2013 ዲሴምበር 3, ማክሰኞ



                                                                   ሀገረ ማርያም

ሀገረማርያም ከተማ  

ከአዲስ አበባ 467 ኪሎ ሜትር ነው፡፡በደቡብ ክልላዊ ምንግስት ቦረና ዞን ውስጥ የምትገኝ የወረዳ ከተማ ናት ሀገረ ማርያም የመጀመሪያ  ስሟ ኩኩ ትባላለች  በኋላ ደግሞ ሀገረ ማርያም ስትባል ቆይታ  አሁን ደግሞ ቡሌ ሆራ እየተባለች ትጠራለች  በቅርቡ በከተማዋ ዳር ላይ የመንግስት ዩኒቨርስቲ ( ቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ/ ተቋቁሟል ፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ቤተ ክርስቲያኒቷ ከሰጠችው ከፍተኛ አደራ ውስጥ ዋናው በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የሚማሩትን የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ተከታዮች ተማሪዎችን  ሥርዓተ ትምህርት ቀርጾ በማስተማር ሃይማኖታቸውን  አጽንተው ይዘው ቤተ ክርስቲያናቸውን ፤ ሀገራቸውን  የሚጠቅሙ መልካም ዜጋ ማፍራት  ተቀዳሚ ተግባሩ ነው፡፡ እኔም ይህንኑ ለመተግበር  ዕለተ ሰኞ በ23/3/2006  ወደ ሀገረ ማርያም ተጉዤ ለ7 ቀናት ያህል ከተማሪዎች ጋር ለመቆየት  ደረስን ሀገረ ማርያም  አንድ ትልቅ የቤተ ክርስቲያን አባት አግኝቼ ጠየቅኳቸው ሀገረ ማርያም ለምን ተባለች? ብዬ እሳቸውም መለሰው ቀድሞ ኩኩ ትባል ነበር በአንድ ዘመን በአካባቢው ትልቅ ጥፋት ያጠፋ ሰው የሚቀጣው በስቅላት ነበርና ሰውዬውን ሲሰቅሉት ገመዱ እየተበጠሰ አስቸገረ ያቀን ደግሞ የእመቤታችን ዕለት ነበረን እመቤታችን ናት ያዳነችው ቦታውንም ከዛሬ ጀምሮ ሀገረ ማርያም ይባል ብለው ተስማሙና ሀገረ ማርያም ተባለች በማለት ነገሩኝ በከተማውም ዕድሜዋ 98 ዓመታት ያስቆጠረች የእመቤታችን  ቤተ ክርስቲያን አለች  ቤተ ክርስቲያኗ ጥንታዊት ናትና በጣም ሰፊ ቦታዎችን  ይዛለች  ከሁሉም የሚያስደስተው  ከk1 እስከ 8ኛ ክፍል ድረስ የሚያስተምር  ቅድስት ማርያም አጸደ ሕጻናትና  1ኛ  ደረጃ ት/ቤ/ት ተከፍቶ  1268 ያህል ተማሪዎችን በማስተማር ላይ ይገናል  በከተማውም ካሉት የግልም ሆነ የመንግስት ት/ቤ/ቶች ተቀዳሚ ተመራጭ መሆኑ የተመሰከረት ይህ የቅድስት ማርያም ት/ቤ/ት ነው ፡፡ በ1980 ዎቹ አጋማሽ የተቋቋመው ይህ ት/ቤ/ት  በደብሩ ሰበካ ጉባኤና በቦርድ አባላት የኋሊትና የፊት በመጎተት ስለሚመራ እድገቱ እዚያው ነው ይላሉ  አንዳንድ ምእመናን  ት/ቤ/ቱ የሚያስከፍለው በጣም አነስተኛ ነው ከሌሎች አንጻር ሲታይ 85.00 የኢት ብር ብቻ  ምክንያቱም ይላሉ የት/ቤ/ቱ መምህራን  የቤተ ክረስቲያናችን ዋና ዓላማ  ገንዘብ ሳይሆን ሰው ማትረፍ ነው  ከ300 በላይ ሕጻናትም በአጸደ ሕጻናቱ  ይማራሉ ፡፡ወላጅ አልባ ተማሪዎችን፤ ተወሰኑ የካህናት ልጆችን ፤ ካህናቱን ቸምሮ በነጻ  እንደሚያስተምርም  የት/ቤ/ቱ ርዕሰ መምህር መ/ር አቢዩ አየለ   በሥርዓተ ትምህርት ጥራት ከዲላ ኒቨርስቲ  የተመረቀውና ልዩ ልዩ ተያያዥ ስልጠናዎችን  የወሰደና ፍላጉት ያለው ነው ርእሰ መምህሩ  ወደፊትም 9ኛ ክፍል ለመቀጠል ዕቅዱ እንዳላቸውም ነግሮኛል ፡፡ የመጻህፍትና ሌሎች  ትምህርት መርጃ መሳርያዎች እጥረት  እንደገጠማቸውና እርዳታ እንደሚፈለጉም እንዲሁ  ፍላጎታችን ብዙ ነው የአቅም ችግር ነው እንጂ ያሉት መላከ ሰላም አባ ኃይለ ገብርኤል  የሀገረ ማርያም ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም  ቤተክርስቲያን  አስተዳደሪ ናቸው  በ5 ብር ክፍያ በጥቂት ጥካራ የቤተ ክርስቲያን ልጆች የአይስኩል መምህራን  ሀሳብ የተጀመረውን ይህንን ት/ቤ/ት በማተናከር በመርዳት በባለሞያ ብቻ እንዲመራ  የትምህርት መርጃ ቁሳቁሶችን በማገዝ  የባለሙያ ድጋፍም እንደሚያስፈልገው ርእሰ መምህሩ አሳስቦአል ፡፡ ት/ቤ/ቱ እስከ አሁን ድረስ ከካህናትም ሌሎችንም ወጣቶች ለከፍተኛ ውጤት  ያበቃ ሲሆን  ወደፊትም አተናክሮ  እንደሚቀጥል ርእሰ መምህሩ ተናግሮአል ፡፡
          
የት/ቤ/ቱ                                            
                                                                                                                                                     
                                                                                    
                                                                                     የት/ቤ/ቱ ርእሰ መምህር                                         
የደብሩ አስተዳዳሪ መላከ ሰላም አባ ኀ/ገብርኤል

2013 ዲሴምበር 1, እሑድ



                                              

                                       ስለ እጨጌ እንባቆም የመናዊ ጽሁፍ አቅራቢዎች                                                                                                  ሊቃውንትን እናስባቸው  የሚል መርሃግብር ተካሄደ

                                                                                                                                              እጨጌ እንባቆም የመናዊ  በተመለከተ የተካሄደው መርሃ ግብር በእጨጌ እንባቆም የሕይወት ታሪክና የተረጎማቸውን መጻሕፍትን እና በታላቁ በደብረ ሊባኖስ ገዳም ለሁለት ጊዜ እጨጌ ሆኖ ማገልገሉን  በቀረበው ጽሁፉ  ተጠቅሶአል፡፡ እጨጌ እንባቆም ትውልዱ የመን ሲሆን የእስልምና ሃማኖት ተከታይ የነበረና በእመቤታችን አማካይነት ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ከተማረ በኋላ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖትን ተቀብሎ ብዙ መጻሕፍትን ከአረቢኛ ወደ ግዕዝ ተርጉሞአል ከእነዚህም መካከል የቅዱስ ጳውሎስን መልእክት  ወደ እብራውን፤ መጽሐፈ በረላም ወይዋስፍ ኦሪት ዘፍጥረትን፤አረጋዊ መንፈሳዊን  ከአረብኛ ወደ ግዕዝ ተርጉሞአል፡፡መጽሐፈ ቄደር አቡሻኸርን የጻፈ ሲሆን አንቀጸ አሚን  የሚባል መጽሐፍ ለአህመድ ግራን መልስ ይሆን ዘንድ በዘመኑ ጽፎአል፡፡ እጨጌ እንባቆም 14 የተለያዩ ቋንቋዎችን ይናገራል፡፡ የዚህ ታላቅ ጻድቅ ገድሉ በደብረ ሊባኖስ ገዳምና ጎንደር ብቻ ለጊዜው ተገኝቶአል ፡፡ ኅዳር 25 ቀን በደብረ ሊባኖስ ገዳም እጨጌ ሆኖ የተሾመበት ዕለት ነው ፡፤ዘመኑም በ16ኛው መ/ክ ነው፡፡ እጨጌ እንባቆም በ1482 ዓ.ም ከየመን ወደ ኢትዮጵያ የመጣ ሲሆን በ1488 ዓ.ም ደብረ ሊባኖስ ገዳም ገብቶ ምንኖ ይኖር ነበር፡፡ እጨጌ እንባቆም በጸሎትና በሥርዓተ ቤተ ክርስቲን የጸና አቅዋም እንደ ነበረው በቀረበው ጽሁፍ ተገልጦአል፡፤ በተለይ በምዕራብ ሸዋ እና በአጠቃላይ ወለጋ አካባቢ በስፋት ያስተማረ ጻድቅ ነው፡፡  በ1553 ዓ.ም በ141 ዓመቱ አርፎ በደብረ ሊባኖስ ገዳም ተቀብሮአል ፡፡‹‹ይህ ሊቃውንትን እናስባቸው ››መርሃ ግብር የተዘጋጀው ዲ/ን ዳንኤል ክብረትና በደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም ምክሐ ደናግል ሰ/ት/ቤት ጋር በመተባበር ሲሆን  ጽሁፉን ያቀረቡት  መጋቤ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ፤ ዲ/ን ዳንኤል ክብረት፤ ዲ/ን አባይነህ ካሴ፤ መ/ር ኃይለማርያም አያሌው ሲሆኑ ቀሲስ መንግስቱ ጎበዜ ደግሞ አወያይ ነበሩ ፡፡ቦታው ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም ሰ/ት/ቤት ሲሆን  ተኅሳስ 27 /2006 ዓ.ም  ስለጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ጥናታዊ ጽሁፍ እንደሚቀርብም ተገልጦ ጥሪ ተላልፎአል፡፡
                                                                               

                                   በአውሮጳ   የካህናት አንድነት ማኅበር ሊቋቋም መሆኑ ታወቀ በ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከመላዋ አውሮጳ   የተውጣጡ ካህናት፡” የ...