|
መጋቢት 17 ቀን 2006 ዓ.ም.
የቀድሞ ስማቸው አባ መዘምር ተገኝ የአሁኑ ብፁዕ አቡነ ቶማስ ጥር 14 ቀን 1932 ዓ.ም ጎጃም ደጋ ዳሞት ዝቋላ አርባዕቱ እንስሳ ተወለዱ፡፡ መሠረታዊ የቤተ ክርስቲያን ትምህርትን በሚገባ ከተማሩ በኋላ ጸዋትወ ዜማን ከመሪጌታ አንዱዓለምና መሪጌታ ካሣ ይልማ ፣ ቅኔ ከመሪጌታ ፈንቴ /ዋሸራ/፣ መጻሕፍተ ሐዲሳትን ከመሪጌታ ብርሃኑ ወልደ ሥላሴ ፣ መጻሕፍተ ሊቃውንትን ከመሪጌታ ቢረሳ ደስታ ተምረዋል፡፡ በዘመናዊ ትምህርትም እስከ 6ኛ ክፍል ፣ የእንግሊዝኛን ቋንቋ በግላቸው የተማሩና የመኪና ጽሕፈት /type writing/ የሚያውቁ ነበሩ፡፡ ብፁዕ አቡነ ቶማስ ዲቁና ከአቡነ ማርቆስ፣ ቅስና ከአቡነ ባስልዮስ፣ ቁምስና ከብፁዕ አቡነ ተክለሃይማኖት ተቀብለዋል፡፡
ብፁዕነታቸው ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ የምእራብ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በመሆን ሲያገለግሉ ቆይተው፤ ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው መጋቢት 16 ቀን 2006 ዓ.ም መንበረ ጵጵስናቸው በሚገኝበት በፍኖተ ሠላም ከተማ ዐርፈዋል፡፡ ሥርዓተ ቀብራቸውም በዚያው በፍኖተ ሰላም እንደሚፈጸም ይጠበቃል፡፡
የአባታችንን ነፍስ በአብርሃምና በይስሐቅ እቅፍ ያኑረልን፡፡
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ