|
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ መሠረት የሚቀርቡ መንፈሳዊ ትምህርቶች ፤መረጃዎች እና የመሳሰሉት የሚስተናገዱበት ገጽ ነው
ሰኞ 9 ኖቬምበር 2015
በ«ተሐድሶ» መሰሪ እንቅስቃሴ ላይ ዛሬም እንንቃ!
ቅዳሜ 7 ኖቬምበር 2015
“ገርፎ የመጮኽ”፡- የተሐድሶዎች የማደናገሪያ ስልት
ክፍል ሁለት
የተሐድሶዎችን
እንቅስቃሴ በተመለከተ በክፍል አንድ ዝግጅታችን በማኅበረ ቅዱሳን ኅትመትና ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ ክፍል በስምዐ
ጽድቅ ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ጋዜጣ በተከታታይ እየወጣ ያለውን ጽሑፍ አቅርበንላችሁ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ክፍል
ሁለትን ደግሞ እነሆ፡-
አማናዊቷ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በክርስቶስ ደም ተመሥርታ
በሐዋርያት ስብከት ከሰፋችበት ጊዜ ጀምሮ ያለ ፈተና አልጋ በአልጋ የሆነ ሕይወት የመራችበት ጊዜ የለም፣ ወደፊትም
አይኖርምም፡፡ በሐዋርያት ዘመን ይሁዳና ቢጽሐሳውያን፣ በሐዋርያውያን አበው ዘመን ግኖስቲኮች፣ በሊቃውንት ዘመን
አርዮስ፣ መቅዶንዮስ፣ ንስጥሮስና ልዮን ቤተ ክርስቲያንን ለመፈተን የተነሡ ነበሩ፡፡ ቤተ ክርስቲያን በየዘመናቱ
እንደ ተጻራሪዎች አሳብ አሉታዊ፣ በእግዚአብሔር ፈቃድ ግን ለምእመናን መንፈሳዊ ዕድገት አዎንታዊ አስተዋጽኦ
የነበራቸው ብዙ መከራዎችን አሳልፋለች፡፡ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ከእናንተ ጋር ነኝ የሚለው የጌታችንና
የአምላካችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቃል ማረጋገጫ በዚህ ሁሉ በማያቋርጥ ማዕበል ውስጥ ቤተ ክርስቲያን
ድል አድራጊ ሆና ወጀቡን ማለፍ መቻሏ ነው፡፡
ባለንበት
ዘመን ቤተ ክርስቲያንን የማዳከምና ምእመናንን የመንጠቅ ተግባር ለይቶላቸው በሌላ የእምነት ጎራ የተሰለፉ አካላት
ተልእኮ መሆኑ ቀርቷል፡፡ ይህ ተግባር ዛሬ ዛሬ ቤተ ክርስቲያን እሷ እንደ ሻማ እየቀለጠች ባበራችላቸው፣ በሥጋዊ
ፈቃዳቸው የእንጀራ ማብሰያ ያደረጉትን ሙያ ባስተማረቻቸው፣ በጉያዋ ባደጉ፣ የእናት ጡት ነካሽ በሆኑ በራሷ ልጆች
የሚፈጸም ሆኗል፡፡ እነዚህ ሰዎች በአለባበሳቸው፣ በአነጋገራቸው (ግእዝ ስለሚጠቅሱ)፣ በአካሔዳቸው (ቤተ ክርስቲያን
ስለሚመላለሱ) እና በአገልግሎታቸው (ተአማኒነት ለመፍጠር ስለሚተጉ) ክርስቲያኖች ሊመስሉን ይችላሉ፡፡ ይህ ሁሉ
ቀን እስኪወጣ ለማደናገሪያነት የተጠቀሙበት ማስመሰያ ጭምብል እንጂ በእውነት ፊት ሚዛን የሚደፋ መንፈሳዊነት ያለበት
ሕይወት አይደለም፡፡ ይህ ድርጊታቸው የሚያስቀርብን ነገር ግላዊ ጥቅም ቢሆን ሁሉን ለእግዚአብሔር ሰጥቶ ማለፍ
ይቻል ነበር፡፡ ነገር ግን ከውስጥ እስከ ውጪ በተዘረጋ መዋቅር፣ ቤተ ክርስቲያንን እስከ መረከብ፣ ካልተቻለ እስከ
መክፈል በሚያደርስ የተቀናጀ ስልት፣ በፕሮቴስታንታዊ በጀት በታገዘ ድጋፍ አምልኮተ እግዚአብሔርን ከምድረ ገጽ ላይ
ለማጥፋት የኤልዛቤልን ዕቅድ የሚያስፈጽሙ አካላትን መታገሥ አግባብ ባለመሆኑ ማንነታቸውን ገልጾ ሕዝብ እንዲያውቀው
ማድረግ መንፈሳዊ ግዴታችን ይሆናል፡፡
እነርሱ መዋቅር ዘርግተው፣ ስልት ነድፈው፣ በጀት መድበው ቤተ
ክርስቲያንን ለማጥፋት እየሠሩ ያሉት የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም ነው፡፡ ከዚህ በፊት በቀረቡ ጥናቶች እንደተገለጸው
ተሐድሶዎች ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን እስከ መክፈል፣ ከተቻለም እስከ መረከብ ያደርሱናል ብለው የዘረጓቸው ስልቶች
አሉ፡፡ እነዚህን ስልቶች እውን ለማድረግ ደግሞ የተለያዩ መንገዶችን ይጠቀማሉ፡፡ ከእነዚህ ተሐድሶዎች ከሚጠቀሟቸው
መንገዶች መካከል ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡
፩.በሚያውቋቸው ሰዎች በኩል መቅረብ፡- ዛሬ ላይ ተሐድሶ ነን በማለት ቤተ ክርስቲያንን እናድሳለን የሚሉ አካላት የተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታዮች ስለነበሩ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ብዙ ሰዎችን ያውቃሉ፡፡ በቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ መዋቅር ውስጥ፣ በአብነት ትምህርት ቤት ወንበር ዘርግተው የሚያስተምሩ የአብነት መምህራንን፣ በልዩ ልዩ ገዳማት የሚገኙ መናንያንን እና አስተዳዳሪዎችን፣ የመንፈሳዊ ትምህርት ተቋማት አስተዳዳሪዎችን፣ መምህራንን እንዲሁም የሰንበት ትምህርት ቤት አመራሮችንና አባላትን ማወቃቸውና መቅረባቸው በእነርሱ በኩል ተልእኳቸውን የማስፈጸም ዕድል ፈጥሮላቸዋል፡፡
ለምሳሌ በ፲፱፻፺ ዓ.ም ቀኖና ተሰጥቶት ተጸጽቶ በመመለስ ፋንታ በኑፋቄው በመግፋቱ ምክንያት በ፳፻ወ፬ ዓ.ም በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባዔ ከተወገዙት ፲፮ የተሐድሶ አራማጅ ግለሰቦች መካከል አንዱ የሆነው፣ አሁንም ኦርቶዶክስ ነኝ በማለት የሚያደናግረው እና በሰሜኑ የአገራችን ክፍል የሚካሔደውን የተሐድሶ እንቅስቃሴ የሚመራው ጽጌ ሥጦታው ብዙ የአብነት መምህራንን ለመቀሰጥ ዕድል ያገኘው በአብነት ትምህ ርት ቤት የሚያውቃቸውን ሰዎች በመጠቀም ነው፡፡ መሠረተ ክርስቶስ ቸርችም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ለማደስ በሚደረገው እንቅስቃሴ ለአገልግሎት የምፈልጋቸው በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ አገልግሎት የሚሰጡ ካህናትን ብቻ ነውÂ ማለቷ የአብነት መምህራንን ለማጥመድ የቤተ ክርስቲያንን ቋንቋ የሚያውቅ አካል አስፈላጊ እንደሆነ በመረዳቷ ነው፡፡ ይህ ሁሉ የሚያሳየን ተሐድሶዎች ከቤተ ክርስቲያኒቷ ቋንቋና ከቤተ ክርስቲያን አባቶች ጋር መተዋወቃቸው በምእመናን ዘንድ ተቀባይ ነትን በማግኘት ተልእኳቸውን ለማሳካት ምን ያህል ያገዛቸው መሆኑን ነው፡፡
፪.በገንዘብ ማታለል፡- ተሐድሶዎች ቤተ ክርስቲያንን ለማጥፋት ከምንጩ ላይ መሥራት አለብን ብለው ትኩረት የሰጧቸው አብዛኛዎቹ ቦታዎች ላይ የሚገኙት የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች የገንዘብ ችግር ያለባቸው ናቸው፡፡ አብነት ትምህርት ቤቶችን ብንወስድ በቤተ ክርስቲያን መዋቅር የተረሱ የቤተ ክርስቲያን የደም ሥሮች ናቸው፡፡ የሕዝቡ የኑሮ ሁኔታ ከመቀየሩ ጋር ተያይዞ በአሁኑ ዘመን ከዚህ በፊት እንደነበረው ቁራሽ እየለመኑ መማር የማይታሰብ እየሆነ መጥቷል፡፡ በዚህ ምክንያት የአብነት ተማሪዎች ሌሎች የገንዘብ ማግኛ ዘዴዎችን እየተጠቀሙ ትምህርታቸውን መቀጠል ይፈልጋሉ፡፡ በዚህ መካከል ከአሜሪካና ከአውሮፓ የፕሮቴስታንት ድርጅቶች በሚላክላቸው ገንዘብ ኪሳቸውን ያደለቡት ተሐድሶዎች አንድ አማራጭ ሆነው አብነት ተማሪዎችን ቀረቧቸው፡፡ ተሐድሶዎቹ ለገዳማት፣ ለመንፈሳዊ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎችና ለገጠሪቷ ቤተ ክርስቲያን ካህናትና ዲያቆናትም ተመሳሳይ ድጋፍ እናደርጋለን በሚል ሰበብ እየበረዟቸው ይገኛሉ፡፡ ባለፈው ዓመት አዲስ አበባ ኮተቤ አካባቢ ባካሔዱት ስብሰባ ላይ ማኅበረ ቅዱሳን ያልደረሰባቸውን አብነት ትምህርት ቤቶችን ቀድመን በድጎማ መልክ መቅረብና መያዝ አለብንÂ የሚል አቅጣጫ መንደፋቸውን ተናግረዋል፡፡
፫.አሠልጥኖ/አሰይጥኖ መመለስ፡- በትውውቅም ሆነ በማታለያ የቀረቧቸውን ሰዎች የጥፋት ዓላማቸውን ለመፈጸም የሚችሉበትን አቅምÂ በሥልጠና ካስታጠቋቸው በኋላ ተልእኳቸውን ሳይረሱ ወደ ቀድሞ ቦታቸው ተመልሰው ሥራቸውን እንዲቀጥሉ ያደርጓቸዋል፡፡ የተሐድሶ ሥልጠናዎችን ወስደው ወይም ሃይማኖታቸውን ትተው ወደ ሌላ በረት ሔደው ከቆዩ በኋላ የጣሉትን ቆብና መስቀል ይዘው ኦርቶዶክሳዊ መስለው የተመለሱ ሰዎች ቁጥር ብዙ ነው፡፡ በዚህ መንገድ ውጪ ድረስ ሔደው ተምረው የመጡ አሁንም አባÂ እገሌ፣ ቄስÂ እገሌ፣ ዲያቆንÂ እገሌ እየተባሉ የሚጠሩ በልብሳቸውና በምላሳቸው ኦርቶዶክሳውያን፣ በልባቸው ግን ፕሮቴስታንት የሆኑ ብዙ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችÂ አሉ፡፡
፬.ሚዲያዎችን መጠቀም፡-
ተሐድሶዎች እንቅስቃሴያቸውን ከግብ ለማድረስ የኅትመት፣ የኤሌክትሮኒክስና የብሮድካስት ሚዲያዎችን ይጠቀማሉ፡፡ ማን
እንዳዘጋጃቸው የማይታወቁ ባለቤት አልባ በራሪ ወረቀቶችን፣ ጋዜጦችን፣ መጽሔቶችንና መጻሕፍትን እንዲሁም የተለያዩ
የምስል ወድምጽ ውጤቶችን በማሠራጨት መርዛቸውን ይረጫሉ፡፡ ድረ ገጾችን፣ የጡመራ መድረኮችን፣ የሬዲዮ እና
የቴሌቪዥን መርሐ ግብራትን በመጠቀም ኑፋቄያቸውቸውን እያስፋፉ ይገኛሉ፡፡
፬.፩.ጋዜጦች
ተሐድሶዎች እያሳተሙ ከሚያሠራጯቸውና መርዛቸውን ከሚረጩባቸው
ጋዜጦቻቸው መካከል መጥቅዕ፣ በሃይማኖት ቁሙ፣ መርከብ፣ መና ተዋሕዶ፣ እውነት፣ ኖኅተ ብርሃን፣ ከሣቴ ብርሃን፣
ርግብ፣ ንቁ፣ ወዘተ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡
፬.፪.መጽሔቶች
ሌሎች ተሐድሶዎች ኑፋቄያቸውን የሚያሠራጩባቸው የኅትመት ውጤቶች መጽሔቶች ናቸው፡፡ ከእነዚህ መጽሔቶች መካከል ጥቂቶቹ አንቀጸ ብርሃን፣ ብሔራዊ ተሐድሶ፣ ከሣቴ ብርሃን ዘኢትዮጵያ፣ ሰላማ ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ፣ ጮራ፣ ቤተ ፍቅር፣ ወዘተ ሲሆኑ ከእነዚህ ባልተናነሰ ሁኔታ ለተሐድሶ እንቅስቃሴው ድጋፍ ሰጪ የሆኑ ጽሑፎችን የሚያቀርቡ ጌሠም፣ ትሪኒቲ፣ ማቴቴስ፣ ካሪዝማ፣ ወዘተ የሚባሉ የፕሮቴስታንት መጽሔቶች አሉ፡፡
፬.፫.መጻሕፍት
ተሐድሶዎች
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስም ከአንድ መቶ ሰማንያ (፻፹) በላይ መጻሕፍት ጽፈዋል፡፡
መጽሐፎቻቸው የክርስቶስን አምላክነትና የእመቤታችንን አማላጅነት ክደው የሚያስክዱ፣ ቤተ ክርስቲያንን የሚነቅፉ፣
ቅዱሳንን የሚሳደቡ፣ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባርን የሚያጥላሉ ናቸው፡፡ ተሐድሶዎች የግብር አባታቸው የሉተር ልጆች
እንጂ ኦርቶዶክሳውያን አለመሆናቸውን መጽሐፎቻቸው ይናገራሉ፡፡ ከቁጥራቸው ብዛት የተነሣ ሁሉንም የተሐድሶ መጻሕፍት
መዘርዘር ከባድ ቢሆንም በ፳፻ወ፬ ዓ.ም ከእነ ጽጌ ሥጦታው ጋር የተወገዘው አሸናፊ መኮንን ብቻ ከሃያ አምስት በላይ
መጻሕፍትን ጽፏል፡፡ የተለያዩ የብዕር ስሞችን በመጠቀም ቤተ ክርስቲያንን መሳደብ የእንጀራ ማብሰያው ያደረገው
ሠረቀ ብርሃን ዘወንጌል መስተብቁዕ ዘሙታን፣ የዘመናት እንቆቅልሽ ሲፈታ፣ ማሳቀልና ሎፌ የሚሉ በመርዝ የተሞሉ
መጻሕፍትን ጽፏል፡፡
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ምእመናንን በስውር መንጠቁ አላጠግባቸው ብሎ ቤተ ክርስቲያንን በግልጽ እየተዋጓት ያሉት ፕሮቴስታንቶችም የተሐድሶ እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እንዳለ እና እንቅስቃሴውም ለእነርሱ ድጋፍ ሰጪ መሆኑን በመጽሐፎቻቸው ገልጸዋል፡፡ ለምሳሌ፡- ጸጋአብ በቀለ የተባለ የፕሮቴስታንት ፓስተር የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ተሐድሶ - ሳታድግ ያረጀች የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንÂ በሚለው መጽሐፉ፣ ዳንኤል ተሾመ የሚባል የመካነ ኢየሱስ ቸርች አባል የሆነ ፕሮቴስታንት የቅርብ ዘመኑ (፲፱፻፸፱-፲፱፻፺፱) የተሐድሶ እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንÂ በሚል ለሁለተኛ ዲግሪ ማሟያ ባዘጋጀው ጽሑፍ እንዲሁም በቀለ ወልደ ኪዳን የተባለ ከሌሊቱ ስንት ሰዓት ነው?በሚለው መጽሐፉ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስላለው የተሐድሶ እንቅስቃሴ ገልጸዋል፡፡ እነዚህ መጻሕፍት የተሐድሶ እንቅስቃሴን ግብና ከፕሮቴስታንት ጋር ያለውን ድርና ማግነት ቁልጭ አድርገው የሚያሳዩ ናቸው፡፡
፬.፬.ድረ ገጾችና የጡመራ መድረኮች
በዚህ ዘመን ሁሉም ነገር በኤሌክትሮኒክስ መቅረብ የሚችል ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ተሐድሶዎች ኑፋቄያቸውን ለመዝራት ከተጠቀሙባቸው ስልቶች መካከል አንዱ ድረ ገጾችንና የጡመራ መድረኮችን መጠቀም ነው፡፡ ቁጥራቸ ውን በትክክል ማወቅ ባይቻልም በዛ ያሉ የተሐድሶ የጡመራ መድረኮችና ድረ ገጾች አሉ፡፡ ከእነዚህ ድረ ገጾችና የጡመራ መድረኮች መካከል አባ ሰላማ፣ ጮራ፣ ደጀ ብርሃን፣ የዲያ ቆን አሸናፊ መኮንን ገጽ፣ ተሐድሶ ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ፣ ዐውደ ምሕረት፣ ማራናታ፣ ቤተ ፍቅርና የዲያቆን አቤኔ ዘር ተክሉ ገጽ ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡
፭.ተገፋን ብሎ መጮህ፡- ጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ ይጮሃልÂ እንደሚባለው፣ ተሐድሶዎች አጥፊዎቹ፣ ቤተ ክርስቲያንን ለማፍረስ የሚተጉት ራሳቸው ሆነው ሳለ በራሳቸው ድረ ገጾች፣ የጡመራ መድረኮችና በተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች በኩል ተገፋን እያሉ ይጮሃሉ፡፡ በ፳፻ወ፮ ዓ.ም የተወሰኑ ዘማርያንÂ አሜሪካ ሔደው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና በማኅበረ ቅዱሳን ለተገፉ ሰባክያንና ዘማርያን በሚል ገንዘብ ሲሰበስቡ ነበር፡፡ በ፳፻ወ፬ ዓ.ም በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባዔ የተወገዘው ማኅበረ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን የተባለው የተሐድሶ ድርጅት ደግሞ የካቲት ፮ ቀን ፳፻ወ፮ ዓ.ም በቁ ጥር አ/ሰ/ማ/18/262/06 በማኅበረ ቅዱሳን አቀነባባሪነት የተወሰነብን የውግዘት ውሳኔ እንዲነሣልን ስለመጠየቅ ይመለከታልÂ የሚል ደብዳቤ በአድራሻ ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ አስገብቶ ነበር፡፡ ደብዳቤው ርእሱ እንደሚናገረው ማኅበረ ቅዱሳንን የሚያወግዝና ውግዘታችን ይነሣልን የሚል ነው፡፡ ድርጅቱ በደብዳቤው፡-
ክልላዊ ማኅበር መመሥረት የለባችሁም፣ በአገር አቀፍ የተፈቀደለት ማኅበረ ቅዱሳን ብቻ ስለሆነ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት ሁኑ፣ ካልሆናችሁ ግን መናፍቃን ናችሁ፣ ትለያላችሁÂ በማለት ሲዝትብን የነበረ ማኅበረ ቅዱሳን ከእኔ በቀር ሌላ ማኅበር መኖር የለበትም የሚል አቋም ይዞ በከፍተኛ ሁኔታ በመንቀሳቀስ ራሱን እንደ ልጅ በመቁጠር እኛን ደግሞ እንደ እንጀራ ልጅ እንድንታይና እንድንወገዝ ካለው ጽኑ አቋሙ የተነሣ ምንም ዐይነት የክህደት ትምህርት ሳንማርም ሆነ ሳናስተምር ያለ ምንም መረጃ ይሁን ማስረጃ በአሉቧልታና በትምክህት መናፍቃን ናቸው እያለ በገንዘብ ኀይል በሁሉም ዘንድ የተሳሳተ ግንዛቤ እንዲኖር በማድረግ ሳንጠየቅ፣ ሳንመከር፣ ሳንገሠጽ፣ እውነት ይሁን አይሁን ሳይጣራ፣ ቀርበን በወቅቱም ምንም ዕድል ሳይሰጠን በማኅበረ ቅዱሳን ከፍተኛ ተዋናይነት የውግዘት ውሳኔ መተላለፉ አሳዝኖናል ይላል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ አባ ሰላማና ተሐድሶ ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ በሚባሉት ድረ ገጾቻቸው በ፳፻ወ፬ ዓ.ም ተሐድሶዎች ሲወገዙ፣ ከዚያም በኋላ እነሱን ለማስቆም ቤተ ክርስቲያኒቱ በምታደርገው እንቅስቃሴ ሁሉ አገልጋዮቿን የምታሳድድ ቤተ ክርስቲያንÂ እያሉ ስሟን ሲያጠፉ ይሰማሉ፡፡ ለምሳሌ ተሐድሶ ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ኑ! እንዋቀስÂ በሚል ርእስ ባወጣው ጽሑፍ እንደ አለመታደል ሆኖ ሲኖዶሳችን መናፍቃንን በመደገፍ ጻድቃንን ያሳድዳል፤ ቀን ሲደርስ የእግዚአብሔርን ፍርድ እናያለን፤ እስከዚያው እንክርዳዱ ከስንዴው ጋር ተናንቆ ያድጋል፡፡ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቃሉና በመንፈሱ ተሐድሶ ይጎብኝልን፡፡በማለት ጽፈዋል፡፡ ሊያ የሚባል መጽሔት ላይ ደግሞ የወንድሞች ከሣሽ ማኅበረ ቅዱሳንÂ በሚል ርእስ ሰፊ ሐተታ ያለው ጽሑፍ ጽፈው ነበር፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ቁጥር በሰባት ሚሊዮን መቀነሱን በይፋ አምናለች፡፡ ቤተ ክርስቲያን እንዲህ ስትል በአንድ ወገን መንጋው አለመጠበቁንና በዚህ ምክንያት መሰረቁን አምናለች፡፡ በሌላ በኩል ግን ሌሎች ሰረቁኝ፣ ወሰዱብኝ ከማለት ያለፈ ምክንያቱን በሚገባ ያጤነችው አትመስልም፡፡ ሌሎች በውጪ አግኝተው ከወሰዷቸው በላይ እንደ ማኅበረ ቅዱሳን ያለ የወንድሞች ከሳሽና አክራሪ ቡድን እኔን አልመሰላችሁምና መናፍቃን ሆናችኋል በሚል ሕገ ወጥ መንገድ ያሳደዳቸው ጥቂቶች አይደሉም፡፡ ምናልባት ለቁጥሩ መቀነስ የማኅበረ ቅዱሳን እጅም እንዳለበት መታመን አለበት ይላል፡፡ (ሊያ መጽሔት ቅጽ ፪ ቁጥር ፳፮ ሚያዝያ ፳፻ወ፭ ዓ.ም)
እስካሁን ያየነው የአገር ውስጡን ጩኸት ነው፡፡ ተሐድሶዎች ከፕሮቴስታንቶች ጋር በመተባበር ይህንን ጩኸት ዐለም አቀፋዊ አድርገውታል፡፡ ዓላማዬ የክርስቲያኖችን ጭቆና ለዓለም ማሳወቅ ነውÂ የሚል ክርስቲያን ሳይንስ ሞኒተርÂ የሚባል አንድ የዜና አውታር አለ፡፡ በቀን ከዐሥር በላይ ከሃይማኖት ጋር ግንኙነት ያላቸውን ዜናዎች ያወጣል፡፡ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮችን በደል አውጥቶ አያውቅም፡፡ በሶርያ በየዕለቱ ከሞት ጋር ስለሚታገሉት ኦርቶዶክሳውያን፣ ስለ ፓትርያርኩ ለዐሥራ አምስት ቀናት የሔዱበት አድራሻ አለመታወቅ የዘገበው ነገር አልነበረም፡፡ ያልዘገበው ግን ባለማወቅ ሳይሆን በዓላማ ነው፡፡ ለዚህ ድርጅት ክርስቲያን ማለት ፕሮቴስታንት ነው፡፡ የሚያሰማውም የእነሱን ጩኸት ነው፡፡
ተቀማጭነቱን አሜሪካ ያደረገ ኦፕን ዶርስ የሚባል ድርጅት አለ፡፡ ድርጅቱ አንድሪው ቫን ደር ቢጅል በሚባል ግለሰብ በ፲፱፻፶፭ የተመሠረተ መንግ ሥታዊ ያልሆነ የክርስቲያን ድርጅት ነው፡፡ እንደ ራሳቸው አገላለጽ በግለሰቦች መዋጮ የሚተዳደር ነው፡፡ ከ፲፱፻፺፩ ጀምሮ በዓለም አቀፍ ደረጃ በክርስቲያኖች ላይ ከፍተኛ ጭቆና የሚያደርሱ የአምሳ አገራትን ዝርዝር ያወጣል፡፡ በዚህ ድርጅት ዘገባ መሠረት አገራችን ኢትዮጵያ ክርስቲያኖችን ከሚጨቁኑት አምሳ አገራት መካከል ባለፉት አምስት ዓመታት ማለትም በ2011 ፵፫ኛ፣ በ2012 ፴፰ኛ፣ በ2013 ፲፭ኛ፣ በ2014 ፲፯ኛ እና በ2015 ፳፪ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡ ድርጅቱ ባለፉት ሁለት ዓመታት ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የክርስቲያኖች ጭቆና ከዓመት ወደ ዓመት እየቀነሰ ነውÂ ይላል፡፡ ይህ አገላለጽ ሲብራራ ተሐድሶዎች ቤተ ክርስቲያንን ለማፍረስ የተሻለ ዕድል እያገኙ ነው ማለት ነው፡፡
ተቋሙ በ2013 ባወጣው ዘገባው ስለ ኢትዮጵያ እንዲህ የሚል ቃል አስቀምጧል፡-
Ethiopia has a complex mix of persecution dynamics.Ecclesiastical arrogance is the country historical persecution dynamic. For years, the Ethiopian Orthodox Church (EOC) has been seriously persecuting believers who have left their ranks or joined the renewal movements within the EOC. (World Watch List 2013)
ኢትዮጵያ ዘርፈ ብዙ የሆነ ጭቆና የሚካሔድባት አገር ናት፡፡ ቤተ ክህነታዊ እብሪትየአገሪቱ ታሪካዊ የጭቆና መታወቂያ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ወጥተው አዲስ የመጣውን የፕሮቴስታንት እምነት እና በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እያሉ የተሐድሶውን ጎራ የተቀላቀሉትን አማኞች ክፉኛ ትጨቁናለች፡፡ካለ በኋላ ቀጥሎ፡-
The fanatic group inside the EOC (Mahibere Kidusan) is a growing threat for non-traditional Protestants and renewal movements within the EOC. The group allegedly wants to control the government policies to restrict the activities of other religions. Mahibere Kidusan is currently riding high. (World Watch List 2013)
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥር የሚገኘው ማኅበረ ቅዱሳን የሚባለው አክራሪ ቡድን ለፕሮቴስታንቶች እና በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ ላሉ ተሐድሶዎች ታላቅ ሥጋት ነው፡፡ ቡድኑ ሌሎች የእምነት ቤቶች የሚያደርጓቸውን እንቅስቃሴዎች ለመገደብ የመንግሥትን ፖሊሲዎች በጥብቅ መቆጣጠር በጥብቅ ይፈልጋል፡፡ Â በአሁኑ ጊዜ ማኅበሩ በፍጥነት እያንሠራራ ነው፡፡
2013 ማለት በኢትዮጵያ ተሐድሶ ዎች የተወገዙበት ዓመት ማግስት ማለት ነው፡፡ ለዚህም ነው እየተጨቆንን ነው የሚለው ጉዳይ ዓለም አቀፋዊ አጀንዳ እንዲሆን እና ፖለቲካዊ አቅጣጫ እንዲይዝ ለማድረግ የሞከሩት፡፡ ተሐድሶዎች የዘረጉት መስመር የት እንደሚደርስ ወይም ተሐድሶው በማን ግፊት እየተመራ እንደሆነ ይህ አገላለጽ ሁነኛ ማሳያ ነው፡፡ ኦርቶዶክስ ሳይሆኑ ኦርቶዶክስ ነንÂ በማለት የቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ ለመቀየር ብሎም ቤተ ክርስቲያንን ለመክፈል የሚሠሩ ወገኖች ቁጥራቸው በርከት ባሉባቸው ቦታዎች ኦርቶዶክሶችን በማሸማቀቅ፣ በማስፈራራትና በመዝለፍ ቤተ ክርስቲያንን ለማጥፋት የተነሡት እነርሱ ሆነው ሳለ ራሳቸው የሠሩትን ግፍና በደል ለቤተ ክርስቲያን አድርገው ተሳደድን ብለው ይጮሃሉ፡፡ ብዙዎቻችንም ዐውቀንም ይሁን ሳናውቅ የእነርሱ ጩኸት ደጋፊዎችና ጠበቆች እየሆን ነው፡፡ የራስን አጥብቆ መያዝና ለሌላ ወገን አላስደፍርም ማለት ማስወቀስና ማስተቸት ከጀመረ ቆይቷል፡፡
እነርሱ እነዚህን መንገዶች ተጠቅመው ቤተ ክርስቲያንን የማዳከም፣ ዶግማና ቀኖናዋን የመቆነጻጸል ተግባራቸውን ቀጥለውበታል፡፡ እኛ ይህ ሁሉ ሲፈጸም ምን ያከናወንነው ተግባር አለ ተብለን ራሳችንን ብንጠየቅ መልሳችን ምንም የሚል ነው፡፡ ስለዚህ ቢያንስ የችግሩን አሳሳቢነትና የአደጋውን አስከፊነት ጠንቅቀን ማወቅና መንገዶቻቸውን ለመዝጋት የሚያስችሉ ሥራዎችን መሥራት ይገባናል፡፡ እነርሱ በገንዘብ ለማታለል ምቹ ሁኔታ ያገኙት እኛ አብነት ትምህርት ቤቶችን እና ገዳማትን ባለመደገፋችን መሆኑን መረዳት አለብን፡፡
ይቆየን
ሐሙስ 5 ኖቬምበር 2015
የተሐድሶን ምንነት ሳታውቁ፣ ስለ ተሐድሶዎች ማንነት አትጠይቁ!!
ሰኞ 2 ኖቬምበር 2015
ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ: በአ/አበባ ሀ/ስብከት በቅዱስ ሲኖዶስ የተመደበቡትን ሓላፊነት እንዳይወጡ መደረጋቸውን ተናገሩ፤“ሥልጣንን አላግባብ በመጠቀም ዐቢይ የሕግ ግድፈት ተፈጽሟል
ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ፡-
- ከቅዱስ ፓትርያርኩም ኾነ ከጠቅላይ ጽ/ቤቱ ጋር በመልካም የሥራ ግንኙነት ላይ ነበርኩ
- የአ/አበባ ሀ/ስብከትን ኹለት ሥራ አስኪያጆች የመለመለውና ያቀረበው አካል አይታወቅም
- ሒሳቡን እንዲያንቀሳቅሱ ሌላ ፈራሚ ሊቀ ጳጳስ የተመደቡበት ኹኔታ አሳዛኝ ክሥተት ነው
- በረዳት ሊቀ ጳጳስነት የመደበኝ ምልዓተ ጉባኤው፣ ለቤተ ክርስቲያን የሚበጅ መፍትሔ ይስጠኝ
- ልዩ ደንብና መመሪያ ባልወጣበት የፓትርያርኩ ልዩ ሀ/ስብከት መኾኑ ክፍተት ፈጥሯል
- የፓትርያርኩ፣ የረዳት ሊቀ ጳጳሱና የሥራ አስኪያጁ ተግባርና ሓላፊነት መታወቅ አለበት
- በሚሻሻለው ቃለ ዐዋዲ የሦስቱ ሓላፊዎች ሥልጣንና ተግባር ተካቶ እንዲቀርብ ተወስኗል
- ፓትርያርኩ ያለረዳት ሊቀ ጳጳሱ ምርጫ ሥራ አስኪያጆችን በመሾም የሕግ ግድፈትና ጣልቃ ገብነት የፈጸሙበትን አካሔድ በመደገፍ “ሕመም ቢኖርብኝም የሥራ ፍላጎት አለኝ” በሚል በአዲስ አበባ ለመመደብ የጠየቁት ሊቀ ጳጳስ ክፉኛ ትዝብት ላይ ወድቀዋል
* * *
ጥቅምት 15 ቀን 2008 ዓ.ም.
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንለቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ
አዲስ አበባ፤
ጉዳዩ፡- በቅዱስ
ሲኖዶስ በተሰጠኝ የሥራ ሓላፊነት ላይ ከሕገ ቤተ ክርስቲያኑና ከቃለ ዐዋዲው ውጭ በደል በመፈጸሙ፤ የተፈጸመውን
የሥራና የሕግ ግድፈት በቅዱስ ሲኖዶሱ ለማሳረምና ትክክለኛ ፍትሕ እንዲሰጠኝ የቀረበ አቤቱታ ነው፤
ብፁዕ ወቅዱስ አባታችን፤ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት አባቶቼ፤
እንደሚታወቀው ኹሉ በጥቅምት 2007 ዓ.ም. በመንፈስ ቅዱስ መሪነት እና የበላይነት በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ
ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በቤተ ክርስቲያኗ ሕግ መሠረት የቅዱስ ፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ በመኾን መመደቤ
ይታወቃል፡፡እኔም በዚህ በመንፈስ ቅዱስ በሚመራው ታላቅ ጉባኤ እና በአባቶቼ የተሰጠኝን ሓላፊነትና አደራ ከተመደብኩበት ጊዜ አንሥቶ አቅሜ በፈቀደ መልኩ ያለውን ነባራዊ ኹኔታ በማገናዘብ ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጋር በመመካከር የጠቅላይ ቤተ ክህነቱንም የሥራና የደረጃ መዋቅርን በመጠበቅ እያገለገልኩ እገኝ ነበር፤ ለዚህም እንደ ማሳያ፡-
ሀ/በሀገረ ስብከቱ የባለጉዳዮች መስተንግዶ ሥርዐት ዘመናዊና ቀልጣፋ እንዲሁም ተጠያቂነት ያለው እንዲኾን በማድረግ የተለያዩ አደረጃጀቶችን ሊጠቅም በሚችል መልኩ በማውጣት፤
ለ/የንብረትና የገንዘብ አጠባበቅ ኹኔታ በመረጃ የተደራጀ እና ዘመናዊ አሠራር እንዲኖረው በማድረግ፤
ሐ/በመንግሥት በኩል ቤተ ክርስቲያኗ ያላትን መብትና ጥቅም በመገንዘብ ከቀረጥ ነጻ በኾነ መንገድ ለቅዱስ ፓትርያርኩ እና ለሀገረ ስብከቱ የትራንስፖርት መገልገያ የሚውሉ መኪናዎች እንዲገቡ ጥረት በማድረግ፤
መ/ሀገረ
ስብከቱ የሚያከናውናቸው ሥራዎች በአጠቃላይ በተጠና ዕቅድ እንዲሠራ፤ የየክፍሎቹ ሓላፊዎች በሚለካና ሊደረስበት
በሚችል መልኩ ዕቅድ እንዲዘጋጅና የቀረበው ዕቅድም በአስተዳደር ጉባኤው ተገምግሞ ሥራ ላይ እንዲውል መመሪያ
በመስጠት ስንሠራ ቆይተናል፡፡
ከላይ ለማሳያነት የጠቀስኋቸው ተግባራት ብዙ ጠለቅ ያለ የአፈጻጸም ሒደቶች ቢኖሯቸውም አቅም በፈቀደ መልኩ ስንቀሳቀስ ቆይቼ ነበር፡፡
ኾኖም ከቅዱስ ፓትርያርኩም ኾነ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ጋር በመልካም የሥራ ግንኙነት፣ በቤተ ክርስቲያኗ ሕግና መመሪያ መሠረት አባቶቼ የሰጣችኹኝን የሥራ ሓላፊነት በመወጣት ላይ ነበርኩ፡፡
ይኹንና ዐቢይ የሕግ ግድፈት በመፈጸሙ ምክንያትና ሥልጣንን አለአግባብ በመጠቀም ጣልቃ ገብነት ሥራዬን በሓላፊነት እንዳላከናውን ተደርጌአለኹ፡፡ ከዕንቅፋቶቹና ከተፈጸሙት የሕግ ስሕተቶችም መካከል፤ከላይ ለማሳያነት የጠቀስኋቸው ተግባራት ብዙ ጠለቅ ያለ የአፈጻጸም ሒደቶች ቢኖሯቸውም አቅም በፈቀደ መልኩ ስንቀሳቀስ ቆይቼ ነበር፡፡
ኾኖም ከቅዱስ ፓትርያርኩም ኾነ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ጋር በመልካም የሥራ ግንኙነት፣ በቤተ ክርስቲያኗ ሕግና መመሪያ መሠረት አባቶቼ የሰጣችኹኝን የሥራ ሓላፊነት በመወጣት ላይ ነበርኩ፡፡
1/
በጥቅምት ወር 2007 ዓ.ም. በቅዱስ ሲኖዶስ ጸድቆ በወጣው ሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ 50፣ የአዲስ አበባ
ሀገረ ስብከት የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ሀገረ ስብከት ነው፤ ካለ በኋላ በንኡስ ቁጥር ሦስት፣ ሀገረ ስብከቱ
የሚገኘው የሀገሪቱ ርእሰ ከተማ ላይ እንደ መኾኑ መጠን ከሌሎች አህጉረ ስብከት የሚለይባቸው ልዩ ኹኔታዎች ስላሉ
እኒኽን ኹኔታዎች ከግምት ያስገባ ለየት ያለ አደረጃጀት በቃለ ዐዋዲው እንዲኖረው እንደሚደረግ ይገልጻል፡፡
በዚህ መሠረት ልዩ መመሪያ ባልወጣበት ኹኔታ አንቀጹን በሌላ መንገድ በመተርጎምና ምክንያቱን በግልጽ ባላወቅሁት መንገድ ሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ 53 ንኡስ ቁጥር 8ን በመተላለፍ፤
1.1) ሊቀ ጳጳሱ ለሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ መልምለው ለቅዱስ ፓትርያርኩ ሳያቀርቡና በሕጉም መሠረት የጋራ ስምምነት ሳይኖረን፤
1.2) በመቀጠልም በሕጉ መሠረት የረዳት ሊቀ ጳጳሱንና የቅዱስ ፓትርያርኩን ይኹንታ መሠረት አድርጎ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ማጽደቅ ሲገባው ይህ መሠረታዊ ሒደት ባልተፈጸመበት ኹኔታ፤
1.2) በመቀጠልም በሕጉ መሠረት የረዳት ሊቀ ጳጳሱንና የቅዱስ ፓትርያርኩን ይኹንታ መሠረት አድርጎ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ማጽደቅ ሲገባው ይህ መሠረታዊ ሒደት ባልተፈጸመበት ኹኔታ፤
1.3)
መልማዩና አቅራቢው በውል ማን እንደኾነ ባልታወቀበትና ሕግ በማይፈቅደው መልኩ በፓትርያርኩ ቀጥተኛ የሹመት ደብዳቤ
ሥራ አስኪያጅ እና ምክትል ሥራ አስኪያጅ ለሀገረ ስብከቱ በመመደቡ ምክንያት ሀገረ ስብከቱ ከፍተኛ ቀውስ ውስጥ
ገባ፡፡
2.
እኒህን ዋነኛ የሕግ ግድፈቶች በመዘርዘር ጉዳዩ በቅዱስ ፓትርያርኩ እንዲታረም በመጀመሪያ በ11/07/2007 ዓ/ም
በመቀጠልም በ16/07/2007 ዓ/ም በተጻፈ ደብዳቤ ጠይቄ ነበር፤ ነገር ግን ምላሽ አልተሰጠኝም፡፡ በተጨማሪም
ጉዳዩ በቋሚ ሲኖዶስ ትኩረት ተሰጥቶት እንዲታረም በ17/7/2007 ዓ/ም አቅርቤ ነበር፡፡
3.
ያለሊቀ ጳጳሱ አቅራቢነትና መልማይነት፣ ያለጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ጽ/ቤት ዕውቅናና አጽዳቂነት ከሕግ ውጭ በቀጥታ
በቅዱስ ፓትርያርኩ ለሀገረ ስብከቱ የተሾሙት ሥራ አስኪያጅ፣ የቃለ ዐዋዲውን አንቀጽ 45 ንኡስ ቁጥር 7ን
በመተላለፍ፣ አሳማኝ እና ምክንያታዊ ባልኾነ መንገድ በሀገረ ስብከቱ በክፍል ዋና ሓላፊነት ተመድበው የሚሠሩትን
ሠራተኞች በ30/08/2007 ዓ/ም ያለሀገረ ስብከቱ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ዕውቅናና ፈቃድ የተወሰኑትን ከደረጃ ዝቅ
በማድረግ፣ የቀሩትንም እዚያው ባለው የሥራ ክፍል አዘዋወሩ፡፡
ከዋና ክፍል ሓላፊዎቹ
በቀረበልኝ አቤቱታ፤ ሕጉን የጣሰና ምክንያቱ በትክክል ያልታወቀ ዝውውርና ከደረጃም ዝቅ ማድረግ በመኾኑ በተጨማሪም
ሠራተኞች በተሰማሩበት የሥራ መስክ ላይ ተረጋግቶ የመሥራት መብትን የሚያሳጣ በመኾኑ ባለኝ ሥልጣንና ሓላፊነት
መሠረት በ30/08/2007 ዓ/ም ዝውውሩንና ከደረጃ ዝቅ ማድረጉን አገድኩ፡፡ ይህም በሕጉ መሠረት ተጢኖ መታየትና
መገምገም ሲኖርበት የቃለ ዐዋዲውን አንቀጽ 60 ቁጥር 2 ፊደል (ሰ)እና(ሸ) ያለአግባብ በመጥቀስና በመጠቀም
በ4/9/2007 ዓ/ም በቅዱስ ፓትርያርኩ በተፈረመ ደብዳቤ እኔ ያስተላለፍኩት ሕጋዊ እግድ ያለአግባብ ተሻረ፡፡
4.
ይህ በእንዲህ እንዳለ በ24/09/2007 ዓ/ም ከቅዱስ ፓትርያርኩ በተጻፈ ደብዳቤ በሥራ ገበታዬ ተገኝቼ ሥራዬን
እንድቀጥል ደብዳቤ ደረሰኝ፡፡ እኔም በ25/09/2007 ዓ/ም ለደብዳቤው፣ በቅን ልቡና ሥራዬን እየሠራሁ መኾኑን፤
የሠራተኞችን ደመወዝ፣ የሚታወቁና አይቀሬ የኾኑትን የሀገረ ስብከቱን ዕለታዊ የሥራ ማስኬጃ ወጪዎችንም እየፈረምኩ
ሥራዎች እየተከናወኑ እንደኾነ በመግለጽ ሥራዬን እንደምሠራ አሳወቅሁ፤ ነገር ግን ባልተለመደ አኳኋን ገንዘብን
በሚመለከት ሌላ ሊቀ ጳጰስ እንደተመደበ ሰማኹ፤ ይህ አሳዛኝ ክሥተት ነው፡፡
ስለዚህም በረዳት ሊቀ ጳጳስነት መመደቤን በመወሰን ሥልጣኑንና ሓላፊነቱን የሰጠኝ ይህ ምልዓተ ጉባኤ እንደ መኾኑ፣ ለቤተ ክርስቲያናችን በሚበጅ አካሔድ መፍትሔ ይስጠኝ ዘንድ እጠይቃለኹ፡፡
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ
ሐሙስ 29 ኦክቶበር 2015
ሰበር ዜና – አጥማቂ ነኝ ባዩ ግርማ ወንድሙ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ዋለ
የአዲስ አበባ ፖሊስ፣ አጥማቂ ነኝ ባዩን ግርማ ወንድሙን በቁጥጥር ሥር አዋለ።
የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ምንጮች፣ አጥማቂ ነኝ ባዩን ግርማ ዛሬ በፖሊስ በቁጥጥር ሥር ውሎ ምርመራ እየተደረገበት መኾኑን ተናግረዋል።
አጥማቂ ነኝ ባዩ ግርማ፣ በማጥመቅ እፈውሳለኹ በሚል በተለያዩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን ሕገ ወጥ ሀብት ሲያካብት እና በርካታ ምእመናንን ለተለያዩ ችግሮች ሲዳርግ ቆይቷል፡፡
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያነገጋረው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት፣ አጥማቂ ነኝ ባዩ ግርማ ዕውቅና እና ፈቃድ በይፋ የተነፈገው ሕገ ወጥ እንደኾነ አረጋግጧል።
የፋና ምንጮች፣ አጥማቂ ነኝ ባዩ ግርማ በፈውስ አገልግሎት ስም የማጭበርበር ወንጀል ሳይጠረጠር እንዳልቀረ ነው የተናገሩት።
ረቡዕ 28 ኦክቶበር 2015
ሰበር ዜና – ፈቃድ የሌላቸው የኢ.ቢ.ኤስ ፕሮግራሞች በቤተ ክርስቲያን ስም እንዳይጠቀሙ ተወሰነ፤ የ24 ሰዓት የቴሌቭዥን አገልግሎት ይጀመራል
- የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ፈቃድ እና ዕውቅና የሌላቸው የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ አቀንቃኞቹ፣ “ታዖሎጎስ” እና “ቃለ ዐዋዲ” በምልአተ ጉባኤው ውሳኔ በስም ተለይተው ተጠቅሰዋል
- በምልአተ ጉባኤው ውሳኔ መሠረት፣ በቋሚ ሲኖዶስ የተቋቋመው የብዙኃን መገናኛ ቦርድ ሥራውን ለመጀመር እየተንቀሳቀሰ ነው
- በፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ ላይ የቀረቡ ማስረጃዎች የበለጠ ተጠናክረው አጀንዳው በልዩ የምልአተ ጉባኤ ስብሰባ እንዲታይ ተወስኗል
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ፣ ከማእከል የተሰጠ ሕጋዊ ፈቃድ ሳይኖራቸው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስም፣ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ሰርቪስ(EBS) የቴሌቭዥን ጣቢያ፣ “ሃይማኖታዊ ትምህርት” የሚያስተላልፉ ፕሮግራሞች፣ የቤተ ክርስቲያንን ስም እንዳይጠቀሙ ወሰነ፡፡
ምልአተ ጉባኤው በዛሬ፣ ጥቅምት 17 ቀን 2008 ዓ.ም. ስድስተኛ ቀን የቀትር በፊት ውሎው ያሳለፈው ውሳኔ ተፈጻሚ እንዲኾን፤ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር እና የኢ.ቢ.ኤስ ቴሌቭዥን በደብዳቤ እንዲያውቁት ይደረግ ዘንድ ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡
በውሳኔው÷ የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ አቀንቃኞቹ፣ “ታዖሎጎስ” እና “ቃለ ዐዋዲ” በስም የተጠቀሱ ሲኾን በፕሮግራሞቹ አዘጋጅነት የሚታወቁት በተለይ የ“ታዖሎጎስ” ግንባር ቀደም ምንደኞች፣ ፕሮግራማቸው “ራሱን የቻለ የሚዲያ ተቋም” እንጂ ከቅዱስ ሲኖዶሱ ይኹን ከጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ጋር ተቋማዊ ግንኙነት እንደሌላቸው በይፋ በሰጡት መግለጫ ማረጋገጣቸው ይታወሳል፡፡
ምልአተ ጉባኤው ከዚሁ ጋር በማያያዝ፤ በሊቃውንት ጉባኤ ሳይመረመሩ እና በማእከል ሳይፈቀዱ በግለሰቦች እየተዘጋጁ የቤተ ክርስቲያንን ስም ይዘው ስለሚወጡ የስብከት፣ የመዝሙር እና የመጻሕፍት ኅትመቶች እንዲኹም የአዳራሽ ጉባኤያት እና ስብሰባዎች ከተወያየ በኋላ ቀደም ሲል ያሳለፋቸውን ውሳኔዎች በማጽናት ተመሳሳይ ትእዛዝ መስጠቱ ታውቋል፡፡
ቅዱስ ሲኖዶሱ፣ “ስብከተ ወንጌል እና ሚዲያን በተመለከተ” በተራ ቁጥር ሦስት በያዘው አጀንዳ፤ ቤተ ክርስቲያን ማእከላዊነቱን ጠብቆ የራስዋን ድምፅ ለዓለም የምታሰማበት እና ስብከተ ወንጌልን የምታስፋፋበት የ24 ሰዓት የቴሌቭዥን አገልግሎት እንዲጀመርም ወስኗል፡፡
ለቤተ ክርስቲያን የብዙኃን መገናኛ ስርጭት የሚያስፈልገውና በስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ አስተባባሪነት ተጠንቶ የቀረበው በጀት ባለፈው ዓመት ግንቦት በምልአተ ጉባኤው የጸደቀ ሲኾን በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የመክፈቻ ንግግር እንደተመለከተው፤ በዚኽ ዓመት በጀቱ በአፋጣኝ ሥራ ላይ እንዲውል የቀረበውን ጥያቄ በመቀበል የፋይናንስ ምንጮቹን ወስኖ ለነገ የሚያቀርብ ሦስት አባላት ያሉት የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት(ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ፣ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል እና ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ) ኮሚቴ በምልአተ ጉባኤ ተሠይሟል፡፡
ምልአተ ጉባኤው ባለፈው ዓመት ግንቦት ባጸደቀው የሚዲያዎች (የሬዲዮ እና የቴሌቭዥን አገልግሎት) ሥርጭት ደንብ መሠረት፤ በስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ ተልእኮ የበላይ ሓላፊ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ የሚመራ የብዙኃን መገናኛ የሥራ አመራር ቦርድ የተቋቋመ ሲኾን ተግባሩን ለመጀመር እየተንቀሳቀሰ እንዳለ ለ34ኛው የመንበረ ፓትርያርክ የሰበካ አስተዳደር አጠቃላይ ጉባኤ የቀረበው ሪፖርት ያስረዳል፡፡
በሪፖርቱ እንደተጠቀሰው፤ ቤተ ክርስቲያኒቱ ስብከተ ወንጌልን ከዐውደ ምሕረት ባሻገር በአጽናፈ ዓለም ለማስፋፋት እና ለማጠናከር ስለሚያስፈልጓት ሚዲያዎች፣ በመምሪያው አስተባባሪነት በብዙኃን መገናኛ ባለሞያዎች የተካሔደውን ጥናት መሠረት አድርጎ መተዳደርያ ደንብ፣ ኤዲቶሪያል ፖሊሲ እና የቴሌቪዥን ሥርጭት መመሪያ/ማኑዋል ተዘጋጅቷል፡፡
በተያያዘ ዜና፣ “የቤተ ክርስቲያኗን ወቅታዊ ኹኔታ በጥልቀት ማየት” በሚል ዐቢይ አጀንዳ ሥር በፊደል ተራ ቁጥር 4/መ፣ “የተሐድሶ እንቅስቃሴን በተመለከተ”፤ የተዘጋጀው ሰነድ በተጨማሪ ማስረጃዎች ተስፋፍቶ እና ተጠናክሮ ራሱን በቻለ ልዩ የምልአተ ጉባኤ ስብሰባ እንዲታይ ቅዱስ ሲኖዶሱ ወስኗል፡፡
የስብሰባው ምንጮች እንደተናገሩት፤ ከፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ግንባር ቀደም መሪዎች በሚሰጣቸው ተልእኮ እና ድጋፍ በቤተ ክርስቲያናችን የአስተዳደር እና የአገልግሎት መዋቅር ውስጥ በመስረግ የኑፋቄውን አስተሳሰብ እና ድርጊት የሚያራምዱ የ66 አካላት እና ግለሰቦች የሰነድ፣ የምስል እና የድምፅ ማስረጃዎች ከኃምሳ ገጾች ማብራሪያ ጋር ተደግፎ ተዘጋጅቷል፡፡
ከቤተ ክርስቲያናችን ዐውደ ምሕረት እና የአስተዳደር መዋቅር ባሻገር፣ የኑፋቄው ግንባር ቀደም መሪዎች እና ምንደኞቻቸው በከፍተኛ ትምህርት ተቋሞቻችን(መንፈሳዊ ኮሌጆች እና የካህናት ማሠልጠኛዎች) ውስጥ በተለያየ ሽፋን የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ትኩረት እንዲደረግበት ምልአተ ጉባኤው ኮሚቴውን አሳስቧል፡፡
በመካከለኛው ምሥራቅ አህጉረ ስብከት፣ ብፁዕ ሊቀ ጳጳሱ ሳያውቁት ከሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን ውጭ በተቋቋመው የኑፋቄው መናኸርያ “ዱባይ ሚካኤል” እና “ቤርያ ቲኦሎጂካል ኢንስቲትዩት” በሚል መሪዎቹ የመሠረቱት ሕገ ወጥ ተቋም በከፍተኛ ደረጃ ያነጋገረ ሲኾን በምልአተ ጉባኤው ጥናት ተካቶ እንዲቀርብ መወሰኑ ተጠቁሟል፡፡
በተመሳሳይ ኹኔታ ጉባኤውን ያነጋገረው፣ በመንበረ ፓትርያርኩ የውጭ ጉዳይ መምሪያ በሓላፊነት የተቀመጡት መልአከ ሰላም አባ ቃለ ጽድቅ የተባሉ ግለሰብ፣ ከፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቁ አንጻር ያላቸው ሃይማኖታዊ አቋም እና ሥነ ምግባራዊ ኹኔታ ነበር፡፡ የግለሰቡ አመጣጥ እና አመዳደብም ከፓትርያርኩ ልዩ ጸሐፊ ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ ጋር ባላቸው የጥቅም ግንኙነት እንደኾነ መጠቆሙ ደግሞ ችግሩ ከግለሰቡም በላይ ልዩ ጽ/ቤቱ እንደ መዋቅር ያለበትን አስከፊ ደረጃና አሳሳቢነቱን ለምልአተ ጉባኤው አለብቧል፡፡
ከዚኽ ውስብስብነቱና ከሚያስፈልገው ጠንካራ ቅንጅት አኳያ፤ አጀንዳው ራሱን በቻለ አስቸኳይ እና ልዩ የምልአተ ጉባኤ ስብሰባ እንዲታይ ቅዱስ ሲኖዶሱ ሲወስን ጊዜው በመጪው ወርኃ ጥር ላይ ሊኾን እንደሚችል ከወዲኹ የተጠቆመ ቢኾንም በኮሚቴው ውጤታማ እንቅስቃሴ ላይ እንደሚመሠረት ነው፣ በብዙኃን የምልአተ ጉባኤው ዘንድ መግባባት የተደረሰበት፡፡
በሕገ ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ የስብሰባ ሥነ ሥርዐት መሠረት፤ አስቸኳይ እና ድንገተኛ ጉዳይ ሲያጋጥም ቅዱስ ፓትርያርኩ ወይም ቋሚ ሲኖዶሱ ወይም የቅዱስ ሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ በሚያደርጉት ጥሪ የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ሊካሔድ ይችላል፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስም በማናቸውም ስብሰባ ላይ ውሳኔዎችን ሲያሳልፍ፤ ሃይማኖትንና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን የሚመለከት ከኾነ በሙሉ ድምፅ ያልፋል፤ በሃይማኖት እና በቀኖና ጉዳይም ድምፀ ተዓቅቦ ማድረግም አይቻልም፡፡
by ሐራ ዘተዋሕዶ
ደንበኛ ይሁኑ ለ፡
ልጥፎች (Atom)
በአውሮጳ የካህናት አንድነት ማኅበር ሊቋቋም መሆኑ ታወቀ በ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከመላዋ አውሮጳ የተውጣጡ ካህናት፡” የ...
-
June 1, 2015 ከሐራ ዘተዋሕዶ በሐዋርያዊት፣ ጥንታዊት እና ብሔራዊት ቤተ ክርስቲያናችን ህልውና እና ዕድገት ፊት ከተጋረጡትና አፋጣኝ እልባት ከ...
-
‹‹…ወንድማችንን እናውቃቸዋለን፤ በእውነቱ ለፌ ወለፌ የማይሉ ደረቅ ሊቅ ናቸው፤ በሃይማኖቱ ዘርፍ ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን፣ ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን አንዲቱም ነጥብ እንዳትዛባ...