በገለልተኛ አስተዳደር ስር የሚኖሩትን አጥቢያዎች ቁጥር በአንድ እንደሚቀንስ ይጠበቃል
- ‹‹እግዚአብሔር ቅዱስ ፍቃዱ ሆኖ ወደ
ህብረትና አንድነታችን አንደምንመለስ ትልቅ ተስፋ ነው ያለኝ፡፡›› ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ከ12 ዓመት በፊት ካደረጉት ቃለ መጠይቅ የተወሰደ

እንደሚታወቀው ይህ አጥቢያ በብፁዕነታቸው ከተመሰረተ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ” ገለልተኛ “ በሚባል አስተዳደር መቆየቱም ይታወሳል። በዚህ ታሪካዊ የብፁዕነታቸው ጉዞም ይህንን አጥቢያ ወደ እናት ቤተክርስቲያን አስተዳደር እንደሚመልሱት እና በቀጥታ በቅዱስ ሲኖዶስ በሚሾመው ሊቀ ጳጳስ እንደሚተዳደር ይጠበቃል። በዚህም በዋሺንግተን ዲሲ አካባቢ በገለልተኛ አስተዳደር ስር የሚኖሩትን አጥቢያዎች ቁጥር በአንድ እንደሚቀንስ እና መልካም እርምጃ እንደሚሆን ይጠበቃል። ሌሎችስ በአሜሪካ እና በተለያዩ የአውሮፓ ምድር ራሳቸውን ገለልተኛ ብለው የሚገኙ የአብያ ክርስቲያናት አስተዳዳሪዎች ምን ይማሩ ይሆን? ከዚች ከአንዲት ቤተክርስቲያን ተገሎ እስከመቼ ይኖራል? እንደ ብዙዎች ምዕመናን አስተያየት ወደፊት እግዚአብሔር በፈቀደው ቀን በውጭ ሀገር የተመሰረተው ሲኖዶስ ከአዲስ አበባው ቅዱስ ሲኖዶስ ጋር እንደሚቀላቀል እና አንድ እንደሚሆን እምነታው ነው ፤ የዛኔ ደግሞ አሁን ላይ ራሳቸውን ገለልተኛ ብለው የተቀመጡት ሌላ ፈተና ይሆናሉ ብለው ሃሳባቸውን ይገልጻሉ ፡፡ ዛሬም በነ አቶ ወይም ዶክተር እከሌ መመራት ወይስ ቀደምት አባቶቻችን በሰሩልን ሥርዓት መቀጠል? እኛ እኮ አባቶቻችን የሰሩልን የእምነት ስርዓት አስቀጣይ እንጂ እንደ አዲስ ጀማሪ መሆን መቻል የለብንም………ይህ መልካም ጅምር ነው ! ቸር ያሰማን
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ