ስለ እጨጌ
እንባቆም የመናዊ ጽሁፍ አቅራቢዎች ሊቃውንትን እናስባቸው
የሚል መርሃግብር ተካሄደ
እጨጌ እንባቆም
የመናዊ በተመለከተ የተካሄደው መርሃ ግብር በእጨጌ እንባቆም የሕይወት
ታሪክና የተረጎማቸውን መጻሕፍትን እና በታላቁ በደብረ ሊባኖስ ገዳም ለሁለት ጊዜ እጨጌ ሆኖ ማገልገሉን በቀረበው ጽሁፉ ተጠቅሶአል፡፡ እጨጌ እንባቆም ትውልዱ የመን ሲሆን የእስልምና ሃማኖት ተከታይ
የነበረና በእመቤታችን አማካይነት ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ከተማረ በኋላ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖትን ተቀብሎ ብዙ መጻሕፍትን ከአረቢኛ
ወደ ግዕዝ ተርጉሞአል ከእነዚህም መካከል የቅዱስ ጳውሎስን መልእክት
ወደ እብራውን፤ መጽሐፈ በረላም ወይዋስፍ ኦሪት ዘፍጥረትን፤አረጋዊ መንፈሳዊን ከአረብኛ ወደ ግዕዝ ተርጉሞአል፡፡መጽሐፈ ቄደር አቡሻኸርን የጻፈ ሲሆን አንቀጸ አሚን የሚባል መጽሐፍ ለአህመድ ግራን መልስ ይሆን
ዘንድ በዘመኑ ጽፎአል፡፡ እጨጌ እንባቆም 14 የተለያዩ ቋንቋዎችን ይናገራል፡፡ የዚህ ታላቅ ጻድቅ ገድሉ በደብረ ሊባኖስ ገዳምና
ጎንደር ብቻ ለጊዜው ተገኝቶአል ፡፡ ኅዳር 25 ቀን በደብረ ሊባኖስ ገዳም እጨጌ ሆኖ የተሾመበት ዕለት ነው ፡፤ዘመኑም በ16ኛው
መ/ክ ነው፡፡ እጨጌ እንባቆም በ1482 ዓ.ም ከየመን ወደ ኢትዮጵያ የመጣ ሲሆን በ1488 ዓ.ም ደብረ ሊባኖስ ገዳም ገብቶ ምንኖ
ይኖር ነበር፡፡ እጨጌ እንባቆም በጸሎትና በሥርዓተ ቤተ ክርስቲን የጸና አቅዋም እንደ ነበረው በቀረበው ጽሁፍ ተገልጦአል፡፤ በተለይ
በምዕራብ ሸዋ እና በአጠቃላይ ወለጋ አካባቢ በስፋት ያስተማረ ጻድቅ ነው፡፡ በ1553 ዓ.ም በ141 ዓመቱ አርፎ በደብረ ሊባኖስ ገዳም ተቀብሮአል ፡፡‹‹ይህ
ሊቃውንትን እናስባቸው ››መርሃ ግብር የተዘጋጀው ዲ/ን ዳንኤል ክብረትና በደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም ምክሐ ደናግል
ሰ/ት/ቤት ጋር በመተባበር ሲሆን ጽሁፉን ያቀረቡት መጋቤ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ፤ ዲ/ን ዳንኤል ክብረት፤ ዲ/ን አባይነህ ካሴ፤
መ/ር ኃይለማርያም አያሌው ሲሆኑ ቀሲስ መንግስቱ ጎበዜ ደግሞ አወያይ ነበሩ ፡፡ቦታው ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም ሰ/ት/ቤት
ሲሆን ተኅሳስ 27 /2006 ዓ.ም ስለጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ጥናታዊ ጽሁፍ እንደሚቀርብም ተገልጦ ጥሪ ተላልፎአል፡፡
ye tsadik metasebiya le zelalem tinoralech!!!
ምላሽ ይስጡሰርዝ