2015 ኖቬምበር 29, እሑድ

“በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የጽሑፍ ቅርስ ላይ ከአለኝ ትዝብት”


የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን

ኒው ዮርክ ከተማ

(የተራድኦ ድግስ ምሽት፥ ኅዳር  ቀን ፳፻፯ . = November 14, 2015) 


ጌታቸው ኃይሌ

ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን እንድታገለግሉ የተመረጣችሁ የተከበራችሁ ካህናትናዲያቆኖት፥ የመድኃኔ ዓለም አባላት እንድትሆኑ የሐዋርያትን ጥሪ ያከበራችሁየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን እኅቶቼና ወንድሞቼ፥ በዚህ የበጎአድራጎት ምሽት ላይ ተገኝቼ ለሥጋ ጣፋጩን የኢትዮጵያ ምግብ በስመጥር ጠጅአያወራረድኩ እንድመገብና ስለመንፈስ አርኪው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የሥነ ጽሑፍ ቅርስ ያሉኝን አንዳንድ ትዝብቶች እንዳጫውታችሁ ስለጋበዛችሁኝ ከልብ አመሰግናለሁ።

እኛ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን የትልቅ ታሪክ ችቦ ተሸካሞችነን። ችቦውን መሸከም መስቀለ ሞቱን የመሸከም ያህል ይከብዳል፤ ግን የኩሩውማንነት መታወቂያችን ስለሆነ ከባዱን ሸክም በደስታና በጸጋ እንሸከመዋለን።ስለችቦውና ስለ አቀጣጣዮቹ ተናገር ስላሉኝ ተደስቻለሁ። ቅዱስ ዳዊት “ተፈሣሕኩእስመ ይቤሉኒ ቤተ እግዚአብሔር ነሐውር” (ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ስላሉኝተደስቻለሁባለው አነጋገር ስለተጠቀምኩ መንፈሱ እንደማይወቅሰኝ እለምነዋለሁ።

ትልቁን ታሪካችንን በመመዝገብ የትልቅ ሕዝብ ቀጣዮች መሆናችንን የነገሩን የቤተክርስቲያን ሊቃውንት ናቸው። ባለውለታዎች ስለሆኑ፥  እናመስግናቸው፤ ቅዱሳንስለሆኑ፥  እንዲጸልዩልን እንለምናቸው።
“ሊቃውንት አባቶቻችን ምን ምን መዘገቡልን? የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ጥናቱእንደቀጠለ ነው። በዚህ ጥናት ላይ የምዕራባውያን ምሁራን ተሳትፎ ከፍ ያለ ቦታይዟል፤ አድናቆትም አለኝ። የምዕራባውያን ምሁራን በምርምራቸው የሚያደርጉትንስሕተት ሁሉ ከክፋታቸው እንደመነጨ አድርጌ አላየውም። ለምሳሌ በኪዳነ ወልድክፍሌ ስም የሚታወቀውን መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስየሚመጥን የግዕዝ መዝገበ ቃላት በኢትዮጵያ አልተጻፈም። የዚህ ድንቅ መጽሐፍመሠረት ጀርመናዊው ዲልማን በላቲን ቋንቋ ያዘጋጀው የግዕዝ መዝገበ ቃላት ነው።እኔም ማስረጂያ ይዤ እንዲያርሙ የምጠይቃቸውን እርማት፥ በማልቀበለውምክንያት እምቢ ያሉበትን ጊዜ አላጋጠመኝም።

የምዕራባውያን ምሁራን የግዕዝን ምንጮች ከሚመረምሩበት ምክንያት አንዱ፥በዓለም ላይ የጠፉ የጥንት የክርስትና ሃይማኖት ምንጮች ኢትዮጵያ ገዳማት ውስጥይገኙ እንደሆነ ለማወቅ ነው። ክርስትና የዛሬውን መልክ እስኪይዝ ብዙ እንቅፋቶችንአልፏል። እንቅፋቶቹን ከፈጠሩት ምክንያቶች አንዱ ብዙ የክርስትናን ታሪክ ዘጋቢዎችመነሣት ነው። እዚህ ላይ በእኛ ዘንድ የተፈጸመውንና የታመነውን የሥራውን ዜናበሥርዐት ሊጽፉ የጀመሩ ብዙዎች ናቸው ያለውን የቅዱስ ሉቃስን ምስክርነትመጥቀስ ይቻላል። የጥንቶቹ ሊቃውንት ከውዝግብ ለመውጣት ሲሉ ጥቂቶቹንመጻሕፍት መርጠው የቤተ ክርስቲያን ሕጋዊ መጻሕፍት አድርገው አወዛጋቢ ነገርያለባቸውን ሌሎቹን ኮነኗቸው፤ አጠፏቸውም። ዛሬ የሃይማኖት ተመራማሪዎችእነዚህ የተኮነኑ መጻሕፍትና በሌላ ምክንያት የጠፉ ስለክርስትና ታሪክ የሚነግሩን ነገርይኖራል በማለት ይፈልጓቸዋል።

በመጠኑም ቢሆን ተገኝተዋል። በጣም የታወቁትን ልተውና አንድ አሜሪካዊ ተማሪበቅርብ ቀን ስላገኘው የጥንታዊ ድርሰት ብጣሽ (fragment) ልናገር። ሙሴናየፈርዖን ጠንቋዮች ታምራት በመሥራት ይወዳደሩ እንደነበረ እናስታውሳለን። አንድያልታወቀ ደራሲው ስለፈርዖን ጠንቋዮች የደረሰው ጥንታዊ ድርሰት ኖሯል። መኖሩየታወቀው የድርሰቱ አንድ ብጣሽ በግሪክኛው ተገኝቶ ነው። ይህ ተማሪ ያገኘውየግዕዝ ብጣሽ ብራና ግሪክኛው ውስጥ ያለውን የሚመሰክርና የጐደለውን የሚያሟላነው። ተማሪው ከማግኘቱ በፊት እንዲህ ያለ ድርሰት በግዕዝ መኖሩን ማንምአያውቅም ነበር። ይቺ ብጣሽ የብራና ጽሑፍ መገኘት ያደረገው አስተዋጽኦ በብጣሹመጠን የሚገመት አይደለም።

በግሌ ወደ አጋጠሙኝ ሁለት ጉዳዮች ልሻገር። አባ ባሕርይ መዝሙረ ክርስቶስንሲደርሱ ከጠቀሟቸው ብዙ መጻሕፍት ውስጥ አንዱ ከሊላ ወድምና የሚባለውመጽሐፍ እንደሆነ ነግረውናል። እኔም ድርሰቶቻቸውን ስተች አንሥቼዋለሁ።መጽሐፉ በብዙ ቋንቋዎች ተተርጒሞ ሳለ በግዕዝ ስላልተገኘ፥ ሊቃውንቱየመነኵሴውን ቃል መጠራጠር ጀምረው ነበር። ግን መጽሐፉ ራሱ ባይገኝም፥ የሐይቅገዳም መጽሐፉ እንደነበረው ማስረጃ አግኝቻለሁ፤ መዝገባቸው ከመዘገባቸውመጻሕፍት አንዱ ከሊላ ወድምና ነበረ። መጽሐፉን አይተውት ይሁን ወይም ስሙንከመዝገብ ላይ አግኝተውት ይሁን ባይታወቅም፥ ሊቀ ጠበብት አክሊለ ብርሃንከአዘጋጁት የመጻሕፍት መዝገብ ውስጥ አግብተውታል።


ሁለተኛው፥ ዮሴፍ ወአስኔት የሚባለውን መጽሐፍ የሚመለከት ነው። ይህምመጽሐፍ በብዙ ቋንቋዎች ተተርጕሞ ሲገኝ በግዕዝ አልተገኘም። ግን አባ ጊዮርጊስዘጋስጫ መጽሐፈ ምስጢር በሚባለው መጽሐፋቸው ውስጥ እመቤታችንን ንህብዘአስኔት (የአስኔት ንብብለዋታል። አስኔት ንብ እንደነበራት የሚነግረን ምንጭዮሴፍ ወአስኔት ብቻ ስለሆነ ደራሲው አባ ጊዮርጊስ መጽሐፉ እንደነበራቸው--ኢትዮጵያ እንደነበራት--ታምኖበታል። እዚህም ላይ ትንሽ አስተዋፅኦ አድርጌያለሁ።

ከእኛ ሊቃውንትም ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴና ሊቀ ጠበብት አክሊለ ብርሃንምን ምን መጻሕፍት እንዳሉን በዝርዝር ጽፈዋል። ግን በቂ አይደለም። ምርምሩይቀጥላል። ምኞቴ በዚህ በተቀደሰ ተግባር ብዙ ወጣት ኢትዮጵያውያን እንዲሰማሩነው። አባቶቻችንን የማደንቀው ለግዕዝ ያንን ሁሉ የሃይማኖት መጽሐፍ የመቀበያችሎታ ማስታጠቃቸው ነው። ይህ የሚያመለክተው ግዕዝ ከአክሱም ዘመነ መንግሥትበፊት ዳብሮ እንደነበረ ነው። ለምሳሌ ግዕዝ ተቆጣ ለማለት ከአራት የማያንሱቃላት እንዳሉት በአጋጣሚ አይቻለሁ፤ መአከ (ተምእከ) መጐጸ(አመጐጸ) ተምዐ (ተምዕዐ) ተቈጥዐ

አማርኛ የሌለው አንዳንድ ቃላትም አጋጥመውኛል፤ ለምሳሌ፥ ሕልበት(nostril)ምንሀብ (factory). አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ሕልበት መተርጐሚያ አማርኛቢያጡ፥ የአፍንጫ ጉንጭ አሉት።

የግዕዝን ችሎታ ብናውቅ ኖሮ፥ bank የሚለው የእንግሊዝኛ ቃል አማርኛ ውስጥአይገባም ነበር። ባንክ በመሠረቱ የገንዘብ መለዋወጫ ጠረጴዛ (bench)ነው።የሉቃስን ወንጌል ስናነብ ምዕራፍ ፲፱ ላይ ጌታችን የሰጠን አንድ ምሳሌ እናገኛለን።እንደምሳሌው፥ አንድ ጌታ ከአሽከሮቹ ለዓሥሩ ነግደው እንዲያተርፉለት ዓሥርምናናት ከፋፍሎ ሰጥቷቸው ነበር። በመጨረሻ ሁሉም ገንዘቡን ከነትርፉ ለጌታቸውሲያስረክቡ፥ አንዱ ብቻ የወሰደውን ሳይነግድበት ሳያተርፍበት እንዳለ ከትቶ እንዳለለጌታው መልሶ ሰጠው። ጌታው አዝኖና ተቆጥቶ እንዲህ አለው፤

“ወለምንት ኢያግባእከ ወርቅየ ውስተ ማእድ”
([ላለመነገድህ ምክንያት ካለህ] ታዲያ ገንዘቤን ለምን ከማእድ አላስገባህም?”
ምንጩ ግሪክኛው የሚለውም “ትራፔዛ” (ጠረጴዛነው። ታዲያ የአማርኛው ትርጕምከላይ እንዳመለከትኩት መሆን ሲገባው፥ የመጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር ትርጉም “ባንክ”፥የኦርቶዶክሶቹ “ለዋጮች” ይላል። ግን ቀደም ብሎ “ማእድ” እንዳለ ከግዕዝ ወደአማርኛ ቢተላለፍ ኖሮ “ባንክ” የሚለውን የእንግሊዝኛ ቃል ምንም ሳይጕድልብንልናስቀረው እንችል ነበር።

የዮሐንስ ወንጌልን ሳነብና  ምዕ 19 . 24 ላይ ስደርስ ደግሞ፥ ስለ ግዕዝ የቃላትብልጽግናና ስለአባቶች ጥንቃቄ የገረመኝና እኛን ልጆቻቸውን የሚወቅስ ነገርአጋጠመኝ፤ ጥቅሱን እንዳለ ልጥቀሰው፤
 
ወሐራሰ ሶበ ሰቀልዎ ለኢየሱስ ነሥኡ አልባሲሁ ወረሰይዎ አርባዕተ ክፍለ ለአሐዱሐራ ክፍለ። ወክዳኖሂ እልታኀ ዘአልቦ ርፍአት ዘእምላዕሉ እኑም ኵለንታሁ።ወተባሀሉ በበይናቲሆሙ ኢንግምድ ወኢንስጥጥ አላ ንትፋሰስ ለዘረከቦ ይርከቦ። ከመይብጻሕ ቃለ መጽሐፍ ዘይቤ። ተካፈሉ አልባስየ ለርእሶሙ ወተዓፀው ዲበ ዐራዝየ።

ወታደሮቹ ኢየሱስን ከሰቀሉት በኋላ፥ ልብሱን ወስደው ለእያንዳንዱ ወታደር አንድ ክፍል እንዲደርስ አራት ቦታ ከፈሉት። መርፌ ስላልነካው ከላይ እስከታች አንድ ወጥ ሆኖ ስለተሠራው ስለ ፈርጅ ቀሚሱ ግን እርስ በርሳቸው (እንዲህ) ተባባሉ፥ “ዕጣ እንጣጣልና ለደረሰው ይድረሰው እንጂ አንቅደደው”። ይህም፥ “ልብሶቼን ለራሳቸው ተከፋፈሉት፤ በቀሚሴም ላይ ዕጣ ተጣጣሉ” ያለው የመጽሐፍ ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው።)
እንግሊዝኛውም እንደ አማርኛው ከሁለቱም ቦታ “ዕጣ ተጣጣሉ”(cast lotsነውየሚለው።
. . . So they said to one another, Let us not tear it, but cast lots for it to see who will get it. This was to fulfill what the scripture says, They divided my clothes among themselves, and for my clothing they cast lots.

በግዕዝ ግን አነጋገሩ የተገለጠው በሁለት የተለያዩ ሐረጎች መሆኑን ልብ እንበል፤ ተፋሰሱ  ተዐፀዉ ለምን እንዲህ ሆነ ብየ የግሪኩን ምንጭ ባየው፥ እውነትምሁለቱ ሐረጎች በግሪክኛውም የተለያዩ ናቸው፡ lachomen እና ebalon kleeron


* * * * * * * *
ባሁኑ ሰዓት ጥሪየ አድርጌ የያዝኩት አባቶቻችን ከውጪው ዓለም ምን ተረጐሙልን፥እነሱስ በተረጐሙት ላይ ምን አከሉበት የሚሉትን ሁለቱን ጥያቄዎች መመለስን ነው።አምሳያቸው እውጪ አገር ካለ ከውጪ የተተረጎሙ ናቸው ማለት አያስቸግርም።ደንቃራ የሆነብኝ አንዳንዶቹን የግዕዝ መጻሕፍት ከምዕራቡ ዓለምና ከመካከለኛውምሥራቅ ጠፍተው ነው እንጂ፣ ትርጕም ናቸው የሚለው አነጋገር ነው። እርግጥከሌላው ዘንድ ጠፍተው እኛ ዘንድ የተገኙ አሉ። ይኸም ቢሆን አባቶቻችንና ቤተክርስቲያናችንን የሚያስመሰግን ነው።

ቢሆንም እኛ ተቀባዮች ብቻ ባንሆን እንመርጣለን፤ ለነገሩ ተቀባዮች ብቻምአይደለንም። ይኸንንም ለማሳየት ለዛሬው ንግግሬ ሁላችሁም በምታውቁትበመጽሐፈ ቅዳሴያችን ላይ አተኩራለሁ። 

የዶክተር ገብረ ጻድቅ ደገፉና የኔ መምህር ቄስ ማርቆስ ዳውድ የመጽሐፈ ቅዳሴውንእንግሊዝኛ ሲያሳትሙ፥ እመቅድሙ ውስጥ እንዲህ ብለው ጽፈዋል፤
 
It is said by the Ethiopian Church authorities that they received their liturgy of fourteen Anaphoras from the Church of Egypt. The Church of Egypt confirms this but has, unfortunately, lost most of the fourteen.
 
(በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ባለሥልጣኖች ዘንድ ዓሥራ አራቱን የቅዳሴ መጻሕፍታቸውን ከግብፅ ቤተ ክርስቲያን እንደወሰዱ ይነገራል። የግብፅ ቤተ ክርስቲያን ይኸንን ታረጋግጣለች። ግን መጥፎ ዕድል ሆኖ ከዓሥራ አራቶቹ አብዛኛዎቹ ጠፍተውባታል።
 የግብፅ ቤተ ክርስቲያን የጠፉባት የቅዳሴ መጻሕፍት ቍጥር የሚታወቀው ኢትዮጵያውስጥ ባሉት መጻሕፍት ቍጥር መሆኑ ነው። እንዲህ ከሆነ፥ ከዓሥራ አራት ሊበልጡነው። ምክንያቱም ቄሱ አልሰሙም እንጂ፥ ቅዳሴዎቹ ወደኻያ ይጠጋሉ። መምህሬ ቄስማርቆስ ዳውድ ይህን መቅድም ሲጽፉና ትርጕሙን ሲያሳትሙ እያወቁ ሁለት በደልፈጽመዋል፤ (1) “የግብፅ ቤተ ክርስቲያን ይኸንን ታረጋግጣለች” ያሉት ማስረጃሳይኖራቸው ነው። (2) መጽሐፈ ቅዳሴውን የተረጐመላቸው አብሮ አደግ ወዳጄናጓደኛየ ዶክተር ገብረ ጻድቅ ደገፉ ነው። ግን እኝህ መንፈሳዊ አባትና መምህር ይኸንንሐቅ ጨቁነውታል፤ የገብረ ጻድቅን ስም ለምስጋና እንኳን አላነሡትም።

ከታተመው መጽሐፈ ቅዳሴ ውስጥ ያሉት የቅዳሴ ጸሎቶች (አኰቴተ ቍርባንዓሥራአራት የሆኑት ለኅትመት የተመረጠው የብራና ቅጂ ውስጥ ያሉት ዓሥራ አራትስለነበሩ ነው። ካህናቱ እንደምታስታውሱት፥ ቅዳሴ ጎርጎርዮስ (ነአኵቶ ለገባሬሠናያት--ነአኵተከ እግዚኦን አይደለምየሚያነሣው ሊቀ ጳጳሱን አባ ዮሐንስን(፲፮ኛው 1676-1718) እና ጳጳሱን አባ ሲኖዳን (1671-1693) ነው። የእትሙምንጭ የተቀዳው በነሱ ዘመን 1676 እና 1693 መካከል በነበረው ዘመን ነውማለት ነው።

ያደረግሁት ምርምር ጥሩ ዕድል ሆኖ ከዓሥራ አራቶቹ አብዛኛዎቹ ከግብፅ ቤተክርስቲያን የመጡ ሳይሆኑ፥ የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ድርሰቶች መሆናቸውንአረጋግጦልኛል። አባ ጊዮርጊስ በአፄ ዳዊትና በአፄ ዘርአ ያዕቆብ ዘመን የኖሩ ብዙመጻሕፍት የደረሱ ታላቅ የቤተ ክርስቲያን ሊቅ ናቸው። ከድርሰቶቻቸው ውስጥኆኅተ ብርሃን፣ አርጋኖነ ውዳሴ (= አርጋኖነ ድንግል) ውዳሴ መስቀል፤ መጽሐፈብርሃን፣ ጸሎተ ፈትቶ፣ ፍካሬ ሃይማኖት፣ መጽሐፈ ምስጢር የሚባሉ መጻሕፍትይገኛሉ።

ደራሲያቸው ያልተረጋገጠውን አኰቴተ ቁርባኖች የመረመርኩትና የጥናቴን ውጤትለኅትመት የላክሁት እነዚህ መጻሕፍት የተጻፉበትን ስልት መሣሪያ በማድረግ ነው።ምርምሬን የጀመርኩት ውበቱን ምዕራባውያን በመሰከሩለት ድርሰታቸው አርጋኖነውዳሴ ነው። ግን መጀመሪያ አርጋኖነ ውዳሴ የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ እንጂ፥እንደሚታመንበት የአርመናዊው ጊዮርጊስ (Giorgis the Armenian)እንዳይደለ ማስመስከር ነበረብኝ። ያስመሰከርኩበት ጥናት የምዕራባውያን ሊቃውንትቀንድ የሆነ ሊቅ፥ The erroneous dating of the Arganonä Wəddase . . . as well as its false attribution to un unknown Giorgis the Armenian have been conclusively refuted ሲል ፍርዱን መዝግቧል።

ይኸ በራሱ አንድ አስደሳች የድካም ውጤት ነው። እርግጥ በኛ ዘንድ አርጋኖነ ውዳሴየአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መሆኑን የሚጠራጠር የለም። ግን የኢትዮጵያ ታሪክ በምዕራቡዓለም በሰፊው ስለሚጻፍ፥ ልጆቻችንም እነሱ ዘንድ ስለሚማሩ፥ ታሪካችንንበተገኘበት ቦታና ጊዜ ሁሉ ማስተካከል ግዴታችን ነው። ከቅዳሴዎቹ አብዛኞቹ የአባጊዮርጊስ ዘጋስጫ መሆናቸውን ለማሳየት የምጥረውም ከግብፅ ቤተ ክርስቲያን የመጡናቸው ተብሎ በሀገራችን ሳይቀር ተቀባይነት ያገኘውን የተሳሳተ እምነት ለማስቀረትነው። አርጋኖነ ውዳሴ የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መሆኑ ከተረጋገጠ የአጻጻፋቸው ስልትምን እንደሚመስል ላሳይ። በድርሰቶቻቸው ላይ ሁሉ በተለይ ከዚህ በታች ያሉትባሕርዮች ጎልተው ይታያሉ፤
1. ይዞታቸው እንደ መጽሐፈ ምስጢር ነገረ መለኮት ማስተማሪያ ናቸው፤
2. በጀመሩበት ቃል ብዙ አረፍተ ነገሮች ያከታትሉበታል፤
3. በአረፍተ ነገሩ መጀመሪያ ሐረግ ላይ ያለውን ሐሳብ በሁለተኛው ሐረግያጠነክሩታ፤
4. በአረፍተ ነገሩ መጀመሪያ ሐረግ ላይ ያለውን ሐሳብ በሁለተኛው ሐረግያፈርሱታል፤
5. አረፍተ ነገሮቹ ቤት የሚመቱ የማይመቱም ቅኔዎች ናቸው፤
6. ካለው ግስ ላይ አዳዲስ ቃላት ይፈጥራሉ፤
7. ለኛ ባልታወቁ የውጪ ቃላት ይጠቀማሉ፤

እነዚህ የአጻጻፍ ባሕርዮች በብዙዎቹ ቅዳሴዎች ላይ ይታያሉ።
ቅዳሴ በመሠረቱ ከጸሎተ ሃይማኖት አልፎ ነገረ መለኮት መተቻ አይደለም። ብዙዎቹቅዳሴዎቻችን ግን እንደ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ድርሰቶች እንደ መጽሐፈ ምስጢር እናእንደ ፍካሬ መለኮት መለኮትን በሰፊው ይተቻሉ። ሁሉንም የአባ ጊዮርጊስን የአጻጻፍባሕርዮች ለማሳየት ከሁሉም ምሳሌ መስጠት መጽሐፈ ቅዳሴውን መገልበጥይሆናል። ግዕዝ የማያውቀውንም ያሰለቸዋል። ሆኖም ከዚህ በታች ያሉትን ብቻእንመልከት፤

ከአርጋኖነ ውዳሴ ለምሳሌ
ኪያኪ፡ ረከብኩ፡ ምጒያየ፡ እሙስና፡ (ከብልሸት መሸሻ አንቺን አገኘሁ ፡)
ኪያኪ፡ ረከብኩ፡ ምጒያየ፡ እምአፈ፡ አናብስት፡ (ከአንበሶች አፍ መሸሻ አንቺን አገኘሁ፡)
ኪያኪ፡ ረከብኩ፡ ምጒያየ፡ እምአፈ፡ ተኵላተ፡ ዐረብ፡ (ከዐረብ ተኵላ አፍ መሸሻ አንቺን አገኘሁ፡)
ኪያኪ፡ ረከብኩ፡ ምጒያየ፡ እምቃለ፡ ዘይጽዕል፡ (ከተሳዳቢ ቃል መሸሻ አንቺን አገኘሁ፡)
ኪያኪ፡ ረከብኩ፡ ምጒያየ፡ እምእደ፡ ኵሎሙ፡ ጸላእትየ፡ (ከጠላቶቼ ሁሉ እጅ መሸሻ አንቺን አገኘሁ፡)

(1) ከቅዳሴ ማርያም፤

አኮ ዘቦቱ ለመለኮት ክበብ . . . አላ መንክር. . .  (መለኮቱ ክበብ የለውም . . . አስደናቂ እንጂ . . .።)
አኮ ዘቦቱ ለመለኮት ግድም ወኑኅ . . . አላ ምሉእ . . . (መለኮቱ አግድሞሽና ርዝመት የለውም . . . በሁሉም ዘንድ የሞላ ነው እንጂ . . .)
አኮ ዘቦቱ ለመለኮት ምስፋሕ . . . አላ ውስተ ኵሉ . . (መለኮቱ መስፋፊያ ቦታ የለውም . . ግዛቱ በሀገሮች ሁሉ ነው እንጂ . . .)
አኮ ዘቦቱ ለመለኮት ዘበላዕሉ ጠፈር . . . አላ ጠፈር ውእቱ . . . (መለኮት በላዩ ጠፈር የለበትም . . . እሱ እራሱ ጠፈር ነው ኢንጂ . . .)

ይህ ጥቅስ (1)ነገረ መለኮት ነው፤ (2) አረፍተ ነገር በጀመረበት ቃል (አኮአረፍተነገር ይደጋግማል፤ (3) በመጀመሪያው ሐረግ ውስጥ ያለውን ሐሳብ በሁለተኛውሐረግ ያፈርሰዋል (አላ)

(2) ከቅዳሴ ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ፤

አልብከ ጽንፍ ወአልብከ ማኅለቅት፤ (ዳርቻ የለህም፥ መጨረሻም የለህም፤)
አልቦ ዘረከቦ ወአልቦ ዘይረክበከ፤ . . . (ያገኘው የለም፥ የሚያገኝህም የለም . . .፤)
አልብከ ጥንት . . . (መጀመሪያ [origin] የለህም. . .፤)
ፈጠርከ፡ ኵሎ፡ እንዘ፡ ኢትትቀነይ፤ (ሳትገዛ ሁሉን ፈጠርክ፤)
ትጸውር፡ ኵሎ፡ እንዘ፡ ኢትደክም፤ (ሳትደክም ሁሉን ትሸከማለህ፤)
ትሴሲ፡ ለኵሉ፡ እንዘ፡ ኢታሐጽጽ፤ (ሳታጓድል ሁሉን ትመግባለህ፤)
ትሔሊ፡ ለኵሉ፡ እንዘ፡ ኢታረምም። (ዝም ሳትል ለሁሉ ታስባለህ፤)
ትሁብ፡ ለኵሉ፡ እንዘ፡ ኢትቀብል  (ሳትጐድል ለሁሉ ትሰጣለህ፤)
ታረዊ፡ ለኵሉ፡ እንዘ፡ ኢትነጽፍ፤ (ሳትጠግ ሁሉን ታጠጣለህ፤) 8

ትዜከር፡ ኵሎ፡ እንዘ፡ ኢትረስዕ። (ሳትረሳ ሁሉን ታስታውሳለህ፤)
ተዐቅብ፡ ኵሎ፡ እንዘ፡ ኢትነውም፤ (ሳትተኛ ሁሉን ትጠብቃለህ፤)
ትሰምዕ፡ ኵሎ፡ እንዘ፡ ኢትጸመም፤ (እምቢ ሳትል ሁሉን ትሰማለህ፤)
ተኀድግ፡ ለኵሉ፡ እንዘ፡ ኢትነሥእ። (ሳትወስድ ለሁሉ ትተዋለህ።)
በተለይ እነዚህን ቀጥሎ የጠቀስኳቸውን ሁለት ጥቅሶች ብናስተያያቸው ሁሉምከአንድ ሰው አእምሮ የወጡ ከመሆናቸው ላይ እንደርሳለን፤

(ከዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ፤
ነሥአ፡ ኅብስተ፡ በእደዊሁ፡ ቅዱሳት፡ ወብፁዓት፡ ሕፄሃ፡ ለመርዓትከ፡ ወኅዳጋቲሃ፡ለእንተ፡ ኀደጋ፡ ምኵራብ።
(በቅዱሳትና ብፁዓት እጆቹ ኅብስት አነሣ። [ኅብስቱ] ለሙሽራህ [ለምእመናንህ/ለቤተ ክርስቲያንህ] ማጫ፥ ለፈታሃት ለምኵራብ መፋቻ ሆኗል።)

(ከውዳሴ መስቀል፤
መስቀል፡ ዘኮነ፡ ሕፄሃ፡ ለመርዓትከ፡ ወኅዳጋቲሃ፡ ለእንተ፡ ደኃርካ፡ በምኵራብ።
(መስቀል የሙሽራህ [የቤተ ክርስቲያንህ] ማጫ በምኵራብ ለፈታሃት [ለሕዝበ አይሁድ] መፍቻ ሆኗል።)

(ከዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ፤
ኅሩም፡ አንተ፡ ወሀሎከ፡ አብ፡ ቅዱስ።
ኅሩም፡ አንተ፡ ወሀሎከ፡ ወልድ፡ ቅዱስ።
ኅሩም፡ አንተ፡ ወሀሎከ፡ መንፈስ፡ ቅዱስ።

(ከመጽሐፈ ምስጢር፤
ኅሩም፡ አብ፡ ዘኢያስተርኢ፡ በህላዌሁ፡ ዘእንበለ፡ ዳእሙ፡ በራእየ፡ ትንቢት፡ለነቢያቲሁ።
ኅሩም፡ ወልድ፡ ዘኢያስተርኢ፡ በመለኮቱ፡ ዘእንበለ፡ ዳእሙ፡ በትስብእቱ።
ኅሩም፡ መንፈስ፡ ቅዱስ፡ ዘኢያስተርኢ፡ በካልእ፡ ግርማሁ፡ ዘእንበለ፡ ዳእሙ፡ በንጻሬ፡ዘይትፈቀድ፡ በዘይረድኦሙ፡ ለቅዱሳን።

እነዚህ  (እና  (የተጠቀሱ ኀይለ ቃሎች ከአንድ ሰው እንጂ ከተለያዩ ሰዎችአእምሮ የወጡ አይደሉም።

(3) ከአትናቴዎስ ቅዳሴ፤

ሰብእሰ፡ እንዘ፡ ክቡር፡ ውእቱ፡ . . . (የሰው ልጅ ክቡር ሆኖ ሳለ . . . )
ሰብእሰ፡ እንዘ፡ ንጉሥ፡ ውእቱ፡ . . . (የሰው ልጅ ንጉሥ ሆኖ ሳለ . . . )
ሰብእሰ፡ እንዘ፡ ባዕል፡ ውእቱ፡ . . . (የሰው ልጅ ሀብታም ሆኖ ሳለ . . . )
ሰብእሰ፡ እንዘ፡ ልቡስ፡ ውእቱ፡ . . . (የሰው ልጅ ብርሃን የለበሰ ሆኖ ሳለ . . . )
ሰብእሰ፡ እንዘ፡ መላኪ፡ ውእቱ፡ . . . (የሰው ልጅ ገዢ ሆኖ ሳለ . . . )
ኦአዳም፡ ምንተኑ፡ ረሰይናክ፡ . . . (አዳም ሆይ ምን አደረግንህ . . .?)
ኦአዳም፡ ምንተኑ፡ ረሰይናክ፡ . . . (አዳም ሆይ ምን አደረግንህ . . .?)
ኦሔዋን፡ ምንተኑ፡ ረሰይናኪ፡. . . (ሔዋን ሆይ ምን አደረግንሽ . . .?)
ኦአዳም፡ ወሔዋን፡ እስመ፡ አኮ፡ . . . (አዳምና ሔዋን ሆይ ልንነቅፋችሁ አይቻልም. . .)
ኦአዳም፡ ወሔዋን፡ አንትሙሰ፡ . . . (አዳምና ሔዋን ሆይ እናንተስ . . .)
ኦአዳም፡ ወሔዋን፡ አንትሙሰ፡ . . . (አዳምና ሔዋን ሆይ እናንተስ . . .)
ኦ፡ ዛቲ፡ ዕለት፡ ቀዳማዊት፡ ይእቲ፡ ወአኮ፡ ደኃራዊት፡ . . .
ኦ፡ ዛቲ፡ ዕለት፡ ደኃራዊት፡ ይእቲ፡ እንተ፡ ትሰፍን፡ ለዓለም።. . .
ኦ፡ ዛቲ፡ ዕለት፡ ለአብርሃም፡ ተከሥተት፡ . . .
ኦ፡ ዛቲ፡ ዕለት፡ ለሙሴ፡ በደብረ፡ ሲና፡ ተከሥተት፡ . . .
ኦ፡ ዛቲ፡ ዕለት፡ በነቢያት፡ ተዐውቀት፡ . . .
ኦ፡ ዛቲ፡ ዕለት፡ ቅድስቱ፡ ለአብ፡ ቡርክቱ፡ ለወልድ፡ ልዕልቱ፡ መንፈስ፡ ቅዱስ።
ኦ፡ ባዕዳት፡ ዕለታት፡ እንተ፡ ባቲ፡ ተአመርክን፡ . . .
ኦ፡ ዛቲ፡ ዕለት፡ እንተ፡ ባቲ፡ ብሊት፡ ተፀርዐት፡ ወሐዳስ፡ ጸንዐት።
ኦ፡ ዛቲ፡ ዕለት፡ እንተ፡ ባቲ፡ ሙቁሓን፡ ተፈትሑ፡ ወአግብርት፡ ግዕዙ።
ኦ፡ ዛቲ፡ ዕለት፡ እንተ፡ ባቲ፡ ምዝቡር፡ ተሐንጸ፡ ወሰይጣን፡ ተኀጕለ።

(4) ቅዳሴ ኤጲፋንዮስ፤

አልቦ፡ ጥንት፡ ለህላዌሁ፤ (አነዋወሩ መጀመሪያ የለውም፤)
ወአልቦ፡ ማኅለቅት፡ ለክዋኔሁ፤ (አኳኋኑም መጨረሻ የለውም፤)
አልቦ፡ ኍልቍ፡ ለመዋዕሊሁ፤ (ዘመኑ ቍጥር የለውም፤)

ወአልቦ፡ ሐሳብ፡ ለዓመታቲሁ። (ዓመቶቹም ልክ ቍጥር የለውም፤)
ወአልቦ፡ ርስዓን፡ ለውርዛዌሁ፤ (ጕልምስናውም እርጅና የለውም፤)
ወአልቦ፡ ድካም፡ ለጽንዐ፡ ኃይሉ፤ (የኀይሉ ጥንካሬ ድካም የለውም፤)
ወአልቦ፡ ሙስና፡ ለመልክኡ፤ (መልኩም ብልሹነት የለውም፤)
ወአልቦ፡ ጽልመት፡ ለብርሃነ፡ ገጹ። (የፊቱም ብርሃን ጨለማ የለውም፤)
አልቦ፡ ድንጋግ፡ ለባሕረ፡ ጥበቡ፤ (የጥበብ ባሕሩ ዳርቻ የለውም፤)
ወአልቦ፡ መስፈርት፡ ለሣህለ፡ ትእዛዙ፤ (የትእዛዙም ምህረት ልክ የለውም፤)
አልቦ፡ ዐቅም፡ ለስፍሐ፡ መንግሥቱ፤ (የመንግሥቱ ስፋት መጠን የለውም፤)
ወአልቦ፡ ወሰን፡ ለራኅበ፡ ምኵናኑ። (የግዛቱም ስፋት ወሰን የለውም፤)

ከዚያ ይህ ይቀጥላል፤
ሥውር፡ ውእቱ፡ (ሥውር ነው)
ወምጡቅ፡ ውእቱ፡ (ምጡቅ ነው)
ነዋኅ፡ ውእቱ፡ (ረጂም ነው)
ቀላይ፡ ውእቱ፡ (ጥልቅ ባሕር ነው)
ልዑል፡ ውእቱ፡ (ልዑል ነው)
ወእሙቅ፡ ውእቱ፡ (ጥልቅ ነው)
ጽኑዕ፡ ውእቱ፡ (ጠንካራ ነው)
መዋዒ፡ ውእቱ፡ (አሸናፊ ነው)
ጠቢብ፡ ውእቱ፡ (ጥበበኛ ነው)
ማእምር፡ ውእቱ፡ (ዐዋቂ ነው)
ኃያል፡ ውእቱ፡ (ኀይለኛ ነው)
ተባዕ፡ ውእቱ፡ (ጀግና ነው)
ክቡር፡ ውእቱ፡ (ክቡር ነው)
ከሀሊ፡ ውእቱ፡ (ቻይ ነው)
ዋሕድ፡ ውእቱ፡ (አንድዬ ነው)
ወብሑት፡ ውእቱ፡ (ብቸኛ ነው)
መንክር፡ ውእቱ፡ (አስደናቂ ነው)
ከዚህ በታች ያለውን በማነጻጸ የእግዚአብሔርን አገላለጽ እንመልከት፤
ኄር፡ ዘእንበለ፡ እከይ፤ (ክፋት የለለበት ደግ፤) 11

ወየዋህ፡ ዘእንበለ፡ በቀል፤ (በቀል የሌለበት የዋህ፤)
ወዕጉሥ፡ ዘንበለ፡ መዓት፤ (ቁጣ የሌለበት ታጋሽ፤)
ጻድቅ፡ ዘእንበለ፡ ኃጢአት፤ (ኀጢአት የሌለበት ጻድቅ፤)
ወንጽሕ፡ ዘእንበለ፡ ርስሐት፤ (እድፍ የሌለበት ንጹሕ፤)
ወራትዕ፡ ዘእንበለ፡ ጥውየት፤ (ጠማማነት የሌለበት ቅን፤)
ወሃቢ፡ ዘእንበለ፡ ክልአት፤ (ንፍገት የሌለበት ሰጪ፤)
ወጸጋዊ፡ ዘእንበለ፡ ደንፅዎ፤ (ስስት የሌለበር ለጋሽ፤)
ሠራዬ፡ ኃጢአት፡ ዘእንበለ፡ በቀል፡ ወቂም፤ (በቀልና ቂም የሌለበት ኀጢአት ይቅር ባይ፤)
መጽያሕት፡ ዘእንበለ፡ ማዕቀፍ፤(እንቅፋት የሌለበት ጥርጊያ ጎዳና፤)
ወዐሠር፡ ንጹሕ፡ ዘእንበለ፡ አሥዋክ። (እሾኽ የሌለበት ንጹሕ ፈለግ፤)

ቅዳሴ ማርያምና ቅዳሴ ዲዮስቆሮስ የአባ ጊዮርጊስ ድርሰቶች ለመሆናቸው ምንምጥርጥር የለውም። ቅዳሴ ያዕቆብ ዘሥሩግና ቅዳሴ ቄርሎስም የሳቸው ሳይሆኑአይቀሩም።

ሌላው የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ሥራ መታወቂያ ካለው ግስ ላይ አዳዲስ ቃላትይፈጥራሉ። በቅዳሴ ማርያም ውስጥ የሚገኙ ቃላት “አማዕበለ” (ማዕበል አነቃነቀ)“መስግዲ” (አሰግድ) “መትሐቲ” (ዝቅ አርጌ) “መቅንዪ” (አስገዥየአባ ጊዮርጊስፍጥረቶች ናቸው።

ለኛ ባልታወቁ የውጪ ቃላት ይጠቀማሉ ብያለሁ። በሥነ ጽሑፍ ውስጥ ፒላስ”(ድንኳንየሚለው ቃል የተገኘው ሦስት ቦታ ብቻ ነው፤ 1. በመጽሐፈ ምስጢር፤ 2.በአርጋኖነ ውዳሴ፤ 3. በቅዳሴ ቄርሎስ፤

 
ሜሎስ (እሳታዊየሚለው ቃል የተገኘው ሦስት ቦታ ብቻ ነው፤ 1. በመጽሐፈምስጢር፤ 2. በቅዳሴ ያዕቆብ ዘሥሩግ፤ (3) በቅዳሴ ቄርሎስ፤

እመቤታችን ታቦት ዘዶርታቦተ ዶር የተባለችው 1. ቅዳሴ ማርያም 2.በመጽሐፈ ምስጢር ውስጥ ብቻ ነው።

የግዕዝ ሥነ ጽሑፍ ቅርሳችን ተዝረክርኳል። እስካሁን የደረሱለት ምዕራባውያን ብቻናቸው። የኛ ዝምታና ቍጭትአልባነት ባለማወቅና አስታዋሽ በማጣት ይመስለኛል።ቢያውቅና አስታዋሽ ቢያገኝ ቍጥሩ ከአምሳ ሚሊዮን የማያንስ ሕዝብ የማንነቱመታወቂያ ቅርሱ ሲወድም ዝም ብሎ አያይም። ሳንውል ሳናድር የኢትዮጵያ ሥነጽሑፍ ቅርስ ድርጅት ማቋቋም አለብን። ድርጅቱ መጻሕፍቱ የሚጠበቁበትን ዘዴይፈልጋል፤ ለሚመረምሯቸው ተማሪዎች የገንዘብ እርዳታ ይሰጣል።

ስላዳመጣችሁኝ ከልብ አመሰግናለሁ።

2015 ኖቬምበር 9, ሰኞ

በ«ተሐድሶ» መሰሪ እንቅስቃሴ ላይ ዛሬም እንንቃ!


ኢትዮጵያ  ያላት ክብርና ታሪክ በመጽሐፍ ቅዱስ በተለያዩ የታሪክ ሰነዶች የተመሰከረ፣ በታላላቅ ማራኪ ቅርሶችም የታጀበ ነው። የነበራት ክብርና ገናናነት ከምዕራብ እስከ ምስራቅ፣ ከሰሜንም እስከ ደቡብ  የታወቀ ነው። ከዚህ ጉልህ ታሪክ ውስጥ የበለጠ ጎልቶ የሚታየው ደግሞ የሀገራችን የሃይማኖት ታሪክ ነው። ኢትዮጵያ ከእስራኤል ወገን ቀጥሎ ብሉይ ኪዳንን በመቀበል ቀዳሚ ሀገር ናት። በመሆኑም በዘመነ ብሉይ ሕግና ነቢያትን በመቀበልና በመፈጸም እንዲሁም የተስፋውን ቃል በመጠበቅ ኖራለች። ጊዜው ሲደርስም የሐዋርያትን ስብከት ተቀብላ የጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነትና ጌትነት አምና ጥምቀትን ወደ ምድሯ አምጥታለች። በመሆኑም ወንጌልን ተቀብላ አምና ስትሰብክ ኖራለች። አሕዛብ ሕግና ነብያትን በናቁበት ጊዜ ከአሕዛብ ወገን ቀድማ ከእስራኤል ሕዝብ ጋር ኦሪትን በመቀበሏ እንዲሁም ደግሞ እስራኤል ወንጌልን በናቁበት፣ ክርስቶስን በጠሉበት ጊዜ ከአሕዛብ ጋር ሐዲስ ኪዳንን በጊዜው በመቀበሏ ሁለቱንም ኪዳናት በጊዜያቸው ያስተናገደች ብቸኛ ሀገር ናት ማለት ይቻላል። ስለዚህ በዓለምም ሆነ በአፍሪካ መድረክ የሚያስከብር የሃይማኖት ታሪክ ባለቤት ናት። ከዚያም በመነጨ ሊሻሩ ከማይችሉት ከሕግና ከነቢያት እንዲሁም ከክርስቶስ ወንጌል፣ ከሐዋርያት ትምህርት፣ ከሊቃውንቱም ትርጓሜ የመነጨ ሰውንም እግዚአብሔርንም ደስ የሚያሰኝ ሥርዓተ አምልኮ ባለቤት ለመሆን አስችሏታል።
 
ይህ ብዙዎችን የሚያስደስተውን ያህል አንዳንዶች ደግሞ በቅናት የሚመለከቱትና ለራሳቸው ፍላጎት ማሰፈጸሚያ አበላሽተው ሊጠቀሙበት ሲቋምጡ ታይተዋል፤ እየታዩም ነው። ይህንንም ታሪክ ለማጥፋት ወይም ባለበት በርዞ ከልሶ የራሳቸውን ኑፋቄና የክህደት አጀንዳ ለማስፈጸም ይሻሉ። በተለይ የምዕራቡ ዓለም «የካህኑ ንጉሥ» ሀገር እያለ የሚጠራትን ኢትዮጵያን ከመስቀል ጦርነት ጀምሮ በመካከለኛው ምስራቅና በአፍሪካ ለሚከተሉት ለየትኞቹም አጀንዳዎቻቸው መንደርደሪያ የማድረግ ጽኑ ፍላጎት እንዳላቸው ግልጽ ነው። ይህ እውን እንዲሆን ደግሞ ለሀገሪቱ አንድነት፣ ሉዓላዊነት፣ ለባህላዊና ማኅበራዊ ትስስር መሠረት ነች የሚሏትን የኦርቶዶክስ ቤተክስቲያን መቆጣጠር፤ በእነርሱም ርዕዮት ማራመድ፤ ካልሆነም ማዳከም፤ ከተቻለም መከፋፈል ይፈልጋሉ።
 

ይህንንም ከሱስንዮስ ዘመን ጀምሮ ለማድረግ የሚችሉትን ያህል ጥረዋል። ይህንን መሰል ቅሰጣና ሰርጎ ገብነት በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የሕንድ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን በመሰሉ ሌሎችም አብያተ ክርስቲያናት ላይ ለመፈጸም ተንቀሳቅሰዋል። ለዚህም በሕንድ ቅኝ ገዢ የነበሩት ፖርቹጋሎችና እንግሊዞች ዋነኞቹ ተጠቃሾች ናቸው። በሚገርም ሁኔታ ኢትዮጵያም ውስጥ ተቀራራቢ በሆነ ጊዜ እነዚሁ ኃይሎች የኢትዮጵያን ቤተ ክርስቲያን ለማዳከም ለማጥፋት ተንቀሳቅሰዋል። ለዚህም በሱስኒዮስ መንግሥት ጊዜያዊ ድጋፍ አግኝተው በነበሩት በነፔድሮኤዝ የሚመራው የፖርቹጋል ሚሲዮናውያን ጥማታቸውን ለማርካት ቢተጉም በኢትዮጵያውያን ሊቃውንትና ምእመናን ጥረት ከሽፏል።
 

ሕንድ ውስጥ ይንቀሳቀስ የነበረው ቸርች ሚሽነሪ ሶሳይቲ /CMS/ የተባለው የአንግሊካን ፕሮቴስታንቶች ሚሽን በንጉሥ ሳህለ ሥላሴ ዘመን አይዘንበርግና ክራፕፍ የተባሉ ግለሰቦችን ወደ ኢትዮጵያ ከመላክ ጀምሮ በተከታታይ በሌሎችም ሚሽነሪዎች ጥረት ቢያደርግም ከስለላ ያለፈ ፋይዳ አልነበረውም። ቅኝ አገዛዙም ሆነ ቤተክርስቲያኒቱን ካቶሊካዊ  ወይም ፕሮቴስታንት የማድረግ ወይም የመከፋፈሉ ሁኔታ ሕንድ ውስጥ እን ደያዘላቸው በዚህ ሀገር ሊሳካ አልቻለም፤ ሌላ በኦርቶዶክሳዊነት ስም የተመሠረተ የተለየ የእምነት ተቋም የለምና።
 

በቤተክርስቲያኒቱ በእነርሱ ምክንያት ወይም በሌላ ምክንያት የሚፈጠሩ ልዩነቶችን በነገሥታቱና በሊቃውንቱ ከፍተኛ ጥረት በጉባኤዎች እየተፈቱ ያለምንም የውጭ ኃይሎች ጣልቃ ገብነት አንድነታችንን ጠብቀን ኖረናል። ይህም ለቤተክርስቲያን ብቻ ሳይሆን ለሀገር አንድነትም መሠረት ሆኗል።

የሀገሪቱ ነጻነትና አንድነት እንዲሁም ለረጅም ዘመን የኖረ የሃይማኖት ታሪክ ባለቤትነት በተለይ አፍሪካውያንንና የዓለምን ጥቁር ሕዝቦች እየሳበ መምጣቱ ለእነዚህ ኃይሎች የበለጠ የሚያንገበግብ ሆኖባቸዋል። ስለዚህ መላውን አፍሪካና ሌላውንም ሕዝብ ለመማረክ የኢትዮጵያን ቤተክርስቲያን መቆጣጠር፤ የተለየና የተወገዘ አስተምህሮአቸውን መጫን ወይም አንሸራቶ ማስገባት፤ ካልሆነም አዳክሞና አጥፍቶ ሌላ መሠረት በመሥራት ወደሌላው ወገን  የመዝመት ብርቱ ዓላማ አላቸው።

በተለይ በአሁን ጊዜ ማንኛውም ወገን በሀገሪቱ የራሱን ሃይማኖት በነጻነት የማራመድ መብት ያለው በመሆኑ የራሳቸውን አምልኮ የሚፈጽሙበት በዓይነት ብዙ ድርጅት ቢኖራቸውም የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በዓለም ላይ ያላትን የሃይማኖት ታሪክ ክብርና ትኩረት ያህል የማግኘት ምንም እድል እንደሌላቸው ተገንዝበዋል። በመሆኑም ሌላ ዘርፈ ብዙ መላ መዘየድ ጊዜው ጠይቁአቸዋል። ለዚህ የመረጡት አካሔድ «ተሐድሶ» የተባለውን የመናፍቃን ተላላኪ ኃይል በቤተክርስቲያን ውስጥ ማስረግ ነው።

«ተሐድሶ» የተባለው በተለያዩ መናፍቃን የሚደገፍ፣ ተቋማዊ ሆኖ ያልተደራጀ፣ ወጥ አስተምህሮ የሌለው፤ ነገር ግን ኦርቶዶክሳዊ ነኝ ብሎ የተሰለፈ፤ በየትኛውም መንገድ የቀጠሩትን የተለያዩ የመናፍቃን ፍላጎት ለማርካት  ቤተክርስቲያንን ለመቆጣጠር በውስጥና በውጭ ያሸመቀ ኃይል ነው።  ከዚህ ቀደም ማኅበራችን ይህንኑ በኅቡዕ የተደራጀ የተወሰኑ መነኮሳት፣ መርጌቶችና  የዲያቆናት የተላላኪነትና የምንፍቅና አካሔድን ካጋለጠ ጀምሮ ግን ካህናትና ምእመናን ጉዳዩን ወደ ማጤን እንዲገቡ አስገድዷል። ይሁን እንጅ በጊዜው ለአንዳንዶች እነዚህ አካላት የቤተክርስቲያን ጠላቶች ሳይሆኑ የማኅበረ ቅዱሳን የአገልግሎት ተገዳዳሪዎች ተደርገው ይታሰቡ ነበር። ይህን ድብቅ እንቅስቃሴያቸውን የሚከታተል ታዛቢ፣ ተመልካች በየሰንበት ትምህርት ቤቱ መኖሩን፤ ካህናቱም እያንዳንዱን እንቅስቃሴ መፈተሽ በመጀመራቸው ለስውር  እንቅስቃሴአቸው በር እየተዘጋ መምጣቱን ተረዱ። በመሆኑም ያላቸው ብቸኛ አማራጭ ግእዝ ተናጋሪ መናፍቅ ሆነው፡ የቤተክርስቲያንን መዓርጋት በስማቸው እየቀጸሉ፡ ለመጻሕፍት፣ መጽሔትና ጋዜጦቻቸው ኦርቶዶክሳዊ ገጽታ እያላበሱ በግልጽ ፕሮቴስታንታዊ አስተምህሮን መዝራት ጀመሩ። ይህ ደግሞ የ«ተሐድሶ»ን እንቅስቃሴ እውነተኛ ምንነትና በቤተክርስቲያን ጠላትነት የተሰለፈ ኃይል እንጂ የማኅበረ ቅዱሳን የአገልግሎት ተገዳዳሪ አለመሆኑን በራሱ እንቅስቃሴ ግልጽ አደረገ።

በመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ላይ የተመሠረተው ኑፋቄን የመዝራት ስልት በመምህራንና በሊቃውንቱ በተደረገው ለእምነት ጠበቃ የመሆን ተከታታይ እንቅስቃሴ ዋጋ እያጣ ሲመጣ ክርክራቸውን ወደ ገድላትና ድርሳናት በማዞር የነርሱን የኑፋቄ ዘር ከማምከኑ እንቅስቃሴ ሊቃውንቱ ዞር ብለው ቤተክርስቲያኒቱ ብቻ በምትጠቀምባቸው በራሷ መጻሕፍት ላይ በመከራከር ሊቃውንቱ ጊዜ እንዲያጠፉ፤ ከተቻለም በቤተክርስቲያን መከፋፈል እንዲፈጠር ተንቀሳቅሰዋል። ይህንን ለማድረግም ግእዝ ጠቃሽ ነን የሚሉ፤ በማኩረፍ፣ ጥቅምን በመፈለግና በመታለል ወዘተ ወጥተው በየጥጋጥጉ የሚወራጩ መርጌቶችን በመጠቀም ነው። ይህ ደግሞ ከመቶ ዓመት በፊት ከሁለት ምዕተ ዓመታት ላላነሰ ጊዜ የቤተክርስቲያኒቱን ሊቃውንት ሲያተራምሱበት እንደቆዩት የቅባትና የጸጋ አስተምህሮ የቤት ሥራ ዓይነት ለሊቃውንቱ የመስጠት ስልት ነው። እነዚሁ «ተሐድሶ» ብለው ራሳቸውን የሚጠሩት የመናፍቃን ተላላኪዎች ቤተክርስቲያናችንን ለመቆጣጠር ያስችለናል የሚሉትን የትኛውንም ስልት ከመጠቀም ወደኋላ የማይሉ አካላት ናቸው። ጎሳና ጎጥን ለማናከስ፣ በፖለቲካ ጉዳዮች በማስመሰል ለመክሰስ፣ ስም በማጥፋት አንዱን በአንዱ ላይ ለማነሣሣት ወዘተ ይጥራሉ፤ እየጣሩም ነው።

የ«ተሐድሶ» ኃይል ከውጭ ተበታትኖ ያለ ፈታኝ ይምሰል እንጂ በሁለት መልኩ ተሰልፎ የሚሠራ እርስ በእርሱ የሚተዋወቅም የማይተዋወቅም ኃይል ያለው ነው። በአንድ ገጽ ከውጭ ኦሮቶዶክሳዊ ነኝ እያለ በግእዝ እየጠቀሰ፣ አሉባልታ እያራባ፣ የሊቃውንቱን ትምህርት እያጣመመ፤ ስልት በመሰለው መንገድ ሁሉ ከአርዮሳውያን ጀምሮ እስከ ንስጥሮሳውያን፣ ከሊዮን እስከ ሉተር የተነሡ መናፍቃንን ትምህርት በተለያዩ መንገዶች /መጻሕፍት በመጻፍ፣ መጽሔትና ጋዜጣ በማሳተም፣ በራሪ ወረቀት በማሳተም/ እየዘራ፡ ከቤተክርስቲያን ውጡ እያለ ወደ ውጭ የሚስብ በፈሪሳውያን መንገድ የቆመ ጎታች ኃይል /pulling power/ ነው። ሌላው ደግሞ ከውስጥ ሆኖ  አውቀውም ሆነ ሳያውቁ ለዓላማው ተባባሪ ከሆኑ የቤተክርስቲያኒቱ የውስጥ አካላት ጋር በተለያየ መንገድ ምእመናንን እያስደነበረ የሚያስወጣ ገፊ ሃይል /pushing power/ ሆኖ በአስቆርቱ ይሁዳ መንገድ የቆመ ነው።
 
በዚሀ ይሁዳዊ ግብር ውስጥ የሚሳተፈው ተላላኪ ቤተክርስቲያንን አሳልፎ ለመስጠት በሚያስችለው መመሳሰል ውስጥ ያለ ሲሆን በምእመናንና በሊቃውንቱ ፊት ተጨባጭ መረጃና ማስረጃ እስከሚቀርብብኝ ድረስ ተሰውሬ እሠራለሁ ብሎ የሚያስብ በተናጠልና በቡድን የሚሹለከለክ ኃይል ነው።

ይሄ ወገን በቤተክርስቲያናችን ውስጥ ሆኖ በተለያዩ የቤተክርስቲያኒቱ መዋቅሮች ውስጥ እንቅፋት እየፈጠረ ቤተ ክርስቲያኒቱ ብቁ አገልግሎት እንዳትሰጥ ያዳክማል። የቤተክርስቲያኒቱ አስተዳደር የበቃና የነቃ አገልግሎት ፈጽሞ ካህናትና ምእመናንን እንዳያረካ፤ በምእመናንና በሊቃውንቱ በቤተ ክርስቲያኒቱም አስተዳደር መካከል መለያየትና መጠራጠር እንዲነግሥ የበኩሉን ሚና ይጫወታል። የካህናትን ስምና ክብር በማጉደፍ ምእመናን ለክህነት ክብር እንዳይኖራቸው፤ የንስሐ አባትና ልጅ ግነኙነታቸው እንዲላላ ያደርጋል።  በካህናት ወይም በሊቃውንት አባቶች በኩል የሚታዩ ግድፈቶች ወይም ጥፋቶችን በማጯጯኽ አጠቃላይ የቤተክርስቲያኒቱ ድክመት አድርጎ በማወራረድ የሚያታልል፤ ምእመናን በቤተ ክርስቲያኒቱ አካሔድ ተስፋ እንዲቆርጡ በጋዜጣና በመሳሰሉት ብዙኃን መገናኛዎች በመዝራት ትርፍ ለማግኘት የሚጥር ነው። ብርቱ አገልግሎት በመፈጸም የቤተክርስቲያኒቱን ተልእኮ ለመወጣት ጥረት የሚያደርጉ ማኅበራትን፣ ሰንበት ትምህርት ቤቶችን፣ መምህራንን፣ አባቶችን ስም በማጥፋት ከምእመናን ለመለይት ይንቀሳቀሳል። «ተሐድሶ» ለዚህ ግብሩ ከምእመናን ጀምሮ እስከ ታላላቅ አባቶች  ድረስ አውቀውም ሳያውቁም የአጀንዳው አስፈጻሚ ወይም መሰላል የሚሆኑ ድጋፍ ሰጭዎችን ለመመልምል ጥረት ያደርጋል:: እነዚህም አካላት የቤተክርስቲያኒቱን አሠራር እንዲያውኩ ብቻ ሳይሆን ገጽታዋን በማበላሸት መንጋው ደንብሮ እንዲበተን መሣሪያ ለማድረግ ነው:: የቤተክርስቲያኒቱን አገልጋዮች መለያ ለብሰው ወይም መስለው፣ በማይገባ ጊዜና ቦታ የማይገባ ነገር ሲያደርጉ በመታየት ምእመናንን በማስቆጣት ላይ ያሉ ሐሳዌ መነኮሳት፣ ቀሳውስት፣ ባህታውያን ወዘተ የዚህ ስልት አስፈጻሚዎች ናቸው:: በመልካም ግብር ለመጽናት ባለመቻላቸው ተስፋ ቆርጠው አላግባብ በእንዝህላልነት የሚራመዱ አንዳንድ አገልጋዮችም የዚህ የጥፋት ዓላማ ተባባሪዎች እየሆኑ ነው:: ተግባራቸው ምእመናንን ከቤተክርስቲያን አስወጥቶ  የሚጥል በመሆኑ በውስጥ እየሠራ ያለው የ«ተሐድሶ» ገፊ ኃይል መሣሪያ ሆነዋል:: ቢያንስ ምእመናንን ላለማሰናከል ጥንቃቄ ሲያደርጉ አታይምና::

ከሁሉም በላይ አሳሳቢው አካሔድ ግን የቤተክርስቲያኒቱን ሐዋርያዊ ተልእኮ ወዴትም እንዳይራመድ አሳስሮ ለማስቀመጥ፤ ይህንን የ«ተሐድሶ» መረብ በጥሰው በማለፍ ለስብከተ ወንጌል አገልግሎት  የሚንቀሳቀሱ አካላትንም ከአስተዳደሩ በማ ጋጨት ወይም ለመከፋፈል በመሞከር ወዘተ ምንም ዓይነት ውጤታማ የአገልግሎት እንቅስቃሴ እንዳይደረግ የሚችለውን ያህል ጥረት ማድረግ ነው:: ቤተ ክርስቲያን ያላትን ሀብት በአግባቡ ጥቅም ላይ አውላ መንፈሳዊ አገልግሎቱን ማቀላጠፍ እንዳትችል ለማድረግ፡ ከዚያም አልፎ የካህናቱን የኑሮ ሁኔታ ሊያሻሽሉ የሚችሉ ውጤታማ ፕሮጄክቶች ስልታዊ በሆነ መንገድ ተግባራዊ እንዳይደረጉ፤ የቤተክርስቲያን የአገልግሎት ተቋማት የመፈጸም አቅም እንዳይጎለብት የተለያዩ መሰናክሎችንና ውዥንብሮችን ለመፍጠር ይጥራል:: ይህን ውዥንብር «ተሐድሶ» የሚፈልግበት ወሳኝ ምክንያት በቤተክርስቲያኒቱ አጠቃላይ አካሔድ አለመርካት እንዲኖር፤ ተስፋ መቁረጥም በምእመናንና ካህናቱ ዘንድ እንዲሰፍን፤ ከዚያም መከፋፈል እንዲፈጠር ለማድረግ ነው::በቤተክርስቲያን አካባቢ አልፎ አልፎ የሚፈጠሩ ውዝንብሮችና ዓላማና ግባቸው የማይታወቁ መጠላለፎች በቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ ገፊ ኃይሎች ሆነው በስውርና በግልጽ የሚንቀሳቀሱ የ«ተሐድሶ» መረብ አባላትና ተባባሪዎቻቸው የሚፈጥሯቸው ውዝግቦች ናቸው::

እነዚህ ገጽታን በማጉደፍና ቁሳዊ ጥቅሞቻቸውን ለማርካት ቤተክርስቲያኒቱን እስከመሸጥ የተሰለፉ አካላት በሕግና በቀኖና መሠረት ቤተክርስቲያን እንዳትሠራ፤ በየትኞቹም ጉዳዮች ለቁጥጥር የሚያመች ማዕከላዊ አሠራር እንዳይዘረጋ ይታገላሉ:: ይህንንም የሚያደርጉበት ምክንያት አዲስ የኑፋቄ ትምህትን አንሸራቶ ለማስገባት ለሚተጉበት እንቅስቃሴያቸው የተመቹ ሁኔታዎችን  ለመትከልና ለ«ተሐድሶ» እንቅስቃሴ አውቀውም ሳያውቁም ገፊ ኃይል በመሆን ለተሰለፉ ግለሰቦችና ቡድኖች ወረታ የሚሆን፣  ለሥጋዊ ፍላጎታቸው የሚጠቀሙበትን ንግድ በስብከተ ውንጌል ስም ለማስፋፋት ነው::

«ተሐድሶ» ቤተክርስቲያኒቱ ያላትን አሠራር በማስረጀት፣ ፕሮቴስታንታዊ አስተምህሮን ወደ ቤተክርስቲያን ለማንሸራተት ሲተጋ ለቤተክርስቲያን የሚያስፈልጋትን የአሠራር የመዋቅር እና የመፈጸም አቅም ተሐድሶ /Renaissance/  ግን ለመቅበር ይታገላል:: ቤተክርስቲያናችን በራሷ ሉዓላዊ አስተዳደር መመራት የጀመረችበት ጊዜ መቶ ዓመት ያልሞላው ከመሆኑ ጋር ተያይዞ እንዲሁም ከዚያም በኋላ የተፈጠሩ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ለውጦች ባስከተሉት ጫና በአሠራር፣ በመዋቅርና በመፈጸም አቅም በተከታታይ ሊደረጉ የሚገባቸው የእድገትና የለውጥ እንቅስቃሴዎች ሳይታሰቡ፤ ሳይተገበሩም ቆይተዋል:: «ተሐድሶ» የተባለው ይህ የመናፍቃን ተላላኪ ደግሞ አስፈላጊውን የለውጥና የማሻሻያ እርምጃ በማፈን በአውሮፓ በመካከለኛው የታሪክ ዘመን እንደተደረገው በተሐድሶ ስም ሌላ የእምነት አስተምህሮን አንሸራቶ ለማስገባት ይሠራል::

ተፈላጊውን ማሻሻያ የሚጠላበት ምክንያት ቤተክርስቲያን በአፈጻጸም ደካማ እየሆነች ስትሔድ ምናልባትም በሚያስቆጣ ደረጃ ምእመናን ያልተደራጀና ከክርስትና ሥነምግባር ውጭ የሆነ አብዮታዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ገብተው በካህናቱ ላይ እንዲነሡ፤  ቤተክርስቲያንም እንድትበታተን ለማድረግ የታለመ ነው:: አሁንም በግልጽ እየታየ ያለው የአባቶች መወጋገዝና መከፋፈል እየጨመረ በጎጥና በዘር ላይ የተመሠረተ የተበታተነ አደረጃጀት እንዲኖር ለማድረግ ነው:: ይህንንም አሁን «ተሐድሶ» በግልጽ እየጻፈ በሚያወጣው መጻሕፍት ከእነ እገሌ ወገን ጳጳሳት ለምን አይሾሙም እያለ የሚያነሣው ከንቱ ልፍለፋ ይህን ያሳያል:: የካቶሊክ ቤተ እምነት በመካከለኛው የአውሮፓ የታሪክ ዘመን በነበረበት የጊዜውን ማኅበረሰብ ያለማርካት ችግር በተፈጠረው ተቃውሞ ቤተ እምነቱን ከሁለት የከፈለ ድንገተኛ ክስተት በ«ተሐድሶ» ስም ማስተናገዱ ይታወቃል:: በዚህ ያለው የመናፍቃን ተላላኪ «ተሐድሶ» ያንን መሰል ተከፍሎ በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ውስጥ እንዲፈጠር ያልማል:: ለዚህም ለተቃውሞ የሚያነሣሡ ብልሹ አሠራሮች በየደረጃው ባሉ የቤተክርስቲያኒቱ አስተዳደር ውስጥ እንዲሰፍን ገፊ ኃይል ሆኖ በውስጥ በሚሹለከለከው መረቡ በኩል ይጥራል:: ማኅበረ ቅዱሳን ከዚህ በፊት በመል እክቱም ደጋግሞ እንደጠቀሰው ቤተ ክርስቲያን ጠፍረው የያዙአትን ኋላቀርና ብልሹ አሠራሮች በተሻለና ሰውና እግዚአብሔርን ደስ በሚያሰኝ፣ መተማመንንና አንድነትን በሚያጸና አሠራር መተካተ እንዳለባቸው ያምናል:: ይህንን ማድረግ ካልቻልን «ተሐድሶ» «ለውጥ! ለውጥ!» በሚለው ድምፅ ውስጥ እነዚህን የአሠራር ችግሮቻችንን ሽፋን አድርጎ በግልጽ የጀመረውን ፕሮቴስታንታዊ አስተምህሮ በሒደት አንሸራቶ ማስገባት የሚችልበት እድል እንሰጠዋለን:: ስለዚህ ያሉብንን የአሠራር ውስንነቶች በሁሉም ካህናትና ሕዝበ ክርስቲያን ተሳትፎ መቅረፍና ወደተፈላጊው ትንሣኤ ልቡና መድረስ አለብን:: ለዚህም ሁሉም የክርስቲያን ወገን ሓላፊነት ቢኖርበትም የብፁዓን አባቶች ድርሻ የጎላ ነው::

ብፁዓን አባቶቻችን በታሪክ አጋጣሚ ይህ የ«ተሐድሶ» መሰሪ ኃይል በውስጥም በውጭም በተደራጀበት ዘመን ላይ ይህቺን በብዙዎች መንፈሳዊ ተጋድሎ እዚህ የደረሰች ቤተክርስቲያን ባለደራዎች ናቸው:: አባቶች ለመንጋው የማይራሩ «ተሐድሶ»ን የመሰሉ ጨካኞች በታዩ ጊዜ ሁሉ ለራሳቸውና ለመንጋው እንዲጠነቀቁ መንፈስ ቅዱስ የዘወትር ማሳሰቢያን የሰጣቸው ናቸው:: በመሆኑም ጊዜው የሚጠይቀውን የጥንቃቄ እርምጃ ከሀገረ ስብከቶቻቸው ጀምሮ እስከ መንበረ ፓትርያርክ ድረስ የሚወስዱበት፣ ለመንፈሳዊ ተጋድሎ ራሳቸውን የሚያዘጋጁበት ወቅት ነው:: ከምንም በላይ «ተሐድሶ» በአባቶችና በልጆች መካከል መለያየትን ለማስፈን የሚሠራ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚፈጠሩ ችግሮችን ሁሉ ያሉት ብፁዓን አባቶች የመፍታተት አቅም የሌላቸው፣ ለእውነትም የመቆም ቁርጠኝነት የሌላቸው አድርጎ ስለሚያሳይ ውጤቱ ቤተክርስቲያንን መጉዳቱ ብቻ ሳይሆን የብፁዓን አባቶችን ክብርና ስብእና የሚጎዳ ሁኔታ ሊከተል ይችላል::

የ«ተሐድሶ» ግብና ዓላማ መንጋውን ከበረቱ መበተን በመሆኑ አባት የምንሆ ንላቸውን ልጆች ከማሳጣቱም ሌላ በታሪክ ተወቃሽ ሊያደርግ የሚችል ነው:: ከዚያም አልፎ በአሠራሮቻችን ድክመት  ክብረ ክህነቱ ሊጎዳ ስለሚችል «ተሐድሶ» ለሚፈልገው ሁሉም ሰው ካህን ነው ወደሚለው ፕሮቴስታንታዊ  ጸረ ሃይማኖት አቋም ያሻግራል:: ስለዚህ በቤተክርስቲያን ውስጥ ተሸሽገው ለሚሠሩ የትኞቹም ገፊ ኃይሎች እንቅስቃሴ የሚመቹ ክፍተቶችን መድፈን፤ በነገሮች ሁሉ የጸናና የተጠና ማዕከላዊ አሠራርን ማስፈን፤ የቤተክርስቲያኒቱ ቀኖናና ሕግጋት ተጠብቆ እንዲሠራ ቁርጠኛ አቋም መያዝ ይገባዋል::


ማኅበረ ቅዱሳን አባቶች እንዲረዱለት የሚፈልገውም ወሳኝ ቁም ነገር እነርሱ ጳጳሳት ሆነው የተሾሙላት ቤተክርስቲያን የሃይማኖት ትምህርት ክብርና ታሪክ ተጠብቆ፡  በብዙ ሊቃውንት ተጋድሎ ተጠብቆ ዘመናትን ተሻግሮ የተቀበልነው ማራኪ ሥርዓትም ቀጣዩ ትውልድ የማየትና የመሳተፍ እድል እንዲኖረው ማድረግ ነው:: የሃይማኖት ትምህርት በዚህ ረገድ አባቶች ለሚኖራቸው እርምጃ ሁሉ በየትኛውም መልክ ቢሆን ድጋፍ መስጠት ማኅበራችን የተቋቋመበት ዓላማ መሆኑንም ያምናል:: በመሆኑም ይህ እውን እንዳይሆን የሚታገሉ የ«ተሐድሶ» መናፍቃንን ሰርጎ ገብ የጥፋት አካሔድ ለመመከት ከአባቶች ቁርጠኛ አቋምና ተከታታይ ሥራዎች ሊኖሩ ይገባል::

ቆሞሳት ቀሳውስት ዲያቆናትና በአጠቃላይ ከብፁዓን አባቶች ቀጥሎ ሓላፊነት ያለባቸው የቤተክህነቱ ወገን ሁሉ ከአጥቢያ እስከ ጠቅላይ ቤተክህነት ባለው አገልግሎት ውስጥ የዚህች ታሪካዊት ቤተክርስቲያን ባላደራዎች እንዲሆኑ መንፈስ ቅዱስ በጳጳሳት እጅ የሾማቸው የመንጋው ጠባቂዎች ናቸው:: በመሆኑም መንጋውን ለመበተን በውስጥና በውጭ ተደራጅቶ በዓይነት ብዙ ፈተናዎችን ለማስከተል እየሠራ ያለውን የ«ተሐድሶ» የኑፋቄ ፍላጻ በመንፈስ ቅዱስ ጥበብ በጸሎት በጾም ከማምከን ጀምሮ ባልንጀሮቻችን በተለያዩ ምክንያቶች በ«ተሐድሶ» ገፊ ኃይል መረብ ውስጥ እየተጠለፉ የጥፋቱ ተባባሪ እንዳይሆኑ መጠበቅ ይገባናል:: የ«ተሐድሶ» እንቅስቃሴ በዋናነት ምስጢረ ክህነትን የሚክድ፣ ሁሉን እንደ ካህን የሚቆጥረውን ፕሮቴስታንታዊ አስተምህሮ አንሸራቶ የማስገባት ፍላጎት ያለው መሆኑን በግልጽ በሚጽፋቸው መልእክቶች መረዳት ይቻላል:: በመሆኑም «ተሐድሶ» በተባለው የመናፍቃን ተላላኪዎች ተንኮል በሃይማኖት፣ በአካልም ሆነ በሥነልቦና የመጀመሪያው ተጎጂዎች የቤተክህነቱ ወገኖች መሆናቸው አሌ የማይባል ነው:: ስለዚህ በየደረጃው ባሉ የቤተክርስቲያናችን የአስተዳደር መዋቅሮች የሚፈጠሩ ችግሮች ዘገምተኛና ስልታዊ ያልሆኑ ኋላቀር አሠራሮች ሌሎችም ችግሮች የሚያስከትሉብንን ተጽእኖዎች ተስፋ ሳያስቆርጡን ወደተሻለ አሠራር ለመግባት  እየጣርን የእነዚህን መናፍቃን የውስጥና የውጭ እንቅስቃሴ በእግዚአብሔር ረድኤት በብቃት መቋቋም አለብን:: ፈተናውንም ልንሻገረው ይገባል:: ቤተክርስቲያኒቱ ያላትን ሀብት ስልታዊ በሆነ መንገድ ማኅበረ ካህናቱንና ከዚያም አልፎ  ለሀገር እድገት ትርጉም ባለው መልክ ባለመጠቀም የካህናቱ ኑሮ እየተጎዳ ገዳማትና አድባራት እየተፈተኑ ቢሆንም፤ ይህንን ውስጣዊ ችግር የሚፈታ ጠንካራና ዘመናዊ የአስተዳደር መዋቅር ተግባራዊ ለማድረግ ከመታገል ጋር የ«ተሐድሶ»ን መሰሪ መረብ መበጣጠስ አለብን::

ይልቁንም የችግሮቻችን ሁሉ ምንጭ ቤተክርስቲያናችንን ለማዳከም ከአሁኑ የበለጠ ጠንካራ አሠራር ዘርግታ  ቀድሞ  ከነበራት ክብርና ታሪክ በላይ መሥራት እንዳትችል የሚፈልጉ በዓይነት ብዙ የሆኑ አጽራረ ቤተክርስቲያን በግልጽና በስውር የሚሠሩት ደባ በመሆኑ በፍጹም ክርስቲያናዊ ወንድማማችነት ተያይዘን መርዛቸውን ማርከስ አለብን:: በተለይ ከውስጥ ሆኖ ገጽታን በማጉደፍ ክርስቲያኖችን በየምክንያቱ በማስደንበር ገፍቶ ለማስወጣት የሚሠራውን የ«ተሐድሶ» ገፊ ሃይል እንቅስቃሴ ለማምከን ተባብረን መቆም አለብን:: ይህ ኃይል በጎ የሚመስሉ ገጽታዎችን ተላብሶ የሚጫዎት የጥፋት ተዋናይ በመሆኑ ከመቼውም ጊዜ በላይ ካህናት ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል:: «ተሐድሶ» በሚፈጠሩ ጥፋቶችም ሁሉ ምእመናን በካህ ናቱ እየፈረዱ፣ በጥላቻም ካህናቱን እያዩ እንዲሄዱ የማለያየት ተልእኮም ስላለው በነገር ሁሉ ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባል:: በየመዋቅሮቻችን ያሉ አስተዳደራዊ ዘይቤዎችንም  ፈጣንና አርኪ ለማድረግ ተገቢ የአሠራር ማሻሻያ ልናደርግ ይገባል:: ለዚህም መተባበር አለብን:: ይህንን ደግሞ የግድ የሚያደርገው ወቅቱ ነው:: ወቅቱ ግድ የሚለን «ተሐድሶ» እንደሚለው ሃይማኖታችንን እንድንለውጥ ሳይሆን በዚህ ጊዜ ውስጥ ሃይማኖታችንን የምናስተምርበት፣ የምናጸናበት፣ ያሉንን ሥርዓተ አምልኮ ለቀጣዩም ትውልድ የምናስተላልፍበትን የተሻለ አስተዳደራዊ ሁኔታ ማስፈን ነው:: ለዚህም ካህናት ሁሉ ሊተባበሩ ይገባል እንላለን::

ሰንበት ትምህርት ቤቶችም «ተሐድሶ» ቤተክርስቲያኒቱን ለማዳከም መሣሪያ ሊያደርጋቸው የሚፈልጋቸው የቤተክርስቲያኒቱ የአገልግሎት ተቋማት ናቸው:: በመሆኑም ይህንን ደባ ከማክሸፍ አንጻር የአገልግሎት አሰጣጣቸውን እየቃኙ ወደ ከፍተኛ የስብከት ወንጌል መድረክነት ሊለወጡ ይገባል:: ሰንበት ት/ቤቶች መረዳት ያለባቸው ወሳኝ ነጥብ የአገልግሎት አሰጣጣችን ወደሚፈለገው ደረጃ አለማደግ በምእመናን ዘንድ ከፍተኛ የቃለ እግዚአብሔር ጥማት ይፈጥራል:: ይህ ደግሞ የራሳቸውን ንግድ ሊያጧጡፉ ለሚፈልጉ አንዳንድ ሰባክያንና ዘማርያን በር ከፍቷል::«ተሐድሶ» ፕሮቴስታንታዊ አስተምህሮን አንሸራቶ በማለማመድ ሊያስገባበት የሚፈልገው ክፍተት ይህ ነው::ስለዚህ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ከነበረው በተሻለ አፈጻጸም ውስጥ ሊገኙ ይገባል:: በአጥቢያ ቤተክርስቲያናቸው ውስጥ የሚደረጉ የትኞቹንም እንቅስቃሴዎች የመከታተል፣ የአጥቢያውን ሰበካ ጉባኤ በሚያከናውናቸው መንፈሳዊና ልማታዊ ተግባራት ውስጥ ድጋፍ መስጠት የአጥቢያውንም ምእመናን ማስተባበር በአጥቢያው ውስጥ እንግዳ ትምህርትና ተገቢ ያልሆኑ ሥርዓቶችን ለማስረግ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን በግልጽ የመቃወም ሓላፊነትም አለባቸው:: አሁን አሁን በአንዳንድ ጠንካራ ሰንበት ትምህርት ቤቶች እንደሚደረገው የአብነት ትምህርቶችን ለሕፃናትና ወጣቶች በመስጠት፣ ካህናትን የሚደግፉና የሚተኩ ወጣቶችን ማፍራት፣ ወቅቱን የሚዋጅ አጽራረ ቤተክርስቲያንን የሚያስታግስ ተከታታይ ትምህርቶችን አርኪ በሆነ መንገድ በዓይነትና በደረጃ ለይቶ መስጠት፣ ስልታዊ በሆኑ የመረጃ ቅብብሎሽ እየታገዙ የ«ተሐድሶ»ን ገፊና ጎታች ኃይል እንቅስቃሴ ለመግታት መተባበር አለባቸው:: በተለይ ወቅቱ ተራ በሆኑ የወጣትነት ስሜቶች የምንዘናጋበት ባለመሆኑ ቤተክርስቲያን ለዚህ ትውልድና ለዚህች ሀገር ማበርከት ያለባትን አስተዋጽኦ ማበርከት እንድትችል የማያቋርጥ ተሳትፎ ልናደርግ ይገባል::

ማኅበራትም ለቤተክርስቲያኒቱ አገልግሎት በተለያየ መንገድ ድጋፍ ለማድረግ የተቋቋሙ በመሆናቸው፡ የ«ተሐድሶ» ሤረኛ እንቅስቃሴ ሰለባና ተባባሪ እንዳይሆኑ ሊጠነቀቁ ይገባል:: ማኅበራት ከመገንባት ይልቅ አፍራሽ በሆነ መንገድ ላይ ሳያውቁት እንዳይቆሙ የሚችሉትን ያህል ጥንቃቄ እያደረጉ ለቤተክርስቲያኒቱ አንድነት መሥራት አለባቸው::በተቻለ መጠን ቤተእግዚአብሔርን ማገልገል የሚፈልጉ የተለያዩ ማኅበራትን ማስተባበር የምትችልበትን አቅም ቤተክርስቲያን አግኝታ፣  ጠንካራ ማዕከላዊ አሠራር ሰፍኖ ተቀናጅተን መሥራት የምንችልበት ሁኔታ እንዲፈጠር ልንተጋ ይገባል:: የማኅበሮቻችን አባላት በውስጥና በውጭ ተደራጅቶ ቤተክርስቲያንን ለማዳከምና ለማፍረስ የሚጥረውን የ«ተሐድሶ» ተንኮል ነቅተው ሊከላከሉ፤ ለዚያ የተንኮል ሥራው ምቹ ሆነው የሚንቀሳቁ ግለሰቦችንና ቡድኖችን ሊመክሩና ሊያስተካክሉ ካልሆነም ሊለዩ ይገባቸዋል እንላለን::

ምእመናን የዚህች የእግዚአብሔር የጸጋ ግምጃ ቤት በሆነች ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በመንፈስ ተወልደው በቃሉ ወተት እያደጉ ያሉ፤ የአገልግሎቱ ደጋፊ፣ ተቀባይ፣ ተሳታፊም በመሆናቸው ቤተክርስቲያን ማለት እነሱ ራሳቸው እንደሆኑ መረዳት ይገባቸዋል:: አባቶቻችን የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ሆኖ ለመባረክ ክርስቶስ ያደረገልንን ማዳንም አምነው፤ በየዘመናቱ የምንነሣ እኛ ልጆቻቸውም በዚያ ጸንተን ለቀጣዩም ትውልድ ባለአደራ እንድንሆን አድርገዋል:: ይህንን ሓላፊነት የተረዱ በየዘመኑ የተነሡ ምእመናን እስከ ሕይወት መስዋዕትነት ድረስ ዋጋ በመክፈል ቤተክርስቲያናቸውን ሊያፈርስ ከመጣ የዲያብሎስ ሠራዊት ጋር ተጋድለዋል:: አሸናፊም ሆነዋል:: በዚህም ምክንያት ምዕተ ዓመታትን ተሻግሮ የመጣን ማራኪ ሥርዓተ ቤተክርስቲያን፣ ሕይወትን የሚሰጥ ሃይማኖትን ለማየትና ለመመስከር በቅተናል:: የያሬድን ዜማ፣ የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫን ሰዓታት የበርካታ ሊቃውንትን ትምህርትና ቅዳሴ የመስማት እድል አግኝተናል::

ይህንን እድል ለቀጣዩ ትውልድ የማስተላለፉ አደራ በእኛ ትውልድ ላይ በወደቀበት በዚህ የታሪክ አጋጣሚ ውስጥ ደግሞ በቀጣዩ ትውልድ ውስጥ በሚሰበሰበው መንጋ ላይ መጨከን የለብንም:: በየዘመናቱ ቤተክርስቲያንን ከአገልግሎት ለማዘግየት የሚወረወረው የሰይጣን ፍላጻ ዓይነቱ ይለያይ እንጂ ይኖራል:: አባቶቻችንም በእግዚአብሔር ረድኤት ያ ፍላጻ ቤተክርስቲያንን ከአገልግሎት እንዳያስተጓጉላት ዋጋ ከፍለዋል:: አሁን ደግሞ ከውስጥም ከውጭም የሚንበለበል «ተሐድሶ» የተባለ ፍላጻ እየወጋን ይገኛል:: የዚህ ሁሉ ውጊያው ዓላማ እናንተን ምእመናንን ከመንጋው ኅብረት ለይቶ ለምድ ለለበሰ ተኩላ ለመስጠት፤ ከተቻለም ራሳቸው ምእመናን የምታገለግላቸውን ቤተክርስቲያን በማጥፋቱ ሒደት እንዲሳተፉ ለማድረግ ነው:: ስለዚህ ምእመናን በዚህ አካሔድ ላይ በመንቃት ጥንቃቄ በተሞላበት እርምጃ ውስጥ እንድንገባ ያስፈልጋል:: በተለይ ትኩረት የሚስቡ የተለያዩ ሁኔታዎችን በስብከተ ወንጌል አገልግሎት ሒደት ውስጥ በማስገባት ብዙ መንጋ ከሰበሰቡ በኋላ ገንዘቡን  ከመብላት አልፈው በሒደት አዲስ ትምህርትን አምጥቶ በማለማመድ ወደ ፕሮቴስታንታዊ አስተምህሮ ማንሸራተት ይፈልጋሉ:: በዚህም ግማሹን መንጋ ይዞ ለመንጎድ ቀውንም በመምህራንና ዘማርያን ላይ እምነት በማሳጣት በቤተክርስቲያኒቱ የትኛውም የስብከተ ወንጌል ማዕድ ላይ እንዳይሳተፉ ለማድረግ ነው:: በመሆኑም ምእመናን ክርስቶስን ትኩር ብሎ ከማየት አዘንብለው በዓለም እንዳለው የግለሰቦች ዝና ገንቢና ሳያውቁት ለሥጋዊና ቡድናዊ ፍላጎታቸው መጠቀሚያ እንዳይሆኑ፤ ብሎም ውሎ አድሮ ለሚያስከትሉት ቤተክርስቲያንን የማዳከም ዘመቻ ተባባሪ እንዳንሆን ልንጠነቀቅ ይገባል:: ቤተክርስቲያን በአገልግሎት ሒደት ውስጥ ያሉባት ክፍተቶች እንዲሞሉ በጸሎት ከመትጋት ጋር የ«ተሐድሶ» ዘርፈ ብዙ ወጥመድ ለመበጣጠስ መቆም አለብን::
በአጠቃላይ «ተሐድሶ» ትናንት ሲያደርግ የነበረውን የተላላኪነት ሤራ ተልእኮ የሰጡት አካላት የሚሰጡትን የገንዘብና የቀሳቁሰ ሰፊ ድጋፍ በመጠቀም ከውጭ ፈሪሳዊ በሆነ መንገድ ከውስጥ ይሁዳዊ በሆነ ስልት ለመዝመት እየጣረ ነው:: ሰይጣን በርካታ ጠላቶችን በቤተ ክርስቲያናችን ላይ እያዘመተ ቢሆንም ከውጭ ያለውን ለማስታገስ እንዳትችል አንቆ የያዛትን የ«ተሐድሶ»ን መሰሪ ኃይል መለየትና በቤተክርስቲያናችን ውስጥ አገልግሎቱን በቅልጥፍና የሚመራ አስተዳደራዊ ትንሣኤ እንዲኖር ማድረግ ግን ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ መሆኑን ማኅበረ ቅዱሳን የጸና እምነት አለው:: ጉዳዩም የህልውና ጉዳይ መሆኑን ያምናል፡፡ ዋጋ ሊያስከፍል እንደሚችልም ያስባል:: ነገር ግን በተናጠልም ይሁን በኅብረት ክርስቲያናዊ ግዳጃችንን መወጣት ለነገ የማይባል ነው:: የራሳችንን ቤተክርስቲያን እንዳንጠብቅ የሚከለክለን ወይም በቁማችን ዓይናችንም እያየ ስትፈርስ እዩአት የሚለን አካል አለ ብለን አናምንም:: ምክንያቱም ቤተክርስቲያኒቱ ወልድ ዋሕድ ብለው የሚያምኑ፣ የቤተክርስቲያኒቱን ቀኖናና ሕግ ጠብቀው፣ አስከብረው የሚሔዱ ብፁዓን አባቶች፤ ቀን ከሌሊት በሚሰጡት የማያቋርጥ አገልግሎት መንጋውን የሚጠብቁ ካህናት፤ በዝማሬ በውዳሴ የሚተጉ ሰንበት ተማሪዎች፤ ሕይወት የሚያገኙባትን ኅብረት በሚሰጡት ዐሥራት በኩራት የሚጠብቁ ምእመናን ቤተክርስቲያን ነችና:: በተለይም ቅጥረኛ ሆኖ በውስጣችን ለመሸመቅ የሚጥረውን ጨካኝና መሰሪ የ«ተሐድሶ» እንቅስቃሴ መታገስ የማይቻል ነው:: ክቡር ዳዊት «ጠላትስ ቢሰድበኝ በታገስሁ ነበር፤ የሚጠላኝም አፉን በላዬ ከፍ ከፍ ቢያደርግ ከእርሱ በተሸሸግሁ ነበር፤ አንተ ሰው አንተ ግን እንደራሴ ነበርህ» /መዝ.4÷02/ እንዳለ የ«ተሐድሶ» ፍላጻ ከውስጥ የሚወረወር በመሆኑ የከፋ ነው:: ስለዚህ እኛ ሁላችን ቤተክርስቲያናችንን ተባብረን የመጠበቅ ሓላፊነት አለብን::  ማኅበረ ቅዱሳን በዚህ ረገድ ያለበትን ሓላፊነት በእግዚአብሔር ረድኤት ከሚመለከታቸው ሁሉም አካላት ጋር በመመካከር በተከታታይ ለመወጣት ያለውን ዝግጁነት በዚሁ አጋጣሚ ለመግለጽ ይወዳል::
                                                   ምንጭ፡ ሐመረ ተዋሕዶ ነሐሴ 2002 ዓ.ም.

2015 ኖቬምበር 7, ቅዳሜ

“ገርፎ የመጮኽ”፡- የተሐድሶዎች የማደናገሪያ ስልት


አትም ኢሜይል
ጥቅምት 26 ቀን 2008 ዓ.ም
ክፍል ሁለት
የተሐድሶዎችን እንቅስቃሴ በተመለከተ በክፍል አንድ ዝግጅታችን በማኅበረ ቅዱሳን ኅትመትና ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ ክፍል በስምዐ ጽድቅ ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ጋዜጣ በተከታታይ እየወጣ ያለውን ጽሑፍ አቅርበንላችሁ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ክፍል ሁለትን ደግሞ እነሆ፡-
አማናዊቷ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በክርስቶስ ደም ተመሥርታ በሐዋርያት ስብከት ከሰፋችበት ጊዜ ጀምሮ ያለ ፈተና አልጋ በአልጋ የሆነ ሕይወት የመራችበት ጊዜ የለም፣ ወደፊትም አይኖርምም፡፡ በሐዋርያት ዘመን ይሁዳና ቢጽሐሳውያን፣ በሐዋርያውያን አበው ዘመን ግኖስቲኮች፣ በሊቃውንት ዘመን አርዮስ፣ መቅዶንዮስ፣ ንስጥሮስና ልዮን ቤተ ክርስቲያንን ለመፈተን የተነሡ ነበሩ፡፡ ቤተ ክርስቲያን በየዘመናቱ እንደ ተጻራሪዎች አሳብ አሉታዊ፣ በእግዚአብሔር ፈቃድ ግን ለምእመናን መንፈሳዊ ዕድገት አዎንታዊ አስተዋጽኦ የነበራቸው ብዙ መከራዎችን አሳልፋለች፡፡ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ከእናንተ ጋር ነኝ የሚለው የጌታችንና የአምላካችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቃል ማረጋገጫ በዚህ ሁሉ በማያቋርጥ ማዕበል ውስጥ ቤተ ክርስቲያን ድል አድራጊ ሆና ወጀቡን ማለፍ መቻሏ ነው፡፡
04menafikanባለንበት ዘመን ቤተ ክርስቲያንን የማዳከምና ምእመናንን የመንጠቅ ተግባር ለይቶላቸው በሌላ የእምነት ጎራ የተሰለፉ አካላት ተልእኮ መሆኑ ቀርቷል፡፡ ይህ ተግባር ዛሬ ዛሬ ቤተ ክርስቲያን እሷ እንደ ሻማ እየቀለጠች ባበራችላቸው፣ በሥጋዊ ፈቃዳቸው የእንጀራ ማብሰያ ያደረጉትን ሙያ ባስተማረቻቸው፣ በጉያዋ ባደጉ፣ የእናት ጡት ነካሽ በሆኑ በራሷ ልጆች የሚፈጸም ሆኗል፡፡ እነዚህ ሰዎች በአለባበሳቸው፣ በአነጋገራቸው (ግእዝ ስለሚጠቅሱ)፣ በአካሔዳቸው (ቤተ ክርስቲያን ስለሚመላለሱ) እና በአገልግሎታቸው (ተአማኒነት ለመፍጠር ስለሚተጉ) ክርስቲያኖች ሊመስሉን ይችላሉ፡፡ ይህ ሁሉ ቀን እስኪወጣ ለማደናገሪያነት የተጠቀሙበት ማስመሰያ ጭምብል እንጂ በእውነት ፊት ሚዛን የሚደፋ መንፈሳዊነት ያለበት ሕይወት አይደለም፡፡ ይህ ድርጊታቸው የሚያስቀርብን ነገር ግላዊ ጥቅም ቢሆን ሁሉን ለእግዚአብሔር ሰጥቶ ማለፍ ይቻል ነበር፡፡ ነገር ግን ከውስጥ እስከ ውጪ በተዘረጋ መዋቅር፣ ቤተ ክርስቲያንን እስከ መረከብ፣ ካልተቻለ እስከ መክፈል በሚያደርስ የተቀናጀ ስልት፣ በፕሮቴስታንታዊ በጀት በታገዘ ድጋፍ አምልኮተ እግዚአብሔርን ከምድረ ገጽ ላይ ለማጥፋት የኤልዛቤልን ዕቅድ የሚያስፈጽሙ አካላትን መታገሥ አግባብ ባለመሆኑ ማንነታቸውን ገልጾ ሕዝብ እንዲያውቀው ማድረግ መንፈሳዊ ግዴታችን ይሆናል፡፡
እነርሱ መዋቅር ዘርግተው፣ ስልት ነድፈው፣ በጀት መድበው ቤተ ክርስቲያንን ለማጥፋት እየሠሩ ያሉት የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም ነው፡፡ ከዚህ በፊት በቀረቡ ጥናቶች እንደተገለጸው ተሐድሶዎች ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን እስከ መክፈል፣ ከተቻለም እስከ መረከብ ያደርሱናል ብለው የዘረጓቸው ስልቶች አሉ፡፡ እነዚህን ስልቶች እውን ለማድረግ ደግሞ የተለያዩ መንገዶችን ይጠቀማሉ፡፡ ከእነዚህ ተሐድሶዎች ከሚጠቀሟቸው መንገዶች መካከል ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡

፩.በሚያውቋቸው ሰዎች በኩል መቅረብ፡- ዛሬ ላይ ተሐድሶ ነን በማለት ቤተ ክርስቲያንን እናድሳለን የሚሉ አካላት የተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታዮች ስለነበሩ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ብዙ ሰዎችን ያውቃሉ፡፡ በቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ መዋቅር ውስጥ፣ በአብነት ትምህርት ቤት ወንበር ዘርግተው የሚያስተምሩ የአብነት መምህራንን፣ በልዩ ልዩ ገዳማት የሚገኙ መናንያንን እና አስተዳዳሪዎችን፣ የመንፈሳዊ ትምህርት ተቋማት አስተዳዳሪዎችን፣ መምህራንን እንዲሁም የሰንበት ትምህርት ቤት አመራሮችንና አባላትን ማወቃቸውና መቅረባቸው በእነርሱ በኩል ተልእኳቸውን የማስፈጸም ዕድል ፈጥሮላቸዋል፡፡


01menafikanለምሳሌ በ፲፱፻፺ ዓ.ም ቀኖና ተሰጥቶት ተጸጽቶ በመመለስ ፋንታ በኑፋቄው በመግፋቱ ምክንያት በ፳፻ወ፬ ዓ.ም በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባዔ ከተወገዙት ፲፮ የተሐድሶ አራማጅ ግለሰቦች መካከል አንዱ የሆነው፣ አሁንም ኦርቶዶክስ ነኝ በማለት የሚያደናግረው እና በሰሜኑ የአገራችን ክፍል የሚካሔደውን የተሐድሶ እንቅስቃሴ የሚመራው ጽጌ ሥጦታው ብዙ የአብነት መምህራንን ለመቀሰጥ ዕድል ያገኘው በአብነት ትምህ ርት ቤት የሚያውቃቸውን ሰዎች በመጠቀም ነው፡፡ መሠረተ ክርስቶስ ቸርችም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ለማደስ በሚደረገው እንቅስቃሴ ለአገልግሎት የምፈልጋቸው በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ አገልግሎት የሚሰጡ ካህናትን ብቻ ነው ማለቷ የአብነት መምህራንን ለማጥመድ የቤተ ክርስቲያንን ቋንቋ የሚያውቅ አካል አስፈላጊ እንደሆነ በመረዳቷ ነው፡፡ ይህ ሁሉ የሚያሳየን ተሐድሶዎች ከቤተ ክርስቲያኒቷ ቋንቋና ከቤተ ክርስቲያን አባቶች ጋር መተዋወቃቸው በምእመናን ዘንድ ተቀባይ ነትን በማግኘት ተልእኳቸውን ለማሳካት ምን ያህል ያገዛቸው መሆኑን ነው፡፡

፪.በገንዘብ ማታለል፡- ተሐድሶዎች ቤተ ክርስቲያንን ለማጥፋት ከምንጩ ላይ መሥራት አለብን ብለው ትኩረት የሰጧቸው አብዛኛዎቹ ቦታዎች ላይ የሚገኙት የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች የገንዘብ ችግር ያለባቸው ናቸው፡፡ አብነት ትምህርት ቤቶችን ብንወስድ በቤተ ክርስቲያን መዋቅር የተረሱ የቤተ ክርስቲያን የደም ሥሮች ናቸው፡፡ የሕዝቡ የኑሮ ሁኔታ ከመቀየሩ ጋር ተያይዞ በአሁኑ ዘመን ከዚህ በፊት እንደነበረው ቁራሽ እየለመኑ መማር የማይታሰብ እየሆነ መጥቷል፡፡ በዚህ ምክንያት የአብነት ተማሪዎች ሌሎች የገንዘብ ማግኛ ዘዴዎችን እየተጠቀሙ ትምህርታቸውን መቀጠል ይፈልጋሉ፡፡ በዚህ መካከል ከአሜሪካና ከአውሮፓ የፕሮቴስታንት ድርጅቶች በሚላክላቸው ገንዘብ ኪሳቸውን ያደለቡት ተሐድሶዎች አንድ አማራጭ ሆነው አብነት ተማሪዎችን ቀረቧቸው፡፡ ተሐድሶዎቹ ለገዳማት፣ ለመንፈሳዊ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎችና ለገጠሪቷ ቤተ ክርስቲያን ካህናትና ዲያቆናትም ተመሳሳይ ድጋፍ እናደርጋለን በሚል ሰበብ እየበረዟቸው ይገኛሉ፡፡ ባለፈው ዓመት አዲስ አበባ ኮተቤ አካባቢ ባካሔዱት ስብሰባ ላይ ማኅበረ ቅዱሳን ያልደረሰባቸውን አብነት ትምህርት ቤቶችን ቀድመን በድጎማ መልክ መቅረብና መያዝ አለብን የሚል አቅጣጫ መንደፋቸውን ተናግረዋል፡፡

፫.€œአሠልጥኖ€/አሰይጥ
ኖ መመለስ፡- በትውውቅም ሆነ በማታለያ የቀረቧቸውን ሰዎች የጥፋት ዓላማቸውን ለመፈጸም የሚችሉበትን አቅም በሥልጠና ካስታጠቋቸው በኋላ ተልእኳቸውን ሳይረሱ ወደ ቀድሞ ቦታቸው ተመልሰው ሥራቸውን እንዲቀጥሉ ያደርጓቸዋል፡፡ የተሐድሶ ሥልጠናዎችን ወስደው ወይም ሃይማኖታቸውን ትተው ወደ ሌላ በረት ሔደው ከቆዩ በኋላ የጣሉትን ቆብና መስቀል ይዘው ኦርቶዶክሳዊ መስለው የተመለሱ ሰዎች ቁጥር ብዙ ነው፡፡ በዚህ መንገድ ውጪ ድረስ ሔደው ተምረው የመጡ አሁንም አባ እገሌ፣ ቄስ እገሌ፣ ዲያቆን እገሌ እየተባሉ የሚጠሩ በልብሳቸውና በምላሳቸው ኦርቶዶክሳውያን፣ በልባቸው ግን ፕሮቴስታንት የሆኑ ብዙ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች አሉ፡፡
02menafikan
፬.ሚዲያዎችን መጠቀም፡- ተሐድሶዎች እንቅስቃሴያቸውን ከግብ ለማድረስ የኅትመት፣ የኤሌክትሮኒክስና የብሮድካስት ሚዲያዎችን ይጠቀማሉ፡፡ ማን እንዳዘጋጃቸው የማይታወቁ ባለቤት አልባ በራሪ ወረቀቶችን፣ ጋዜጦችን፣ መጽሔቶችንና መጻሕፍትን እንዲሁም የተለያዩ የምስል ወድምጽ ውጤቶችን በማሠራጨት መርዛቸውን ይረጫሉ፡፡ ድረ ገጾችን፣ የጡመራ መድረኮችን፣ የሬዲዮ እና የቴሌቪዥን መርሐ ግብራትን በመጠቀም ኑፋቄያቸውቸውን እያስፋፉ ይገኛሉ፡፡

፬.፩.ጋዜጦች
ተሐድሶዎች እያሳተሙ ከሚያሠራጯቸውና መርዛቸውን ከሚረጩባቸው ጋዜጦቻቸው መካከል መጥቅዕ፣ በሃይማኖት ቁሙ፣ መርከብ፣ መና ተዋሕዶ፣ እውነት፣ ኖኅተ ብርሃን፣ ከሣቴ ብርሃን፣ ርግብ፣ ንቁ፣ ወዘተ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

፬.፪.መጽሔቶች

ሌሎች ተሐድሶዎች ኑፋቄያቸውን የሚያሠራጩባቸው የኅትመት ውጤቶች መጽሔቶች ናቸው፡፡ ከእነዚህ መጽሔቶች መካከል ጥቂቶቹ አንቀጸ ብርሃን፣ ብሔራዊ ተሐድሶ፣ ከሣቴ ብርሃን ዘኢትዮጵያ፣ ሰላማ ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ፣ ጮራ፣ ቤተ ፍቅር፣ ወዘተ ሲሆኑ ከእነዚህ ባልተናነሰ ሁኔታ ለተሐድሶ እንቅስቃሴው ድጋፍ ሰጪ የሆኑ ጽሑፎችን የሚያቀርቡ ጌሠም፣ ትሪኒቲ፣ ማቴቴስ፣ ካሪዝማ፣ ወዘተ የሚባሉ የፕሮቴስታንት መጽሔቶች አሉ፡፡

፬.፫.መጻሕፍት
03menafikanተሐድሶዎች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስም ከአንድ መቶ ሰማንያ (፻፹) በላይ መጻሕፍት ጽፈዋል፡፡ መጽሐፎቻቸው የክርስቶስን አምላክነትና የእመቤታችንን አማላጅነት ክደው የሚያስክዱ፣ ቤተ ክርስቲያንን የሚነቅፉ፣ ቅዱሳንን የሚሳደቡ፣ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባርን የሚያጥላሉ ናቸው፡፡ ተሐድሶዎች የግብር አባታቸው የሉተር ልጆች እንጂ ኦርቶዶክሳውያን አለመሆናቸውን መጽሐፎቻቸው ይናገራሉ፡፡ ከቁጥራቸው ብዛት የተነሣ ሁሉንም የተሐድሶ መጻሕፍት መዘርዘር ከባድ ቢሆንም በ፳፻ወ፬ ዓ.ም ከእነ ጽጌ ሥጦታው ጋር የተወገዘው አሸናፊ መኮንን ብቻ ከሃያ አምስት በላይ መጻሕፍትን ጽፏል፡፡ የተለያዩ የብዕር ስሞችን በመጠቀም ቤተ ክርስቲያንን መሳደብ የእንጀራ ማብሰያው ያደረገው ሠረቀ ብርሃን ዘወንጌል መስተብቁዕ ዘሙታን፣ የዘመናት እንቆቅልሽ ሲፈታ፣ ማሳቀልና ሎፌ የሚሉ በመርዝ የተሞሉ መጻሕፍትን ጽፏል፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ምእመናንን በስውር መንጠቁ አላጠግባቸው ብሎ ቤተ ክርስቲያንን በግልጽ እየተዋጓት ያሉት ፕሮቴስታንቶችም የተሐድሶ እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እንዳለ እና እንቅስቃሴውም ለእነርሱ ድጋፍ ሰጪ መሆኑን በመጽሐፎቻቸው ገልጸዋል፡፡ ለምሳሌ፡- ጸጋአብ በቀለ የተባለ የፕሮቴስታንት ፓስተር የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ተሐድሶ - ሳታድግ ያረጀች የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በሚለው መጽሐፉ፣ ዳንኤል ተሾመ የሚባል የመካነ ኢየሱስ ቸርች አባል የሆነ ፕሮቴስታንት የቅርብ ዘመኑ (፲፱፻፸፱-፲፱፻፺፱) የተሐድሶ እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሚል ለሁለተኛ ዲግሪ ማሟያ ባዘጋጀው ጽሑፍ እንዲሁም በቀለ ወልደ ኪዳን የተባለ ከሌሊቱ ስንት ሰዓት ነው?በሚለው መጽሐፉ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስላለው የተሐድሶ እንቅስቃሴ ገልጸዋል፡፡ እነዚህ መጻሕፍት የተሐድሶ እንቅስቃሴን ግብና ከፕሮቴስታንት ጋር ያለውን ድርና ማግነት ቁልጭ አድርገው የሚያሳዩ ናቸው፡፡

፬.፬.ድረ ገጾችና የጡመራ መድረኮች

በዚህ ዘመን ሁሉም ነገር በኤሌክትሮኒክስ መቅረብ የሚችል ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ተሐድሶዎች ኑፋቄያቸውን ለመዝራት ከተጠቀሙባቸው ስልቶች መካከል አንዱ ድረ ገጾችንና የጡመራ መድረኮችን መጠቀም ነው፡፡ ቁጥራቸ ውን በትክክል ማወቅ ባይቻልም በዛ ያሉ የተሐድሶ የጡመራ መድረኮችና ድረ ገጾች አሉ፡፡ ከእነዚህ ድረ ገጾችና የጡመራ መድረኮች መካከል አባ ሰላማ፣ ጮራ፣ ደጀ ብርሃን፣ የዲያ ቆን አሸናፊ መኮንን ገጽ፣ ተሐድሶ ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ፣ ዐውደ ምሕረት፣ ማራናታ፣ ቤተ ፍቅርና የዲያቆን አቤኔ ዘር ተክሉ ገጽ ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

፭.ተገፋን ብሎ መጮህ፡- ጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ ይጮሃል እንደሚባለው፣ ተሐድሶዎች አጥፊዎቹ፣ ቤተ ክርስቲያንን ለማፍረስ የሚተጉት ራሳቸው ሆነው ሳለ በራሳቸው ድረ ገጾች፣ የጡመራ መድረኮችና በተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች በኩል ተገፋን እያሉ ይጮሃሉ፡፡ በ፳፻ወ፮ ዓ.ም የተወሰኑ ዘማርያ አሜሪካ ሔደው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና በማኅበረ ቅዱሳን ለተገፉ ሰባክያንና ዘማርያን በሚል ገንዘብ ሲሰበስቡ ነበር፡፡ በ፳፻ወ፬ ዓ.ም በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባዔ የተወገዘው ማኅበረ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን የተባለው የተሐድሶ ድርጅት ደግሞ የካቲት ፮ ቀን ፳፻ወ፮ ዓ.ም በቁ ጥር አ/ሰ/ማ/18/262/06 በማኅበረ ቅዱሳን አቀነባባሪነት የተወሰነብን የውግዘት ውሳኔ እንዲነሣልን ስለመጠየቅ ይመለከታል የሚል ደብዳቤ በአድራሻ ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ አስገብቶ ነበር፡፡ ደብዳቤው ርእሱ እንደሚናገረው ማኅበረ ቅዱሳንን የሚያወግዝና ውግዘታችን ይነሣልን የሚል ነው፡፡ ድርጅቱ በደብዳቤው፡-

05menafikanክልላዊ ማኅበር መመሥረት የለባችሁም፣ በአገር አቀፍ የተፈቀደለት ማኅበረ ቅዱሳን ብቻ ስለሆነ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት ሁኑ፣ ካልሆናችሁ ግን መናፍቃን ናችሁ፣ ትለያላችሁ በማለት ሲዝትብን የነበረ ማኅበረ ቅዱሳን ከእኔ በቀር ሌላ ማኅበር መኖር የለበትም የሚል አቋም ይዞ በከፍተኛ ሁኔታ በመንቀሳቀስ ራሱን እንደ ልጅ በመቁጠር እኛን ደግሞ እንደ እንጀራ ልጅ እንድንታይና እንድንወገዝ ካለው ጽኑ አቋሙ የተነሣ ምንም ዐይነት የክህደት ትምህርት ሳንማርም ሆነ ሳናስተምር ያለ ምንም መረጃ ይሁን ማስረጃ በአሉቧልታና በትምክህት መናፍቃን ናቸው እያለ በገንዘብ ኀይል በሁሉም ዘንድ የተሳሳተ ግንዛቤ እንዲኖር በማድረግ ሳንጠየቅ፣ ሳንመከር፣ ሳንገሠጽ፣ እውነት ይሁን አይሁን ሳይጣራ፣ ቀርበን በወቅቱም ምንም ዕድል ሳይሰጠን በማኅበረ ቅዱሳን ከፍተኛ ተዋናይነት የውግዘት ውሳኔ መተላለፉ አሳዝኖናል ይላል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ አባ ሰላማና ተሐድሶ ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ በሚባሉት ድረ ገጾቻቸው በ፳፻ወ፬ ዓ.ም ተሐድሶዎች ሲወገዙ፣ ከዚያም በኋላ እነሱን ለማስቆም ቤተ ክርስቲያኒቱ በምታደርገው እንቅስቃሴ ሁሉ አገልጋዮቿን የምታሳድድ ቤተ ክርስቲያን እያሉ ስሟን ሲያጠፉ ይሰማሉ፡፡ ለምሳሌ ተሐድሶ ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ኑ! እንዋቀስ በሚል ርእስ ባወጣው ጽሑፍ እንደ አለመታደል ሆኖ ሲኖዶሳችን መናፍቃንን በመደገፍ ጻድቃንን ያሳድዳል፤ ቀን ሲደርስ የእግዚአብሔርን ፍርድ እናያለን፤ እስከዚያው እንክርዳዱ ከስንዴው ጋር ተናንቆ ያድጋል፡፡ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቃሉና በመንፈሱ ተሐድሶ ይጎብኝልን፡፡በማለት ጽፈዋል፡፡ ሊያ የሚባል መጽሔት ላይ ደግሞ የወንድሞች ከሣሽ ማኅበረ ቅዱሳን በሚል ርእስ ሰፊ ሐተታ ያለው ጽሑፍ ጽፈው ነበር፡፡

06menafikanየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ቁጥር በሰባት ሚሊዮን መቀነሱን በይፋ አምናለች፡፡ ቤተ ክርስቲያን እንዲህ ስትል በአንድ ወገን መንጋው አለመጠበቁንና በዚህ ምክንያት መሰረቁን አምናለች፡፡ በሌላ በኩል ግን ሌሎች ሰረቁኝ፣ ወሰዱብኝ ከማለት ያለፈ ምክንያቱን በሚገባ ያጤነችው አትመስልም፡፡ ሌሎች በውጪ አግኝተው ከወሰዷቸው በላይ እንደ ማኅበረ ቅዱሳን ያለ የወንድሞች ከሳሽና አክራሪ ቡድን እኔን አልመሰላችሁምና መናፍቃን ሆናችኋል በሚል ሕገ ወጥ መንገድ ያሳደዳቸው ጥቂቶች አይደሉም፡፡ ምናልባት ለቁጥሩ መቀነስ የማኅበረ ቅዱሳን እጅም እንዳለበት መታመን አለበት ይላል፡፡ (ሊያ መጽሔት ቅጽ ፪ ቁጥር ፳፮ ሚያዝያ ፳፻ወ፭ ዓ.ም)

እስካሁን ያየነው የአገር ውስጡን ጩኸት ነው፡፡ ተሐድሶዎች ከፕሮቴስታንቶች ጋር በመተባበር ይህንን ጩኸት ዐለም አቀፋዊ አድርገውታል፡፡ ዓላማዬ የክርስቲያኖችን ጭቆና ለዓለም ማሳወቅ ነው የሚል ክርስቲያን ሳይንስ ሞኒተር የሚባል አንድ የዜና አውታር አለ፡፡ በቀን ከዐሥር በላይ ከሃይማኖት ጋር ግንኙነት ያላቸውን ዜናዎች ያወጣል፡፡ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮችን በደል አውጥቶ አያውቅም፡፡ በሶርያ በየዕለቱ ከሞት ጋር ስለሚታገሉት ኦርቶዶክሳውያን፣ ስለ ፓትርያርኩ ለዐሥራ አምስት ቀናት የሔዱበት አድራሻ አለመታወቅ የዘገበው ነገር አልነበረም፡፡ ያልዘገበው ግን ባለማወቅ ሳይሆን በዓላማ ነው፡፡ ለዚህ ድርጅት ክርስቲያን ማለት ፕሮቴስታንት ነው፡፡ የሚያሰማውም የእነሱን ጩኸት ነው፡፡

07menafikanተቀማጭነቱን አሜሪካ ያደረገ ኦፕን ዶርስ የሚባል ድርጅት አለ፡፡ ድርጅቱ አንድሪው ቫን ደር ቢጅል በሚባል ግለሰብ በ፲፱፻፶፭ የተመሠረተ መንግ ሥታዊ ያልሆነ የክርስቲያን ድርጅት ነው፡፡ እንደ ራሳቸው አገላለጽ በግለሰቦች መዋጮ የሚተዳደር ነው፡፡ ከ፲፱፻፺፩ ጀምሮ በዓለም አቀፍ ደረጃ በክርስቲያኖች ላይ ከፍተኛ ጭቆና የሚያደርሱ የአምሳ አገራትን ዝርዝር ያወጣል፡፡ በዚህ ድርጅት ዘገባ መሠረት አገራችን ኢትዮጵያ ክርስቲያኖችን ከሚጨቁኑት አምሳ አገራት መካከል ባለፉት አምስት ዓመታት ማለትም በ2011 ፵፫ኛ፣ በ2012 ፴፰ኛ፣ በ2013 €“፲፭ኛ፣ በ2014€“ ፲፯ኛ እና በ2015€“ ፳፪ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡ ድርጅቱ ባለፉት ሁለት ዓመታት ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የክርስቲያኖች ጭቆና ከዓመት ወደ ዓመት እየቀነሰ ነው ይላል፡፡ ይህ አገላለጽ ሲብራራ ተሐድሶዎች ቤተ ክርስቲያንን ለማፍረስ የተሻለ ዕድል እያገኙ ነው ማለት ነው፡፡

ተቋሙ በ2013 ባወጣው ዘገባው ስለ ኢትዮጵያ እንዲህ የሚል ቃል አስቀምጧል፡-

Ethiopia has a complex mix of persecution dynamics.Ecclesiastical arrogance is the country historical persecution dynamic. For years, the Ethiopian Orthodox Church (EOC) has been seriously persecuting believers who have left their ranks or joined the renewal movements within the EOC. (World Watch List 2013)

ኢትዮጵያ ዘርፈ ብዙ የሆነ ጭቆና የሚካሔድባት አገር ናት፡፡ ቤተ ክህነታዊ እብሪትየአገሪቱ ታሪካዊ የጭቆና መታወቂያ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ወጥተው አዲስ የመጣውን የፕሮቴስታንት እምነት እና በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እያሉ የተሐድሶውን ጎራ የተቀላቀሉትን አማኞች ክፉኛ ትጨቁናለች፡፡ካለ በኋላ ቀጥሎ፡-

The fanatic group inside the EOC (€˜Mahibere Kidusan) is a growing threat for non-traditional Protestants and renewal movements within the EOC. The group allegedly wants to control the government policies to restrict the activities of other religions. Mahibere Kidusan is currently riding high. (World Watch List 2013)

08menafikanበኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥር የሚገኘው ማኅበረ ቅዱሳን የሚባለው አክራሪ ቡድን ለፕሮቴስታንቶች እና በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ ላሉ ተሐድሶዎች ታላቅ ሥጋት ነው፡፡ ቡድኑ ሌሎች የእምነት ቤቶች የሚያደርጓቸውን እንቅስቃሴዎች ለመገደብ የመንግሥትን ፖሊሲዎች በጥብቅ መቆጣጠር በጥብቅ ይፈልጋል፡፡  በአሁኑ ጊዜ ማኅበሩ በፍጥነት እያንሠራራ ነው፡፡

2013 ማለት በኢትዮጵያ ተሐድሶ ዎች የተወገዙበት ዓመት ማግስት ማለት ነው፡፡ ለዚህም ነው እየተጨቆንን ነው የሚለው ጉዳይ ዓለም አቀፋዊ አጀንዳ እንዲሆን እና ፖለቲካዊ አቅጣጫ እንዲይዝ ለማድረግ የሞከሩት፡፡ ተሐድሶዎች የዘረጉት መስመር የት እንደሚደርስ ወይም ተሐድሶው በማን ግፊት እየተመራ እንደሆነ ይህ አገላለጽ ሁነኛ ማሳያ ነው፡፡ ኦርቶዶክስ ሳይሆኑ ኦርቶዶክስ ነን በማለት የቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ ለመቀየር ብሎም ቤተ ክርስቲያንን ለመክፈል የሚሠሩ ወገኖች ቁጥራቸው በርከት ባሉባቸው ቦታዎች ኦርቶዶክሶችን በማሸማቀቅ፣ በማስፈራራትና በመዝለፍ ቤተ ክርስቲያንን ለማጥፋት የተነሡት እነርሱ ሆነው ሳለ ራሳቸው የሠሩትን ግፍና በደል ለቤተ ክርስቲያን አድርገው ተሳደድን ብለው ይጮሃሉ፡፡ ብዙዎቻችንም ዐውቀንም ይሁን ሳናውቅ የእነርሱ ጩኸት ደጋፊዎችና ጠበቆች እየሆን ነው፡፡ የራስን አጥብቆ መያዝና ለሌላ ወገን አላስደፍርም ማለት ማስወቀስና ማስተቸት ከጀመረ ቆይቷል፡፡

እነርሱ እነዚህን መንገዶች ተጠቅመው ቤተ ክርስቲያንን የማዳከም፣ ዶግማና ቀኖናዋን የመቆነጻጸል ተግባራቸውን ቀጥለውበታል፡፡ እኛ ይህ ሁሉ ሲፈጸም ምን ያከናወንነው ተግባር አለ ተብለን ራሳችንን ብንጠየቅ መልሳችን ምንም የሚል ነው፡፡ ስለዚህ ቢያንስ የችግሩን አሳሳቢነትና የአደጋውን አስከፊነት ጠንቅቀን ማወቅና መንገዶቻቸውን ለመዝጋት የሚያስችሉ ሥራዎችን መሥራት ይገባናል፡፡ እነርሱ በገንዘብ ለማታለል ምቹ ሁኔታ ያገኙት እኛ አብነት ትምህርት ቤቶችን እና ገዳማትን ባለመደገፋችን መሆኑን መረዳት አለብን፡፡

ይቆየን

2015 ኖቬምበር 5, ሐሙስ

የተሐድሶን ምንነት ሳታውቁ፣ ስለ ተሐድሶዎች ማንነት አትጠይቁ!!

አትም ኢሜይል
ጥቅምት 23 ቀን 2008 ዓ.ም
ክፍል አንድ
በተሐድሶ ዙሪያ በስምዐ ጽድቅ ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ጋዜጣ የተጻፉትን ጽሑፎች ከክፍል አንድ ጀምሮ ተከታትለን እናቀርብላችኋለን፡፡
ስለ ነገረ ተሐድሶ ለመጻፍ የሚነሣ ሰው ከሚቸገርባቸው ጉዳዮች አንዱ €œከእንቅስቃሴው ውስጥ ምኑ ላይ ባተኩር አንባብያን ላይ የሚፈለገውን ግንዛቤ መፍጠር እችላለሁ€ የሚለው ነው፡፡ ስለ ታሪካዊ ዳራውና አመጣጡ፣ ስለ ምንነቱ፣ ስለእንቅስቃሴው መሪዎች ማንነት፣ ስለ ተሐድሶዎች €œአስተምህሮ€፣ ከፕሮቴስታንት ጋር ስላለው አንድነትና ተመሳሳይነት (ልዩነት ስለሌለው) ወይስ ስለ ምን መጻፍ ቀላል፣ የሁሉንም ልብ የሚያኳኳ፣ ለመፍትሔው የሚያነሣሣ ይሆናል የሚለው የጸሐፊውን ልብ የሚያስጨንቅ ጥያቄ ነው፡፡ እኛም ከምኑ ጀምረን ወደ የት መሔድ እንዳለብን ብንቸገርም የእንቅስቃሴውን ምንነትና መገለጫ ሳያውቁ ወደ ሌላ ርእሰ ጉዳይ መግባት ግን መልካም መስሎ አይታየንም፡፡
ከዚህ በፊት በአንድ ጽሑፍ ላይ እንደገለጽነው ተሐድሶ እንቅስቃሴ እንጂ እምነት ስላልሆነ የራሱ ዶግማ፣ ቀኖና እና ሥርዓት የለውም፡፡ ይህንንም ራሳቸው ባዘጋጁት ጽሑፍ ላይ:- €œወደፊት ከምንሠራቸው ሥራዎች አንዱ የሃይማኖት ምዕላድ ማዘጋጀት ነ€ ስላሉ እስካሁን በጋራ የተስማሙበት ቋሚ የእምነት መሠረት እንደሌላቸው ሆነው የቀረቡበት ነው፡፡ ሆኖም ግን እስካአሁን እየገለጡት ካለው መረዳት እንደሚቻለው የተስማሙበት ዶግማና ቀኖናቸው ቤተ ክርስቲያንን ማፍረስና ፕሮቴስታንታዊ ማድረግ የሚለው ነው፡፡ በዚህ ምክንያት የተሐድሶን ምንነት በቀላሉ መግለጽ ከባድ ይሆናል፡፡ ምክንያቱም እንደ ቡድኑና እንደ ግለሰቦች አቅም የሚወሰን እንጂ ቋሚ የሆነ አስተምህሮ ስለሌለው፡፡ የእንስሳትን ትርጉም ከመናገር ምሳሌ መስጠቱ እንደሚቀለው ሁሉ፣ ለተሐድሶም ትርጉም ከመስጠት ይልቅ ዓላማውንና ተግባሩን ማሳየት የተሻለ ገላጭ ስለሚሆን በእርሱ እንጀምራለን፡፡
ተሐድሶ በአገራችን ዐውድ ሲታይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ዶግማ፣ ቀኖና፣ ትውፊት እና ሥርዓት በመቀየጥ፣ በመቀየር ወይም በማጥፋት ፕሮቴስታንት ማድረግ፣ ምእመናንን ደግሞ በእምነት ስም አታሎ አስገብቶ ዓለማዊ (ሴኪዩላር) የማድረግ እንቅስቃሴ ነው፡፡ ፕሮቴስታንቲዝም በምዕራባውያን ዘንድ እምነትነቱ ቢያልፍበትም በእኛ አገር ግን እስከ አሁን ድረስ €œሃይማኖታዊ መልክ እንደ ተላበሰ ስለሆነ ተሐድሶን ለፕሮቴስታንቲዝም ዓላማ ማስፈጸሚያ መሣሪያነት እየተጠቀሙበት ነው፡፡ ተሐድሶና ፕሮቴስታንቲዝም በአካሔድ፣ በስልትና በግብ አንድ ዐይነት ናቸው፡፡ የሁለቱም ግብ ኦርቶዶክሳውያንን ፕሮቴስታንት ከዚያም ዓለማዊ ማድረግ ነው፡፡ ይህንን ቁርኝታቸውን መጋቢት ፳፻፮ ዓ.ም በወጣው ከሣቴ ብርሃን በሚባል ጋዜጣቸው ሲገልጹት፡-

ባለፉት አሥርና አሥራ ሁለት ዓመታት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና በወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት መካከል ስላለው መሠረታዊ ልዩነት ለማጥናት ሞክረናል፡፡ ያገኘነው ውጤት እኛ እንድትኖረን የምንፈልጋት የታደሰችና ጥንታዊቷ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያናችን ከወንጌላውያኑ ጋር ያላት ልዩነት የአምልኮት ባህልና የቋንቋ ብቻ መሆኑን በሚገባ ተገንዝበናል ይላሉ፡፡
ይህንን የተናገረው ገድል ወይስ ገደል€ የሚለውን መጽሐፍ የጻፈው ጌታቸው ምትኩ ነው፡፡ ጌታቸው ምትኩ በሌላ ገጽ ላይ ስለ ከሣቴ ብርሃን የተሐድሶ ማኅበር አመሠራረት፣ ስለ ደረሰባቸው ስደት€ እና ስለ ወሰዱት እርምጃ ሲገልጽ ደግሞ እንዲህ ብሏል፡-
በተሐድሶ ጥያቄ ሰበብ በማኅበር ከተሰበሰቡት የቤተ ክርስቲያኒቱ አገልጋዮች ብዙዎች ከሥራ የመባረር፣ ከቤተሰቦቻቸው የመለያየትና ማኅበራዊ ተቀባይነትን የማጣት ዕጣ ሲገጥማቸው የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናትን ድጋፍ በመሻት፣ በነጻነት ቃለ እግዚአብሔርን ለማወቅና ለመማር እንዲሁም አምልኮተ እግዚአብሔርን ለመፈጸም በገፍ ነጉደዋል፡፡ በእርግጥ በመሠረታዊው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ረገድ ከወንጌላውያን ጋር የጎላ ልዩነት ባለመኖሩ ወደዚያ መሔዳቸው ክፋት ባይኖረውም €ተሐድሶውን ጎድቶታል፡፡

ይህ ገለጻ የተሐድሶ ዓላማና ግብ ምን እንደሆነ በግልጽ ያሳያል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከሦስት ሺ ዓመታት በላይ እግዚአብሔርን ስታመልክ፣ ላለፉት ሁለት ሺ ዓመታት ወንጌልን ስትሰብክ እንዳልኖረች ሁሉ ዛሬ ክርስቶስን እንዳልሰበከች በድፍረት የሚናገሩ የውስጥ እሾሆች በቀሉባት፡፡ ባያውቁት ነው እንጂ €œመታደስ አለባት የሚሉት ሰዎች ራሳቸው እግዚአብሔርን ያወቁት በእናት ቤተ ክርስቲያን አማካኝነት ነበር፡፡ ለቤተ ክርስቲያን ወንጌል እንደ አዲስ ሊሰበክላት ይገባል ብለው እየተሳደቡ የማርቲን ሉተርን ዓላማ ለማስፈጸም የተቋቋሙትን ድርጅቶች ደግሞ €œወንጌላውያን€ ብለው ጠሯቸው፡፡ እነቅዱስ አትናቴዎስ ከአርዮስ ጋር፣ እነቅዱስ ቄርሎስ ከንስጥሮስ ጋር፣ እነቅዱስ ዲዮስቆሮስ ከልዮን ጋር እስከ ነፍስ ሕቅታ የተጋደሉላት ንጽሕት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ከሉተር ድርጅቶች ጋር በአስተምህሮ አንድነት ስትፈረጅ ከመስማት በላይ የሚያም ነገር የለም፡፡

የተሐድሶ እንቅስቃሴው ከተጀመረ በጣም ጥቂት ጊዜ ቢያስቆጥርም የመጀመሪያዎቹ የተሐድሶ መነኮሳት ኅብረት ከተወገዙበት ከ፲፱፻፺ ዓ.ም ወዲህ ግን መልኩን እየቀየረና እየተስፋፋ እንደመጣ ግልጽ ነው፡፡ በተለይም በቅርብ ጊዜ (፳፻ወ፬ ዓ.ም) በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ሰባት ማኅበራትና ዐሥራ ስድስት ግለሰቦች ከተወገዙ በኋላ ሁላችንም የተሐድሶ ጉዳይ ያበቃ መስሎን እጃችንን አጣጥፈን ተቀምጠን ሳለን እነርሱ መረባቸውን ዓለም አቀፋዊ አድርገው እየተንቀሳቀሱ ነው፡፡ ከአሜሪካ እስከ እንግሊዝ፣ ከዱባይ እስከ ኢትዮጵያ የሚደርስ ሰፊ መረብ ዘርግተዋል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ከተናጠል እንቅስቃሴ በጋራ መሆን ይሻላል በሚል ከዐሥር በላይ የሚሆኑ የተሐድሶ ማኅበራት €œየወንጌል አገልግሎት ማኅበራት ኅብረት€ የሚባል ማኅበር አቋቁመዋል፡፡ ኅብረቱ በከሣቴ ብርሃን አነሣሽነት የተመሠረተ የተሐድሶ ኅብረት ነው፡፡ ሁለተኛ ዓመት የምሥረታ በዓሉን አስመልክቶ መጋቢት ፳፻ወ፯ ዓ.ም ባወጣው ልዩ ዕትም መጽሔት ላይ ኅብረቱ የካቲት ፴/፳፻ወ፭ ዓ.ም እንደ ተመሠረተ፣ መስከረም ፲፮/፳፻ወ፯ ዓ.ም ከፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሕጋዊ ዕውቅና እንዳገኘ ገልጸዋል፡፡ በመጽሔቱ የኅብረቱ ሥራዎች ተብለው ከተጠቀሱት ጉዳዮች መካከል፡-

የጋራ የሆነ የእምነት መግለጫ ማዘጋጀት፣

የጋራ የሆነ በየደረጃው ላሉ የሚያ ለግል የማስተማሪያና የማሠልጠኛ ማቴሪያል ማዘጋጀት፣

የቤተ ክርስቲያኒቷ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚጠቀሙበት የጋራ የሆነ ሥርዐተ ትምህርት መቅረጽ፣

የቤተ ክርስቲያኗን ብርቱ ጎንና ደካማ ጎን ለይቶ በማውጣትና በመጽሐፍ ቅዱስ በመመዘን ሊጸና የሚገባው እንዲጸና፣ ሊወገድ የሚገባው እንዲወገድ፣ ሊሻሻል የሚገባው እንዲሻሻል፣ ቤተ ክርስቲያኒቱ ልትይዘው ሲገባ ያልያዘችውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነት ደግሞ እንድትይዝ ለማድረግ ብርቱ የሆነ የጋራ ተሐድሶአዊ ምእላድ ማዘጋጀት የሚሉት ይገኙበታል በማለት የወደፊት ዕቅዳቸውን ገልጸዋል፡፡

ተሐድሶ እስከ አሁን እንቅስቃሴ ብቻ እንደ ነበረ አሁን ግን እየሰፋና ወደ ተቋምነት እያደገ እንደሆነ ይህ ሁነኛ ማሳያ ነው፡፡ እነርሱ በየጽሑፎቻቸው ኦርቶዶክሳዊ አይደለንም፣ የፕሮቴስታንት ቅጥያዎች ነን እያሉ እየገለጹ ዛሬም ስለ ተሐድሶ መኖር አለመኖር የሚከራከሩ የዋሀን አሉ፡፡ እንቅስቃሴው ገባን የሚሉት እንኳን ማወቅ የሚፈልጉት ተሐድሶዎች እነማን እንደሆኑ እንጂ ስለ እንቅስቃሴው ምንነት፣ ስፋት፣ አደጋና ከእነሱ ስለሚጠበቀው ድርሻ አይደለም፡፡ በመጀመሪያ የተሐድሶዎችን ማንነት ማወቅ ብቻውን ዕውቀት አይደለም፡፡ ለሚዲያ ፍጆታ ካልሆነ በስተቀር ለቤተ ክርስቲያን የሚሰጠው ጥቅምም የለም፡፡ ስለ ተሐድሶ ሲታሰብ የሰዎችን ማንነት ከማወቅ ያለፈ ሥራ ማሰብ ይጠይቃል፡፡ ሁሉ ነገር እንዲነገረን መፈለግ ሳይሆን መገለጫ ቸውን ዐውቀን በዚህ መሠረት ማንነታቸውን መለየት እና መመዘን የእኛ ሥራ መሆን አለበት፡፡

ብዙ ሰዎች የሚጠይቋቸው የተለመዱ ጥያቄዎች አሉ፡፡ €œእገሌ ተሐድሶ ነው? ከሆነ ለምን ከቤተ ክርስቲያን አልታገደም? ለምን አልተወገዘም? ስለ እመቤታችን እያስተማረ ለምን ተሐድሶ ይባላል? ግእዝ እየጠቀሰ ለምን ኦርቶዶክስ አይደለም ትላላችሁ?የሚሉ ጥያቄዎች ይሰማሉ፡፡ ይህ ብቻ አይደለም፣ €œእገሌ በጣም የምንወደው ሰባኪ ስለሆነ ተሐድሶ እንዳትሉት፣ እገሊት ስትዘምር ድምጿ ስለሚያምር እንዳትነኩብን€ ብለው ሰዎችን ከቤተ ክርስቲያን በላይ ያስቀመጡም አሉ፡፡ እነዚህ ሁሉ የተሐድሶን ምንነት ካለ መረዳት የሚመጡ ችግሮች እንደሆኑ ግልጽ ነው፡፡ በመጀመሪያ ይህንን እንወቅ፡፡ ግእዝ የሚጠቅስ፣ ስለ እመቤታችን የሚያስተምር (ስልት ስለሆነ)፣ ወይም ድምጹ የሚያስገመግም ሰባኪ ሁሉ ኦርቶዶክሳዊ አይደለም፡፡ ራሳቸው አንድ ሥልጠና ላይ የተናገሩትን ከዚህ መጥቀስ ይበጃል፡፡

ስትሰብኩ ኢየሱስ ብቻ አትበሉ፣ መድኀኔ ዓለም፣ መድኀኒታችን አምላካችን፣ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ በሉ፡፡ ከቻላችሁ ግእዝ ጥቀሱ፣ ግእዝ ከተናገራችሁ ትታመናላችሁ፣ ሕዝቡ ይሰማችኋል፡፡ ከአዋልድ መጻሕፍትም ለምሳሌ፡- ከውዳሴ ማርያም፣ ከሰዓታት፣ ከዚቅ፣ ከመልክአ መልኮች ጠቅሳችሁ ማስተማር ትችላላችሁ፡፡ ስለ ማርያምም አስተምሩ፣ ድንግል ስለመሆኗ፣ በከብቶች በረት ኢየሱስን ስለ መውለዷ፣ በስደት ስለ መንገላታቷ አስተምሩ፡፡ ብቻ ዓላማችሁን ሳትስቱ ሰዎች በሚሰሟችሁና በምትታመኑበት መንገድ ካስተማራችሁ ሕዝቡን መያዝ ትችላላችሁ፣ ቆይታችሁ ዋናውን ትምህርት ታስተምራላችሁ ብለዋል፡፡

ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም መናገር የማደናገሪያ ስልት እንጂ የስብከታቸው ዓላማ እንዳልሆነ መረዳት አለብን፡፡ በመሆኑም ቤተ ክርስቲያን በማታውቃቸው የቴሌቪዥን መርሐ ግብራት የእመቤታችንን ሥዕል ከጐናቸው አድርገው ቢያስተምሩ ተአማኒነትን ለማግኘት እንጂ በእመቤታችን አማላጅነት ወይም በሥዕላት ክብር አምነው እንዳልሆነ እነርሱም እኛም እናውቃለን፡፡ ስለ እመቤታችን እናስተምራለን ብለው ጀምረው ስለ እመቤታችን አንድም ነገር ሳይናገሩ €œጸሎተኞች፣ ጸሎታችሁ ያልተሰማው በስሙ ስለማ ትጸልዩ ነው ብለው በቅዱሳን ስም መጸለይ እንደማይገባ ሲናገሩ ካልገባን እየበለጡን ነው፡፡ ታዲያ ይሄ ኦርቶዶክሳዊ በሚመስል ርእስ እኛን በመሸንገል ኑፋቄያቸውን ለማስገባት ምቹ ሁኔታ እየፈጠሩ እንጂ ስለ ቅዱሳን ክብር በመቆርቆር እየተናገሩ ነው የሚያስብል ምን ነገር አለው?

እነሱም ይህ ስልት የበለጠ አዋጭና ለአቅጣጫ ማስቀየሪያ እንደሚበጅ ዐውቀው በደንብ እየተጠቀሙበት ነው፡፡ እነሱ ቅኔ ሲቀኙ፣ የተማሩባቸውን እና ያስተማሩባቸውን ወይም ያገለገሉባቸ ውን አጥቢያዎች ሲናገሩ፣ የእኛ አጀንዳ የተሐድሶ አደገኛነት ሳይሆን የተናገሩት ጉዳይ እውነትነት ላይ ይሆናል፡፡

ለምሳሌ ብንጠቅስ የሰሜኑን የተሐድሶ እንቅስቃሴ (በተለይ አብነት መምህራን ላይ ትኩረት አድርጎ የሚንቀሳቀስ) ከጽጌ ሥጦታው ጋር ሆኖ የሚመራው ሙሴ መንበሩ የሚባል ግለሰብ፡- €œቤተ ክርስቲያን እንደምታውቀኝ ለማረጋገጥ እነብሴ ሣር ምድር ሔዳችሁ መጠየቅ ትችላላችሁ ብሎ ስድስት አድባራትን ይጠራል፡፡ ከዚያም ቅኔ ይቀኛል፡፡ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ መሪ ጌታ እንደሆነም ይናገራል፡፡ የሚገርመው ግን ይህንን ሁሉ የሚልበት ቪሲዲ ርእስ ኦርቶዶክስ መልስ ካላት እኛም ጥያቄ አለን€ የሚል ነው፡፡ የቪሲዲው ርእስ ራሱ አቅራቢዎቹ ኦርቶዶክሳውያን እንዳልሆኑ አፍ አውጥቶ እየተናገረ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ነው ያለነው ብለው ሊያሳምኑን ይፈልጋሉ፡፡ አንዳንድ የዋሀን ደግሞ ይህንን ተከትለው €œኦርቶዶክሳዊ ናቸው፣ ይሄው ቅኔ እየተቀኙ፣ የቀደሱበትን ቦታ እየተናገሩ€ ብለው ይከተሏቸዋል፡፡

ሌላ አንድ ማሳያ ብናይ አንድ የመጋቤ ሐዲስነት ማዕርግ የተሰጠው ሰው የጻፈው መጽሐፍ ላይ እንዲህ የሚል አሳብ አስፍሯል €œይህ ሄኖክ የተናገረውና በሐዋርያው በይሁዳም የተጠቀሰውን ትንቢት ቃል በቃል በዚህ በ፷፮ቱ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ባይገኝም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በምትጠቀምበት በሰማንያ አሐዱ መጽሐፍ (መጽሐፈ ሄኖክ) ላይ ተጠቅሶ ይገኛል€ ይላል፡፡ ይህ ንግግር ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአፍኣ ያለ ሰው የተናገረው እንጂ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መድረክ ላይ ቆሞ የሚሰብክ ሰባኬ አይመስልም፡፡ የገጸ ንባቡ አሳብ መጽሐፍ ቅዱስ የሚባለው ስድሳ ስድስቱ እንደሆነ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሌላ የተለየ መጽሐፍ ቅዱስ እንዳላት የሚያደርግ ነው፡፡ ይኸው ሰው በአንድ ወቅት በአንድ የቴሌቪዥን መርሐ ግብር ላይ €œእኔ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደ ተቋም ተሐድሶ አለ ብየ አላምንም፣ ካለ ቢሮውን ቢያሳዩን€ ብሎ ሲከራከር የነበረ መሆኑን ስናስብ ብዙ ነገር ያስጠረጥራል፡፡ ከዚህ ንግግሩ በኋላ ደግሞ ቦንጋ ሔዶ በዝግ ስብሰባ €œተሐድሶ የሚባሉ የተወሰኑ አካላት አሉ፣ ብዙዎቹ ግን ማኅበረ ቅዱሳን ያሳደዳቸው ናቸው€ ብሎ ማኅበረ ቅዱሳንን በመክሰስ ራሱን ነጻ ለማድረግ ሲተጋ ነበር፡፡
እነርሱ ለእኛ ማደናገሪያና መከራከሪያ የሚሆኑ ጉዳዮችን እየጫሩ እኛ በማይጠቅመው ነገር ስንወጠር ሥራቸውን እየሠሩ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ተረፈ አርዮሳዊ የሆኑ ሰዎች ቤተ ክርስቲያን በማታውቀው ግን በቤተ ክርስቲያን ስም በሚተላለፍ መርሐ ግብር ላይ €œበምድር ላይ ሞቼ ነበር ብሎ ቆሞ ሲያወራ የሰማነው ወይም ሲናገር ያየነው ፍጡር አልነበረም፣ የለምም፣ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር፡፡ የሚል ስብከት እንዲሰበክ ዕድል ፈጠርንላቸው፡፡ በብዙ ድካምና በብዙ መከራ የሚገባባትን የእግዚአብሔርን መንግሥት መጠጥ ቤት የመግባት ያህል አቃለው ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃል፣ በአፉ መስክሮ ይድናልና፣ መንገዱ ረጅም አይደለም ወገኖቼ፤ ውጣ ውረድ የለበትም፡፡ የምትከፍለው አይደለም፣ የተከፈለበት ነው፡፡ አንተ የምታደርገው ነገር አይደለም፣ የተደረገልህ ነው፡፡ የምትሆነው አይደለም፣ የሆነልህ ነው፡፡ ይህንን ብታምን በአፍህ ብትመሰክር ትድናለህ፡፡ ከምንድንነው የምትድ ነው? ከኀጢአትና ኀጢአት ከሚያመጣው ሞት€ በማለት በወንጌል ቃል ይሳለቁበት ጀመር፡፡ እንዲያውም ዋናው ዓላማቸው በጸጋው ድናችኋልና አትድከሙ በመሆኑ ዕለት ዕለት የሚሉን €œየእግዚአብሔር ቃል የሚነግረን መዳን ማለት በልብ ማመንና በአፍ መመስከር እንጂ እኛ በድካም የለመድነውን አይደለም፡፡ እየታገልን አንዴ ሲሳካ አንዴ ሳይሳካ እያለቃቀስን የምንኖረውን አይደለም€ የሚል ያለፈበት የፕሮቴስታንት €œስብከት€ ነው፡፡
ይህ ሁሉ የሆነው በእኛ መተኛት እንጂ በእነርሱ ትጋት እንዳልሆነ ሁላችን ውስጣችንን ስንፈትሽ የምንረዳው እውነት ነው፡፡ ስለ ጉዳዩ ትኩረት ሰጥተን ያልሰማንበት ጊዜ ረጅም ነው፣ እስካሁንም ከዚህ አዚም ያልተላቀቅን እንኖራለን፣ ጉዳዩን የምናውቀውም ትኩረት ሰጥተን የሰማንበት ጊዜ ሩቅ እንዳልሆነ እናውቃለን፡፡ ለቤተ ክርስቲያን ከማድላት ይልቅ ለሰዎች የወገንንበት ጊዜ ብዙ ነው፡፡ ዛሬም ዓላማቸውን ራሳቸው ስለገለጹት እንጂ እኛ መርምረን ደርሰንበት አይደለም፡፡ ከእንቅልፋችን እስካልነቃን ድረስ ችግሩ ይቀጥላል፡፡ በመጀመሪያ አንድ ሰው ኦርቶዶክሳዊ ለመባል መስፈርቱ ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ ማስተማሩ እንጂ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ነኝ ማለቱ አይደለም፡፡

ተሐድሶ ማለትም ጫካ ውስጥ የኖረ አውሬ ማለት ሳይሆን ከቤተ ክርስቲያን ጉያ የወጣ ጠላት ነው፡፡ ስለዚህ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ነበሩ፣ አሁንም አሉ፣ ነገር ግን በትምህርታቸውም ሆነ በዓላማቸው ከቤተ ክርስቲያን ወገን አይደሉም ነው የተባለው፡፡ እነ አርዮስም እስከሚወገዙ ድረስ ጳጳስ ነበሩ፡፡ ከተወገዙም በኋላ ብዙዎችን ከመንገድ ያስወጡት መናፍቃን ነን ብለው ሳይሆን ክርስቲያኖች ነን ብለው ነው፡፡ ዛሬም ሰዎች ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተምረናል፣ ቀድሰናል፣ እናም ኦርቶዶክሳውያን ነን ቢሉም ትመምህርታቸው ግን ኦርቶዶክሳዊ አይደለም፡፡ ቤተ ክርስቲያን የቤተ ክርስቲያን አባቶች ብላ ዕውቅና የሰጠቻቸው ቅዱሳን አበው ይህንን ዕውቅና ሲሰጡ መስፈርቶቹ የቅድስና ሕይወት፣ ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ፣ የቤተ ክርስቲያን ምስክርነትና ጥንታዊነት ናቸው እንጂ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያላቸው የአገልግሎት ቦታ አይደለም፡፡

ስለዚህ ከዚህ በኋላ ተሐድሶዎች እነማን እንደሆኑ ንገሩን ማለት መብቃት አለበት፡፡ ሚዛኑ ካለን በሚዛን መዝነን ማንነታቸውን ማወቅ ከባድ አይሆንም፡፡ ምናልባት ማንነታቸውን የምንጠይቀው የራሳችንን ሥራ ለማቃለልና ሥናወራ እንዲመቸን ለማድረግ ካልሆነ በቀር በሥራቸው ታውቋቸዋላችሁ ስለተባልን በሥራቸው መመዘን ነው፡፡ በድምጽ መጎርነን እና ማማር፣ በመልክ ማማር፣ በታዋቂነት፣ ወዘተ ስም ሰዎችን ከቤተ ክርስቲያን የምናስበልጥ ከሆነ ክርስትና ውስጥ አይደለንም ማለት ነው፡፡ ስለ እንቅስቃሴው ሲነገረን ጆሮ ዳባ ልበስ የምንል ከሆነ እግዚአብሔርን ከመስማት ይልቅ እናንተን እንሰማ ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት የሚገባ እንደሆነ ቁረጡ እኛስ ያየነውንና የሰማነውን ከመናገር ዝም ማለት አንችልም አሉዋቸው€ /የሐዋ. ሥራ ፬፥፲፱-፳/ በማለት የተናገሩትን የአባቶቻችንን የሐዋርያትን አሰረ ፍኖት ከመከተል ይልቅ በከንቱ ውዳሴ ተጠልፎ አርዮስን ከውግዘቱ በመፈታቱ እንደተቀሰፈው አኪላስ መሆናችንን መረዳት ይገባናል፡፡ በሃይማኖታችን እያሾፍንበት እንደሆነ ማወቅም ይገባናል፡፡ ቤተ ክርስቲያን የገሃነም ደጆች አይችሏትም ስለ ተባለች ሁሉንም ፈተናዎች አሸንፋ እስከ ዓለም ፍጻሜ ትዘልቃለች፡፡ እኛ ግን ነቅተን ቅጽራችንን ካልጠበቅን የተቀደሰውን አሳልፈን እንሰጣለን፣ ከሰማያዊ ርስትም ዕጣ ፈንታ እናጣለን፡፡ ስለዚህ በዚህ ዘመን ጸንተን ብንገኝና በአቅማችን እኔስ ምን ማድረግ እችላለሁ? ብለን ብንነሣ፣ በጠላት የተዘጋጀልን ፈተና የተሐድሶ እንቅስቃሴ መሆኑን ተረድተን መንፈሳዊ መሣሪያዎቻችንን ሁሉ ታጥቀን መነሣት አለብን፡፡ ፈተና ከሌለ ጽናት፣ ጽናት ከሌለ ድል፣ ድል ከሌለ የድል አክሊል አይገኝምና፡፡

ምንጭ፡- ስምዐ ጽድቅ ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ፣ 23ኛ ዓመት ቁጥር 1/ቅጽ 23፣ቁጥር 329 መስከረም 16-30 ቀን 2008 ዓ.ም

ይቆየ

2015 ኖቬምበር 2, ሰኞ

ከቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ


አትም ኢሜይል
ጥቅምት 22 ቀን 2008 ዓ.ም
06tikm sinodosየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ከጥቅምት 11-22 ቀን 2008 ዓ.ም ሲያካሔድ የቆየውን መደበኛ ስብሰባ በዛሬው ዕለት አጠናቋል፡፡

ከቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠውን መግለጫ እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡
01tikm sinod
02tikm sinod
03tikm sinod
04tikm sinod
05tikm sinodos

ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ: በአ/አበባ ሀ/ስብከት በቅዱስ ሲኖዶስ የተመደበቡትን ሓላፊነት እንዳይወጡ መደረጋቸውን ተናገሩ፤“ሥልጣንን አላግባብ በመጠቀም ዐቢይ የሕግ ግድፈት ተፈጽሟል


?
ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ፡-
  • ከቅዱስ ፓትርያርኩም ኾነ ከጠቅላይ ጽ/ቤቱ ጋር በመልካም የሥራ ግንኙነት ላይ ነበርኩ
  • የአ/አበባ ሀ/ስብከትን ኹለት ሥራ አስኪያጆች የመለመለውና ያቀረበው አካል አይታወቅም
  • ሒሳቡን እንዲያንቀሳቅሱ ሌላ ፈራሚ ሊቀ ጳጳስ የተመደቡበት ኹኔታ አሳዛኝ ክሥተት ነው
  • በረዳት ሊቀ ጳጳስነት የመደበኝ ምልዓተ ጉባኤው፣ ለቤተ ክርስቲያን የሚበጅ መፍትሔ ይስጠኝ
በምልአተ ጉባኤው ስብሰባ፡-
  • ልዩ ደንብና መመሪያ ባልወጣበት የፓትርያርኩ ልዩ ሀ/ስብከት መኾኑ ክፍተት ፈጥሯል
  • የፓትርያርኩ፣ የረዳት ሊቀ ጳጳሱና የሥራ አስኪያጁ ተግባርና ሓላፊነት መታወቅ አለበት
  • በሚሻሻለው ቃለ ዐዋዲ የሦስቱ ሓላፊዎች ሥልጣንና ተግባር ተካቶ እንዲቀርብ ተወስኗል
  • ፓትርያርኩ ያለረዳት ሊቀ ጳጳሱ ምርጫ ሥራ አስኪያጆችን በመሾም የሕግ ግድፈትና ጣልቃ ገብነት የፈጸሙበትን አካሔድ በመደገፍ “ሕመም ቢኖርብኝም የሥራ ፍላጎት አለኝ” በሚል በአዲስ አበባ ለመመደብ የጠየቁት ሊቀ ጳጳስ ክፉኛ ትዝብት ላይ ወድቀዋል
*            *            *
ጥቅምት 15 ቀን 2008 ዓ.ም.
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
ለቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ
አዲስ አበባ
ጉዳዩ፡- በቅዱስ ሲኖዶስ በተሰጠኝ የሥራ ሓላፊነት ላይ ከሕገ ቤተ ክርስቲያኑና ከቃለ ዐዋዲው ውጭ በደል በመፈጸሙ፤ የተፈጸመውን የሥራና የሕግ ግድፈት በቅዱስ ሲኖዶሱ ለማሳረምና ትክክለኛ ፍትሕ እንዲሰጠኝ የቀረበ አቤቱታ ነው
ብፁዕ ወቅዱስ አባታችን፤ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት አባቶቼ፤ እንደሚታወቀው ኹሉ በጥቅምት 2007 ዓ.ም. በመንፈስ ቅዱስ መሪነት እና የበላይነት በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በቤተ ክርስቲያኗ ሕግ መሠረት የቅዱስ ፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ በመኾን መመደቤ ይታወቃል፡፡
እኔም በዚህ በመንፈስ ቅዱስ በሚመራው ታላቅ ጉባኤ እና በአባቶቼ የተሰጠኝን ሓላፊነትና አደራ ከተመደብኩበት ጊዜ አንሥቶ አቅሜ በፈቀደ መልኩ ያለውን ነባራዊ ኹኔታ በማገናዘብ ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጋር በመመካከር የጠቅላይ ቤተ ክህነቱንም የሥራና የደረጃ መዋቅርን በመጠበቅ እያገለገልኩ እገኝ ነበር፤ ለዚህም እንደ ማሳያ፡-
ሀ/በሀገረ ስብከቱ የባለጉዳዮች መስተንግዶ ሥርዐት ዘመናዊና ቀልጣፋ እንዲሁም ተጠያቂነት ያለው እንዲኾን በማድረግ የተለያዩ አደረጃጀቶችን ሊጠቅም በሚችል መልኩ በማውጣት፤
ለ/የንብረትና የገንዘብ አጠባበቅ ኹኔታ በመረጃ የተደራጀ እና ዘመናዊ አሠራር እንዲኖረው በማድረግ፤
ሐ/በመንግሥት በኩል ቤተ ክርስቲያኗ ያላትን መብትና ጥቅም በመገንዘብ ከቀረጥ ነጻ በኾነ መንገድ ለቅዱስ ፓትርያርኩ እና ለሀገረ ስብከቱ የትራንስፖርት መገልገያ የሚውሉ መኪናዎች እንዲገቡ ጥረት በማድረግ፤
መ/ሀገረ ስብከቱ የሚያከናውናቸው ሥራዎች በአጠቃላይ በተጠና ዕቅድ እንዲሠራ፤ የየክፍሎቹ ሓላፊዎች በሚለካና ሊደረስበት በሚችል መልኩ ዕቅድ እንዲዘጋጅና የቀረበው ዕቅድም በአስተዳደር ጉባኤው ተገምግሞ ሥራ ላይ እንዲውል መመሪያ በመስጠት ስንሠራ ቆይተናል፡፡
ከላይ ለማሳያነት የጠቀስኋቸው ተግባራት ብዙ ጠለቅ ያለ የአፈጻጸም ሒደቶች ቢኖሯቸውም አቅም በፈቀደ መልኩ ስንቀሳቀስ ቆይቼ ነበር፡፡
ኾኖም ከቅዱስ ፓትርያርኩም ኾነ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ጋር በመልካም የሥራ ግንኙነት፣ በቤተ ክርስቲያኗ ሕግና መመሪያ መሠረት አባቶቼ የሰጣችኹኝን የሥራ ሓላፊነት በመወጣት ላይ ነበርኩ፡፡
ይኹንና ዐቢይ የሕግ ግድፈት በመፈጸሙ ምክንያትና ሥልጣንን አለአግባብ በመጠቀም ጣልቃ ገብነት ሥራዬን በሓላፊነት እንዳላከናውን ተደርጌአለኹ፡፡ ከዕንቅፋቶቹና ከተፈጸሙት የሕግ ስሕተቶችም መካከል፤
1/ በጥቅምት ወር 2007 ዓ.ም. በቅዱስ ሲኖዶስ ጸድቆ በወጣው ሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ 50፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ሀገረ ስብከት ነው፤ ካለ በኋላ በንኡስ ቁጥር ሦስት፣ ሀገረ ስብከቱ የሚገኘው የሀገሪቱ ርእሰ ከተማ ላይ እንደ መኾኑ መጠን ከሌሎች አህጉረ ስብከት የሚለይባቸው ልዩ ኹኔታዎች ስላሉ እኒኽን ኹኔታዎች ከግምት ያስገባ ለየት ያለ አደረጃጀት በቃለ ዐዋዲው እንዲኖረው እንደሚደረግ ይገልጻል፡፡
በዚህ መሠረት ልዩ መመሪያ ባልወጣበት ኹኔታ አንቀጹን በሌላ መንገድ በመተርጎምና ምክንያቱን በግልጽ ባላወቅሁት መንገድ ሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ 53 ንኡስ ቁጥር 8ን በመተላለፍ፤
1.1) ሊቀ ጳጳሱ ለሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ መልምለው ለቅዱስ ፓትርያርኩ ሳያቀርቡና በሕጉም መሠረት የጋራ ስምምነት ሳይኖረን፤
1.2) በመቀጠልም በሕጉ መሠረት የረዳት ሊቀ ጳጳሱንና የቅዱስ ፓትርያርኩን ይኹንታ መሠረት አድርጎ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ማጽደቅ ሲገባው ይህ መሠረታዊ ሒደት ባልተፈጸመበት ኹኔታ፤
1.3) መልማዩና አቅራቢው በውል ማን እንደኾነ ባልታወቀበትና ሕግ በማይፈቅደው መልኩ በፓትርያርኩ ቀጥተኛ የሹመት ደብዳቤ ሥራ አስኪያጅ እና ምክትል ሥራ አስኪያጅ ለሀገረ ስብከቱ በመመደቡ ምክንያት ሀገረ ስብከቱ ከፍተኛ ቀውስ ውስጥ ገባ፡፡
2. እኒህን ዋነኛ የሕግ ግድፈቶች በመዘርዘር ጉዳዩ በቅዱስ ፓትርያርኩ እንዲታረም በመጀመሪያ በ11/07/2007 ዓ/ም በመቀጠልም በ16/07/2007 ዓ/ም በተጻፈ ደብዳቤ ጠይቄ ነበር፤ ነገር ግን ምላሽ አልተሰጠኝም፡፡ በተጨማሪም ጉዳዩ በቋሚ ሲኖዶስ ትኩረት ተሰጥቶት እንዲታረም በ17/7/2007 ዓ/ም አቅርቤ ነበር፡፡
3. ያለሊቀ ጳጳሱ አቅራቢነትና መልማይነት፣ ያለጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ጽ/ቤት ዕውቅናና አጽዳቂነት ከሕግ ውጭ በቀጥታ በቅዱስ ፓትርያርኩ ለሀገረ ስብከቱ የተሾሙት ሥራ አስኪያጅ፣ የቃለ ዐዋዲውን አንቀጽ 45 ንኡስ ቁጥር 7ን በመተላለፍ፣ አሳማኝ እና ምክንያታዊ ባልኾነ መንገድ በሀገረ ስብከቱ በክፍል ዋና ሓላፊነት ተመድበው የሚሠሩትን ሠራተኞች በ30/08/2007 ዓ/ም ያለሀገረ ስብከቱ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ዕውቅናና ፈቃድ የተወሰኑትን ከደረጃ ዝቅ በማድረግ፣ የቀሩትንም እዚያው ባለው የሥራ ክፍል አዘዋወሩ፡፡
ከዋና ክፍል ሓላፊዎቹ በቀረበልኝ አቤቱታ፤ ሕጉን የጣሰና ምክንያቱ በትክክል ያልታወቀ ዝውውርና ከደረጃም ዝቅ ማድረግ በመኾኑ በተጨማሪም ሠራተኞች በተሰማሩበት የሥራ መስክ ላይ ተረጋግቶ የመሥራት መብትን የሚያሳጣ በመኾኑ ባለኝ ሥልጣንና ሓላፊነት መሠረት በ30/08/2007 ዓ/ም ዝውውሩንና ከደረጃ ዝቅ ማድረጉን አገድኩ፡፡ ይህም በሕጉ መሠረት ተጢኖ መታየትና መገምገም ሲኖርበት የቃለ ዐዋዲውን አንቀጽ 60 ቁጥር 2 ፊደል (ሰ)እና(ሸ) ያለአግባብ በመጥቀስና በመጠቀም በ4/9/2007 ዓ/ም በቅዱስ ፓትርያርኩ በተፈረመ ደብዳቤ እኔ ያስተላለፍኩት ሕጋዊ እግድ ያለአግባብ ተሻረ፡፡
4. ይህ በእንዲህ እንዳለ በ24/09/2007 ዓ/ም ከቅዱስ ፓትርያርኩ በተጻፈ ደብዳቤ በሥራ ገበታዬ ተገኝቼ ሥራዬን እንድቀጥል ደብዳቤ ደረሰኝ፡፡ እኔም በ25/09/2007 ዓ/ም ለደብዳቤው፣ በቅን ልቡና ሥራዬን እየሠራሁ መኾኑን፤ የሠራተኞችን ደመወዝ፣ የሚታወቁና አይቀሬ የኾኑትን የሀገረ ስብከቱን ዕለታዊ የሥራ ማስኬጃ ወጪዎችንም እየፈረምኩ ሥራዎች እየተከናወኑ እንደኾነ በመግለጽ ሥራዬን እንደምሠራ አሳወቅሁ፤ ነገር ግን ባልተለመደ አኳኋን ገንዘብን በሚመለከት ሌላ ሊቀ ጳጰስ እንደተመደበ ሰማኹ፤ ይህ አሳዛኝ ክሥተት ነው፡፡
ስለዚህም በረዳት ሊቀ ጳጳስነት መመደቤን በመወሰን ሥልጣኑንና ሓላፊነቱን የሰጠኝ ይህ ምልዓተ ጉባኤ እንደ መኾኑ፣ ለቤተ ክርስቲያናችን በሚበጅ አካሔድ መፍትሔ ይስጠኝ ዘንድ እጠይቃለኹ፡፡
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ

                                   በአውሮጳ   የካህናት አንድነት ማኅበር ሊቋቋም መሆኑ ታወቀ በ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከመላዋ አውሮጳ   የተውጣጡ ካህናት፡” የ...