ሰኞ 28 ኦክቶበር 2013

መጽሐፈ ቅዳሴ” ወደ ኦሮምኛ ተተረጎመ

www.youtube.com/watch?v=UYHqDqUEqoE   Cached
Ethiopian Orthodox Tewahedo Church Kidase 1 of 9. Ethiopian Orthodox Tewahedo Church Kidase 1 of 9. Sign in . Upload . Search . Guide Loading...

በመልካሙ ተክሌ
(አዲስ አድማስ ጥቅምት 16 2006 ዓ.ም)፡- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን “መጽሐፈ ቅዳሴ” ወደ ኦሮምኛ ቋንቋ ተተረጎመ፡፡ ለብዙ ዘመናት “መጽሐፈ ቅዳሴ”ን በግእዝ እና በአማርኛ ስትጠቀምበት የቆየችው ቤተክርስትያኗ፤መፅሃፉን በኦሮምኛ ማስተርጎም የጀመረችው በ1999 ዓ.ም እንደሆነ ታውቋል፡፡ የመጽሐፉ መተርጎም በኦሮሚያ ክልል ላሉ አብያተ ክርስትያናት በኦሮምኛ ለመቀደስ ያስችላቸዋል ተብሏል፡፡ የቤተክርስትያኒቱ ቅዱስ ሲኖዶስ እያካሄደ ባለው የጥቅምት ምልዐተ ጉባዔው ትኩረት ከሰጣቸው ዋና አጀንዳዎቹ አንዱ ስብከተ ወንጌልን ማዳረስ እንደሆነ የገለፁት ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፤ የመጽሐፉ  ሕትመት እንዲቀላጠፍ ትዕዛዝ እንዳስተላለፉም  ለማወቅ ተችሏል፡፡ “መጫፈ ቂዳሴ” በሚል ርዕስ የተተረጎመው የኦሮምኛ መጽሐፉ፤በቅርቡ ዝግጅቱን የተቀላቀሉትን ብፁዕ አቡነ ዮሴፍን ጨምሮ፣ በርካታ ጳጳሳት ተሳትፈውበታል፡፡ መጽሐፉ በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት እየታተመ ሲሆን በዚህ ሳምንት ከተጠናቀቀ በቅዱስ ሲኖዶስ ጉባዔ መዝጊያ ላይ ሊመረቅ እንደሚችል ታውቋል፡፡

ረቡዕ 23 ኦክቶበር 2013

የሃይማኖት እንከን የሌለባትና ተቆርቋሪ ምእመናን ያሏት ቤተ ክርስቲያናችን በአመራርና በአያያዝ ምክንያት የምትወቀስበትና ልጆቿን የምታጣበት ታሪክ ሊገታ ይገባል – ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ

His Holiness meglecha 11
ፎቶ- ማኅበረ ቅዱሳን
ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በመጀመሪያው ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባው ስለሚያተኩርባቸው ጉዳዮች ዛሬ፣ ጥቅምት ፲፪ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ጥዋት በጽርሐ መንበረ ፓትርያርኩ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
በቅዱስነታቸው መግለጫ መሠረት ምልአተ ጉባኤው÷ ስብከተ ወንጌልን በማስፋፋት ምእመናንን ስለ መጠበቅና ማብዛት፣ የቤተ ክርስቲያንን የትምህርት ተቋሞች በጥራትና አደረጃጀት በመለወጥ ከመማርና መሠልጠን አልፎ መከራን ለመቀበል የተዘጋጁ ላእካነ ወንጌልን አብቅቶ ስለማውጣት፣ ፍጹም የዕድገት ለውጥ ለማምጣት ስለሚያስችለው የፋይናንስና የመልካም አስተዳደር ጅምር ጥናት ሂደት፣ በቅዱስ ሲኖዶሱ የውሳኔ አሰጣጥ የቤተ ክህነት ልዩ ልዩ ክፍሎች ሓላፊዎች፣ ካህናት፣ ሊቃውንት፣ ወጣቶችና ምእመናን ውክልናና ተሳትፎ ስለሚረጋገጥበትና የቅዱስ ሲኖዶሱ ውሳኔ ሰፊ ድጋፍና ተቀባይነት ስለሚያገኝበት አሠራር ይመክራል፤ ውሳኔም ያሳልፋል፡፡
‹‹የአክራሪነት፣ አሸባሪነትና ጽንፈኝነት›› ተግባራትን በማውገዝ የክርስቶስ መልእክት የኾነውን ሰላምና እኩልነት፣ መከባበርና መቻቻል፣ አብሮ መልማትና ማደግ ለሕዝቡ በየቀኑ ማስተማርና መስበክ እንደሚገባ የገለጹት ፓትርያርኩ፣ ‹‹የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ችግሮችን በውይይትና በውይይት ብቻ የመፍታት ባህል መደገፍና ማጎልበት አለብን፤›› ሲሉም መክረዋል፡፡
አጀንዳዎቹ÷ በፍትሕ መንፈሳዊ በተደነገገው መሠረት የተሰበሰበው ምልአተ ጉባኤው መንፈስ ቅዱስ በሚገልጽለት መንፈሳዊ ጥበብ እየተመራ መፍትሔ ማግኘት ያለባቸው ጉዳዮች መፍትሔ እንዲያገኙ፣ በጥልቀት፣ በማስተዋልና የሓላፊነት መንፈስ በተላበሰ ወኔ በመወያየት ሊወስንባቸውና ለተግባራዊነታቸው ሊረባረብባቸው እንደሚገባ ምልአተ ጉባኤውን በርእሰ መንበርነት የሚመሩት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በመግለጫቸው አሳስበዋል፡፡
በመጨረሻም ፓትርያርኩ፣ መንፈስ ቅዱሳዊና ሐዋርያዊ ዐቢይ ጉባኤው በስብሰባው መጨረሻ የሚደርስበት ውሳኔና የሚያወጣው መመሪያ በውጤቱ÷ ቤተ ክርስቲያንን የሚያስፋፋ፣ ማኅበረ ካህናቱንና ማኅበረ ምእመናኑን የሚያስደስት፣ በሁሉም የቤተ ክርስቲያናችን ተከታዮች ዘንድ በናፍቆት የሚጠበቀውን የለውጥና የዕድገት ጎዳና የሚከፍት እንዲኾን በመግለጽ መግለጫቸውን ደምድመዋል፡፡
የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የምልአተ ጉባኤ ስብሰባመክፈቻጋዜጣዊ መግለጫ ዐበይት የትኩረት ነጥቦች
በድንበር የለሽ ስብከተ ወንጌል በርከት ያሉ በጎችን የማርባትና የመጠበቅ ሥራ
  • ከትንሹ የሥልጣነ ክህነት ሹም ጀምሮ እስከ ትልቁ የቤተ ክርስቲያን ባለሥልጣን ድረስ ለስብከተ ወንጌል መስፋፋት ተልእኮ በንቃት፣ በሙሉ ዕውቀት፣ በተነሣሽነት፣ በፍጹም ፈቃደኛነት እንዲነሣሣና እንዲሰለፍ የሚጠበቀውን ያህል አልተሠራም፡፡
  • ቤተ ክርስቲያን በጥምቀት ወልዳ፣ በሥጋ ወደሙ አሳድጋ፣ ወልደ ማርያም፣ ገብረ ሚካኤል ብላ የሠየመቻቸው ልጆቿ ከጉያዋ እየተነጠቁ ወደ ሌላ ካምፕ ሲወሰዱ እርስዋ የወላድ መሐን የኾነችበት፣ ያልወለዱና ያላሳደጉ ባለብዙ ቤተሰብ የኾኑበት ክሥተት እያጋጠመ ነው፡፡
  • የቅዱሳን ሐዋርያት ሥልጣን ወራሾች እንደመኾናችን ቁጥር አንድ ሥራችን በድንበር ሳይገደቡ ስብከተ ወንጌልን ማስፋፋት ነው፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ በሥሩ ያሉትን በጎች መጠበቅ ብቻ ሳይኾን ድንበር የለሽ ትምህርትና ስብከት በማካሄድ ከዛሬ ጀምሮ በየዓመቱ በርከት ያሉ በጎችን የማርባትና የመጠበቅ ሥራ ሊያሠራው የሚችል አሠራር መቀየስ አለበት፡፡

የትምህርት ተቋሞቻችንን በብዛትም በጥራትም በአደረጃጀትም በመለወጥ ትንሣኤዎቻቸውን ማብሠር፤
  • የምንሾማቸው ዲያቆናት፣ ቀሳውስትም ኾኑ ኤጲስ ቆጶሳት በተለምዶ የተሾሙ ሳይኾኑ ጌታችን እንዳደረገው የተማሩ፣ የሠለጠኑ፣ ነገሩ የገባቸውና መከራውን ለመቀበል የተዘጋጁ ሊኾኑ ይገባል፡፡
  • የአብነት ት/ቤቶቻችን፣ የካህናት ማሠልጠኛዎቻችንና የከፍተኛ ትምህርት ተቋሞቻችን በብዛትም በጥራትም በአደረጃጀትም ተማሪውን በትክክል ለመለወጥና ለመቅረጽ በሚያስችል አዲስ አሠራር ማስተካከልና ማብቃት አለብን፡፡
  • ቤተ ክርስቲያናችን የሃይማኖት እንከን ሳይኖራት፣ ሞያ ሳያንሳት፣ ተቆርቋሪ ምእመናን እያሏት በአያያዝና በአመራር ምክንያት የምትወቀስበትና ልጆቿን የምታጣበት ታሪክ መገታት አለበት፡፡ ይህን በወሳኝ መልኩ ለማስተካከል የትምህርት ቤቶቻችንን ትንሣኤ የሚያበሥር፣ ዕድገታቸውንና ጥራታቸውን የሚያፋጥን ጠንካራ መሠረት ዛሬ ማስቀመጥ ይኖርበታል፡፡

ስለ ዘመናዊ የፋይናንስ አሠራርና መልካም አስተዳደር የተጀመረው ጥናት ሂደት
  • ምእመናን የሚፈለገውን ዐሥራት፣ በኵራትና ቀዳምያት በሕጉ መሠረት እየሰጡ አይደለም፤ የሚሰጡትም ስጦታ በየመንገዱ እየተንጠባጠበ ወፎች የሚለቃቅሙት ይበዛዋል፡፡ የሚፈለገውን ያህል ተደራጅተን፣ መስለን ሳይኾን ኾነን፣ በሁሉም ነገር ተዘጋጅተን ማስተማር፣ ዘመኑ በሚፈቅደው የፋይናንስ ቁጥጥርና አያያዝ መጠቀም አለብን፡፡
  • ከወገንተኝነትና አድሏዊነት በአግባቡ ያልተላቀቀው አስተዳደራችን የቤተ ክርስቲያናችንን ተሰሚነት ክፉኛ እየጎዳው ነው፡፡ በመልካ አስተዳደር ዙሪያ ጉባኤው የማፍረስ ሳይኾን የመገንባት ግብ ያለው ራእይ አንግቦ ሥር ነቀል የኾነ ፍጹም የዕድገት ለውጥ ለማምጣት የሚያስችለውን አሠራር መቀየስ ይገባዋል፡፡

በቅዱስ ሲኖዶስ የውሳኔ አሰጣጥ የካህናትና ምእመናን ተሳትፎ ስለማረጋገጥ
  • ቅ/ሲኖዶስ በጉዳዮች ካህናትንና ምእመናንን እያሳተፈና በሐዋርያዊ ሥልጣኑ እያጸደቀ የውሳኔውን ተቀባይነትና ድጋፍ የሚያሰፋበትንና የሚያረጋግጥበትን አሠራር ይተክላል፡፡
  • የቅ/ሲኖዶስ አባላት ችግሮችን በውይይት ብቻ የመፍታት ባህል ለማጎልበት መሥራት አለባቸው

ሐሙስ 17 ኦክቶበር 2013

መንበረ ፓትርያርክ

የመንበረ ፓትርያርክ 32ኛው ጉባኤ የረቡዕ ዕለት ከሰዓት ውሎ ካለፉት የተለየ ነበር፡፡ ዋና አጀንዳው ‹መቻቻልን› የተመለከተ ሲሆን አቅራቢዎቹም ከፌዴራል ጉዳዮች የተወከሉ አካላት መሆናቸውን በዕለቱ የመርሐ ግብር ዝርዝር ላይ ተገልጧል፡፡ ከሰኞ ጀምሮ ይቀርብ በነበረው የአህጉረ ስብከት ሪፖርቶች ላይ የመብት ጥሰትና ሥልጣንን ለግል ሃይማኖት ማስፋፊያ የመጠቀም አዝማሚያዎች መኖራቸውን፣ በሕገ መንግሥቱ የተረጋገጠው እምነትን የመያዝ፣ የማስፋፋትና የአምልኮ ቦታ የማግኘት መብት እየተጣሰ መሆኑን የሚገልጡ ዘገባዎች ይሰሙ ነበር፡፡

በትናንትናው የከሰዓት ውሎ ስለ መቻቻል ገለጣ ከተሰጠ በኋላ ብጹዐን ሊቃነ ጳጳሳትና የጉባኤው ተሰብሳቢዎች የየአካባቢያቸውን ችግሮች በዝርዝር ነበር ያነሷቸው፡፡ ‹‹መቻቻል እስከ ምን ድረስ ነው›› ብለው ነበር ብጹዕ አቡነ ቄርሎስ የጠየቁት፡፡ ‹‹አሁን በምዕራብ ወለጋ ያለው ሁኔታ መንግሥት በአገሩ ያለ ይመስላል ወይ? ሰው እግሩን እሳት እየበላው ቻል ይባላል እንዴእንድንቻቻል አድርጉን፣ እንችላለን›› ነበር ያሉት፡፡
የምዕራብ ወለጋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ሄኖክ ‹በነጆ ወረዳ በሕጋዊ መንገድ ተሠርቶ የነበረው ቤተ ክርስቲያን በአካባቢው ባለ ሥልጣናት ተጽዕኖ እንዲፈርስ መደረጉን፣ ለምን ታፈርሳላችሁ ብለው ድርጊቱን የተቃወሙ ስድሳ ምእመናን መታሠራቸውን›› በኀዘን ነበር የገለጡት፡፡ አያይዘውም ‹‹በባኮ ወረዳ የተመደቡ አንድ ካህን እያረሱ እያሉ የአካባቢው ባለ ሥልጣናት መጡ፤ ካህኑን በሰደፍ እየደበደቡ ‹ከዚህ ሀገር ልቀቁ፣ ይህ የነፍጠኛ መኖሪያ አይደለም› እያሉ አሰቃዩዋቸው፡፡ ካህኑን ሲደበድቧቸው አንበርክከው፣ ለ15 ደቂቃ አተኩረው ፀሐይዋን እንዲያዩ እያስገደዱ ነበር፡፡ ድብደባውን ሰምተው የወጡት ባለቤታቸው በድንጋጤ ታመው ከጥቂት ቀናት በኋላ ሕይወታቸው አለፈ››
‹‹በሰንበትና በቅዱስ ሚካኤል ቀን ምእመናን ሊያስቀድሱ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲሄዱ ‹ለቅዳሴ ካህናቱ ይበቃሉ፤ እናንተ ውጡ›› እየተባሉ እንዳያስቀድሱ ይደረጋሉ፡፡ ከእኛ ቤተ ክርስቲያን 70 ሜትር ርቀት ላይ ሆን ተብሎ እርስ በርስ ለማጋጨት ለፕሮቴስታንቶች የጸሎት ቦታ ተሰጠ፡፡ ለምን ታጨቃጭቁናላችሁ፤ ይህ ቦታ ለእነርሱ አይሆንም ብሎ በመከራከሩ አንድ ዲያቆን ተደብድቦ ሞተ፡፡ የሕክምና ውጤቱም ሆን ተብሎ በወባ በሽታ ሞተ ተብሎ ተሠራ፡፡ ለሁለት ዓመት ያህል ተከራክረን አሁን ቦታው ለእኛ ተወሰነ፡፡
ጊምቢና መንዲ ላይ የምእመናን ልጆች ትምህርት ቤት ውስጥ በፖሊስ ማተባችሁን በጥሱ እየተባሉ ነው፡፡ ለምን ስንላቸው ከላይ የወረደ መመሪያ አለ ይሉናል፡፡››
ቀጥለው የሀገረ ስብከታቸውን ችግር ያቀረቡት የጋሞጎፋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ኤልያስ ነበሩ፡፡ ‹‹በጋሞ ጎፋ መቱ ወረዳ፣ ዋጁ ኡቆ ላይ የመስቀል ማክበሪያ ቦታችን ለሱቅ መሥሪያ ቦታ ተሰጠ፡፡ አቤት ብንል የሚሰማን በማጣታችን ዘንድሮ በኢትዮጵያ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ መስቀል ሳናከብር ዋልን፡፡ ሀገሪቱ በችግር ላይ በነበረች ጊዜ እንኳን መስቀል ሳይከበር ቀርቶ አያውቅም ነበር፡፡ የቤተ ክርስቲያን የይዞታ ቦታ ለመንግሥት እየተሰጠ ነው፡፡ በአቡነ ጳውሎስ ዘመን በቅዱስነታቸው በኩል ለክልሉ ደብዳቤ ጻፍን፡፡ ክልሉ ወሰነልን፡፡ ነገር ግን እስካሁን አልተረከብንም፡፡››
ቀጥለው ሃሳባቸውን የሰጡት የባሰ ካልመጣ በቀር ድምጻቸው ማይሰማው ብጹዕ አቡነ ያሬድ የሶማሌ ክልል ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ነበሩ፡፡ ‹‹በሶማሌ ክልል አምስት አብያተ ክርስቲያናት ብቻ ናቸው ያሉን፡፡ ምእመናኑ ብዙ ናቸው፡፡ ሲወልዱ የሚያስጠምቁበት፣ ሲያርፉ የሚቀበሩበት ቤተ ክርስቲያን እንትከል ብንል የሚሰማን አጥተናል፡፡ ቤተ ክርስቲያንን የሚረዱ ምእመናን በግላቸው ጥቃት እየደረሰባቸው ነው፡፡ ለዚህ መልሳችሁ ምንድን ነው›› ብለዋል፡፡
በገለጻው ላይ ኢትዮጵያ ክርስትናን የተቀበለችው በ4ኛው መክዘ ነው የሚለውን የተቃወሙት ብጹዕ አቡነ ማርቆስ ‹‹ታሪክ ክፉም ሆነ በጎ እንደ ታሪክነቱ መተረክ አለበት፤ አቅራቢው ወንድማችን በ4ኛው መክዘ ክርስትና ገባ ያልከው ተሳስተሃል፡፡ ለመሆኑ ይህንን ለማለት ‹ላይሰንስ አለህ?› አባቱን የሚኮንን ልጅ ምን ያደርጋል? ነገሥታቱን ወቀሳችሁ፣ ቤተ ክርስቲያንን ነቀፋችሁ፤ ለመሆኑ ከማን ነው ይህቺን ሀገር የተረከባችሁት? ክርስትና ወደ ኢትዮጵያ የገባው ጌታ ባረገ ዓመት ባልሞላው ጊዜ ውስጥ ነው፡፡ በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 8 ላይ አለ፡፡ ይህንን ዛሬ ‹ግራጁዌት አድርገው›፤ ልዑካኑ ስትመጡ ስለምትናገሩት ነገር ዕወቁ፤››
የደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ እንድርያስም ‹‹በቤተ መንግሥት የወርቅ ዕቃ ብቻ አይኖርም፣ የእንጨትም፣ የድንጋይም ዕቃ አለ፡፡ በቤተ ክርስቲያንም ሁሉም ጥሩ አይሆንም፣ መጥፎም ይኖራል፡፡ ነገር ግን እስከ መጨረሻው የጸና ይድናል ብሏል፡፡ በእኔ ሀገረ ስብከት ስድስት አብያተ ክርስቲያናት ተቃጥለዋል፡፡ ሦስቱ በአንድ አካባቢ፣ ሦስቱ በሌላ ቦታ፡፡ ይህንን ለክልሉ መንግሥት ብናሳውቅ አልረዱንም፡፡ የተበደለ ሰው ይጮኻል፤ ሲጮህ ደግሞ ፖለቲካ ነው ይባላል፡፡ ድሮ ያስቸገረን የንዋያተ ቅድሳት ዘረፋ ነበር፡፡ አሁን ደግሞ ቤተ ክርስቲያን ወደ ማቃጠል ተዛውሯል፡፡ አንዱ ባለ ሥልጣን እንዲያውም ችግሩን ሳቀርብለት ተቆጣኝ፤ ብዙ ብናገር ነፋስ ስለሚወስደው እዚህ ላይ ይብቃ››
ከብጹዐን ሊቃነ ጳጳሳት ቀጥሎ የተናገሩት የወላይታ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ‹‹በበዴሳ ወረዳ ያለ አንድ የሌላ እመነት ተከታይ የሆነ ዳኛ ከኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ጋር ቄራ አንካፈልም፤ በመኪና አብረን አንሄድም› ብሎ ዐወጀ፡፡ በጋራ በመቻቻል የኖርንበትን ዕድር ሁሉ ለዩ ብሏል፡፡ ታድያ እንዴት መቻቻል ሊመጣ ይችላል፡፡››
ከጉባኤው የቀረበውን ቅሬታና ሃሳብ ያዳመጡት የፌዴራል ጉዳዮች የሥራ ኃላፊዎች የቀረቡት ቅሬታዎች በሰነድ ተደግፈው ቢደርሷቸው እነርሱም በመፍትሔው ላይ መሥራት እንደሚችሉ፤ ኢትዮጵያ የሃይማኖቶች ጉባኤም ጉዳዩ በየደረጃው ቢቀርብለት መፍታት እንደሚችል፡፡ ቅሬታዎችን እንደዚህ ባለ መድረክ ከሚሆን በየጊዜው እየተገናኙ መፍታት ቢቻል›. የሚሉ ሃሳቦችን ሠንዝረዋል፡፡
የዘንድሮው የሰበካ አጠቃላይ መንፈሳዊ ጉባኤ በአደረጃጀቱ ውበት፣ በተሳታፊዎቹ ብዛት፣ በአህጉረ ስብከቶች ቁጥር(50 ደርሰዋል)፣ በስብሰባው ቁም ነገረኛነት ካለፉት የተለየ ነበር፡፡ እነ ሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጬ የሰበካ ጉባኤ ስብሰባ ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን በብርቱ እንደ ደከሙበት ያሳያል፡፡ በየዘገባዎቹ የተሰሙትን የመብት ጥሰቶች፣ ሥልጣንን ተገን በማድረግ የሚፈጸሙ ጫናዎች፣ የአምልኮ ቦታ እጥረቶች፣ በካህናቱ ላይ የሚፈጸሙትን ግፎችና፣ የቤተ ክርስቲያንን ይዞታ የመንጠቅ ርምጃዎች ግን ሊገቱ ይገባቸዋል፡፡ ከአንዳንድ ክልሎች በቀር በብዙዎቹ የዞንና የክልል ባለ ሥልጣናት ችግሩን ተረድተው ለመፍታት እንደሚጥሩ ተገልጧል፡፡ በወረዳ ደረጃ የሚገኙት ግን ሥልጣንን ተገን በማድረግ የግል እምነታቸውን እያስፋፉ መሆኑን ያሳያል፡፡ በደቡብ ጎንደርና በምሥራቅ ጎጃም የተፈጸሙት የአብያተ ክርስቲያናትን የማቃጠል ርምጃዎች በጊዜው ተጣርተው መፍትሔ ካልተሰጣቸው ፍጻሜያቸው አያምርም፡፡
በየአካባቢው በሚገኙ ባለ ሥልጣናት የሚፈጸሙ ትንኮሳዎችም መቆም አለባቸው፡፡ ብጹዐን ሊቃነ ጳጳሳቱ ‹አታስቆጡን› እያሉ ደጋግመው የተናገሩት ነገር የዋዛ አይደለም፡፡ ኃላፊነት የማይሰማቸው አካላት የሚፈጽሙት ገደብ አልባ ትንኮሳና ጫና ወዴት እያመራ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡
ቤተ ክርስቲያኒቱም አደረጃጀቷንና አሠራርዋን ይበልጥ የምትፈትሽበት፣ አሁን ለገጠማት ተግዳሮት ብቁ የሚሆን አሠራና አወቃቀር የምትይዝበት፣ ችግሮችን በስብሰባ ብቻ ሳይሆን በአካባቢያዊ ውይይት፣ በሕግ መሥመርና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተቀራርቦ በመሥራት የምትፈታበት መንገድ ሊኖር ይገባል፡፡  
ያለበለዚያ መጋቤ ምሥጢር ወልደ ሩፋኤል የተረተው ተረት መድረሱ የማይቀር ነው፡፡
በጣልያን ጊዜ ነው አሉ፡፡ ጎንደር ላይ ጣልያን በድማሚት አንዱን ተራራ ያናውጠዋል፡፡ ተራራው ‹እድም› እያለ ይፈርሳል፡፡ አንዲት የከብት እረኛ ልጅ ፈርታ ወደ እናቷ ሄደችና ‹እማዬ ኧረ ጣልያን ተራራውን እያፈረሰው ነው›› አለቻት፡፡ እናቷም ‹‹እነ ደጃዝማች እገሌ፣ እነ ፊታውራሪ እገሌ፣ እነ ራስ እገሌ እጅ አንሰጥም ብለው እየተጋደሉ ዐለፉ፡፡ ተራራውንስ ተይው ያፍርሰው፤ እርሱም መቀመጡን አብዝቶት ነበረ፡፡›› አለቻት አሉ፡፡ 

ማክሰኞ 15 ኦክቶበር 2013









 ሰበረ‹ዜና  ረጅም ዕድሜ ያስቆጠሩ ተላላቅ አሥር አቢያተ ክርስቲያናት ተቃጠሉ
32ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አጠቃላይ ዓለማቀፍ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባዔ ከተጀመረ ዛሬ ሁለተኛ ቀን ሆኖታል ፡፡ በዚህ ተላቅ ጉባዔ ላይ እጅግ አሳዛኝ ሪፖርቶች ተሰምተዋል ጥቂቶቹ
1.     የደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት ሪፖርት በጉባዔው ላይ እንዳስደመጠው  አምስት ታላላቅ አድባራት  ማንነታቸው ባልታወቀ አጽራረ ቤተክርስቲያን  መቃጠላቸውን  በሪፖርቱ አስደምጦአል አድባራቱ  ታሪካዊና ውድ የሆኑ ቅርሶች የሚገኙበት በመሆናቸው ቤተከርስቲያኒቱን አሳዝኖአል በተያያዘ የኮነኔል ማእረግ የተለጠፈላቸው ሁለት ግለሰቦች ቅርሶችን የመዝረፍ ሙከራ እያደረጉ እያሉ በሀገረ ስበከቱና በህዝበ ክርስቲያኑ ርብርብ የዳነ መሆኑንም ጨምሮ የገለጸው ሪፖርቱ ሀገረ ስብከቱ ረጅም ዕድሜ ያስቆጠሩ ቅርሶች ሚገኙበት በመሆኑ የቅረስ ዘረፋም ከመጠን በላይ መሆኑንም ቸምሮ ገልጦአል እንዲሁም የ15 አቢያተ ክርስቲናት ይዞታ ጉዳይም ከብዙ ክረክር በኋላ መፍትሔ እንዳገኙ ተገልጦአል ፡፡
2.    ምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት  በዚህም ሀገረ ስብከትም አሥር አቢያተ ክርስቲያናት መቃጠላቸውን የሀገረ ስብከቱ ሪፖርት ገለጸ  በሪፖርቱ እንደተገለጸው አቢያተ ክርስቲያናቱ ታሪካዊና የብዙ ቅርስ ባለቤት ሆኑት ተመርጠው መቃጠላቸው ህዝበ ክርስቲያኑን አሳዝኖአል እነዚህ የሀገር ሀብት ቅርሶች ሲወድሙ ዝም ማለትና ወንጀለኞችን ለህግ አለማቅረብ  ጉባዔውን በጣም ያሳዘነ መሆኑን ሪፖርቱ ጨምሮ ገልጦአል የዞኑም አስተዳደር ጉዳዩን በአጽንኦት ተመልክቶ መፍትሔ ሊወስድ ይገባል ሲሉ የጉባኤው ታዳሚዎች አስተያየታቸውን ገልጠዋል ፡፡
3.    ምዕራብ ወለጋ ሀገረ ስብከት  ሕዝቡን በሚገባ ያስተዳድራሉ ይመራሉ ተብለው ሓላፊነት የተሰጣቸው  የዞኑ እና የወረዳው ባለሥልጣናት  የአቢያተ ክርስቲያናቱን ቦታ  በመቀማት፤ ካህናቱን በመደብደብ፤ በቅዳሴ ሰዓት ሕዝቡን ከቅዳሴ ላይ ሂዱ ወደ ስብሰባ በማለት በመረበሽ ፤ በዚሁ ምክንያት አንድ ሴትና አንድ ወንድ  በድብደባ ለሞት መዳረጋቸውን የሀገረ  ስብከቱ ሪፖርት ገልጦአል  ባለሥልጣናቱ በሣሪያ አፈሙዝ በማስፈራራት በይፋ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮችን  መደብደብና ማንገላታት የዘወትር ስራቸው በመሆኑ በዞኑ ለመኖር አለመቻላቸውን ሪፖርቱ ጨምሮ ገልጦአል  የጉባዔው ተሳታፊዎችም መንግስት እንዲህ ያሉትን የግል አጀንዳ ያላቸውን ባለሥልጣናት በመከታተል እርምጃ ሊወስድ ይገባል ብለዋል ይህ ካልሆነ በሕዝቡ መካከል ተከባብሮ የኖረውን ሕዝብ ለማጨት መሆኑ የአደባባ ምሥጢር ነው ብለዋል ተሳታፊዎቸሁ ፡፡ በየሀገረ ስብከቶቹ ሁሉ ተመሳሳይ ችግሮች እንዳሉ  ሀገረስብከቶቹ  በየሪፖርታቸው ገለጠዋል ፡፡
ይሁን እንጂ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረስብከት በሀገረ ስበከቱ በየደብሩ ላይ   የተፈጸመውን   ፍንዳታ፤ የአቢያተ ክርስቲያናት መዘጋትና ሌሎች ችግሮችን ጨርሶ አለማንሳቱ ከፍተኛ ጥርጣሬ አሳድሮአል ችግሮቹ በሕዝቡ ዘንድ የሚታወቅ ቢሆንም የሀገረ ስብከቱ ሪፖርት ችግሩን ለጉባዔው አለማቅረቡ የችግሩ ተበባሪ አስመስሎታል   የሀገረ ስብከቱ ሥራስኪያጁ  እንደሚያሳየው ከሆነ ከላይ የተጠቀሱት ችግሮች እተባባሱ መሄዳቸው የሚታወቅ ቢሆንም  የአድባራቱን በመናፍቃን መወረርና መቃጠል ችግሮቻውን ከመቅረፍ ይልቅ ማባበሱ ላይ ያቶከሩ ናቸው በማለት ተሳታፊዎች ገልጠዋል፡፡ አንባቢዎች የሀገረስብከቱ አጠቃላይ ችግሮች ስላልተነሱ በዝርዝር የምናቀርብ ይሆናል፡፡


  • Participants of the 32nd SGGA03


   
 
ሰበር ዜና ጅም ዕድሜ ያስቆጠሩ ተላላቅ አሥር አቢያተ ክርስቲያናት ተቃጠሉ

32ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አጠቃላይ ዓለማቀፍ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባዔ ከተጀመረ ዛሬ ሁለተኛ ቀን ሆኖታል ፡፡ በዚህ ተላቅ ጉባዔ ላይ እጅግ አሳዛኝ ሪፖርቶች ተሰምተዋል ጥቂቶቹ እነሆ!
1.     የደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት ሪፖርት በጉባዔው ላይ እንዳስደመጠው  አምስት ታላላቅ አድባራት  ማንነታቸው ባልታወቀ አጽራረ ቤተክርስቲያን  መቃጠላቸውን  በሪፖርቱ አስደምጦአል አድባራቱ  ታሪካዊና ውድ የሆኑ ቅርሶች የሚገኙበት በመሆናቸው ቤተከርስቲያኒቱን አሳዝኖአል በተያያዘ የኮነኔል ማእረግ የተለተፈላቸው ሁለት ግለሰቦች ቅርሶችን የመዝረፍ ሙከራ እያደረጉ እያሉ በሀገረ ስበከቱና በህዝበ ክርስቲያኑ ርብርብ የዳነ መሆኑንም ጨምሮ የገለጸው ሪፖርቱ ሀገረ ስብከቱ ረጅም ዕድሜ ያስቆርጠሩ ቅርሶች ሚገኙበት በመሆኑ የቅረስ ዘረፋም ከመጠን በላይ መሆኑንም ቸምሮ ገልጦአል እንዲሁም የ15 አቢያተ ክርስቲናት ይዞታ ጉዳይም ከብዙ ክረክር በኋላ መፍትሔ እንዳገኙ ተገልጦአል ፡፡
2.    ምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት  በዚህም ሀገረ ስብከትም አሥር አቢያተ ክርስቲያናት መቃጠላቸውን የሀገረ ስብከቱ ሪፖርት ገለጸ  በሪፖርቱ እንደተገለጸው አቢያተ ክርስቲያናቱ ታሪካዊና የብዙ ቅርስ ባለቤት ሆኑት ተመርጠው መቃጠላቸው ህዝበ ክርስቲያኑን አሳዝኖአል እነዚህ የሀገር ሀብት ቅርሶች ሲወድሙ ዝም ማለትና ወንጀለኞችን ለህግ አለማቅረብ  ጉባዔውን በጣም ያሳዘነ መሆኑን ሪፖርቱ ጨምሮ ገልጦአል የዞኑም አስተዳደር ጉዳዩን በአጽንኦት ተመልክቶ መፍትሔ ሊወስድ ይገባል ሲሉ የጉባኤው ታዳሚዎች አስተያየታቸውን ገልጠዋል ፡፡
3.    ምዕራብ ወለጋ ሀገረ ስብከት  ሕዝቡን በሚገባ ያስተዳድራሉ ይመራሉ ተብለው ሓላፊነት የተሰጣቸው  የዞኑ እነ የወረዳው ባለሥልጣናት  አቢያተ ክርስቲያናቱን ቦታ  በመቀማት፤ ካህናቱን በመደብደብ፤ በቅዳሴ ሰዓት ሕዝቡን ከቅዳሴ ላይ ሂዱ ወደ ስብሰባ በማለት በመረበሽ ፤ በዚሁ ምክንያት አንድ ሴትና አንድ ወንድ  በድብደባ ለሞት መዳረጋቸውን የሀገረ  ስብከቱ ሪፖርት ገልጦአል  ባለሥልጣናቱ በሣሪያ አፈሙዝ በማስፈራራት በይፋ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮችን  መደብደብና ማንገላታት የዘወትር ስራቸው በመሆኑ በዞኑ ለመኖር አለመቻላቸውን ሪፖርቱ ጨምሮ ገልጦአል  የጉባዔው ተሳታፊዎችም መንግስት እንዲህ ያሉትን የግል አጀንዳ ያላቸውን ባለሥልጣናት በመከታተል እርምጃ ሊወስድ ይገባል ብለዋል ይህ ካልሆነ በሕዝቡ መካከል ተከባብሮ የኖረውን ሕዝብ ለማጨት መሆኑ የአደባባ ምሥጢር ነው ብለዋል ተሳታፊዎቸሁ ፡፡ በየሀገረ ስብከቶቹ ሁሉ ተመሳሳይ ችግሮች እንዳሉ  ሀገረስብከቶቹ  በየሪፖርታቸው ገለጠዋል ፡፡
ይሁን እንጂ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረስብከት በሀገረ ስበከቱ በየደብሩ ላይ   የተፈጸመውን   ፍንዳታ፤ የአቢያተ ክርስቲያናት መዘጋትና ሌሎች ችግሮችን ጨርሶ አለማንሳቱ ከፍተኛ ጥርጣሬ አሳድሮአል ችግሮቹ በሕዝቡ ዘንድ የሚታወቅ ቢሆንም የሀገረ ስብከቱ ሪፖርት ችግሩን ለጉባዔው አለማቅረቡ የችግሩ ተበባሪ አስመስሎታል   የሀገረ ስብከቱ ሥራስኪያጁ  እንደሚያሳየው ከሆነ ከላይ የተጠቀሱት ችግሮች እተባባሱ መሄዳቸው የሚታወቅ ቢሆንም  የአድባራቱን በመናፍቃን መወረርና መቃጠል ችግሮቸሁን ከመቅረፍ ይልቅ ማባበሱ ላይ ያቶከሩ ናቸው በማለት ተሳታፊዎች ገልጠዋል፡፡ አንባቢዎች የሀገረስብከቱ አጠቃላይ ችግሮች ስላልተነሱ በዝርዝር የምናቀርብ ይሆናል፡፡

                                   በአውሮጳ   የካህናት አንድነት ማኅበር ሊቋቋም መሆኑ ታወቀ በ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከመላዋ አውሮጳ   የተውጣጡ ካህናት፡” የ...