በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ መሠረት የሚቀርቡ መንፈሳዊ ትምህርቶች ፤መረጃዎች እና የመሳሰሉት የሚስተናገዱበት ገጽ ነው
ሐሙስ 20 ፌብሩዋሪ 2014
ል ረገድ ከፍተኛ ተስፋ የተጣለባቸውና በቋሚ ሲኖዶሱ ላይ ርክክብ የተካሔደባቸው የመዋቅር የአደረጃጀት የአሠራር ጥናት ሰነዶች ብዛት ዐሥራ ሦስት ሲኾን ከአንድ ሺሕ ገጽ ያላነሰ ጠቅላላ ብዛት ያላቸው እንደኾኑ ከቋሚ ሲኖዶሱ ርክክብ አንድ ቀን አስቀድሞ በሀ/ስብከቱ ጽ/ቤት በተካሔደ መርሐ ግብር ላይ ተገልጧል፡፡ His Grace Abune Estifanos with the 12 documentsየጥናት ሰነዶቹም የአደረጃጀትና የመዋቅር ጥናትና መመሪያ፣ የአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ደረጃ መስፈርት ጥናትና መመሪያ፣ የአገልግሎት መደቦች የሥራ ዝርዝር ሰነድ፣ የተፈላጊ ችሎታ መመሪያና የሰው ኃይል ትመና ሰነድ፣ የደመወዝ ስኬል ጥናት ሰነድ፣ የአገልጋዮች ማስተዳደርያ፣ የፋይናንስ፣ የልማት ሥራዎች፣ የግዥ፣ ሽያጭና ንብረት አስተዳደር፣ የዕቅድ ዝግጅት፣ ሪፖርትና ግምገማ፣ የኦዲትና ኢንስፔክሽን ፖሊሲዎችና ዝርዝር የአፈጻጸም መመሪያዎች እንዲኹም የሥልጠና ማእከልና የአረጋውያንና የሕፃናት መርጃ ማእከል ፕሮጀክት ጥናት ሰነድ እንደኾኑ ተዝርዝሯል፡፡ የጥቅምት ቅ/ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ለጥናቱ በሰጠው ይኹንታና በሰጠው አቅጣጫ መሠረት የጥናት ሰነዱ ለርክክብ ከመቅረቡ አስቀድሞ÷ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የመምሪያና ድርጅት ሓላፊዎችን ጨምሮ የሀገረ ስብከቱ የዋና ክፍል ሓላፊዎች፣ የክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጆች፣ የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪዎች፣ የሀገረ ስብከቱ ማኅበረ ካህናት፣ ማኅበረ ምእመናንና የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች እንደተወያዩበት ተገልጦአል፡፡ በውይይት የተነሡት ሐሳቦች በአግባቡ ተመዝግበውና ተገምግመው በእያንዳንዱ የመዋቅርና የአሠራር መመሪያ ውስጥ እንዲካተቱ መደረጉን የባለሞያ ቡድኑ ሰብሳቢ አቶ ታደሰ አሰፋ ያስረዱ ሲኾን ለ14 ቀናት በጥናቱ ላይ በተካሔደው ውይይት 96 በመቶ ተቀባይነት እንዳገኘ ማረጋገጣቸውን ተናግረዋል፡፡ ‹‹ጥናቱን እንድናደርግ የተሰጠን ዕድል ታሪካዊ ነው፤›› ያሉት አቶ ታደሰ፣ ችግር ፈቺ እንደኾነ ለሚያምኑበት የጥናት ሰነድ ዝግጅት መሳካት አስተዋፅኦ አድርገዋል ያሏቸውን ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ የሀገረ ስብከቱን ሓላፊዎችና አገልጋዮች እንዲኹም የለውጥ እንቅስቃሴውን ያስጀመሩትንና ከጅምሩ እስከ ፍጻሜው በኹሉ ነገር አልተለዩም ያሏቸውን ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስን አመስግነዋል፤ የቤተ ክርስቲያኒቱ የበላይ አካል የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ እንደወሰነውም በካህናት፣ ምእመናንና የሰንበት ት/ቤቶች ወጣቶች አስተያየት ዳብሮ የቀረበው የጥናት ሰነዱ በቋሚ ሲኖዶሱ ጸድቆ ወደ ተግባር ይገባ ዘንድ አደራ ብለዋል፡፡ በተያያዘ ዜና፣ በትውፊታዊውና ጥንታዊው የቤተ ክርስቲያኒቱ የትምህርት ማእከላት በኾኑት አብያተ ጉባኤያት ወንበር ተክለው የሚያስተምሩ የአብነት መምህራን ዋነኛ የጤና ችግር ከዐይን እክል ጋር የተያያዘ መኾኑን ሰንደቅ የደረሰው መረጃ ጠቁሟል፡፡ An Accomplished Scholars of the Ethiopain Orthodox Tewahido Church Traditional Schools አባ ሰረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል የውስጥና የውጭ ተባባሪዎቻቸውን አሰልፈው በፓትርያርኩ ደብዳቤ ያሳገዱት የሦስተኛው ዙር ሀገር አቀፍ የአብነት መምህራን ጉባኤ ተሳታፊ የምስክር ሊቃውንት በማኅበረ ቅዱሳን የዋናው ማእከል ጽ/ቤት በራፍ ማኅበረ ቅዱሳን ለሦስተኛ ጊዜ ባዘጋጀውና በፓትርያርኩ ደብዳቤ እንደታገደ በተገለጸው የአብነት መምህራን ሀገር አቀፍ ጉባኤ ላይ ለመገኘት ከኹሉም አህጉረ ስብከት ተውጣጥተው ወደ አዲስ አበባ ከመጡት 202 የምስክር መምህራን መካከል ለ170ዎቹ ተሳታፊዎች የጤና ምርመራ መደረጉን መረጃው ያመለክታል፡፡ W.ro Alemtsehay Meseret, Deputy Board Chair of Kidusat Mekanat Limat ena Mahiberawi Agelgilot ወ/ሮ ዓለም ፀሐይ መሠረት የማኅበረ ቅዱሳን ቅዱሳት መካናት ልማትና ማኅበራዊ አገልግሎት ዋና ክፍል ምክትል የቦርድ ሰብሳቢ የንዋያተ ቅድሳት ምርት ከቤተ ክርስቲያናችን የገቢ ማስገኛ ዘዴዎች በአማራጭነት ሊካተት ይችላል፡፡ ንዋያተ ቅድሳት በቅድስት ቤተ ክርስቲያን በቅዳሴና በልዩ ልዩ መንፈሳዊ አገልግሎቶች የምትጠቀምባቸውን ግብአቶች ያጠቃልላል፡፡ እነዚህ ግብዓቶች ቤተ ክርስቲያን ካላት መንፈሳዊ አገልግሎት÷ ቅዳሴ፣ ክርስትና፣ ተክሊልና ፍትሐት ስፋት እንዲኹም የምእመናኑና የአብያተ ክርስቲያኑ ብዛት ከግምት ስናስገባው ከፍተኛ ምርትንና ሽያጭን ይጠይቃል፡፡ ምርቱና ሽያጩ ለቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች የገቢ ምንጭ ለመፍጠር ብቻ ሳይኾን የአመራረቱን ትውፊትና ሥርዐት ለመጠበቅ፣ ከከተማ ውጭ ያሉትን ገዳማትና አድባራት የንዋያተ ቅድሳት እጥረት ለመቀነስ በከፍተኛ ኹኔታ ያግዛል፡፡ ለዚኽ ገለጻ ተብሎ በተሰበሰበው መረጃ መሠረት፣ በአኹኑ ሰዓት ንዋያተ ቅድሳት በገበያ ላይ ለሽያጭ የሚቀርቡት 95% ከቤተ ክርስቲያን ጋራ ምንም ግንኙነት በሌላቸው ለትርፍ በተቋቋሙ ወይም በሚሠሩ የግል አቅራቢዎች ወይም አምራቾች ነው፡፡ ለምሳሌ ያህል፡- 95 በመቶ የጧፍ ምርት በአብዛኛው ከመርካቶ የግል አቅራቢዎች የሚቀርብ ነው፡፡ ምእመናን በአነስተኛ ግምት በዓመት ወደ 93 ሚልዮን ብር ለጧፍ ግዥ ያወጣሉ፡፡ ከ93 ሚልዮን ብር ሽያጭ 20 ሚልዮን ብር ትርፍ ይገኛል ተብሎ ሊሰላ ይችላል፡፡ ይህ ትውፊቱን ጠብቆ በቤተ ክርስቲያን ካህናት ተመርቶ ቢኾን ኖሮ የካህናቱም ገቢ በዚኹ መጠን ያድግ ነበር፡፡ የጧፍ ምርት፡- የሰው ኃይል፣ የፈትል ክር፣ ሰም ወይም ዋክስ በአካባቢ በሚሠራ ቴክኖሎጂ በመጠነኛ ዋጋ የሚዘጋጅ ነገር ግን ኹሌም ገበያ ያለው ምርት ነው፡፡ የተለየም ሞያ የማይጠይቅ ሥራ ነው፡፡ በመቶ ሺሕ የሚቆጠሩ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ካህናት፣ የካህናት ሚስቶች በቀላሉ ሥልጠና ቢሰጣቸው ኑሯቸውን ሊያሻሽሉ ይችላሉ፡፡ ጧፍ በቤተ ክርስቲያን ካለመመረቱ የተነሣ በአኹኑ ሰዓት አምራቾች የሚጠቀሙበት የሰም ዋጋ ውድ ከመኾኑ ጋራ ተያይዞ ትውፊቱን ለመጠበቅ የሚያስችል ምክንያት ስለሌላቸው በአብዛኛው ሻማና ሞራ እንዲኹም ልዩ ልዩ ኬሚካሎች በመጠቀም ጣፉን በማምረት ላይ ናቸው፡፡ ይህም ከጧፉ ጢስ ጋራ በተያያዘ ካህናትን ለጤና ችግር እየዳረጋቸው ይገኛል፡፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ማኅበረ ቅዱሳን የልማት ተቋማት የጧፍ ማምረቻ ማሽን ፈብርኮ በየዓመቱም 250‚000 ጧፍ ከሰም ያመርታል፡፡ ምርቱን ለማምረት ለሚፈልጉ አብያተ ክርስቲያናት የማሽን ሥራና ሥልጠና ይሰጣል፡፡ /የምጣኔ ሀብትና የሕዝብ ጤና አጠባበቅ ባለሞያዋ ወ/ሮ ዓለም ፀሐይ በ፴፪ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ዓመታዊ ስብሰባ ላይ ‹‹በቤተ ክርስቲያን ልዩ ልዩ አነስተኛ የገቢ ማስገኛ ዘዴዎችን ተግባራዊ ስለማድረግ›› በሚል ርእስ ካቀረቡት ጥናታዊ ጽሑፍ የተወሰደ/
ማክሰኞ 18 ፌብሩዋሪ 2014
ተጠቃሚው ማነው?
ማኅበረ ቅዱሳን ለሦስተኛ ጊዜ ያዘጋጀው የአብነት መምህራን ጉባኤ መታገዱን
መግለጫዎችና ዜናዎች እያሳወቁን ነው፡፡ የአብነት መምህራን በቤተ ክህነቱ ‹ለአበል የተረሱ፣ ለሹመት የሚታወሱ› ሆነዋል፡፡
ስብሰባ፣ ዐውደ ጥናት፣ ሥልጠና፣ ጉዞ፣ ሲሆን እነርሱን የሚያስታውስ የለም፡፡ የጵጵስና ሹመት ሲመጣ ግን ‹ከእገሌ ይህንን
ከእገሌም ያንን ተማርኩ› የሚለው ይበዛል፡፡ የቤተ ክርስቲያኒቱም ሆነ የሀገሪቱ ሀገራዊ ዕውቀት ማዕከል መሆናቸው ተረስቶ
ይህንን ያህል ዘመን ሲኖሩ ‹ቤት ልሥራላቸው፣ ዘር ልዝራላቸው› ያለ ቤተ ክህነት አልገጠመንም፡፡ እንዲያውም እነ መምሬ
በዕውቀቱን እነ አያ ብሩ እየቀደሟቸው ቦታ ቦታውን ይዘውታል፡፡
ማኅበረ ቅዱሳን ለውጥ አምጭ ሥራ ከሠራባቸው ዘርፎች አንዱ የአብነት ትምህርት ቤቶች
መሆናቸውን እስላም ከክርስቲያኑ የሚመሰክረው ነው፡፡ ለአብነት መምህራን ደመወዝ ከመክፈል ቤት እስከ መሥራት፣ ትምህርት
ቤቶቻቸውን ከመገንባት ለተማሪዎቹ ቁሳቁስ እስከ ማቅረብ፣ የጤና መርሐ ግብሮችን ከማከናወን እስከ ካሪኩለም ቀረጻ ሰፊ ሥራዎች
ተሠርተዋል፡፡
ለአንድ ሊቅ ከቁሳዊ ነገር በላይ መንፈሳዊ ነገሩ ይበልጥበታል፡፡ ጽድቁ፣ ክብሩ፣
ስሙ፣ መዓርጉ፣ ታሪኩ ታላቅ ነገሮች ናቸው፡፡ ከቁሳዊው ድጋፍም ሞራላዊው ድጋፍ ታላቅ ነው፡፡ እነዚህ የአብነት መምህራን ቦታና
ዐቅም ወስኗቸው፣ እድሜና አሠራር ገድቧቸው እንዳይቀሩ፤ እርስ በርስ ተገናኝተው እንዲመክሩ፤ አሠራራቸውን እንዲያዘምኑ፣ ዕውቀት
እንዲከፋፈሉ፣ ልምድ እንዲለዋወጡ፣ ህልውናቸውን እንዲተዋወቁ፣ ወጥ አሠራር እንዲዘረጉ መደረጉ የሚያስመርቅ እንጂ የሚያስረግም
አልነበረም፡፡
በርግጥ ይህንን መሰል ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸውን ሥራዎች ለመሥራት ተገቢ የሆኑ
ቢሮክራሲያዊ መንገዶችን አሟጦ መጓዝ፤ ማወቅ ያለበት እንዲያውቅ፣ መስማት ያለበትም እንዲሰማ ማደረግ፣ ማሳመንና ማግባባት፣
በአሠራሩና በዓላማው ላይ ቀደም ብሎ ከሚመለከታቸው ጋር መወያየት ያስፈልጋል፡፡ አንድን ታላቅ መኪና የአንዲት ብሎን መላላትና
መውለቅ እንደምታስቆመው ሁሉ የጥቂት ቤተ ክህነታዊ አሠራሮች አለመጠበቅ ታላቁን ዓላማ ሊያደናቅፈው እንደሚችል ማወቅ ተገቢ
ነው፡፡ ትናንት እንዲህ ስለሠራን ነው ማለቱ ብዙም አያዋጣም፡፡ ሁልጊዜ ፋሲካ የለምና፡፡
በዚያም ሆነ በዚህ ግን የአብነት መምህራኑ መሰባሰብና በሞያቸውና አገልግሎታቸው ዙሪያ
መምከር የሚጠቅመው ማንን እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ሲሆን ቤተ ክህነቱ ራሱ አስቦ መሥራት ነበረበት፤ ካልሆነም ደግሞ የሚሠሩትን
ማትጋትና ማገዝ ይገባው ነበር፡፡ ሁለቱም ግን አልሆኑም፡፡ ማኅበሩ በቤተ ክህነቱ አሠራር ያላከናወናቸው ነገሮች አሉ ከተባለ
እንዲያከናውን ማድረግ እንጂ አገር አቋርጠው ወንበር አጥፈው የመጡትን ሊቃውንት ማንገላታት የሚገባ አልነበረም፡፡ ጉባኤው
ተስተካክሎ በመካሄዱ የምትጠቀመው ቤተ ክርስቲያን ናት ባለ መደረጉ ግን ከሰይጣን በቀር ተጠቃሚው ማነው
በሌላ በኩልም ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና የፓትርያርኩ ጽ/ቤት በጉዳዩ አፈታት ላይ
የሄዱበት መንገድም አስገራሚ፣ አስተዛዛቢም ነው፡፡ የማኅበሩ ጽ/ቤት ከቤተ ክህነቱ በ50 ሜትር ርቀት ላይ መኖሩ እየታወቀ
ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁም ሆኑ ፓትርያርኩ ያንን ሁሉ የደብዳቤ ውርጅብኝ ማዝነብ ለምን አስፈለጋቸው? ደግሞስ ጉዳዩ የውስጥ ጉዳይ ነው፤ ለእነዚያ ሁሉ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የመጻፉ
ዓላማው ምንድን ነው? አስፈላጊ ከሆነ ልጆቹን ጠርቶ ‹ጉባኤውን
አቁሙ› ማለት ይቻል የለም እንዴ? ደግሞስ መጀመሪያውኑ ሳያጣሩ
መጻፍ፣ ከዚያ ደግሞ የመሻሪያ ደብዳቤ መጻፍ፣ አከታትሎ ደግሞ የመሻሪያ መሻሪያ መጻፍ የቤተ ክህነቱን ተቋማዊ ኪሣራ ከማሳየት
በቀር ሌላ ምን ያሳያል?
የዛሬን አያድርገውና የፓትርያርክ ደብዳቤኮ የእምነት መግለጫ፣ የሚጠቀስ፣ በክብር
የሚቀመጥ፣ በሃይማኖተ አበው መጽሐፍ ላይ የሚሠፍር ነበር፡፡ እንዲህ ጊዜ በሰጠ ቁጥር መዥለጥ እየተደረገ የሚጻፍ አልነበረም፡፡
ደግሞስ አንድ አባት ልጆቹን ጠርቶ መምከር እየቻለ ‹‹ልጆቼ እንዲህ ያሉ ናቸው›› ብሎ ለዓለም መንገር ከየት ያመጣነው ሥርዓት
ነው? ዓለም ችግሯን ለቤተ ክርስቲያን ታቀርባለች እንጂ ቤተ
ክርስቲያን ችግሯን እንዴት ለዓለም አቤት ትላለች?
የሊቃውንቱ መሰባሰብና መወያየት ለቤተ ክርስቲያኒቱ የወንጌል ሥምሪት ወሳኝ ነው፡፡
እንዲያውም ከሲኖዶሱ ጉባኤ በፊት ሊደረግ የሚገባው ነገር ቢኖር የሊቃውንቱ ጉባኤ ነበር፡፡ በቤተ ክርስቲያኒቱ የትምህርተ
ሃይማኖት፣ የሥርዓትና የትውፊት ጉዳዮች ላይ መክረው የውሳኔ ሃሳቦችን ማቅረብ የነበረባቸው ሊቃውንቱ ናቸው፡፡ ይህ ባለመሆኑም
ይመስላል የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ አጀንዳዎች ሃይማኖታዊ ከመሆን ይልቅ አስተዳደራዊና ቢሮክራሲያዊ የሆኑት፡፡ ስንትና ስንት
የምእመናን ጥያቄዎች እያሉ የሹመትና የበጀት ጥያቄዎች ዋነኛ መነጋገሪያዎች የሚሆኑት፡፡
የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንኮ የራስዋን ጳጳሳት እንድትሾም የተሟገቱት ከመላዋ ሀገሪቱ
የተሰባሰቡ ሊቃውንት ነበሩ፡፡ ምነው መሠረቱ ተዘነጋ፡፡
አሁንም ሊቃውንቱን ተዋቸው፣ ቤተ ክርስቲያን እንደነርሱ ላሉት ናትና፡፡ በጉባኤያቸው
ተገኝቶ መወያየት፣ የጉባኤውን አጀንዳ አብሮ መቅረጽ፣ ጉባኤውን መምራት፣ አሠራሩን ማሳየት ይገባል፣ የአባትም ነው፡፡ የገዛ
ሊቃውንቶቻችንን ግን አትሰብሰቡ፣ አትመካከሩ፣ አትወያዩ፣ ችግር አትፍቱ ብሎ ማገድ፣ እምቢ ካላችሁ ‹ለመንግሥት እነግርባችኋለሁ›› ብሎ መንግሥትን ማስፈራሪያ ማድረግ
ሃይማኖታዊ አይደለም፡፡ ምነው በጎንደሩ የጥምቀት ኤግዚቢሽ የመንግሥት አካላት ሊቃውንቱን ሲያከብሩ ባየን፤ ይህቺ ቤተ ክርስቲያንኮ ያለ ኢትዮጵያውያን ጳጳሳት
ኖራ ታውቃለች፣ ያለ ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ግን የኖረችበት ዘመን የለም፣ አይኖርምም፡፡
አሁንም እጠይቃለሁ፤ የሊቃውንቱን ጉባኤ ማገድ ጥቅሙ ለማን ነው? ባሏን ጎዳሁ ብላ..... እንደተባለው ካልሆነ በቀር፡፡ ሊቃውንቱንም አስተምረው ለወግ
ለመዓርግ ባበቋቸው ልጆቻቸው ሲታገዱ ማየት የስምንተኛውን ሺ መግባት ከማሳየት በቀር ሌላ ምን ያሳያል፡፡
ማክሰኞ 4 ፌብሩዋሪ 2014
በቅዱስ ላልይበላ ደብር የተፈጠረው አለመግባባት በሰላም ተፈታ
በሀገራችን ታሪክ መቀዳሚነት ዓለምን በማስደነቅ የሚታወቀውና በዩኔስኮ ተመዝግቦ ሀገሪቱን በከፍተና ደረጃ የሚያስተዋውቀው
የቅዱስ ላልይበላ ደብር በቀድሞው አሰተዳዳሪ አበ ገብረ ኢየሱስ አስተዳደር ፤ የከተማው ባለሃብት እና በከተማው የቱሪስት አስጎብኚ
ማህበራት መካከል አለመግባባት ተፈጥሮ ረጅም ጊዜ የፈጀ መሆኑን የተለያዩ የዜና ምንጮች ሲዘግቡት መቆታቸው ይታወቃል ይሁን እንጂ በሶስት ተከፍለው ማለትም በደብሩ አስተዳደር፤ በከተማው ባለሀብት
እና በከተማው ያሉ አስጎብኚ ማህበራት መካከል የአሰራር ክፍተቶች
እንደ ነበረና በተለይ በደብሩ የቀድሞ አስተዳደር አማካይነት የተፈጠሩ የአሰሠራር ችግሮች ስለነበሩ የደብሩ አስተዳዳሪ
አባ ገብረ ኢየሱስ ከስተዳዳሪነት እንዲነሱ ተደርጓል፡፡ ነገር ግን በወቅቱ የተከሰተውን አለመግባባትን ለመፍታት
የከተማው አስተዳደር እና የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት የሰላም ኮሚቴ አዋቅሮ ስለነበር ኮሚቴው የሶስቱንም አካላት ችግሮች ካጠና በኋላ
ለሶስቱም የሚስማማ የእርቀ ሰላም ሰነድ አዘጋጅቶ ጥር 25/2006ዓ.ም በዚያው በላልይበላ ጽርሐ ቤተ አብርሃም አዳራሽ የደብሩ
ሊቃውንት፤ ሰበካ ጉባዔ፤ የከተማው ባለሃብት፤ አስጎብኚ ማህበራት በተገኙበት ለደብሩ አዲስ በተመደቡት አስተዳዳሪ መ/ር አባ ወልደ ትንሣኤ አስተባባሪነት በከተማው ከንቲባና
እና በሰላም ኮሚቴው ከፍተኛ ጥረት ሁሉም አካላት እንዲታረቁ ሆኖአል፡፡ በእርቀ ሰነዱ ላይም የሚከተሉት ስምምነቶች ተካተዋል፡፡
እርቀ ሰላሙ ሲፈጸም
በደብሩ አስተዳደር
1 . በቀድሞው አስተዳዳሪ የተባረሩት
ሊቃውንት ካህናትና ልዩልዩ ሠራተኞች እንዲመለሱ
2. በደብሩ ግልጽና ተጠያቂነት
ያለው አሠራር እንዲኖር
3. የአብነት መምህራን ሊቃውንቱ ከፍተኛ ትኩረት እንዲሰጣቸው
4.ደብሩ ልዩ ልዩ እቅዶችን እያቀደ
ከህዝቡ ጋር እተመካከረ እንዲሠራ
5. የደብሩ ትኩረት ከቱሪስቱ ባለፈ
ለአካባቢው ሕዝብ የሚሆን የልማት አውታር ቢቀርጽ እና ተግባራዊ ቢያደርግ
የሚሉት እና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡
በከተማው ባለሀብት
1.
በደብሩ የሚፈጠረውን ማንኛውንም
ችግሮችን ዝም ማለቱ ቀርቶ ችግሩን በጋራ መፍታት
2.
በልማት ሆነ በመሳሰሉት አገልግሎት
ተሳታፊ እንዲሆኑ
3.
በከተማው የሚስተናገዱትን ቱሪስቶች
በትብብር ማስተናገድና የመሳሰሉትን አካቶአል
የከተማው
አስጎብኚ ማኅበራት
1.
የደብሩን ታሪክ በሚገባ አጥንተው
ሳይጨመርና ሳይቀነስ ቱሪስቱን እንዲያስረዱ
2.
ሃይማኖታዊ ሥነ ምግባርን በተላበሰ
መልኩ የማስጎብኘት ተግባራትን እንዲያከናውኑ
3.
የከተማውን ሰላም በማስፈን ረገድ
ከፍተኛ ድርሻ ስላላቸው የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ
4.
በገንዘባቸውም ሆነ በመሳሰሉት ደብሩን
የመደገፍ ሥራ እንዲሰሩ እና የመሳሰሉትን እንዲተገብሩ በእርቀ ሰላሙ ሰነድ ላይ ከተካተተው ውስጥ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ በአጠቃላይ ወደፊት ችግሮች ቢኖሩም
በውይይት እንዲፈታ እና ሁሉም የቤተ ክርስቲያን ልጆች እንደ መሆናችን መጠን ለቤተ ክርስቲያናችን የሚገባንን ሁሉ ለመወጣት ዝግጁ
ነን በማለት እርቀ ሰላሙ ተፈጽሟል፡፡
የጉባኤው ተሳታፊዎች በከፊል
ደንበኛ ይሁኑ ለ፡
ልጥፎች (Atom)
በአውሮጳ የካህናት አንድነት ማኅበር ሊቋቋም መሆኑ ታወቀ በ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከመላዋ አውሮጳ የተውጣጡ ካህናት፡” የ...
-
June 1, 2015 ከሐራ ዘተዋሕዶ በሐዋርያዊት፣ ጥንታዊት እና ብሔራዊት ቤተ ክርስቲያናችን ህልውና እና ዕድገት ፊት ከተጋረጡትና አፋጣኝ እልባት ከ...
-
‹‹…ወንድማችንን እናውቃቸዋለን፤ በእውነቱ ለፌ ወለፌ የማይሉ ደረቅ ሊቅ ናቸው፤ በሃይማኖቱ ዘርፍ ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን፣ ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን አንዲቱም ነጥብ እንዳትዛባ...