በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ መሠረት የሚቀርቡ መንፈሳዊ ትምህርቶች ፤መረጃዎች እና የመሳሰሉት የሚስተናገዱበት ገጽ ነው
2015 ሴፕቴምበር 18, ዓርብ
2015 ሴፕቴምበር 9, ረቡዕ
ወሪድዬ ብሄረ ሮሜ /ቅዱስ ያሬድ/
ካታኮምፕ
ቅዱስ ጳውሎስ የታሠረበት
ቅዱስ ጳውሎስ የታሠረበት
የቅዱሳን የተጋድሎ አደባባይ ፡ ሐዋርያት ስለ ሃይማኖታቸው እውነትን መስክረው
አንገታቸውን ለሠይፍ የሰጡባት
የተሰቀሉባት የቅዱሳን በአት የጸሎት ዋሻቸው
የተዋሕዶ ሃይማኖት የኪነ ጥበብ
ምድር የነበረች ዛሬም እንኳን ያ ሁሉ የቅዱሳን የገድል ውጤት የሚታይባት
የዓለም ጎብኚዎች የሚተሙባት ምድረ ሮሜን
በመንፈስ ተመርቶ በርቀት ተመልክቶ
ወደ ሮሜ ወረድኩ ወርጄ ስለቤተ ክርስቲያን
ተናገርኩ በማለት ቅዱስ ያሬድ ተናገረ እኔም “ በከመ ሰማዕነ ከማሁ ርኢነ “ እንደ ሰማን እንዲሁ ተመለከትን” ተብሎ እንደ ተጻፈ ቅዱስ ጳውሎስ አንገቱን የተሰየፈበት ቅዱስ ጴጥሮስ ቁልቁል
የተሰቀለበት የቅዱሳን በአት የጸሎት ዋሻቸው “ ካታኮምፕ “ የወቅቱ
ነገሥታት ቅዱሳኑን ከአንበሳ ጋር ያታገሉበት ቦታ ምን አደከማችሁ የቅዱሳን የተጋድሎ አደባባይ
ነበረች ሮማ የዛሬውን አያድርገውና፤፤ ሰሞኑን እያየሁ
ነበረ የቱሪስቱ ሰልፍ ለካ ! የትም ሀገር
ሰልፍ አይቀሬ ነው ዓይነቱ ይለያያል እንጂ አልኩና ዕድሜና
ጤንነት ለወንድም በለጠ እና ለባለቤቱ ቤተልሔም እየተመኘሁ ከእነሱ ጋር በመዘዋወር በጽሁፍ ያነበብኩትን
በዓይኔ ተመለከትኩ የሮማንንም ካቶሊክ ላመሰግን ወደድኩ /ባቲካንን/ ለምንም ይሁን ለምን በጥንቃቄ ይዛ
ታስጎበኛለች እኛ ብንሆን እስከ ዛሬ አንጠብቀውም
ይልቁንም የሚሸጠውን እንሸጠው ነበረ ። ሀገራችን ብዙ የቅዱሳን ቦታዎች አሉ ግን በአግባቡ አልያዝናቸውም የቅዱሳኑ ቦታ በሙሉ በሌሎች ተይዞ ሲታይ ያሳዝናል ፤፤ ጌታችን ቅዱስ ጳውሎስን እንዲህ በማለት ወደ ሮሜ ልኮታል
“አስተርአዮ እግዚእነ ለጳውሎስ ወይቤሎ ተአመን በከመ ኮንከኒ ሰማእትዬ በኢየሩሳሌም ከማሁ ሀለውከ ትኩነኒ ሰማእትዬ በሮሜሂ “
ሥራ 23. 11
ጳውሎስ ሆይ በኢየሩሳሌም ስለ እኔ እንደ መሰከርህ እንዲሁ በሮሜም ትመሰክርልኝ ዘንድ ይገባልና አይዞህ አለው ።
ይህ የጌታችንን ጥሪ በደስታ የተቀበለው ቅዱስ ጳውሎስ ሄዶ መከራን በመቀበሉ ዛሬ ሮማውያን የሱን የገድል
ውጤት ኢያሳዩ /ኢያስጎበኙ ይኖራሉ ።
ለአንክሮ
Ø የባቲካን የቅዱሳኑን ቦታዎችን አክብራ ለቱሪስት ምቹ
አድርጋ መጠቀሟ
Ø ከተማዋ
/ሮም ማለቴ ነው በሙሉ የጥንት ሃይማኖታዊ መልኳን ሳትለውጥ መቀጠሏ
ማሳሰቢያ
Ø ኢትዮጵያውያን በሮማ ላላችሁ
ሁላችሁም በሮማ ከተማ ያለውን ታሪካዊ የቅዱሳንን ቦታዎች ያላያሁ
ትኖራላችሁና እንድታዩት አሳስባለሁ። በሮሜ ላላችሁ ሁሉ ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ
ይሁን ። ሮሜ . ፩ ፡ ፯
2015 ሴፕቴምበር 5, ቅዳሜ
የደቡብ ምሥራቅ እና ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት ፪ኛ ዙር ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔውን ትናንት ጀመረ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የደቡብ ምሥራቅ እና ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት የ፪ኛ ዙር ዓመታዊ ጠቅላላ
ጉባዔውን
ነሐሴ 29 /2007 ዓ ሞ እንደሚጀምር ታወቀ
በጀርመን ፍራንክፈርት ለ፫ ቀናት በሚደረገው ጠቅላላ ጉባዔ ላይ በሀገረ ስብከቱ የሚገኙ ከ30 በላይ የሚሆኑ የአድባራት አስተዳዳሪዎች ፤ በማኅበረቅዱሳን የአውሮፓ ማእከል ተወካዮች ምእመናን እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ይሳተፋሉ . ጉባዔው ዓመታዊ የአድባራት አገልግሎት አፈጻጸም ሪፖርት እና የቀጣይ ዓመት ዕቅድ ላይ የሚወያይ ሲሆን በገለልተኛ አቢያተክርስቲያናት ጉዳይም ጠቅላላ ጉባዔው አንድ ውሳኔ እንደሚወስን ይጠበቃል ጠቅላላ ጉባዔውን አስመልክቶ በፍራንክፈርት የሚገን አንድ ጋዜጣ እንደ ዘገበው የከተማዋ ከንቲባ በተጋባዥነት በጉባዔው እንደ ሚገኙና የሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ የአቡነ ሙሴ መንበረ ጵጵስና ለአገልግሎት ምቹ ይሆን ዘንድ ጠቅሶ በከተማችን በንበረ ጵጵስና መኖሩ እድለኞች ያደርገናል ሲል ዘግቧ በመጨረሻም በሀገረ ስብከቱ ከፍተኛ የአገልግሎት አፈጻጸም ያገኙ አስተዳዳሪዎች በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሙሴ ሽልማት እንደሚበረከትላቸው ለማወቅ ተችሏል በሊቀ ጳጳሱ አቡነ ሙሴ በማግባባት ላይ የተመሠረተ መንፈሳዊ የማስተዳደር ጥበብ የተነሳ ሀገረ ስብከቱ ሰላማዊና አድባራቱ የራሳቸው ቤተ ክርስቲያን እንዲኖራቸው የሚደረገው እንቅስቃሴ ምስክር ነው በቅርቡ የራሳቸው ቤተ ክርስቲያን ለመግዛት ዝግጅታቸውን ያጠናቀቁ የሙኒክ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤልን የሚጠቀሱ ሲሆን የበርሊን ደብረ ገነት አማኑኤል ቤተ ክርስቲያን ደግሞ የራሳቸውን ቤተ ክርስቲያን ገዝተዋል ሌሎቹም ከፍተኛ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ እንደሚገኙ የሀገረ ስብከቱ ያመለክታል
በጀርመን ፍራንክፈርት ለ፫ ቀናት በሚደረገው ጠቅላላ ጉባዔ ላይ በሀገረ ስብከቱ የሚገኙ ከ30 በላይ የሚሆኑ የአድባራት አስተዳዳሪዎች ፤ በማኅበረቅዱሳን የአውሮፓ ማእከል ተወካዮች ምእመናን እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ይሳተፋሉ . ጉባዔው ዓመታዊ የአድባራት አገልግሎት አፈጻጸም ሪፖርት እና የቀጣይ ዓመት ዕቅድ ላይ የሚወያይ ሲሆን በገለልተኛ አቢያተክርስቲያናት ጉዳይም ጠቅላላ ጉባዔው አንድ ውሳኔ እንደሚወስን ይጠበቃል ጠቅላላ ጉባዔውን አስመልክቶ በፍራንክፈርት የሚገን አንድ ጋዜጣ እንደ ዘገበው የከተማዋ ከንቲባ በተጋባዥነት በጉባዔው እንደ ሚገኙና የሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ የአቡነ ሙሴ መንበረ ጵጵስና ለአገልግሎት ምቹ ይሆን ዘንድ ጠቅሶ በከተማችን በንበረ ጵጵስና መኖሩ እድለኞች ያደርገናል ሲል ዘግቧ በመጨረሻም በሀገረ ስብከቱ ከፍተኛ የአገልግሎት አፈጻጸም ያገኙ አስተዳዳሪዎች በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሙሴ ሽልማት እንደሚበረከትላቸው ለማወቅ ተችሏል በሊቀ ጳጳሱ አቡነ ሙሴ በማግባባት ላይ የተመሠረተ መንፈሳዊ የማስተዳደር ጥበብ የተነሳ ሀገረ ስብከቱ ሰላማዊና አድባራቱ የራሳቸው ቤተ ክርስቲያን እንዲኖራቸው የሚደረገው እንቅስቃሴ ምስክር ነው በቅርቡ የራሳቸው ቤተ ክርስቲያን ለመግዛት ዝግጅታቸውን ያጠናቀቁ የሙኒክ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤልን የሚጠቀሱ ሲሆን የበርሊን ደብረ ገነት አማኑኤል ቤተ ክርስቲያን ደግሞ የራሳቸውን ቤተ ክርስቲያን ገዝተዋል ሌሎቹም ከፍተኛ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ እንደሚገኙ የሀገረ ስብከቱ ያመለክታል
2015 ኦገስት 25, ማክሰኞ
ሁለተኛው ስደትና መፍትሔው
ሰዎች ከአንዱ ሀገር ወደ ሌላው ሀገር በስደት መዘዋወሩ
በጎላ በተረዳ
ይታወቃል ። ይሁን እንጂ ታዲያ የሚያሳዝነው ስደቱን እጥፍ የሚያደርገው የመንፈሳዊ አገልግሎት ፤የማኅሌቱ፤ የቅዳሴው
፤ የስብከተ ወንጌሉ እና የመሳሰለው መንፈሳዊ አገልግሎት መተግበሪያ
/ መገልገያ ቤተክርስቲያን አለመኖሩ ነው ። ምንም እንኩዋን በአውሮጳ
/ፓ የሉተራውያን የካቶሊካወያን አቢያተ እምነታት በሙሉ የተዘጉ እና
የእምነቱ ተከታዮች ሁሉን ነገር ትተውታል ። እጅግ በሚያስደንቅ ጥበብ የታንጹ አቢያተ እምነቶቻቸው በጣም ያሳዝናሉ ። ጥቂት የሚሆኑ
የእምነቱ ተከታዮች አረጋወያን በቻ እሁድ ረፋድ ላይ ይገኛሉ ። በስደት የሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን መእመናን በየአካባቢያችው ይህንኑ
ቤተ እምነት አስፈቅደው ይገለግሉበታል አንዳንዶቹም አቅሙ ያላቸው ውርሃዊ ክፍያ በመክፈል ይክራዩታል። ይህንን ማድረግ ያልቻሉ ግን እሁድ ጠዋት
ሲከፈት ገብተው ቶሎ ቶሎ ብለው ቅዳሴውን ቀድሰው ንዋዬ ቅዱሳቱን
ይዘው ይወጣሉ ። ነሐሴ ኪዳነ ምሕረት የእመቤታችንን በዓለ ዕርገት
ለማክበር ከሐምቡርግ ፍራንክፈርት አቅራቢያ ወደ ምትገኝ ሐመረ ኖህ ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን ተጓዝን በዓሉ
የተከበረው ነሓሴ 17 ነበረ ቅዳሴው በብፁዕ
አቡነ ሙሴ የደቡብ መዕራብና ምሥራቅ አውሮጳ/ፓ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳሳት ኢየተመራ እያለ ሰዓት ደረሰ ቶሎ ታቦቱ ወጥቶ ቶሎ መግባት
አለበት ስለተባለ ቶሎ ቶሎ ታቦተ ድንግል ማርያም ቶሎ ቶል ተብሎ ወጥቶ ቶሎ ተመልሶአል ወዲያውኑ ምንጣፉን መጋረጃውን የመሳሰሉትን ንዋዬ ቅዱሳቱን ሰብስቦ መሮጥ ነው ።ይህኛውስ ስደት መፍትሔው
ምንድንነው?
ብቸኛው አማራጭ የሉተራውያንን አቢያተ ክርስቲያናትን መግዛት
ይህንን ለማድረግ የሚያስፈልገው አንደኛ ስለቤተ ክርስቲያን ጉዳይ በሚገባ የተረዳ በእምነቱ ጠንካራ የሆነ ምእመን፤ ማለትም
መሰረታዊ የሃይማኖታችንን ትምህርት በሚገባ የተገነዘበ ለወደፊቱ ለልጆቹ በትኩረት የሚያስብ ያይማኖታዊ ዕቅድ ያለውና ምእመናኑን
በማስተማር፤ በማስተባበር ጥሩ ምሳሌ የሚሆን የሕዝቡን መሰረታዊ ችግር
ተረድቶ መፍትሔ የሚፈልግ አስተዳዳሪ ካለ በቀላሉ መግዛት ይቻላል ። ለዚህ ጥሩ ምሳሌ መላከ ገነት ቆሞስ አባ ብርሃነ
መስቀል የበርሊን ደብረ ገነት አማኑኤል ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ
ከፍተኛ እንቅስቃሴ የሕዝቡ ተሳትፎ ያመጣው ውጤት በበርሊን ደረጃውን የጠበቀ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን መግዛታችው ትልቅ የምሥራች
ነው ። መላክ ገነት አባ ብርሃን መስቀልን ምስጋና ይገባቸዋል ። የሙኒክ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ከርስቲያን የመግዝት እንቅስቃሴም በመፋጠን ላይ ይገኛል። የሀገረ ስብከቱም
ሊቀ ጳጳስ አቡነ ሙሴ ከሀገረ ሰብከቱ ሠራተኞች ፤ የአድባራት አስተዳዳሪዎች
በማኅበረ ቅዱሳን አውሮጳ/ፓ ማዕከል ፤ ምእመናንን በማስተባበር ውጤታማ ሥራ በመሥራት ላይ ይገኛሉ።
ይሁን እንጂ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለዚህ ሁሉ ጅምር በጎ
አገልግሎት በተለይ በአውሮጳ/ፓ እንቅፋት እየሆነ የመጣው እንፈውሳለን
፤ እናጠምቃለን ባሕታውያን ነን የሚሉ ገለሰቦች ለበጎ ነገር በአንድነት ተባብሮ ያገለግል ይገለገል የነበረውን ዳግመኛ እንዳይስማማ አድርገው በመከፋፈል ላይ መገኘታቸውና ሕዝቡም ያለ ማስተዋል
መከተሉ ትልቅ ችግር ሆኖ ይታያል ፡፤ ከዚህ በተረፈ ግን የራሳችንን ቤተ ክርስቲያን የመግዛቱን ነገር በትኩረት መመልከት ይገባል
። እግዚአብሔር ይርዳን ።
ማስገንዘቢያ ሁለቱ የሉተራን ቤተ እምነት ናቸው
2015 ኦገስት 24, ሰኞ
ሀገሬን ከሀገሬ ውጪ አገኘኋት
ሐምቡርግ
ዩኒቨርስቲ
ከሀገር ሲወጣ ያየውን ሁሉ ከሀገሩ ጋር በማወዳደር ይህን ሀገሬ ቢኖራት እያሉ መመኘት ልማድ ነው ። እኔም በተለያዩ የኣውሮጳ/ፓ
ሀገራት ለአገልግሎት ስዘዋወር እንዲሁ መመኘቴ አልቀረም ይሁን እንጂ ግን ሀገሬን ከሀገሬ ውጪ አገኘኋት ያልኩበት ነገሩ
እንዲህ ነው ። ዐርብ ጠዋት ከጀርመን ዋና ከተማ በርሊን ተነስተን ከመላከ
ገነት ቆሞስ አባ ብርሃነ መስቀል የበርሊን ደብረ ገነት አማኑኤል
ቤተ ክርስቲያንና የሐምቡርግ ደብረ መድኃኒት ኪዳነምሕረት አብያተ ክርስቲያናት አስተዳዳሪ ጋር ነሐሴ 1የእመቤታችንን በዓለ ዕርገት ለማክበር ወደ
ሐምቡርግ ከተማ አመራን ዕድሜ ለቤተክርስቲያን ልጆች ተቀበሉን እንደሰማችሁ /እንዳያችሁት ሐምቡርግ ሲነሳ የሐምቡርግ ዩኒቨርስቲ መነሳቱ አይቀሬ ነው ። እኔም ከታላቁ ሊቅ መጋቤ ስብሐት ተክሌ ሲራክ ጋር በመሆን ሐምቡርግ ዩኒቨርስቲን መጎብኘት ጀመርን ዕድሜና ጤንነት
ለዶ/ር ጌቴ ገላዬ በጀርመን ሐምቡርግ ዩኒቨርስቲ የአማርኛ
ቛንቛ ሥነ ጽሑፍ እና የአፍሪቃ ሥነ ቃል መምህር ናቸው በተለይ ስለገራችን ባህልና ቛንቛዎች ጉዳይ እያነሱ ብዙ
ሥራ ባለመሰራቱ እየተቃጠሉ ይኖራሉ። በቁጭት ቃላት እያብራሩ
የአፍሪቃና የኢትዮጵያ ቛንቛዎች እና ባህል ጥናት ክፍ ል
ጀምረን ጉብኝታችንን ቀጠልን ምን ልበላችሁ! የሀገራችንን ቛንቛ ባህል ከፍተኛ
ትኩረትና ክብር ተሰጥቶ በዚሁ ክፍል የሚማሩ ሩሲያውያንና የሌሎች
ሀገሮች ዜጎች ፈረንጆች በኢትዮጵያ ቛንቛዎችና ባህል እንዲሁም በቅዱሳን ገድላት ላይ ጥናት ሲያደርጉ የግዕዝ መዝገበ
ቃላት ጥናት
ሲያደርጉ በየቢሮአቸው የኢትዮጵያ ባህልና ገዳማትን የሚገልጡ
ፎቶዎችን በመለጠፍ አማርኛ ቛንቛ ሲናገሩ
ስመለከት ሀገሬን ከሀገሬ ወጪ አገኘኋት አልኩ አለመታደል ሆኖ እኛ ለሃይማኖታችን
ለባህላችን የኛ ለምንናቸው ሁሉ ትኩረት አለመስጠታችን ሀገራችን ከሀገራችን ውጪ ትገኛለች። ሀገር ማለት ሃይማኖት ከነሥርዓቱ ፤የሕዝቡ ባህልና አለባበስ በዓላትና አከባበራቸው ወዘተ .... ማለት ነው እነዚህ ከተሰደዱ ሀገሪቷ ከሀገር ወጣች ያስብላልና ።ይቆየን
2015 ኦገስት 5, ረቡዕ
በእንተ ሙኒክ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያንና ሊቀ ብርሃናት ቆሞስ አባ ገብረ ሕይወት ፍስሐ [ጀርመን ]
ምእመናን ከአንዱ ሀገር ወደ ሌላው ሀገር በተለያየ ምክንያት መሰደዳቸው አይቀሬ
ነው:: ታዲያ ሲሰደዱ በሄዱበት ሀገር ሁሉ ቤተክርስቲያን ያስፈልጋቸዋል :: ምንም አያጠያይቅም የተመቻቹ ሁኔታዎችም አሉ :: ቤተክርስቲያን መግዛት ይቻላል :; ምናልባት የሀገረ ስብከቶች ወጥ የሆነ መዋቅር አለመኖር የምእመናኑ
አንድ ሐሳብ አለመሆን ወዘተ ችግሮች ውጤታማ የሆነ መንፈሳዊ አገልግሎት ለመስጠት ችግሮች ይታያሉ :: የህዝቡ መንፈሳዊ ተነሳሽንት
ግን ይበል የሚያሰኝ ነው :: በተለይ አንዳንድ አድባራት
ቤተክርስቲያን ለመግዛት የሚያደርጉት እንቅስቃሴ በጣም ግሩም ነው :;ለዛሬ የማካፍላችሁ ስለሙኒክ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ነው
[ጀርመን ] ሙኒክ /ሙንሽን ማለት የመነኮሳት
ከተማ ማለት ነው :: ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አለ በዚያ የሚኖሩ ምእመናን በጣም ጠንካሮች ናቸው
:: “ጓደኛህን ንገረኝና ማንነትህን ልንገርህ” እንደተባለው
የሕዝቡ ጥንካሬ የቤተክርስቲያን
ግዥ እንቅስቃሴውን ልነግራችሁ አልችልም;;
ምስጢሩ ደግሞ ልንገራችሁ ? ; የሊቀ ብርሃናት ቆሞስ አባ ገብረ ሕይወት ፍስሐ ከፍተኛ እንቅስቃሴ ውጤት ነዋ !
ሊቀ ብርሃናት ቆሞስ አባ ገብረ ሕይወት ፍስሐ በጀርመን
የሙኒክ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል
ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ናቸው:: ሀገር ቤት / ኢትዮጵያ አዲስ አበባ
ኢያሉ በተለያዩ አድባራት በአስተዳዳሪነት ለረጅም ጊዜያት
አገልግለዋል::
ሊቀ ብርሃናት አባ ገብረ ሕይወት የቅዳሴ መምህር ናቸው አቋቋም
አዋቂ ማኅሌታዊ ናቸው ከሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ
በዲፕሎማ ; ከቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ የመጀመሪያ ድግሪ አግኝተዋል ሙኒክ ከሚገኘው ሉድቪግ ማክስሚልያንስ ዩኒቨርሲቲ የጀርመንኛ ቋን ቋ ሰርተፍኬት
ተቀብለዋል አሁንም በመማር ላይ ይገኛሉ :: ሲቀድሱ ማኅሌት ሲቆሙ
ሲያስተምሩ ሕዝቡን ለበጎ ነገር
ሲያስተባብሩ በተለይ ቤተክርስቲያን ለመግዛት በሚያደርጉት የማስተባበር የማስተዳድር
ልዩ ስጦታቸ በሀገር ቤትም ሆነ በዚሁ በጀርመን በሀገረ
ስብከቱም ሆነ በሕዝቡ ዘንድ የተመሰከረላቸው ናቸው አስቀዳሹ ሁሉ
ሳይቀር መልክዐ ውዳሴውን በሚገባ አሰልጥነዋል ለድቁናም የበቁ ደቀመዛሙርትም አፍርተዋል
በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ሊቀብርሃናት ሊቀብርሃናት ደከመኝ ሰለቸኝ
ማለት አያውቁም :: ታዲያ እንዲህ ያሉ አባቶች ከአገልግሎት ፍላጎት እስክ ብቃት .ከብቃት
እስከ ውጤታማንት የተዋጣላቸው አባቶቻች ጥቂቶች ቢሆኑም ምእመናኑ እንደነዚህ
ያሉ አባቶችን ከጎናቸው በመቆም አብሮ ማገልገል ይገባል :: በሙኒክ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያንን
ለመግዛት እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴ
በጣም የሚበረታታ ነው :: 2015 ጁላይ 9, ሐሙስ
ሕጻናት በስደት ሀገር .............
የሰው ልጅ በተለያየ ምክንያት ከአንዱ ሀገር ወደ አንዱ
ሀገር ይዘዋወራል፡ ለትምህርት ፡ለኑሮ ለመሳሰሉት ሁሉ ይሰደዳል ከዚሁ
ጋር ትዳር መያዝ ልጅ መውለድ እይቀሬ ነው ይልቁንም ለሕጻናት መብት ፡ለልጆች ትምህርት ወዘተ የተሻለ ነውና / ተብሎ ስለሚታሰብ
ቤተሰብእ፡ያለሐሳብ ልጅ ወልዶ ለመኖር ይወስናል፡፡ እንደ የሀገሩም ሕግ በተለይ የሕጻናት እንክብካቤ ቁጥጥርም በሉት ከባድ ነው ፡፡በየጊዜው
ቁመታቸው፡ ክብደታቸው፡ የጭንቅላታቸሀው እድገት ፡ ጸጉራቸው ፡ጥርሳቸው ሁሉ ሳይቀር ሁል ጊዜ በህክምና ባለሙያ ይታያል ፡ዘጠና ዘጠኝ ፐርሰንት ቁጥጥሩ የሀገሪቱ መንግስት ነው ወላጆች ስለ ልጆቻቸው መናግርና ውሳኔ ማሳለፍ አይችሉም
በዚህ ምክንያት ባህላቸው ሃይማኖታቸው ሥርዓተ ቤተክርስቲያናቸው ቛንቛቸው
ሁሉ እየጠፋ ነው ስለዚህ በስደት ሀገር ስለሕጻናት ጠበቅ ጠለቅ ያለ
ሀሳብ ማሰብ ማቀድ ያስፈልጋል በውጪ ሀገር ያለች ቤተ ክርስቲያን
ዘመኑን በዋጀ መልኩ የሀገሪቱን የትምህርት ሥርዓት በመሰለ መልኩ መንፈሳዊ ሥርዓተ ትምህርት በፍጥነት ማዘጋጀት ያስፈልጋል ይህ
ካልሆነ በስደት ያሉት ሕጻናት በቅርብ ጊዜ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ሀገራቸውን ሃይማኖታቸውን….. ያጣሉ ለዚሁ ጥሩ ጅምር ማኅበረ ቅዱሳን የአሜሪካው ማዕከል የጀመረው አመርቂ ጅምር ይበል
የሚያሰኝ ነው ፡፡ የማኅበረ ቅዱሳን አውሮፓው ማዕከልም በፍራንክፈርት
ከተማ ጀርመን የ፲፭ኛው ዓመት ጠቅላላ ጉባዔውን ባደረገበት ውቅት በቀጣዩ ዓመት ከአጸደቀው እቅዶች መካከል አንዱ «በውጭው ዓለም የሚገኙ ሕጻናትን
በቤተ ክርስቲያን በተቀናጀ መልኩ እንዴት እናስተምር? በሚል ያቀደው እቅድ ሊበረታታና ሁሉም ሰው ሊረባረብበት ይገባል
በተለይ በውጭ ሀገር ያሉ ነዋሪዎች ልጆቻቸው ራሳቸው ልጆች ኢትዮጵያውያን
ሆነው ሃይማኖታቸውን በጎ ባህላቸውን ጠብቀው ይቀጥሉ ዘንድ መረባረብ
ይገባል ያለበለዚያ ሕጻናት ከሃይማኖታቸው፡ ከመልካም ባህላቸው፡ ከሥርዓተ ቤተክርስቲያናቸው እንዳይሰደዱ ሊታሰብበት ይገባል።
የአውሮፓ ማዕከል ፲፭ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በፍራንክፈርት ፥ ጀርመን አካሄደ
በብዙኀን መገናኛ እና ቴክኖሎጂ አገልግሎት ክፍል
ሐምሌ 02 ቀን 2007 ዓ.ም.
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሰንበት ት/ቤቶች
ማደረጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን የአውሮፓ ማዕከል አስራ አምስተኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በጀርመን ሀገር በፍራንክፈርት
ከተማ በምትገኘው በደብረ ፀሐይ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ከሰኔ ፳፮ እስከ ፳፰ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. አካሄደ።
በጉባኤው
ላይ ብፁዕ አቡነ ሙሴ የደቡብ፣ ምሥራቅና ምዕራብ አውሮፓ አኅጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ መጋቤ ምሥጢር ኅሩይ
ኤርምያስ የደቡብ ምሥራቅና ምዕራብ አኅጉረ ስብከት ዋና ጸሐፊ፣ የዋናው ማዕከል እና የአሜሪካ ማዕከል ተወካዮች
እንዲሁም በጀርመን የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት የደብር አስተዳዳሪዎች እና ከመላው
አውሮፓ የተሰባሰቡ ከ፺ በላይ የሚሆኑ የማኅበሩ አባላት ተገኝተዋል።
ሰኔ ፳፮ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. ቀትር ጀምሮ እንግዶች ወደ ጉባኤው ቦታ ፍራንክፈርት ደብረ ፀሐይ
ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የደረሱ ሲሆን ጉባኤው ሠርክ ላይ በአባቶች መሪነት በጸሎተ ኪዳን ተጀምሮ በዲ/ን
ዶ/ር ቴዎድሮስ በለጠ ትምህርተ ወንጌል ተሰጥቷል። በመቀጠልም የእራት መስተንግዶ በጀርመን ቀጣና ማዕከል ከተደረገ
በኋላ በጠቅላላ ጉባኤው አዘጋጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶ/ር ደረጀ ወርቁ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ተላልፎ
በመጨረሻም የአባላት የእርስ በርስ የትውውቅ መርሐ ግብር ከተከናወነ በኋላ የእለቱ መርሐ ግብር ፍጻሜ ሆኗል።
ሰኔ ፳፯
ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. ጠዋት ጸሎተ ወንጌል (ማቴ.፯ ፥ ፳፬) በብጹዕ አቡነ ሙሴ መሪነት ደርሶ ቀሲስ ለማ በሱፍቃድ
«እውነተኛ የቤተ ክርስቲያን ልጅ የቱ ነው?» (ሉቃ.፲፭ ፥ ፲፩ - ፴፪) በሚል ርዕስ ትምህርት ሰጥተዋል። ቀጥሎም
የማዕከሉ ሰብሳቢ ዲ/ን ሰሎሞን አስረስ ለተጋባዥ እንግዶች እና ለማዕከሉ አባላት የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት
አስተላልፈዋል። የ፳፻፯ ዓ.ም. የማዕከሉ የአገልግሎት ክፍሎች እና የማዕከላት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት በማዕከሉ
ሰብሳቢ የቀረበ ሲሆን ጉባኤው የሂሳብ፣ የኦዲትና ኢንስፔክሽንን ዕቅድ ክንውን ሪፖርት ካዳመጠ በኋላ በሪፖርቱ ላይ
ሰፊ ውይይት አድርጓል። ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችም የሥራ አስፈጻሚ ጉባኤ አባላት ማብራሪያ እና ምላሽ ከሰጡ
በኋላ አጠቃላይ ኃሳቦች በብጹዕ አቡነ ሙሴ እና በተጋበዙ እንግዶች ተሰጥተው ሪፖርቱን ጉባኤው አጽድቆታል።
የደቡብ፣ ምሥራቅና ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከትን መልእክት
ያስተላለፉት ዋና ጸሐፊው መጋቤ ኅሩይ ኤርምያስ ማዕከሉ ለሀገረ ስብከቱ እያደረገ ላለው ድጋፍ አመስግነው ወደፊትም
ከማዕከሉ ጋር አብሮ ለመሥራት ሀገረ ስብከቱ ዝግጁ እንደሆነ ተናግረዋል። «በማዕከሉ የተሠሩ ሥራዎችንÂ በማየቴ
ተደስቻለሁ፤ እኛ ያላየናቸውን የአገልግሎት ክፍተቶች በማየታችሁ ፣ በመሥራታችሁ እግዚአብሔር ይስጣችሁ » በማለት
ዋና ጸሐፊው መልእክታቸውን ቋጭተዋል። ሊቀ ብርሃናት ቆሞስ አባ ገብረ ሕይወት ፍሥሐ በበኩላቸው «ከዋክብት ሰማይን ፣
አበቦች ምድርን እንደሚያስጌጡ ሁሉ ፣ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ደግሞ ለቤተ ክርስቲያን ጌጦች ናቸው፤ እናንተም
ለቤተ ክርስቲያን ጌጦች ናችሁ» በማለት ማኅበሩ በአገልግሎት እንዲተጋ አበረታትተዋል።
በመጨረሻም
ብጹዕ አቡነ ሙሴ ባስተላለፉት መልእክት ማኅበሩ በተለይም ግቢ ጉባኤያትን በማስተማር እና የተዘጉ ገዳማት እና
የአብነት ትምህርት ቤቶችን በማስከፈት በቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉትን ብዙ ክፍተቶች ሸፍኗል። አሁንም ማኅበሩ ይህንን
መልካም ሥራውን አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባዋል ሲሉ ብፁዕነታችው መልእክታቸውን ለጉባኤው አስተላልፈዋል። ወደፊትም
ማዕከሉ ከሀገረ ስብከቱ እና ከአባቶች ጋር ከዚህ የበለጠ ተቀራርቦ እንዲሠራ በማለት መመሪያ ካስተላለፉ በኋላ
የጠዋቱን መርሐ ግብር በጸሎት ዘግተዋል።
በእለቱ ከምሣ መስተንግዶ መልስ በመልአከ ስብሐት ተክሌ ሲራክ
በጀርመን የካርልስሩኸ ምዕራፈ ቅዱሳን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ወረብና መዝሙር፣ በማዕከሉ
አባላት ወረብ እንዲሁም በጀርመን የሙኒክ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ በሆኑት በሊቀ
ብርሃናት ቆሞስ አባ ገብረ ሕይወት ፍሥሐ መዝሙር ቀርቧል። በዚሁ እለት ከሰዓት በኋላ ጉባኤው ሰፊ ጊዜ ሰጥቶ
የተወያየበት አንዱ ርዕሰ ጉዳይ «በውጭው ዓለም የሚገኙ ሕፃናትን በቤተ ክርስቲያን በተቀናጀ መልኩ እንዴት
እናተምር?» የሚል ነው። በዚህም ርዕሰ ጉዳይ ላይ ችግሮችን ፣ መፍትሔዎችን እና ተሞክሮዎችን የዳሰሰ ጥናት
ለጉባኤው ቀርቧል። በቀረበው ጥናታዊ ጽሑፍ ዙርያ በተደረገው ውይይት ማኅበሩ ከዚህ በፊት የቀረፀው ሥርዓተ ትምህርት
መኖሩ ተወስቶ ወደፊት ግን በአዲሱ የውጭ ማዕከላት መዋቅር መሰረት ሕፃናት እና አዳጊ ወጣቶችን የማስተማር ሥራ
እራሱን በቻለ «የተተኪ ትውልድ ሥልጠና» በሚባል ክፍል ተመስርቶ በርካታ ውጤታማ ሥራዎችን መሥራት እንዳለበት
አፅንኦት ተሰጥቶበታል።
ከዚህ በመቀጠልም «ሚዲያ ለቤተ ክርስቲያን ሁለንተናዊ እድገት» በሚል ርዕስ ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን በርካታ ገንቢ ኃሳቦች ተሰጥተዋል።
በዚሁ እለት ምሽት ከእራት በኋላ ከዋናው ማዕከል ተወክለው
በመጡት አቶ ፋንታሁን ዋቄ « የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት እና ተግዳሮቶች » በሚል ርዕስ ጽሑፍ
ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል። ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችም ማብራሪያ በጽሑፉ አቅራቢ ተሰጥቶባቸዋል። የዕለቱ
መርሐ ግብርም መንፈቀ ሌሊት ሲሆን ተፈጽሟል።
ጉባኤው እሑድ ሰኔ ፳፰ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. ከቅዳሴ በኋላ እኩለ
ቀን ላይ ቀጥሎ የተሻሻለውን የውጭ ማዕከላት መመሪያና መዋቅር አተገባበርን በተመለከተ ውይይት ተደርጓል። የማዕከሉ
የአገልግሎት ክፍሎች እና የኦዲት እና ኢንስፔክሽን የመጪው ዘመን የ፳፻፰ ዓ.ም. ዕቅድ ቀርቧል። በእቅዱ ላይ
ለተነሱ ጥያቄዎች የሥራ አስፈጻሚ ጉባኤ አባላቱ ማብራሪያ እና ምላሽ ከሰጡ በኋላ እቅዱ በጠቅላላ ጉባኤው ጸድቋል።
በመቀጠልም ሕጻናት መዝሙር አቅርበው ፣ የሰሜን አሜሪካ ማዕከል
ተወካይ ዲ/ን ብዙአየሁ ልመንህ የማዕከሉን መልእክት ካስተላለፉ በኋላ የማዕከላቸውን ልምድ ለጉባኤው አካፍለዋል።
እንዲሁም ሁለቱ ማዕከላት በጋራ ሊያገለግሉባቸው የሚችሉባቸውን የአገልግሎት ዘርፎች ለጉባኤው አቅርበዋል። የዋናው
ማዕከል መልእክትም በተወካዩ በአቶ ፋንታሁን ዋቄ ለጉባኤው ቀርቧል።
በመጨረሻም የማዕከሉ ሰብሳቢ ዲ/ን ሰሎሞን አስረስ ለዚህ ጉባኤ
መሳካት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረጉት መልአከ ፀሐይ ቆሞስ አባ ሲራክ ተድላ የፍራንክፈርት ደብረ ፀሐይ ቅድስት
ማርያም ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ፣ ለቤተ ክርስቲያኗ ሰብካ ጉባኤ፣ አባታዊ ምክርና ገንቢ አስተያየቶችን በመስጠት
ለጉባኤው ሞገስ ለሆኑት አባቶች ፣ ተወካይ በመላክ ልምዳቸውን እንድናገኝ ላደረገው የሰሜን አሜሪካ ማዕከል
እንዲሁም ፲፭ኛውን ጠቅላላ ጉባኤ ላዘጋጁት የጀርመን ቀጣና ማዕከል አባላት ከፍተኛ ምስጋና አቅርበው፣ በጠቅላላ
ጉባኤው ላይ የተነሱና ውሳኔ ያገኙ ጉዳዮችን ለመተግበር ሁሉም አባላት እንዲተባበሩ ጥሪ በማስተላለፍ ፲፭ኛው ጠቅላላ
ጉባኤ ተጠናቋል። ቀጣዩን የማዕከሉን ፲፮ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ለማዘጋጀት የዩኬና የኔዘርላንድ ማዕከላት ጥያቄ ያቀረቡ
ሲሆን የማዕከሉ ሥራ አስፈጻሚ ጉባኤ ነባራዊ ሁኔታዎችን በማገናዘብ ወስኖ ለአባላት እንደሚገልጽ አሳውቋል።
በጉባኤው ማግስት ሰኞ ሰኔ ፳፱ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. የተወሰኑት
አባላት ከፍራንክፈርት የአንድ ሰዓት ገደማ ርቀት ላይ ወደሚገኘው የግብፅ ኮፕቲክ ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ እንጦስ
ገዳም በመሄድ ጉብኝት አድርገዋል።
|
ደንበኛ ይሁኑ ለ፡
ልጥፎች (Atom)
በአውሮጳ የካህናት አንድነት ማኅበር ሊቋቋም መሆኑ ታወቀ በ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከመላዋ አውሮጳ የተውጣጡ ካህናት፡” የ...
-
June 1, 2015 ከሐራ ዘተዋሕዶ በሐዋርያዊት፣ ጥንታዊት እና ብሔራዊት ቤተ ክርስቲያናችን ህልውና እና ዕድገት ፊት ከተጋረጡትና አፋጣኝ እልባት ከ...
-
‹‹…ወንድማችንን እናውቃቸዋለን፤ በእውነቱ ለፌ ወለፌ የማይሉ ደረቅ ሊቅ ናቸው፤ በሃይማኖቱ ዘርፍ ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን፣ ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን አንዲቱም ነጥብ እንዳትዛባ...