ሰበር ዜና – የመስቀል ደመራ ክብረ በዓል የመጀመሪያው የኢትዮጵያ የዓለም መንፈሳዊ ቅርስ ኾኖ በዩኔስኮ ተመዘገበ
(ሪፖርተር፤ ኅዳር ፳፮ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም.)
ኄኖክ ያሬድ
ስለ ቅርሱ የመረመረው ኮሚቴ ባቀረበው ውሳኔ ሐሳብ ላይ እንደተመለከተው፣የመስቀል ክብረ በዓል የኢትዮጵያን ሃይማኖታዊና ባህላዊ ትውፊቶችን የያዘ፣ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ መምጣቱና በአገሪቱ ማኅበራዊ አንድነትንና የርስ በርስ ትስስርን፣ ብዝኃነትንም የሚያንጸባርቅ፣ በበርካታ ብሔረሰቦች ባህሎች መካከል ትስስርን የፈጠረ በመኾኑ ዓለም አቀፍ መስፈርቱን አሟልቷል ብሎታል፡፡
የዩኔስኮ ኮሚቴው በረቡዕ ስብሰባ ውሎው ከመስቀል ሌላ ከተለያዩ አገሮች 13 መንፈሳዊ ባህላዊ ቅርሶችን በሰው ዘር ቅርስነት መመዝገቡንም በድረ ገጹ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡ መስቀልን ጨምሮ እ.ኤ.አ. በ2013 የተመረጡትን የ14ቱ መንፈሳዊ ባህላዊ ቅርሶች ገጽታ የሚያሳዩ ቪዲዮዎችና ፎቶዎችም በዕለቱ በድረ ገጹ ላይ መለቀቃቸው ታውቋል፡፡
በየዓመቱ መስከረም 17 ቀን በመላ አገሪቱ በአደባባይ ደመራ የሚከበረው የመስቀል ክብረ በዓል የመጀመርያው መንፈሳዊ (ኢንታንጅብል) ባህላዊ ቅርስ ኾኖ በዩኔስኮ የተመዘገበላት ኢትዮጵያ፣ ዘጠኝ ግዙፍ (ታንጀብል) ቅርሶች ማስመዝገቧ ይታወቃል፡፡
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ