ጥምቀት በኖርዌይ ስታቨንገር 2010 |
የጥምቀት በዓል በኖርዌይ
በስደት ሆኖ በተለይ በዓላትን ማክበር በጣም ከባድ ነው ይህንን ከባድ ችግር የሚያውቁት የቤተ ክርስቲያኑ አገልጋዮች
ካህናትና የሰበካ ጉባኤ አባላት እንዲሁም የተወሰኑት በአገልግልቱ ጠለቅ ብለው የሚያገለግሉ ምእመናን ናቸው። በተለይ የአደባባይ በዓላትን
ማለትም እንደ ጥምቀትና የመስቀል ደመራበዓላትን ማክበር በጣም ከባድ ከሚያደርጋቸው ነገሮች መካከል በተለይ እንደ ሰሜን አውሮፓ ሀገሮች አካባቢ
በጥምቀት በዓል ወቅት ያለው ቅዝቃዜ ተዉኝ ላላየ ሰው በጽሑፍ መግለጥ ከባድ
ነው ታቦታቱን አክብሮ አይደለም በአደባባይ አዳራሽ ውስጥ እንኳን ይዞ መውጣት እንዴት ይከብዳል ? ሌላው በተለይ በርከት ያሉ ሕዝበ ክርስቲያን
ያሉባቸው አካባቢሆች ደግሞ ለዚያ ሁሉ የሚሆን አዳራሽ ማግኘቱ ሌላ
ስደት ይሆናል ስንቱ ይነገራል
የዘንድሮውን የጥምቀት በዓል አዘጋጅ በስታቨንገር ደብረ ገነት
መድኃኔዓለም ወኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ናት። በኖርዌይ የጥምቀት
በዓል በአንድነት ማክበር ከተጀመረ ሰባት ዓመቱን አስቆጥሮአል
፡በስታቨንገር ደብረ ገነት መድኃኔዓለም ወኪዳነ ምሕረት
፡ክርስቲያን ሳንድ ቅድስት ማርያም
፡በርገን ቅዱስ ሚካኤል
፡ትሮንዳሄም ቅዱስ ጊዮርጊስ አቢያተ ክርስቲያናት በጋራ የጥምቀት በዓልን ያከብራሉ ። የዘንድሮው የትምቀት በዓል ላይ
እኔም ተገኝቼ ነበር በጣም ደስ ይል ነበር በተለይ በስደት ደግሞ ደስታው እጥፍ ይሆናል፡፤
የቅኔው መምህር መጋቤ ምሥጢር አባ ቴዎድሮስ ቅኔ ሲያደርጉ |
ስታቫንገር ከሌሎች የኖርዌይ ከተሞች የአየር ፀባይዋ የተሻለ
ነው ቅዝቃዜው ብዙ አይደለም። ዘንድሮ ግን የጥምቀት በዓልን ለማክበር ይመስላል ከተማዋ በበረዶ ተሸፍናለች ፈረንጆቹ የገና በዓላቸውን
ሲያከብሩ በረዶ እንዲወርድ ይጸልያሉ በዓሉ በበረዶ ተሸፍኖ ሲውል ደስ ይላቸዋል ያንን የለመደ የአየር ፀባይ የኛንም የጥምቀት በዓል
ሰዉ ብቻ ሳይሆን ምድሯ ሳይቀር ነጭ ለብሳ ውላለች የደብሩ አስተዳዳሪ እና የስካንድኖቭያ ቤተ ክህነት ዋና ጸሐፊ መጋቤ ምሥጢር
አባ ቴዎድሮስ የበዓሉ አዘጋጅ ናቸው ።መጋቤ ምሥጢር አባ ቴዎድሮስ በማስተባበር በመሳሰሉት መንፈሳዊ አገልግሎት ገና ከአዲስ አበባ ጀምሮ በሁሉ አባቶች ዘንድ
ይታወቃሉ። በኖርዌይ የዘንድሮውንም የጥምቀት በዓል የአዲስ አበባን ጃንሆይ
ሜዳ እስኪመስ ድረስ ነው ዝግጅቱ ካህናቱም ከአሜሪካ ፡ ከጀርመን እና ከዚያው ከኖርዌይ ከተለያዩ ከተሞች በመሰባሰብ ተከብሯል በማያያዝም የራሳችንን ቤተ ክርስቲያን መግዛት ይገባናል በማለት በመጋቤ
ምሥጢር አባ ቴዎድሮስ አስተባባሪነት አንድ ሚልዮን ክሮነር ለመስጠት ሕዝቡ ቃል ገብቶአል። በቅርብ ጊዜ ወስጥ ቤተ ክርስቲያን እንደሚገዛም
ይጠበቃል ፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በመላው አውሮፓ በየ አቅራቢያው ያሉት አቢያተ ክርስቲያናት በጋራ የጥምቀትን በዓል በጋራ በአንድነት
ማክበሩ እየተለመደ መምጣቱእየጎላ መጥቶአልና ሊበረታታ ይገባል።
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ