መስከረም 27 ቀን 2007 ዓ.ም.
እንዳለ ደምስስ
የጅማ ሀገረ ስብከት ያስገነባው ባለ 5 ፎቅ ሁለገብ ዘመናዊ ሕንፃ መስከረም 25 ቀን 2007 ዓ.ም. በቅዱስ ፓትርያርኩና በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዚዳንት ተመረቀ፡፡
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ከብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፤ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት የልዩ ልዩ መምሪያ ሓላፊዎችና ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ክፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር በመሆን የጅማ ሀገረ ስብከት ከሃያ ስምንት ሚሊዮን አምስት መቶ አራት ሺሕ ብር በላይ በሆነ ወጪ ያስገነባውን ባለ አምስት ፎቅ ዘመናዊ ሁለገብ ሕንፃ ባርከው ሲመርቁ በሰጡት ቃለ ምእዳን “ይህ ሁለገብ ዘመናዊ ሕንፃ በጣም የሚያስደንቅና ለቤተ ክርስቲያናችን ተጨማሪ ሀብት መሆን የቻለ ነው፡፡ ለሌሎች ሀገረ ስብከቶችም ታላቅ ምሳሌና በአርአያነቱም ተጠቃሽ የሚሆን ነው” ብለዋል፡፡
የጅማ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ባቀረቡት ሪፖርትም በጅማ ሀገረ ስብከት 308 አብያተ ክርስቲያናት እንደሚገኙና፤ የዚህ ሕንፃ መገንባት ዋነኛ ዓላማ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት አብያተ ክርስቲያናት በካህናትና በበጀት እጥረት ምክንያት የተቸገሩ በመሆናቸው ሕንፃው ተከራይቶ በሚያስገኘው ገቢ እነዚህን አብያተ ክርስቲያናት በመደገፍ አገልግሎት እንዳይቋረጥ ለማስቻል እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
ዝርዝሩንእንደደረሰልን እናቀርባለን፡፡
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ