንፈሳዊ አገልግሎት ፤የማኅሌቱ፤ የቅዳሴው ፤ የስብከተ ወንጌሉ እና የመሳሰለው መንፈሳዊ አገልግሎት  መተግበሪያ / መገልገያ ቤተክርስቲያን  አለመኖሩ ነው ። ምንም እንኩዋን በአውሮጳ /ፓ የሉተራውያን የካቶሊካወያን አቢያተ እምነታት  በሙሉ የተዘጉ እና የእምነቱ ተከታዮች ሁሉን ነገር ትተውታል ። እጅግ በሚያስደንቅ ጥበብ የታንጹ አቢያተ እምነቶቻቸው በጣም ያሳዝናሉ ። ጥቂት የሚሆኑ የእምነቱ ተከታዮች አረጋወያን በቻ እሁድ ረፋድ ላይ ይገኛሉ ። በስደት የሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን መእመናን በየአካባቢያችው ይህንኑ ቤተ እምነት አስፈቅደው  ይገለግሉበታል  አንዳንዶቹም አቅሙ ያላቸው  ውርሃዊ ክፍያ በመክፈል ይክራዩታል። ይህንን ማድረግ ያልቻሉ ግን እሁድ ጠዋት ሲከፈት ገብተው ቶሎ ቶሎ  ብለው ቅዳሴውን ቀድሰው ንዋዬ ቅዱሳቱን ይዘው ይወጣሉ ። ነሐሴ ኪዳነ ምሕረት የእመቤታችንን በዓለ ዕርገት  ለማክበር  ከሐምቡርግ  ፍራንክፈርት አቅራቢያ ወደ ምትገኝ ሐመረ ኖህ ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን  ተጓዝን  በዓሉ የተከበረው ነሓሴ 17 ነበረ   ቅዳሴው  በብፁዕ አቡነ ሙሴ የደቡብ መዕራብና ምሥራቅ አውሮጳ/ፓ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳሳት ኢየተመራ እያለ ሰዓት ደረሰ ቶሎ ታቦቱ ወጥቶ ቶሎ መግባት አለበት ስለተባለ ቶሎ ቶሎ  ታቦተ ድንግል ማርያም  ቶሎ ቶል ተብሎ ወጥቶ ቶሎ ተመልሶአል ወዲያውኑ ምንጣፉን መጋረጃውን  የመሳሰሉትን ንዋዬ ቅዱሳቱን ሰብስቦ መሮጥ ነው ።ይህኛውስ ስደት መፍትሔው ምንድንነው?
                               ብቸኛው አማራጭ የሉተራውያንን አቢያተ ክርስቲያናትን መግዛት  

ይህንን ለማድረግ የሚያስፈልገው አንደኛ ስለቤተ ክርስቲያን ጉዳይ በሚገባ የተረዳ በእምነቱ ጠንካራ የሆነ ምእመን፤ ማለትም መሰረታዊ  የሃይማኖታችንን ትምህርት በሚገባ የተገነዘበ  ለወደፊቱ ለልጆቹ በትኩረት የሚያስብ ያይማኖታዊ ዕቅድ ያለውና ምእመናኑን በማስተማር፤ በማስተባበር  ጥሩ ምሳሌ የሚሆን የሕዝቡን መሰረታዊ ችግር ተረድቶ መፍትሔ የሚፈልግ  አስተዳዳሪ  ካለ በቀላሉ መግዛት ይቻላል ። ለዚህ ጥሩ ምሳሌ መላከ ገነት ቆሞስ አባ ብርሃነ መስቀል የበርሊን ደብረ ገነት አማኑኤል ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ  ከፍተኛ እንቅስቃሴ የሕዝቡ ተሳትፎ  ያመጣው ውጤት  በበርሊን ደረጃውን የጠበቀ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን መግዛታችው ትልቅ የምሥራች ነው ። መላክ ገነት አባ ብርሃን መስቀልን ምስጋና ይገባቸዋል ። የሙኒክ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል  ቤተ ከርስቲያን የመግዝት እንቅስቃሴም በመፋጠን ላይ ይገኛል። የሀገረ ስብከቱም ሊቀ ጳጳስ አቡነ ሙሴ ከሀገረ ሰብከቱ  ሠራተኞች ፤ የአድባራት አስተዳዳሪዎች በማኅበረ ቅዱሳን አውሮጳ/ፓ ማዕከል ፤ ምእመናንን በማስተባበር ውጤታማ ሥራ በመሥራት ላይ ይገኛሉ።
ይሁን እንጂ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ  ለዚህ ሁሉ ጅምር በጎ አገልግሎት በተለይ በአውሮጳ/ፓ እንቅፋት  እየሆነ የመጣው እንፈውሳለን ፤ እናጠምቃለን  ባሕታውያን ነን የሚሉ ገለሰቦች  ለበጎ ነገር በአንድነት ተባብሮ ያገለግል ይገለገል የነበረውን  ዳግመኛ እንዳይስማማ አድርገው በመከፋፈል ላይ መገኘታቸውና ሕዝቡም ያለ ማስተዋል መከተሉ ትልቅ ችግር ሆኖ ይታያል ፡፤ ከዚህ በተረፈ ግን የራሳችንን ቤተ ክርስቲያን የመግዛቱን ነገር በትኩረት መመልከት ይገባል ። እግዚአብሔር ይርዳን ።

 ማስገንዘቢያ ሁለቱ የሉተራን ቤተ እምነት ናቸው

ሰኞ 24 ኦገስት 2015

ሀገሬን ከሀገሬ ውጪ አገኘኋት

          ሐምቡርግ ዩኒቨርስቲ
አንድ ሰው
  ከሀገር ሲወጣ ያየውን ሁሉ ከሀገሩ ጋር በማወዳደር  ይህን ሀገሬ ቢኖራት እያሉ መመኘት ልማድ ነው ። እኔም በተለያዩ የኣውሮጳ/ፓ ሀገራት ለአገልግሎት ስዘዋወር እንዲሁ መመኘቴ አልቀረም ይሁን እንጂ ግን ሀገሬን ከሀገሬ ውጪ አገኘኋት  ያልኩበት ነገሩ እንዲህ ነው ። ዐርብ ጠዋት   ከጀርመን ዋና ከተማ በርሊን  ተነስተን ከመላከ ገነት ቆሞስ አባ ብርሃነ መስቀል  የበርሊን ደብረ ገነት አማኑኤል ቤተ ክርስቲያንና የሐምቡርግ ደብረ መድኃኒት ኪዳነምሕረት አብያተ ክርስቲያናት  አስተዳዳሪ ጋር ነሐሴ 1የእመቤታችንን በዓለ ዕርገት ለማክበር ወደ ሐምቡርግ ከተማ አመራን  ዕድሜ ለቤተክርስቲያን ልጆች ተቀበሉን   እንደሰማችሁ /እንዳያችሁት  ሐምቡርግ ሲነሳ የሐምቡርግ ዩኒቨርስቲ መነሳቱ አይቀሬ ነው ። እኔም ከታላቁ ሊቅ መጋቤ ስብሐት ተክሌ ሲራክ  ጋር በመሆን ሐምቡርግ ዩኒቨርስቲን መጎብኘት ጀመርን  ዕድሜና ጤንነት ለዶ/ር ጌቴ ገላዬ  በጀርመን ሐምቡርግ ዩኒቨርስቲ የአማርኛ ቛንቛ ሥነ ጽሑፍ እና የአፍሪቃ ሥነ ቃል መምህር ናቸው በተለይ ስለገራችን ባህልና  ቛንቛዎች  ጉዳይ  እያነሱ  ብዙ ሥራ ባለመሰራቱ እየተቃጠሉ  ይኖራሉ።  በቁጭት ቃላት እያብራሩ  የአፍሪቃና  የኢትዮጵያ ቛንቛዎች እና ባህል ጥናት ክፍ  ል ጀምረን  ጉብኝታችንን ቀጠልን  ምን ልበላችሁ! የሀገራችንን ቛንቛ  ባህል  ከፍተኛ ትኩረትና ክብር ተሰጥቶ  በዚሁ ክፍል የሚማሩ ሩሲያውያንና የሌሎች ሀገሮች ዜጎች ፈረንጆች  በኢትዮጵያ ቛንቛዎችና ባህል  እንዲሁም በቅዱሳን ገድላት ላይ ጥናት ሲያደርጉ  የግዕዝ  መዝገበ ቃላት  ጥናት  ሲያደርጉ  በየቢሮአቸው የኢትዮጵያ ባህልና ገዳማትን የሚገልጡ ፎቶዎችን  በመለጠፍ  አማርኛ ቛንቛ ሲናገሩ  ስመለከት ሀገሬን ከሀገሬ ወጪ አገኘኋት  አልኩ አለመታደል ሆኖ እኛ  ለሃይማኖታችን ለባህላችን  የኛ ለምንናቸው ሁሉ ትኩረት አለመስጠታችን  ሀገራችን ከሀገራችን ውጪ ትገኛለች።  ሀገር ማለት ሃይማኖት  ከነሥርዓቱ ፤የሕዝቡ ባህልና አለባበስ በዓላትና አከባበራቸው  ወዘተ ....  ማለት ነው እነዚህ ከተሰደዱ  ሀገሪቷ ከሀገር ወጣች ያስብላልና ።ይቆየን
ከሐምቡርግ  ጀርመን                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                  እነዚህን ፎቶዎችን  ተመልከቱ
                                                                               
                                                           የግዕዝ ጥናት ፕሮጀክት







ረቡዕ 5 ኦገስት 2015

በእንተ ሙኒክ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያንና ሊቀ ብርሃናት ቆሞስ አባ ገብረ ሕይወት ፍስሐ [ጀርመን ]


ምእመናን  ከአንዱ ሀገር ወደ  ሌላው ሀገር በተለያየ ምክንያት  መሰደዳቸው አይቀሬ  ነው:: ታዲያ ሲሰደዱ በሄዱበት  ሀገር  ሁሉ ቤተክርስቲያን ያስፈልጋቸዋል :: ምንም አያጠያይቅም  የተመቻቹ  ሁኔታዎችም  አሉ :: ቤተክርስቲያን መግዛት ይቻላል :; ምናልባት የሀገረ ስብከቶች   ወጥ የሆነ መዋቅር አለመኖር  የምእመናኑ  አንድ ሐሳብ አለመሆን  ወዘተ  ችግሮች  ውጤታማ  የሆነ መንፈሳዊ አገልግሎት ለመስጠት  ችግሮች ይታያሉ :: የህዝቡ መንፈሳዊ  ተነሳሽንት  ግን ይበል የሚያሰኝ ነው :: በተለይ አንዳንድ  አድባራት ቤተክርስቲያን ለመግዛት  የሚያደርጉት እንቅስቃሴ  በጣም ግሩም ነው :;ለዛሬ የማካፍላችሁ  ስለሙኒክ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል  ቤተክርስቲያን ነው  [ጀርመን ] ሙኒክ /ሙንሽን  ማለት  የመነኮሳት  ከተማ  ማለት ነው :: ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አለ  በዚያ የሚኖሩ ምእመናን በጣም  ጠንካሮች  ናቸው :: “ጓደኛህን ንገረኝና ማንነትህን  ልንገርህ”  እንደተባለው  የሕዝቡ  ጥንካሬ  የቤተክርስቲያን  ግዥ እንቅስቃሴውን  ልነግራችሁ  አልችልም;;  ምስጢሩ  ደግሞ ልንገራችሁ ?  ; የሊቀ ብርሃናት ቆሞስ  አባ ገብረ ሕይወት ፍስሐ  ከፍተኛ  እንቅስቃሴ  ውጤት ነዋ !
ሊቀ ብርሃናት  ቆሞስ አባ ገብረ ሕይወት ፍስሐ   በጀርመን  የሙኒክ  ደብረ ብሥራት  ቅዱስ  ገብርኤል ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ  ናቸው:: ሀገር ቤት /  ኢትዮጵያ አዲስ አበባ  ኢያሉ  በተለያዩ  አድባራት  በአስተዳዳሪነት  ለረጅም ጊዜያት  አገልግለዋል::

ሊቀ ብርሃናት አባ ገብረ ሕይወት  የቅዳሴ መምህር  ናቸው  አቋቋም አዋቂ ማኅሌታዊ ናቸው  ከሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ  መንፈሳዊ ኮሌጅ  በዲፕሎማ  ; ከቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ  የመጀመሪያ ድግሪ አግኝተዋል ሙኒክ ከሚገኘው  ሉድቪግ ማክስሚልያንስ  ዩኒቨርሲቲ  የጀርመንኛ  ቋን ቋ  ሰርተፍኬት ተቀብለዋል አሁንም በመማር ላይ ይገኛሉ :: ሲቀድሱ ማኅሌት ሲቆሙ  ሲያስተምሩ  ሕዝቡን  ለበጎ ነገር  ሲያስተባብሩ  በተለይ ቤተክርስቲያን ለመግዛት  በሚያደርጉት የማስተባበር  የማስተዳድር  ልዩ ስጦታቸ  በሀገር ቤትም ሆነ በዚሁ በጀርመን በሀገረ ስብከቱም  ሆነ በሕዝቡ ዘንድ የተመሰከረላቸው ናቸው አስቀዳሹ ሁሉ ሳይቀር መልክዐ ውዳሴውን  በሚገባ አሰልጥነዋል  ለድቁናም የበቁ ደቀመዛሙርትም  አፍርተዋል 
በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ሊቀብርሃናት ሊቀብርሃናት  ደከመኝ ሰለቸኝ ማለት አያውቁም :: ታዲያ እንዲህ ያሉ አባቶች ከአገልግሎት  ፍላጎት እስክ  ብቃት  .ከብቃት እስከ ውጤታማንት  የተዋጣላቸው አባቶቻች  ጥቂቶች  ቢሆኑም  ምእመናኑ እንደነዚህ  ያሉ አባቶችን  ከጎናቸው በመቆም  አብሮ ማገልገል ይገባል :: በሙኒክ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል  ቤተክርስቲያንን  ለመግዛት  እየተደረገ  ያለው እንቅስቃሴ  በጣም የሚበረታታ  ነው :: 

                                   በአውሮጳ   የካህናት አንድነት ማኅበር ሊቋቋም መሆኑ ታወቀ በ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከመላዋ አውሮጳ   የተውጣጡ ካህናት፡” የ...