2014 ማርች 14, ዓርብ

ዐቢይ ጾም አራተኛ ሳምንት "መጻጉዕ"

ይህ ሳምንት የዐቢይ ጾም አራተኛ ሳምንት እሁድ ነው። ስሙም መጻጉዕ ይባላል። በዚህ እለት ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ድውያንን ፈውሷል፥ ጎባጣዎችን አቅንቷል፣ እውራንን አብርቷል፣ አንካሶችንም አድኗል ለምፃሞችንም በመለኮታዊ ሃይሉ አንጽቷል። ቤተ ክርስቲያናችንም በዚህ ዕለት ስለ ጌታችነ ገቢረ ተዓምራትና ስለ ድውያን ፈውስ በሰፊው ታስተምራለች። በቅዳሴ ጊዜ ይህንኑ የሚያስረዱ የመፃሕፍት ክፍሎችም ይነበባሉ። እነሱንም እንደሚከተለው ማየት እንችላለን።
የመጀመሪያ ምንባብ የሐዋርያው የቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት ወደ ገላትያ ሰዎች
ምዕራፍ 
፩. በነጻነት ልንኖር ክርስቶስ ነጻነት አወጣን፤ እንግዲህ ጸንታችሁ ቁሙ እንደ ገናም በባርነት ቀንበርአትያዙ። ፪. እነሆ፥ እኔ ጳውሎስ እላችኋለሁ። ብትገረዙ ክርስቶስ ምንም አይጠቅማችሁም። ፫.ሕግንም ሁሉ እንዲፈጽም ግድ አለበት ብዬ ለሚገረዙት ሁሉ ለእያንዳንዶች ደግሜ እመሰክራለሁ።፬. በሕግ ልትጸድቁ የምትፈልጉ ከክርስቶስ ተለይታችሁ ከጸጋው ወድቃችኋል። ፭.  እኛ በመንፈስከእምነት የጽድቅን ተስፋ እንጠባበቃለንና። ፮. በክርስቶስ ኢየሱስ ሆኖ፥ በፍቅር የሚሠራ እምነትእንጂ መገረዝ ቢሆን ወይም አለመገረዝ አይጠቅምምና። ፯. በመልካም ትሮጡ ነበር፤ ለእውነትእንዳትታዘዙ ማን ከለከላችሁ?፰.  ይህ ማባበል ከሚጠራችሁ አልወጣም። ጥቂት እርሾ ሊጡን ሁሉያቦካል። ፱-፲. የተለየ ነገር ከቶ እንዳታስቡ እኔ በጌታ ስለ እናንተ ታምኜአለሁ፤ የሚያናውጣችሁ
ማንም ቢኖር ግን ፍርዱን ሊሸከም ነው። ፲፩. ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ እኔ ገና እስከ አሁንመገረዝን ብሰብክ እስከ አሁን ድረስ ለምን ያሳድዱኛልእንኪያስ የመስቀል ዕንቅፋት ተወግዶአል።፲፪. የሚያውኩአችሁ ይቆረጡ። ፲፫. ወንድሞች ሆይ፥ እናንተ ለአርነት ተጠርታችኋልና፤ ብቻአርነታችሁ ለሥጋ ምክንያትን አይስጥ፥ ነገር ግን በፍቅር እርስ በርሳችሁ እንደ ባሪያዎች ሁኑ። ፲፬. ሕግ ሁሉ በአንድ ቃል ይፈጸማልና፥
እርሱም። ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ የሚል ነው። ፲፭. ነገር ግን እርስ በርሳችሁ
ብትነካከሱ ብትበላሉ እርስ በርሳችሁ እንዳትጠፋፉ ተጠንቀቁ። ፲፮.  ነገር ግን እላለሁ፥ በመንፈስተመላለሱ፥ የሥጋንም ምኞት ከቶ አትፈጽሙ። ፲፯. ሥጋ በመንፈስ ላይ መንፈስም በሥጋ ላይይመኛልና፥ እነዚህም እርስ በርሳቸው ይቀዋወማሉ፤ ስለዚህም የምትወዱትን ልታደርጉ አትችሉም።፲፰.  በመንፈስ ብትመሩ ግን
ከሕግ በታች አይደላችሁም። ፲፱. የሥጋ ሥራም የተገለጠ ነው እርሱም ዝሙት፥ ርኵሰት፥ ፳.መዳራት፥ ጣዖትን ማምለክ፥ ምዋርት፥ ጥል፥ ክርክር፥ ቅንዓት፥ ቁጣ፥ አድመኛነት፥ ፳፩.  መለያየት፥መናፍቅነት፥ ምቀኝነት፥ መግደል፥ ስካር፥ ዘፋኝነት፥ ይህንም የሚመስል ነው። አስቀድሜምእንዳልሁ፥ እንደዚህ ያሉትን የሚያደርጉ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም። ፳፪. የመንፈስፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥
እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው።፳፫.  እንደዚህ ያሉትን የሚከለክል ሕግ የለም። ፳፬. የክርስቶስ ኢየሱስም የሆኑቱ ሥጋን ከክፉ መሻቱና ከምኞቱ ጋር ሰቀሉ። ፳፭. በመንፈስ ብንኖርበመንፈስ ደግሞ እንመላለስ። ፳፮. እርስ በርሳችን እየተነሣሣንና እየተቀናናን በከንቱ አንመካ።
ሁለተኛ ምንባብ የያዕቆብ መልእክት
ምዕራፍ 
፲፬. ከእናንተ የታመመ ማንም ቢኖር የቤተ ክርስቲያንን ሽምግሌዎች ወደ እርሱ ይጥራ፤ በጌታምስም እርሱን ዘይት ቀብተው ይጸልዩለት። ፲፭.  የእምነትም ጸሎት ድውዩን ያድናል ጌታምያስነሣዋል፤ ኃጢአትንም ሠርቶ እንደ ሆነ ይሰረይለታል። ፲፮. እርስ በርሳችሁ በኃጢአታችሁተናዘዙ። ትፈወሱም ዘንድ እያንዳንዱ ስለ ሌላው ይጸልይ፤ የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግኃይል ታደርጋለች። ፲፯. ኤልያስ እንደ እኛ የሆነ ሰው ነበረ፥ ዝናብም እንዳይዘንብ አጥብቆ ጸለየ፥በምድርም ላይ ሦስት ዓመት ከስድስት ወር አልዘነበም፤ ሁለተኛም ጸለየ፥ ፲፰. ሰማዩም ዝናብን ሰጠምድሪቱም ፍሬዋን አበቀለች። ፲፱. ወንድሞቼ ሆይ፥ ከእናንተ ማንም ከእውነት
ቢስት አንዱም ቢመልሰው፥ ፳. ኃጢአተኛን ከተሳሳተበት መንገድ የሚመልሰው ነፍሱን ከሞትእንዲያድን፥የኃጢአትንም ብዛት እንዲሸፍን ይወቅ።
ሦስተኛው ምንባብ የሐዋርያት ሥራ
ምዕራፍ 3
፩. ጴጥሮስና ዮሐንስም በጸሎት ጊዜ በዘጠኝ ሰዓት ወደ መቅደስ ይወጡ ነበር። ፪. ወደ መቅደስምከሚገቡት ምጽዋት ይለምን ዘንድ፥ ሰዎች ተሸክመው መልካም በሚሉአት በመቅደስ ደጅ በየቀኑያስቀምጡት የነበሩ ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ አንካሳ የሆነ አንድ ሰው ነበረ። ፫. እርሱም ጴጥሮስናዮሐንስ ወደ መቅደስ ሊገቡ እንዳላቸው ባየ ጊዜ፥ ምጽዋትን ለመናቸው። ፬. ጴጥሮስም ከዮሐንስ ጋርትኵር ብሎ ወደ እርሱ ተመልክቶ። ወደ እኛ
ተመልከት አለው። ፭. እርሱም አንድ ነገር ከእነርሱ እንዲቀበል ሲጠብቅ ወደ እነርሱ ተመለከተ።፮. ጴጥሮስ ግን። ብርና ወርቅ የለኝም፤ ይህን ያለኝን ግን እሰጥሃለሁ፤ በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስስም ተነሣና ተመላለስ አለው።
፯.  በቀኝ እጁም ይዞ አስነሣው፤ በዚያን ጊዜም እግሩና ቍርጭምጭምቱ ጸና፥ ፰. ወደ ላይ ዘሎምቆመ፥ ይመላለስም ጀመር፤ እየተመላለሰም እየዘለለም እግዚአብሔርንም እያመሰገነ ከእነርሱ ጋር ወደመቅደስ ገባ። 9 ሕዝቡም ሁሉ እግዚአብሔርን እያመሰገነ ሲመላለስ አዩት፤ ፲. መልካምምበሚሉአት በመቅደስ ደጅ ስለ ምጽዋት ተቀምጦ የነበረው እርሱ እንደ ሆነ አወቁት፤ በእርሱምከሆነው የተነሣ መደነቅና መገረም ሞላባቸው። ፲፩. እርሱም ጴጥሮስንና ዮሐንስን ይዞ ሳለ፥ ሕዝቡሁሉ እየተደነቁ የሰሎሞን ደጅ መመላለሻ በሚባለው አብረው ወደ እነርሱ
ሮጡ። ፲፪. ጴጥሮስም አይቶ ለሕዝቡ እንዲህ ሲል መለሰ። የእስራኤል ሰዎች ሆይ፥ በዚህ ስለ ምንትደነቃላችሁወይስ በገዛ ኃይላችን ወይስ እግዚአብሔርን በመፍራታችን ይህ ይመላለስ ዘንድእንዳደረግነው ስለ ምን ትኵር ብላችሁ ታዩናላችሁ?
የዕለቱ ምስባክ
እግዚአብሔር ይረድኦ ውስተ ዓራተ ሕማሙ
ወይመይጥ ሎቱ ኩሉ ምስካቤሁ እምደዌሁ
አንሰ እቤ እግዚኦ ተሣሃለኒ።         መዝ.፵፥፫
እግዚአብሔር በደዌው አልጋ ሳለ ይረዳዋል
መኝታውን ሁሉ በበሽታው ጊዜ ያነጥፍለታል
እኔስ አቤቱ ማረኝ።       መዝ.፵፥፫
የዕለቱ ወንጌል የዮሐንስ ወንጌል
ራፍ 5
፩. ከዚህ በኋላ የአይሁድ በዓል ነበረ፥ ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ። ፪. በኢየሩሳሌምም በበጎችበር አጠገብ በዕብራይስጥ ቤተ ሳይዳ የምትባል አንዲት መጠመቂያ ነበረች፤ አምስትም መመላለሻነበረባት። ፫. በእነዚህ ውስጥ የውኃውን መንቀሳቀስ እየጠበቁ በሽተኞችና ዕውሮች አንካሶችምሰውነታቸውም የሰለለ ብዙ ሕዝብ ይተኙ ነበር። ፬. አንዳንድ ጊዜ የጌታ መልአክ ወደመጠመቂያይቱ ወርዶ ውኃውን ያናውጥ ነበርና፤ እንግዲህ ከውኃው መናወጥ በኋላ በመጀመሪያ የገባከማናቸው ካለበት ደዌ ጤናማ ይሆን ነበር። ፭. በዚያም ከሠላሳ ስምንት ዓመት ጀምሮ የታመመአንድ ሰው ነበረ፤ ፮. ኢየሱስ ይህን ሰው ተኝቶ ባየ ጊዜ፥ እስከ አሁን ብዙ ዘመን እንዲሁ እንደ ነበረአውቆ። ልትድን ትወዳለህንአለው። ፯. ድውዩም። ጌታ ሆይ፥ ውኃው በተናወጠ ጊዜበመጠመቂያይቱ ውስጥ የሚያኖረኝ ሰው የለኝም ነገር ግን እኔ ስመጣ ሳለሁ ሌላው ቀድሞኝይወርዳል ብሎ መለሰለት። ፰. ኢየሱስ። ተነሣና አልጋህን ተሸክመህ ሂድ አለው። ፱. ወዲያውምሰውዬው ዳነ አልጋውንም ተሸክሞ ሄደ። ፲. ያም ቀን ሰንበት ነበረ። ስለዚህ አይሁድ የተፈወሰውንሰው። ሰንበት ነው አልጋህንም ልትሸከም አልተፈቀደልህም አሉት። ፲፩. እርሱ ግን። ያዳነኝ ሰው። አልጋህን ተሸክመህ ሂድ አለኝ ብሎ መለሰላቸው። ፲፪. እነርሱም። አልጋህን ተሸክመህ ሂድያለህ ሰው ማን ነውብለው ጠየቁት። ፲፫. ዳሩ ግን በዚያ ስፍራ ሕዝብ ሰለ ነበሩ ኢየሱስ ፈቀቅብሎ ነበርና የተፈወሰው ሰው ማን እንደ ሆነ አላወቀም። ፲፬.  ከዚህ በኋላ ኢየሱስ በመቅደስአገኘውና። እነሆ፥ ድነሃል፤ ከዚህ የሚብስ እንዳይደርስብህ ወደ ፊት ኃጢአት አትሥራ አለው። ፲፭.ሰውዬው ሄዶ ያዳነው ኢየሱስ እንደ ሆነ ለአይሁድ ነገረ። ፲፮. ስለዚህም በሰንበት ይህን ስላደረገአይሁድ ኢየሱስን ያሳድዱት ነበር ሊገድሉትም ይፈልጉ ነበር። ፲፯. ኢየሱስ ግን። አባቴ እስከ ዛሬይሠራል እኔም ደግሞ እሠራለሁ ብሎ መለሰላቸው። ፲፰. እንግዲህ ሰንበትን ስለ ሻረ ብቻአይደለም፥ ነገር ግን ደግሞ ራሱን ከእግዚአብሔር ጋር አስተካክሎ። እግዚአብሔር አባቴ ነው ስላለ፥ስለዚህ አይሁድ ሊገድሉት አብዝተው ይፈልጉት ነበር። ፲፱. ስለዚህ ኢየሱስ መለሰ እንዲህምአላቸው። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብ ሲያደርግ ያየውን ነው እንጂ ወልድ ከራሱ ሊያደርግምንም አይችልም፤  የሚያደርገውን ሁሉ ወልድ ደግሞ ይህን እንዲሁ ያደርጋልና። ፳. አብ ወልድንይወዳልና፥ የሚያደርገውንም ሁሉ ያሳየዋል፤ እናንተም ትደነቁ ዘንድ ከዚህ የሚበልጥ ሥራ ያሳየዋል።፳፩. አብ ሙታንን እንደሚያነሣ ሕይወትም እንደሚሰጣቸው፥ እንዲሁ ወልድ ደግሞ ለሚወዳቸውሕይወትን ይሰጣቸዋል።
፳፪-፳፫. ሰዎች ሁሉ አብን እንደሚያከብሩት ወልድን ያከብሩት ዘንድ፥ ፍርድን ሁሉ ለወልድሰጠው እንጂ አብ በአንድ ሰው ስንኳ አይፈርድም። ወልድን የማያከብር የላከውን አብንአያከብርም። ፳፬. እውነት እውነት
እላችኋለሁ፥ ቃሌን የሚሰማ የላከኝንም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፥ ከሞትም ወደ ሕይወትተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም። ፳፭. እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ሙታን የእግዚአብሔርንልጅ ድምፅ የሚሰሙበት ሰዓት ይመጣል እርሱም አሁን ነው፤ የሚሰሙትም በሕይወት ይኖራሉ።

2014 ማርች 13, ሐሙስ

የቤተ ሰብእ መሪ

                                            አርባ ምንጭ መንበረ ጵጵስና

                                                                                                                                                              ከካቲት 28- 30 ድረስ ለመንፈሳዊ አገልግሎት ወደ አርባ ምንጭ  ከባልደረቦቼ መጋቤ ሐዲስ መንግስቱ አማረ ፤ ዲ. ተመስገን ዘገዬ እና ዘማሪት መሠረት ማሞ ጋር በመሆን ተጉዘን ነበር  አርባ ምንጭ እንደሚታወቀው ሁለቱን ሐይቆች አባያ እና ጫሞን ዓይን አድርጋ ውበትን የተላበሰች ቱሪስቶች ሁል ጊዜ የማይለይዋት ሞቃት ከተማ ናት ፡ አርባ ምንጭ  በከተማዋ ከላይና ከታች/ ከመግቢያዋና ከመወጫዋ ታላላቅ ዩኒቨርስቲዎች ይገኛሉ ፡፡ የሀገረ ስብከቱም ሊቀጳጳስ አቡነ ኤልያስም በቅርቡ አሰርተው በቅዱስ ፓትርያርኩ ያስመረቁትም ሁለገብ የሆነ መንበረ ጵጵስና ሁለቱን ሀይቆች በርቀት ይቆጣጠራል፡፡ እኛም የተጓዝንበትም አገልግሎት ውጤታማ ነበረ፡እሁድ ከቅዳሴ በኋላ በከተማዋ መሃል በሚገኘው ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ቅጥር ገቢ ወደ ሚገኘው የማኅበረ ቅዱሳን አርባ ምንጭ ማዕከል ብቅ አልን አባላቱ ውይይት ላይ ናቸው፡፡ የመወያያ አጀንዳው ‹‹የቤተ ሰብእ መሪ ›› የሚል ነበር  አባላቱ መንፈሳዊ አገልግሎትን  ለማጠናከር ሲሉ አሥር ያህል አባላት ያሉት ቡድን አዋቅረዋል  አንድ የቤተ ሰብእ መሪ አለው፡፡ ቤተ ሰብእ መሪው ስለመንፈሳዊ ሕይወታቸው አጠቃላይ ይከታተል ዘንድ ተመርጧል ለምሳሌ፤
                                ከንስሐ አባታቸው ጋር ያለቸውን   ግንኙነት
                                 በሰንበት ት/ቤት አገልግሎት
                                 በሰበካ ጉባኤ ያለቸውን ተሳትፎ
                                 በማህበራዊ ኑሮ
                                 ከሀገረ ስብከቱ እና አድባራት አገልጋዮች ያለቸውን መልካም ግንኙነት ይከታተላል የቤተ ሰብእ መሪው ፤ እኔም ይህ ተሞክሮ ለሌሎች የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮ ጥሩ ምሳሌ ስለሆነ ይበል እንላለን፡፡
                                           
2014 ማርች 5, ረቡዕ

ፓትርያርኩ የቤተ ክርስቲያኒቷን አስተዳደር የማሻሻል አቋሜ ‹‹አልተበረዘም፤ አልተከለሰም›› አሉ

  • ‹‹የፀረ ሙስና አቋማቸው ራሳቸውን ከማስተዋወቅ ያለፈ ውጤት አላመጣም›› /ተቺዎች/
(ሰንደቅ፤ የካቲት ፳፮ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም.)
Sendek front pageየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፍትሕ፣ ርትዕና እኩልነት የሞላባት፣ መልካም አስተዳደር የሰፈነባት ለማድረግ በዕለተ ሢመተ ፕትርክናቸው የተናገሩት ቃል ኹሉ እንደጸና መኾኑንና ከቅዱስ ሲኖዶስ አባላት፣ ከሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና ከምእመናን ጋር በመኾን እንደሚያጠናክሩት ፓትርያርኩ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ተናገሩ፡፡
የቤተ ክርስቲያኒቱ ስድስተኛ ፓትርያርክ ኾነው የተሾሙበት አንደኛ ዓመት ከትላንት በስቲያ በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በተከበረበት ወቅት ‹‹ሙስና ካልጠፋ ሕይወት አይኖርም›› ሲሉ የተናገሩት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚሰበሰበው ገንዘብ ከድኾች የተገኘ ሀብት ስለኾነ የድኾችን ገንዘብ በከንቱ የሚያማስነውን እግዚአብሔር እንደሚፈርድበት፣ በዚኽም እግዚአብሔርን ማታለልና በእግዚአብሔር ላይ መቀለድ እንደማይቻል አስጠንቅቀዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያን የእውነትና የሐቅ መገኛ ትኾን ዘንድ መንፈሳዊ ባሕርይዋ የሚያስገድዳትና አገልግሎትዋም በእግዚአብሔር ስም የሚሠራ በመኾኑ አሠራርዋ ከአድሏዊነትና ወገንተኝነት መጽዳት፣ ታማኝነትንና ፍትሐዊነትን መጎናጸፍ ይኖርበታል ብለዋል ፓትርያርኩ፡፡
ቤተ ክርስቲያን ሲባል ሕንፃ ቤተ መቅደሱ ብቻ ሳይኾን የካህናትና የምእመናን አንድነትም መኾኑን ያስረዱት አቡነ ማትያስ፣ በይበልጥም ቤተ ክርስቲያኒቷን በሓላፊነት ለመጠበቅ ጥሪው ያላቸው ካህናት በአበው ሥርዐት በተደነገገው መሠረት÷ ቀኖናዋንና ትውፊቷን መጠበቅና ማስጠበቅ፣ ምእመኖቿን በስብከተ ወንጌል ማርካትና በግብረ ገብነት እንዲታነፁ ማድረግ የዉሉደ ክህነት ሓላፊነት ነው፤ ከዚኽ አንጻር ዉሉደ ክህነት የቤተ ክርስቲያኒቱ ተልእኮ ፈሩን ሳይስት እንዲፈጸም የማድረግ መንፈሳዊ ግዴታ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
በዓለ ሢመቱ የአንድ መሪ ግለሰብ በዓል እንዳልኾነ ያስገነዘቡት ፓትርያርኩ፣ በዓሉ የቤተ ክርስቲያኒቱ ኹለንተናዊ ልዕልናና ክብር በፊት እንዴት እንደነበር፣ አኹን ምን ላይ እንዳለና በቀጣይ ሐዋርያዊ ተልእኮዋን በስኬት ለማከናወን ምን መደረግ እንዳለበት እየታሰበ እንደሚከበር አብራርተዋል፡፡ ከሥርዐተ ሢመታቸው ወዲህ ባለፈው የአንድ ዓመቱ ጉዞ ውስጥ ተከናውነዋል ያሏቸውን ተግባራት ፓትርያርኩ በንግግራቸው ዘርዝረዋል፡፡
‹‹የቤተ ክርስቲያኒቱ ሕግ እየተሻሻለ ነው፤ በመልካም አስተዳደር፣ በመሪ ዕቅድ እንድትመራ ጥረት እየተደረገ ነው፤›› በማለት ክንውኑን የጠቀሱት ፓትርያርኩ፣ ‹‹ችግሩ ለዘመናት የተከማቸና በአጭር ጊዜ ለውጥ ለማምጣት ስለሚያዳግት በትዕግሥት መጠባበቁ መልካም ይኾናል፤›› ብለዋል፡፡ በበዓለ ሢመታቸው ቀን የአስተዳደር መዋቅር ማሻሻያን አስመልክቶ ተናግረዋቸው የነበሩ ቃላት ኹሉ ‹‹እንደጸኑ ናቸው፤ አልተበረዙም፤ አልተከለሱም፤ እንዲያውም ከሲኖዶስ አባላት፣ ከሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና ከምእመናን ጋር በመኾን አጠናክራቸዋለኹ›› ያሉት አቡነ ማትያስ፣ ለመልካም አስተዳደር መረጋገጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ባለድርሻ አካላት ኹሉ መነሣት እንደሚኖርባቸው ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፤ ‹‹ይህ ግዴታ ነው›› ሲሉም አክለዋል፡፡
የቤተ ክርስቲያኒቱ የአስተዳደር መዋቅር እንዲሁም አደረጃጀትና አሠራር ከመሠረታዊ ክህነታዊና የስብከተ ወንጌል ተልእኮዋ ጋራ እንዲጣጣም፣ ሙስናና ብልሹ አሠራር እንዲወገድ የተደረጉ የሙከራ ትግበራዎችና በመደረግ ላይ ያሉ ጥረቶች፣ ‹‹ይኹንታ ካገኙበት የቅ/ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ውሳኔ በተፃራሪ ዕንቅፋት ገጥሟቸዋል፤›› የሚሉ የቅርብ ታዛቢዎች በበኩላቸው÷ ፓትርያርኩ ሙስናን በየአጋጣሚው በመቃወምና ስለመልካም አስተዳደር ደጋግሞ በመናገር ራሳቸውን አስተዋውቀው እንደኾነ እንጂ ያመጡት ተስፋ ሰጭ ውጤት የለም፤ እንዲያውም በደሉና ጥፋቱ መልኩን ለውጡ እየረቀቀና እየተባባሰ መምጣቱን በምሬት ይናገራሉ፡፡
በቤተ ክርስቲያኒቱ አስተዳደር ውስጥ ሥር ሰዷል ያሉት ጎሰኝነት ከቀድሞም ጀምሮ ስማቸው ሲጠቀስ በቆዩና በተለይ በፓትርያርኩ ጽ/ቤት ዙሪያ በተሰባሰቡ ግለሰቦች ተጽዕኖ እየገዘፈ መምጣቱን ታዛቢዎቹ ከማስረዳታቸውም በላይ፣ ፓትርያርኩ ‹‹እንደ ጸና ነው›› የሚሉት አቋማቸው በላቀ አመራርና የውሳኔ ሰጭነት አቅም ተፈትኖና በተግባር ተገልጦ ማየት እንደሚሹ ለሰንደቅ ገልጸዋል፡፡

2014 ማርች 4, ማክሰኞ

ፓትርያርኩ ከአማሳኞችና ጎሰኞች ጋራ ተዋርደው ከመምከር እንዲታቀቡና በዐደባባይ ቃል የገቡበትን ተቋማዊ ለውጥ በተግባር እንዲያስፈጽሙ ሊቃነ ጳጳሳቱ አሳሰቧቸው

His Grace Abune Elsa on 32 SGGA
ብፁዕ አቡነ አልሳዕ
  • ‹‹ቅዱስነትዎ÷ ይህን ታላቅ ሓላፊነት ሲቀበሉ ቅ/ሲኖዶስ አዲስ ዋና ጸሐፊ፣ አዲስ ዋና ሥራ አስኪያጅ አድርጎ ሰጥዎታል፤ መምከር ያለብዎ ከእነርሱ ጋራ ነው፤ ከዚያም ካለፈ ከቋሚ ሲኖዶሱ ነው፤ አስፈላጊ ከኾነም ጠቅላላው ጉባኤው ይሰበሰባል፡፡ እርስዎ ግን ወርደው ከማን ጋራ ነው እየተማከሩ ያሉት?››
  • ‹‹በአገራችን ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት እና ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በመላው ኢትዮጵያ ሲያገለግሉ ከየት መጣኽ አልተባባሉም፤ ከሥራ ወንድምችዎ ጋራ ከየት መጣኽ ሳንባባል በአንድነት እየተመካከርን ነው ማገልገል ያለብን፤ ከዚያ ወርደን መገኘት የለብንም፡፡››
  • ‹‹የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት በመጀመሪያ ቅዱስ ወንጌል ከዚያ የሐዋርያት፣ የሊቃውንት እያሉ ነው የሚቀጥሉት፤ እርስዎም ከብፁዕ ዋና ጸሐፊ፣ ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ ከቋሚ ሲኖዶስ፣ ከምልዓተ ጉባኤ ጋራ ነው፡፡ ከዚያ ሲወርድ ግን ከሊቃውንት መጽሐፍም ወርዶ ልቦለድ መጽሐፍ እንደ ማንበብ ነው!!›› /ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ፣ የሰሜን ጎንደር ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ/
His Grace gen sec of the patriarchate Abune Mathewos speaking on the enthronment anniv.
ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ አቡነ ማቴዎስ
  • ‹‹እግዚአብሔር ለሚወደው ሕዝብ ነቢይ ኾኖ ትንቢት የሚነግራቸውን፣ አስተዳዳሪ ኾኖ የሚመራቸውን፣ ኖላዊ ኾኖ የሚጠብቃቸውን አባት ያዘጋጅላቸዋል፤ የዛሬው ቀን ይህን እግዚአብሔር የሚወደውን ሕዝብ ለቅዱስነትዎ ያስረከበበት ቀን ነው፡፡››
  • ‹‹የዛሬው ቀን ለቤተ ክርስቲያን ችግሯን ፈቺ፣ ለዕድገቷ ፕላን አውጪ፣ ለአስተዳደሯ መመሪያ ሰጪ ለመኾን በዐደባባይ ቃል የገቡበት ቀን ስለኾነ በታላቅ አክብሮትና ደስታ እናስታውሰዋለን፡፡ ራስን ለሌላው አሳልፎ መስጠት በቀላል አይመጣም፤ የልብ መሻትና መሠበርን ይፈልጋል፤ ማዕርግ ከነክብሩ፣ ሥልጣን ከነእውነቱ፣ መስቀል ከነትዕግሥቱ ካልተሰጠ አይቻልም፡፡ /ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ/
His Holiness giving benediction on the day of His enthronment
ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ
  • ‹‹የዛሬ ዓመት የተናርኋቸው ቃላት ኹሉ እንደጸኑ ናቸው፤ አልተበረዙም፤ አልተከለሱም፤ እንዲያውም ከቅ/ሲኖዶስ አባላት፣ ከሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና ከምእመናን ጋራ በመኾን አጠናክራቸዋለኹ፡፡››
  • ‹‹የቤተ ክርስቲያን ጥሪ በምድር ላይ ለመከራ መስቀል እንጂ ለተድላ ሥጋ አይደለም፤ ተድላውና ደስታው የተዘጋጀው በላይኛው ዓለም ነው፤ የቤተ ክርስቲያን መሪ፣ አገልጋይና ተከታይ የኾነ ኹሉ በውል መገንዘብ ያለበት ይህን ነው፤ የተጠራነው ለሰማያዊ ሀብትና ሹመት እንጂ እንደ ሣር ቅጠል ለጊዜው ታይቶ ለሚጠፋ ምድራዊ ሀብትና ሥልጣን አይደለም፡፡››
  • ‹‹የቤተ ክርስቲያናችን አሠራር እንዳይቃና እየተጠላለፉና እየተመሰቃቀሉ ብዙ እንዳንራመድ የሚያደርጉን ምክንያቶች ከማንም ይኹን ከየት ምንጫቸው ከፍቅረ ንዋይና ከፍቅረ ሢመት ውጭ ናቸው የሚል ግንዛቤ የለም፤ ለእነዚኽ ደግሞ ቁልፍ መፍትሔያቸው ራስን ክዶ መስቀልን ለመሸከም በቁርጥ ከመነሣት በቀር ሌላ ሊኾን አይችልም፡፡ እኛ የቤተ ክርስቲያናችን ተጠሪዎች ሥራችን ሊቃና፣ ተደማጭነታችን ሊሰፋ፣ ተልእኳችን ሊሠምር፣ ሕዝባችን ሊያምነንና ሊከተለን የሚችለው የጌታችንን ቃል አክብረንና ራሳችንን ክደን ለእውነት የቆምን እንደኾን ብቻ ነው፡፡››
  • ‹‹ባሳለፍነው የአንድ ዓመት ጉዞ ቅ/ሲኖዶስ ቤተ ክርስቲያናችን በዕቅድ እንድትመራ፣ የቤተ ክርስቲያን ሀብትና ንብረት እንዳይባክን በዘመናዊ አያያዝ እንዲያዝ፣ መልካም አስተዳደር፣ ፍትሕና ርትዕ፣ እኩልነት፣ ግልጽነትና ተጠያቂነት እንዲሰፍን ከመወሰን ባሻገር ይህን በሕግ ማህቀፍ፣ በደንብና በመመሪያ አጠናክራ ለመሥራት በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና በዕውቅ ምሁራን አማካይነት ልዩ ልዩ ጥናቶችን እያካሔደች ትገኛለች፡፡ ይህ የተጀመረው የአሠራር ለውጥ ተፈጽሞ ሲታይ ኹሉን እንደሚያስደስት ጥርጥር የለውም፤ ቤተ ክርስቲያናችን በሕግና በሥርዐት ስትመራ፣ የቤተ ክርስቲያናችን ኢኮኖሚ ጠንካራ ይኾናል፤ መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎታችንም ለሕዝበ ክርስቲያን በአግባቡ ተደራሽ ይኾናል፡፡ እነዚኽን ዐበይት ጉዳዮች ከሥራ ላይ ለማዋል የኹሉም ቀና መንፈስና ትብብር ያስፈልጋል፤ ራስን መካድ ያስፈልጋል፡፡›› /ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ/
*                                  *                                  *
  • ለአንደኛ ዓመት በዓለ ሢመት አከባበር በእንግሊዝኛ የወጣው የመርሐ ግብሩ ዝርዝር የታየበት የአጻጻፍ ውስንነትና የእውነታ ስሕተት በታዳሚዎች ተተቸ – ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስን “the 1st patriarch of the Ethiopia Orthodox Tewahido Church” ያደርጋቸዋል፤  ‹‹Message from the Acting patriarch of EOTC” የሚል መርሐ ግብርም አለው! የሰዓት አገላለጹማ….
  • የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታይ የኾኑት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ባለቤ ለቤተ ክርስቲያን በማይገባ አለባበስ (በአጭር ቀሚስ) የበዓለ ሢመቱ እንግዳ መኾናቸው ቅሬታ ፈጥሯል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ይከታተሉ፡

2014 ማርች 3, ሰኞ

የፓትርያርኩ የለውጥ ተግዳሮትና ተስፋ – በአንደኛ ዓመት በዓለ ሢመት ዋዜማ

Abune Mathias 1st anniv. enthronment
  • የብልሹ አሠራርና ሙስናን ችግር በዐደባባይ የተናገሩ የመጀመሪያው ፓትርያርክ ናቸው
  • ጽኑ አቋም ስለሚጎድላቸው ለጣልቃ ገብነት የተመቹ ኾነዋል
  • ጣልቃ ገብነቶችን መቋቋምና የቅ/ሲኖዶሱን ልዕልና ማስከበር ይጠበቅባቸዋል
  • የተጠጓቸውን ‹አማካሪዎች› ማንነት መለየትና ዙሪያቸውን መፈተሽ አለባቸው
  • የተሟላና ብቃት ያለው የአማካሪ መዋቅር ያስፈልጋቸዋል
(አዲስ አድማስ፤ ቅጽ ፲፫ ቁጥር ፯፻፴፯፤ የካቲት ፳፪ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም.)
Admas logoየካቲት 21 ቀን 2005 ዓ.ም.፤ ለስድስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ምርጫ ከቀረቡት አምስት ዕጩዎች መካከል በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ማትያስ በከፍተኛ ድምፅ መመረጣቸው ተነገረ፡፡ ሊቀ ጳጳሱ በቤተ ክርስቲያኒቱ የፓትርያርኮች ምርጫ ታሪክ ከፍተኛውን የመራጮች ድምፅ በማግኘት አሸናፊ መኾናቸው በተገለጸበት ወቅት የብዙዎችን ትኩረት በሳበ ኹኔታ በመስቀላቸው ሲያማትቡ ታዩ፡፡
የወቅቱን ስሜታቸውን አስመልክቶ ‹‹ዜና ቤተ ክርስቲያን›› በተሰኘው መጽሔት ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ÷ ‹‹ፓትርያርክ እኾናለሁ የሚል መንፈስ በውስጤ ስላልነበረ ውጤቱ ሲገለጽ፣ እንዴት ነው ይህ የእግዚአብሔር ሥራ ምንድን ነው ከሚል ደነገጥኹኝ፤ በዚያው ቅጽበት የተሰማኝ፣ እግዚአብሔር ይህን ታላቅ ሓላፊነት እንዴት እችለዋለሁ? በል አንተ ታውቃለህ፤›› የሚል እንደነበር አስረድተዋል፡፡
ከምርጫው ሦስት ቀናት በኋላ የካቲት 24 ቀን 2005 ዓ.ም. በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በተከናወነው ሥርዐተ ሢመት÷ ለፓትርያርክነት መመረጣቸው የቤተ ክርስቲያኒቱ ጥሪ እንደኾነና ጥሪውን የተቀበሉት መኾኑን፣ መቀበላቸውም ለክብርና ለልዕልና ሳይኾን ለመሥዋዕት በመታዘዝ በመኾኑ የቅዱስ ሲኖዶሱን አባላት በመያዝ በጋራ እንደሚወጡት ያላቸውን እምነት ተናግረው ነበር፡፡
ፓትርያርኩ በዚያ ንግግራቸው ‹‹ቅዱስ ሲኖዶሱ በራሱ መተማመን አለበት›› ሲሉ በአጽንዖት የተናገሩ ሲኾን እንደ አንድ ልብ አሳቢ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ኾኖ በሥምረት ከሠራ፣ ችግር ይኖራል ብለው እንደማያምኑ ገልጸዋል፡፡ በቅ/ሲኖዶሱ ሊሠሩ ይገባል በሚል ካሳወቋቸው ተግባራት መካከልም ቤተ ክርስቲያኒቱ ፍትሕ ርትዕ እኩልነት የሞላባት፣ መልካም አስተዳደር የሰፈነባት የእውነትና የሐቅ መገኛ እንድትኾን በመንፈሳዊነት፣ ታማኝነትና ተጠያቂነት የተደገፈ መጠነ ሰፊ የሥራ እንቅስቃሴ ማድረግን ይጨምራል፡፡ ‹‹እምነትና ሐቅ በቤተ ክርስቲያን ካልተገኙ ከየት ይገኛሉ?›› ሲሉ የጠየቁት ፓትርያርኩ፣ ካህናትና ቤተ ክርስቲያኒቱን በሞያቸውና በልግሥናቸው አቅፈው ደግፈው የያዙ ምእመናን የድርሻቸውን ለመወጣት ብርቱ ጥረት ማድረግ አለባቸው ማለታቸውም ይታወሳል፡፡
ከፕትርክና ሢመቱም በኋላ ለብዙኃን መገናኛዎች በሰጧቸው ቃለ ምልልሶች÷ ሰው ሊመሰገንም ሊሾምም፣ ሊሻርም፣ ሊወቀስም የሚገባው በጠባዩ፣ በግብረ ገብነቱ፣ በትምህርቱ ብቻ እየተመዘነ እንጂ በዘሩ አንወደውም አንጠላውም በማለት በቤተ ክርስቲያኒቱ አስተዳደር ውስጥ ሥር የሰደደ የመጠቃቀሚያ መንገድ ነው የሚባለውን በጎሰኝነት መሳሳብን ተቃውመዋል፡፡
ቤተ ክርስቲያኒቷ ታላቅ መኾኗንና ለታላቅነቷ የሚመጥኑ ሰዎች መገኘት እንዳለባቸው በአጽንዖት የተናገሩት ፓትርያርኩ፣ ‹‹የተሟላና የተቃና ሥራ ለመሥራት ከኹሉ አስቀድሞ ብቃትና ጥራት ያለው ሥራ መሥራት ያስፈልጋል፡፡ ለዚኽ ደግሞ ሰው በሰው ላይ መደራረብ ሳይኾን ትምህርትና ችሎታ ያለው፣ ለተመደበበት የሥራ ደረጃ የሚመጥን ሰው መቀመጥ አለበት፤›› ብለዋል፡፡
የቤተ ክህነቱ አስተዳደር ከላይ እስከ ታች ተስተካክሎ የመልካም ሥራ አብነት ይኾን ዘንድ ‹‹ሙስና ይጥፋ፤ ተጠያቂነትና ሐቀኝነት ይስፋፋ›› የሚለውን ዐዋጅ ደጋግመው በማሰማት እየታወቁ የመጡት ፓትርያርኩ፣ ቅ/ሲኖዶስ የቤተ ክርስቲያኒቱን ስም ለመጠበቅና ክብርዋን ለመመለስ ሊወስዳቸው ይገባል ያሏቸውን የለውጥ ርምጃዎች በመዘርዝር በምልዓተ ጉባኤው በአጀንዳነት አስይዘው ዐቢይ ውሳኔ ለማስወሰን አስችለዋል፡፡
ፓትርያርኩ ሥር ነቀል ለውጥን የሚያመጡና ቆራጥ አቋምን የሚሹ ናቸው ያሏቸው እኒህ ዐበይት ርምጃዎች÷ ብልሹ አሠራር በፀረ ሙስና እንቅስቃሴ የሚታረምበትና የሚወገድበት፣ የአስተዳደር መዋቅሩና የሚሠራባቸው ደንቦችና ሕጎች ግልጽነትና ተጠያቂነት እንዲኖራቸው ተደርገው የሚሻሻሉበት፣ የቤተ ክርስቲያኒቱ ራእይና ተልእኮ በግልጽ የሚታይበት ስትራተጅያዊ የአመራር ሥርዐት የሚነደፍበት፣ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት እስከ አጥቢያ ላለው የገንዘብ ፍሰትና አያያዝ አንድ ወጥ የኾነ ሥርዐት የሚዘረጋበት እንደኾነ አመልክተዋል፡፡
His Holiness Abune Mathias with thier Graces the Archbishops
ቅዱስነታቸው ከብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ጋራ
አቡነ ማትያስ፣ አሳፋሪና አሳዛኝ ነው ያሉት የአሠራር ብልሽት ሳይታረም ቢቀጥል ቤተ ክርስቲያኒቱ ለሚገጥማት አስከፊ ችግር ፓትርያርኩ ራሳቸውን ከተወቃሾች ተርታ በመቁጠር ቤተ ክርስቲያኒቱን የሚታደግና ችግሮቿን የሚቀርፍ አጀንዳ በመያዝ በእግዚአብሔር፣ በታሪክና በመጪው ትውልድ ፊት የሚመዘን ችግር ፈቺ ውሳኔ እንዲወሰን የቅ/ሲኖዶሱን አባላት አነሣስተዋል፡፡
ፓትርያርኩ ከሹመታቸው በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በርእሰ መንበርነት የመሩትና በግንቦት ወር 2005 ዓ.ም. በተካሔደው የቅ/ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በይፋ ባስታወቁት በዚኽ መግለጫቸው ላይ በመወያየት ቤተ ክርስቲያኒቱ ማኅበራዊና መንፈሳዊ ሥራዎቿን በመሪ ዕቅድ በመምራት ሙስናንና የመልካም አስተዳደር ዕጦትን ከሥሩ ለመቅረፍ የሚያስችል ጥናት የሚያቀርብ ከሊቃነ ጳጳሳት፣ ከሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ ከቤተ ክህነቱ የሥራ ሓላፊዎችና ከምሁራን ምእመናን የተውጣጣ ዐቢይ ኮሚቴ ተሠይሟል፡፡
ይኸው የቅ/ሲኖዶሱ የምልዓተ ጉባኤ ስብሰባ፣ የቤተ ክርስቲያኒቱ የአደረጃጀትና አሠራር ጥናት የሁሉም አህጉረ ስብከት ማእከልና የመንበረ ፓትርያርኩ መቀመጫ በኾነው በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት እንዲደረግ መመሪያ ሰጥቷል፤ ሀ/ስብከቱም በመዋቅርና አደረጃጀት፣ በሰው ሀብት አስተዳደር፣ በሒሳብ አሠራርና ቁጥጥር የሚታይበትን የገዘፈና የተመሰቃቀለ ችግሩን ለመፍታት የባለሞያ ቡድን አቋቁሞ በፍጥነት ወደ ተግባር መግባቱ ተዘግቧል፡፡
በመንበረ ፓትርያርክም በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ደረጃም የተቋቋሙት ሁለቱም አካላት የጥናት ውጤታቸውን በጥቅምት ወር 2006 ዓ.ም. ለተካሔደው የቅ/ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ አቅርበው በማስገምገም የወሳኝ አካሉን ይኹንታ ከማግኘታቸውም በላይ ቀጣይ የአፈጻጸም አቅጣጫ ተሰጥቷቸዋል፤ የመሪ ዕቅድ ማህቀፉን ያስገመገመው ዐቢይ ኮሚቴ በቀጣይ ዕቅዱን በሥራ ለመተርጎም በሚያስችል አኳኋን በዝርዝር አዘጋጅቶ እንዲያቀርብ መመሪያ ተሰጥቶታል፡፡
የአዲስ አበባ ሀ/ስብከትን የአደረጃጀትና የአሠራር ለውጥ ጥናት የሠራው የባለሞያ ቡድንም ጥናቱን ወደ ታች አውርዶ በካህናት፣ በምእመናንና በሰንበት ት/ቤት ወጣቶች በውይይት ካዳበረ በኋላ ለቋሚ ሲኖዶስ እንዲያቀርብና በቋሚ ሲኖዶሱ እንዲጸድቅ በምልዓተ ጉባኤው በተሰጠው የአፈጻጸም አቅጣጫ መሠረት ተግባሩን አከናውኖ በውይይቱ የብዙኃኑን ካህናትና ምእመናን ተቀባይነት ያረጋገጠውን የጥናት ሰነድ በሀ/ስብከቱ አማካይነት ለቅ/ሲኖዶሱ አስረክቧል፡፡
ከነገ በስቲያ ሰኞ፣ የካቲት 24 ቀን 2006 ዓ.ም. በሚከበረው አንደኛ ዓመት የበዓለ ሢመት ዋዜማቸው ላይ የሚገኙት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ፣ በቀጣዩ የሥራ ዘመናቸው የተናገሯቸውንና ተጠንቶ የቀረቡላቸውን በተግባር ለመተርጎም የሚንቀሳቀሱበት እንደሚኾን አዲስ አድማስ ያነጋገራቸው የቤተ ክርስቲያኒቱ ሓላፊዎች፣ አገልጋይ ካህናትና ምእመናን ተስፋቸውን ገልጸዋል፡፡
ቤተ ክህነቱ ያለበትን መሠረታዊ ተልእኮውን የማያገለግል የተንዛዛ ቢሮክራሲ፣ ወገንተኝነትና ሙስና በፓትርያርክ ደረጃ አምነውና ተቀብለው በዐደባባይ ገልጠው ለመናገር አቡነ ማትያስ የመጀመሪያው እንደኾኑ የተናገሩ አንድ አገልጋይ÷ የፓትርያርኩ ተደጋጋሚ መግለጫዎች በየአጥቢያቸው ችግሩን የሚጋፈጡ ወገኖችን በልዩ ልዩ መንገድ ለተቋማዊ ለውጥና ለፀረ ሙስና ትግል እንዳነሣሣ፣ ይህም ቢያንስ ብልሹ አሠራሩን ለሕገ ወጥ ጥቅም ያዋሉ አማሳኞችን እንዳሸማቀቀ ይገልጻሉ፡፡
ለዓመታት የተከማቸው የቤተ ክርስቲያኒቱ ዘርፈ ብዙ ችግር በአንድ ዓመት ተጠንቶ ሊታወቅ ይችል እንደኾነ እንጂ መፍትሔ ያገኛል ተብሎ እንደማይጠበቅ የጠቀሱት አገልጋዩ፣ አንድ ዓመት የፓትርያርኩን ስኬት ለመገምገም በቂ አይደለም ይላሉ፡፡ ፓትርያርኩ በጵጵስና ከተሾሙበት ጊዜ ጀምሮ ለሠላሳ ዓመታት በውጭ የነበሩ እንደመኾናቸው ቤተ ክህነቱን በበላይነት የመምራት ልምድ ሊያንሳቸው እንደሚችል ጠቁመው፣ ይህን ክፍተት የሚጠቀሙ ከቀድሞም የነበሩና ዛሬም ያልታጠፉ የጥፋት እጆችን ተጽዕኖ በፓትርያርኩ ዙሪያ እንደሚያስተውሉ ገልጸዋል፡፡ ለዚህም ፓትርያርኩ የሚያስጠጓቸውን አማካሪዎች ማንነት በጥንቃቄ መለየት እንደሚኖርባቸው አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
ስለ ፓትርያርኩ የአንድ ዓመት ጉዞ የተጠየቁትና ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ከፍተኛ የሥራ ሓላፊ፣ ፓትርያርኩ ከተሾሙበት ዕለት አንሥቶ ያስተጋቧቸውን የተቋማዊ ለውጥ ዕሴቶችና መርሖዎች ተግባራዊ ለማድረግ ዙሪያቸውን መፈተሽ አለባቸው የሚለውን አስተያየት የሚጋሩት ሓላፊው፣ ‹‹ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ያለው ኹኔታ ብቃት ያላቸውን እውነተኛ ባለሞያዎች ከፓትርያርኩ የሚያሸሽ እንጂ የሚያቀርብ አይደለም፤›› ይላሉ፡፡
የአስተዳደራዊ መዋቅር ማሻሻያ ሒደት የራሱ ተግዳሮቶች እንዳሉት የሚናገሩት የሥራ ሓላፊው፣ የአመራር ብቃትና ብስለት ተግዳሮቶቹን ለበጎ ለውጦ በመጠቀም እንደሚረጋገጥ ያስረዳሉ፡፡ ፓትርያርኩ ሥር ነቀልና ቆራጥ ተግባራዊ ርምጃ እወስዳለኹ ብለው በጀመሩት እንቅስቃሴ ተቃውሞ ሲገጥማቸው፣ ተቃውሞውን የማዳመጥ አባታዊ ሓላፊነት ቢኖርባቸውም ዋናውን የቅ/ሲኖዶሱን ውሳኔ ሳይቀር እስከማመቻመች መድረሳቸው የፀረ ሙስና አቋማቸው ራሳቸውን ከሚያስተዋውቅ የሚዲያ ፍጆታና ከንግግር ያላለፈ፣ የሚናገሩትንም ያህል ጠንካራና ጽኑ አቋም የሚይዙ ውሳኔ ሰጭ ናቸው ብለው እንዳያምኑ እንዳደረጋቸው አስረድተዋል፡፡ ይህም በውጤቱ የተቋማዊ ለውጥ ተቃዋሚዎቹን በማፈርጠምና የለውጥ ተስፋውን በማመንመን ሒደቱ ዳግመኛ እንዳይነሣ አድርጎ አደጋ ውስጥ ሊከተውና የቤተ ክርስቲያኒቱን ችግር የበለጠ ሊያወሳስበው እንደሚችል ስጋታቸውን ገልጸዋል፡፡
‹‹ለፓትርያርኩ የአቋም ጽናት የሊቃነ ጳጳሳቱ የአቋም አንድነት አስፈላጊ ነው፤›› የሚሉት ሌላው አስተያየት ሰጪ፣ አቡነ ማትያስ ከምንጊዜውም በላይ በቤተ ክህነቱ ላይ ተባብሶ የሚታየውን የተቋማዊ ለውጡን ሒደት የሚያደናቅፉ አላስፈላጊ ጣልቃ ገብነቶችን መቋቋምና የቅዱስ ሲኖዶሱን የውሳኔ ልዕልና ማስከበር እንደሚጠበቅባቸው ያሳስባሉ፡፡
ፓትርያርኩ በተመረጡበት ቀን ‹‹እግዚአብሔር ይህን ታላቅ ሓላፊነት እንዴት እችለዋለሁ? በል አንተ ታውቃለህ፤›› ማለታቸው በርግጥም የሚገባ ነው ያሉት እኚኹ አስተያየት ሰጪ፣ ታላቋንና ጥንታዊቷን ቤተ ክርስቲያን ርእሰ አበው ኾኖ ለመምራት የውስጥ ችግሩና የውጭ ተግዳሮቱ የበዛ ቢኾንም ቤተ ክርስቲያኒቱን ወደ ዕድገትና ስሉጥነት የሚያደርሰው ጎዳና በአቡነ ማትያስ ዘመነ ፕትርክና መጠረግና መደልደል ይገባዋል ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል፡፡

                                   በአውሮጳ   የካህናት አንድነት ማኅበር ሊቋቋም መሆኑ ታወቀ በ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከመላዋ አውሮጳ   የተውጣጡ ካህናት፡” የ...