2014 ማርች 14, ዓርብ

ዐቢይ ጾም አራተኛ ሳምንት "መጻጉዕ"

 


ይህ ሳምንት የዐቢይ ጾም አራተኛ ሳምንት እሁድ ነው። ስሙም መጻጉዕ ይባላል። በዚህ እለት ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ድውያንን ፈውሷል፥ ጎባጣዎችን አቅንቷል፣ እውራንን አብርቷል፣ አንካሶችንም አድኗል ለምፃሞችንም በመለኮታዊ ሃይሉ አንጽቷል። ቤተ ክርስቲያናችንም በዚህ ዕለት ስለ ጌታችነ ገቢረ ተዓምራትና ስለ ድውያን ፈውስ በሰፊው ታስተምራለች። በቅዳሴ ጊዜ ይህንኑ የሚያስረዱ የመፃሕፍት ክፍሎችም ይነበባሉ። እነሱንም እንደሚከተለው ማየት እንችላለን።
የመጀመሪያ ምንባብ የሐዋርያው የቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት ወደ ገላትያ ሰዎች
ምዕራፍ 
፩. በነጻነት ልንኖር ክርስቶስ ነጻነት አወጣን፤ እንግዲህ ጸንታችሁ ቁሙ እንደ ገናም በባርነት ቀንበርአትያዙ። ፪. እነሆ፥ እኔ ጳውሎስ እላችኋለሁ። ብትገረዙ ክርስቶስ ምንም አይጠቅማችሁም። ፫.ሕግንም ሁሉ እንዲፈጽም ግድ አለበት ብዬ ለሚገረዙት ሁሉ ለእያንዳንዶች ደግሜ እመሰክራለሁ።፬. በሕግ ልትጸድቁ የምትፈልጉ ከክርስቶስ ተለይታችሁ ከጸጋው ወድቃችኋል። ፭.  እኛ በመንፈስከእምነት የጽድቅን ተስፋ እንጠባበቃለንና። ፮. በክርስቶስ ኢየሱስ ሆኖ፥ በፍቅር የሚሠራ እምነትእንጂ መገረዝ ቢሆን ወይም አለመገረዝ አይጠቅምምና። ፯. በመልካም ትሮጡ ነበር፤ ለእውነትእንዳትታዘዙ ማን ከለከላችሁ?፰.  ይህ ማባበል ከሚጠራችሁ አልወጣም። ጥቂት እርሾ ሊጡን ሁሉያቦካል። ፱-፲. የተለየ ነገር ከቶ እንዳታስቡ እኔ በጌታ ስለ እናንተ ታምኜአለሁ፤ የሚያናውጣችሁ
ማንም ቢኖር ግን ፍርዱን ሊሸከም ነው። ፲፩. ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ እኔ ገና እስከ አሁንመገረዝን ብሰብክ እስከ አሁን ድረስ ለምን ያሳድዱኛልእንኪያስ የመስቀል ዕንቅፋት ተወግዶአል።፲፪. የሚያውኩአችሁ ይቆረጡ። ፲፫. ወንድሞች ሆይ፥ እናንተ ለአርነት ተጠርታችኋልና፤ ብቻአርነታችሁ ለሥጋ ምክንያትን አይስጥ፥ ነገር ግን በፍቅር እርስ በርሳችሁ እንደ ባሪያዎች ሁኑ። ፲፬. ሕግ ሁሉ በአንድ ቃል ይፈጸማልና፥
እርሱም። ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ የሚል ነው። ፲፭. ነገር ግን እርስ በርሳችሁ
ብትነካከሱ ብትበላሉ እርስ በርሳችሁ እንዳትጠፋፉ ተጠንቀቁ። ፲፮.  ነገር ግን እላለሁ፥ በመንፈስተመላለሱ፥ የሥጋንም ምኞት ከቶ አትፈጽሙ። ፲፯. ሥጋ በመንፈስ ላይ መንፈስም በሥጋ ላይይመኛልና፥ እነዚህም እርስ በርሳቸው ይቀዋወማሉ፤ ስለዚህም የምትወዱትን ልታደርጉ አትችሉም።፲፰.  በመንፈስ ብትመሩ ግን
ከሕግ በታች አይደላችሁም። ፲፱. የሥጋ ሥራም የተገለጠ ነው እርሱም ዝሙት፥ ርኵሰት፥ ፳.መዳራት፥ ጣዖትን ማምለክ፥ ምዋርት፥ ጥል፥ ክርክር፥ ቅንዓት፥ ቁጣ፥ አድመኛነት፥ ፳፩.  መለያየት፥መናፍቅነት፥ ምቀኝነት፥ መግደል፥ ስካር፥ ዘፋኝነት፥ ይህንም የሚመስል ነው። አስቀድሜምእንዳልሁ፥ እንደዚህ ያሉትን የሚያደርጉ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም። ፳፪. የመንፈስፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥
እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው።፳፫.  እንደዚህ ያሉትን የሚከለክል ሕግ የለም። ፳፬. የክርስቶስ ኢየሱስም የሆኑቱ ሥጋን ከክፉ መሻቱና ከምኞቱ ጋር ሰቀሉ። ፳፭. በመንፈስ ብንኖርበመንፈስ ደግሞ እንመላለስ። ፳፮. እርስ በርሳችን እየተነሣሣንና እየተቀናናን በከንቱ አንመካ።
ሁለተኛ ምንባብ የያዕቆብ መልእክት
ምዕራፍ 
፲፬. ከእናንተ የታመመ ማንም ቢኖር የቤተ ክርስቲያንን ሽምግሌዎች ወደ እርሱ ይጥራ፤ በጌታምስም እርሱን ዘይት ቀብተው ይጸልዩለት። ፲፭.  የእምነትም ጸሎት ድውዩን ያድናል ጌታምያስነሣዋል፤ ኃጢአትንም ሠርቶ እንደ ሆነ ይሰረይለታል። ፲፮. እርስ በርሳችሁ በኃጢአታችሁተናዘዙ። ትፈወሱም ዘንድ እያንዳንዱ ስለ ሌላው ይጸልይ፤ የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግኃይል ታደርጋለች። ፲፯. ኤልያስ እንደ እኛ የሆነ ሰው ነበረ፥ ዝናብም እንዳይዘንብ አጥብቆ ጸለየ፥በምድርም ላይ ሦስት ዓመት ከስድስት ወር አልዘነበም፤ ሁለተኛም ጸለየ፥ ፲፰. ሰማዩም ዝናብን ሰጠምድሪቱም ፍሬዋን አበቀለች። ፲፱. ወንድሞቼ ሆይ፥ ከእናንተ ማንም ከእውነት
ቢስት አንዱም ቢመልሰው፥ ፳. ኃጢአተኛን ከተሳሳተበት መንገድ የሚመልሰው ነፍሱን ከሞትእንዲያድን፥የኃጢአትንም ብዛት እንዲሸፍን ይወቅ።
ሦስተኛው ምንባብ የሐዋርያት ሥራ
ምዕራፍ 3
፩. ጴጥሮስና ዮሐንስም በጸሎት ጊዜ በዘጠኝ ሰዓት ወደ መቅደስ ይወጡ ነበር። ፪. ወደ መቅደስምከሚገቡት ምጽዋት ይለምን ዘንድ፥ ሰዎች ተሸክመው መልካም በሚሉአት በመቅደስ ደጅ በየቀኑያስቀምጡት የነበሩ ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ አንካሳ የሆነ አንድ ሰው ነበረ። ፫. እርሱም ጴጥሮስናዮሐንስ ወደ መቅደስ ሊገቡ እንዳላቸው ባየ ጊዜ፥ ምጽዋትን ለመናቸው። ፬. ጴጥሮስም ከዮሐንስ ጋርትኵር ብሎ ወደ እርሱ ተመልክቶ። ወደ እኛ
ተመልከት አለው። ፭. እርሱም አንድ ነገር ከእነርሱ እንዲቀበል ሲጠብቅ ወደ እነርሱ ተመለከተ።፮. ጴጥሮስ ግን። ብርና ወርቅ የለኝም፤ ይህን ያለኝን ግን እሰጥሃለሁ፤ በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስስም ተነሣና ተመላለስ አለው።
፯.  በቀኝ እጁም ይዞ አስነሣው፤ በዚያን ጊዜም እግሩና ቍርጭምጭምቱ ጸና፥ ፰. ወደ ላይ ዘሎምቆመ፥ ይመላለስም ጀመር፤ እየተመላለሰም እየዘለለም እግዚአብሔርንም እያመሰገነ ከእነርሱ ጋር ወደመቅደስ ገባ። 9 ሕዝቡም ሁሉ እግዚአብሔርን እያመሰገነ ሲመላለስ አዩት፤ ፲. መልካምምበሚሉአት በመቅደስ ደጅ ስለ ምጽዋት ተቀምጦ የነበረው እርሱ እንደ ሆነ አወቁት፤ በእርሱምከሆነው የተነሣ መደነቅና መገረም ሞላባቸው። ፲፩. እርሱም ጴጥሮስንና ዮሐንስን ይዞ ሳለ፥ ሕዝቡሁሉ እየተደነቁ የሰሎሞን ደጅ መመላለሻ በሚባለው አብረው ወደ እነርሱ
ሮጡ። ፲፪. ጴጥሮስም አይቶ ለሕዝቡ እንዲህ ሲል መለሰ። የእስራኤል ሰዎች ሆይ፥ በዚህ ስለ ምንትደነቃላችሁወይስ በገዛ ኃይላችን ወይስ እግዚአብሔርን በመፍራታችን ይህ ይመላለስ ዘንድእንዳደረግነው ስለ ምን ትኵር ብላችሁ ታዩናላችሁ?
የዕለቱ ምስባክ
እግዚአብሔር ይረድኦ ውስተ ዓራተ ሕማሙ
ወይመይጥ ሎቱ ኩሉ ምስካቤሁ እምደዌሁ
አንሰ እቤ እግዚኦ ተሣሃለኒ።         መዝ.፵፥፫
እግዚአብሔር በደዌው አልጋ ሳለ ይረዳዋል
መኝታውን ሁሉ በበሽታው ጊዜ ያነጥፍለታል
እኔስ አቤቱ ማረኝ።       መዝ.፵፥፫
የዕለቱ ወንጌል የዮሐንስ ወንጌል
ራፍ 5
፩. ከዚህ በኋላ የአይሁድ በዓል ነበረ፥ ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ። ፪. በኢየሩሳሌምም በበጎችበር አጠገብ በዕብራይስጥ ቤተ ሳይዳ የምትባል አንዲት መጠመቂያ ነበረች፤ አምስትም መመላለሻነበረባት። ፫. በእነዚህ ውስጥ የውኃውን መንቀሳቀስ እየጠበቁ በሽተኞችና ዕውሮች አንካሶችምሰውነታቸውም የሰለለ ብዙ ሕዝብ ይተኙ ነበር። ፬. አንዳንድ ጊዜ የጌታ መልአክ ወደመጠመቂያይቱ ወርዶ ውኃውን ያናውጥ ነበርና፤ እንግዲህ ከውኃው መናወጥ በኋላ በመጀመሪያ የገባከማናቸው ካለበት ደዌ ጤናማ ይሆን ነበር። ፭. በዚያም ከሠላሳ ስምንት ዓመት ጀምሮ የታመመአንድ ሰው ነበረ፤ ፮. ኢየሱስ ይህን ሰው ተኝቶ ባየ ጊዜ፥ እስከ አሁን ብዙ ዘመን እንዲሁ እንደ ነበረአውቆ። ልትድን ትወዳለህንአለው። ፯. ድውዩም። ጌታ ሆይ፥ ውኃው በተናወጠ ጊዜበመጠመቂያይቱ ውስጥ የሚያኖረኝ ሰው የለኝም ነገር ግን እኔ ስመጣ ሳለሁ ሌላው ቀድሞኝይወርዳል ብሎ መለሰለት። ፰. ኢየሱስ። ተነሣና አልጋህን ተሸክመህ ሂድ አለው። ፱. ወዲያውምሰውዬው ዳነ አልጋውንም ተሸክሞ ሄደ። ፲. ያም ቀን ሰንበት ነበረ። ስለዚህ አይሁድ የተፈወሰውንሰው። ሰንበት ነው አልጋህንም ልትሸከም አልተፈቀደልህም አሉት። ፲፩. እርሱ ግን። ያዳነኝ ሰው። አልጋህን ተሸክመህ ሂድ አለኝ ብሎ መለሰላቸው። ፲፪. እነርሱም። አልጋህን ተሸክመህ ሂድያለህ ሰው ማን ነውብለው ጠየቁት። ፲፫. ዳሩ ግን በዚያ ስፍራ ሕዝብ ሰለ ነበሩ ኢየሱስ ፈቀቅብሎ ነበርና የተፈወሰው ሰው ማን እንደ ሆነ አላወቀም። ፲፬.  ከዚህ በኋላ ኢየሱስ በመቅደስአገኘውና። እነሆ፥ ድነሃል፤ ከዚህ የሚብስ እንዳይደርስብህ ወደ ፊት ኃጢአት አትሥራ አለው። ፲፭.ሰውዬው ሄዶ ያዳነው ኢየሱስ እንደ ሆነ ለአይሁድ ነገረ። ፲፮. ስለዚህም በሰንበት ይህን ስላደረገአይሁድ ኢየሱስን ያሳድዱት ነበር ሊገድሉትም ይፈልጉ ነበር። ፲፯. ኢየሱስ ግን። አባቴ እስከ ዛሬይሠራል እኔም ደግሞ እሠራለሁ ብሎ መለሰላቸው። ፲፰. እንግዲህ ሰንበትን ስለ ሻረ ብቻአይደለም፥ ነገር ግን ደግሞ ራሱን ከእግዚአብሔር ጋር አስተካክሎ። እግዚአብሔር አባቴ ነው ስላለ፥ስለዚህ አይሁድ ሊገድሉት አብዝተው ይፈልጉት ነበር። ፲፱. ስለዚህ ኢየሱስ መለሰ እንዲህምአላቸው። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብ ሲያደርግ ያየውን ነው እንጂ ወልድ ከራሱ ሊያደርግምንም አይችልም፤  የሚያደርገውን ሁሉ ወልድ ደግሞ ይህን እንዲሁ ያደርጋልና። ፳. አብ ወልድንይወዳልና፥ የሚያደርገውንም ሁሉ ያሳየዋል፤ እናንተም ትደነቁ ዘንድ ከዚህ የሚበልጥ ሥራ ያሳየዋል።፳፩. አብ ሙታንን እንደሚያነሣ ሕይወትም እንደሚሰጣቸው፥ እንዲሁ ወልድ ደግሞ ለሚወዳቸውሕይወትን ይሰጣቸዋል።
፳፪-፳፫. ሰዎች ሁሉ አብን እንደሚያከብሩት ወልድን ያከብሩት ዘንድ፥ ፍርድን ሁሉ ለወልድሰጠው እንጂ አብ በአንድ ሰው ስንኳ አይፈርድም። ወልድን የማያከብር የላከውን አብንአያከብርም። ፳፬. እውነት እውነት
እላችኋለሁ፥ ቃሌን የሚሰማ የላከኝንም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፥ ከሞትም ወደ ሕይወትተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም። ፳፭. እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ሙታን የእግዚአብሔርንልጅ ድምፅ የሚሰሙበት ሰዓት ይመጣል እርሱም አሁን ነው፤ የሚሰሙትም በሕይወት ይኖራሉ።





2014 ማርች 13, ሐሙስ

የቤተ ሰብእ መሪ

                      

                                            አርባ ምንጭ መንበረ ጵጵስና

                                                                                                                                                              ከካቲት 28- 30 ድረስ ለመንፈሳዊ አገልግሎት ወደ አርባ ምንጭ  ከባልደረቦቼ መጋቤ ሐዲስ መንግስቱ አማረ ፤ ዲ. ተመስገን ዘገዬ እና ዘማሪት መሠረት ማሞ ጋር በመሆን ተጉዘን ነበር  አርባ ምንጭ እንደሚታወቀው ሁለቱን ሐይቆች አባያ እና ጫሞን ዓይን አድርጋ ውበትን የተላበሰች ቱሪስቶች ሁል ጊዜ የማይለይዋት ሞቃት ከተማ ናት ፡ አርባ ምንጭ  በከተማዋ ከላይና ከታች/ ከመግቢያዋና ከመወጫዋ ታላላቅ ዩኒቨርስቲዎች ይገኛሉ ፡፡ የሀገረ ስብከቱም ሊቀጳጳስ አቡነ ኤልያስም በቅርቡ አሰርተው በቅዱስ ፓትርያርኩ ያስመረቁትም ሁለገብ የሆነ መንበረ ጵጵስና ሁለቱን ሀይቆች በርቀት ይቆጣጠራል፡፡ እኛም የተጓዝንበትም አገልግሎት ውጤታማ ነበረ፡እሁድ ከቅዳሴ በኋላ በከተማዋ መሃል በሚገኘው ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ቅጥር ገቢ ወደ ሚገኘው የማኅበረ ቅዱሳን አርባ ምንጭ ማዕከል ብቅ አልን አባላቱ ውይይት ላይ ናቸው፡፡ የመወያያ አጀንዳው ‹‹የቤተ ሰብእ መሪ ›› የሚል ነበር  አባላቱ መንፈሳዊ አገልግሎትን  ለማጠናከር ሲሉ አሥር ያህል አባላት ያሉት ቡድን አዋቅረዋል  አንድ የቤተ ሰብእ መሪ አለው፡፡ ቤተ ሰብእ መሪው ስለመንፈሳዊ ሕይወታቸው አጠቃላይ ይከታተል ዘንድ ተመርጧል ለምሳሌ፤
                                ከንስሐ አባታቸው ጋር ያለቸውን   ግንኙነት
                                 በሰንበት ት/ቤት አገልግሎት
                                 በሰበካ ጉባኤ ያለቸውን ተሳትፎ
                                 በማህበራዊ ኑሮ
                                 ከሀገረ ስብከቱ እና አድባራት አገልጋዮች ያለቸውን መልካም ግንኙነት ይከታተላል የቤተ ሰብእ መሪው ፤ እኔም ይህ ተሞክሮ ለሌሎች የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮ ጥሩ ምሳሌ ስለሆነ ይበል እንላለን፡፡
                                           

2014 ማርች 5, ረቡዕ

ፓትርያርኩ የቤተ ክርስቲያኒቷን አስተዳደር የማሻሻል አቋሜ ‹‹አልተበረዘም፤ አልተከለሰም›› አሉ


  • ‹‹የፀረ ሙስና አቋማቸው ራሳቸውን ከማስተዋወቅ ያለፈ ውጤት አላመጣም›› /ተቺዎች/
(ሰንደቅ፤ የካቲት ፳፮ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም.)
Sendek front pageየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፍትሕ፣ ርትዕና እኩልነት የሞላባት፣ መልካም አስተዳደር የሰፈነባት ለማድረግ በዕለተ ሢመተ ፕትርክናቸው የተናገሩት ቃል ኹሉ እንደጸና መኾኑንና ከቅዱስ ሲኖዶስ አባላት፣ ከሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና ከምእመናን ጋር በመኾን እንደሚያጠናክሩት ፓትርያርኩ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ተናገሩ፡፡
የቤተ ክርስቲያኒቱ ስድስተኛ ፓትርያርክ ኾነው የተሾሙበት አንደኛ ዓመት ከትላንት በስቲያ በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በተከበረበት ወቅት ‹‹ሙስና ካልጠፋ ሕይወት አይኖርም›› ሲሉ የተናገሩት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚሰበሰበው ገንዘብ ከድኾች የተገኘ ሀብት ስለኾነ የድኾችን ገንዘብ በከንቱ የሚያማስነውን እግዚአብሔር እንደሚፈርድበት፣ በዚኽም እግዚአብሔርን ማታለልና በእግዚአብሔር ላይ መቀለድ እንደማይቻል አስጠንቅቀዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያን የእውነትና የሐቅ መገኛ ትኾን ዘንድ መንፈሳዊ ባሕርይዋ የሚያስገድዳትና አገልግሎትዋም በእግዚአብሔር ስም የሚሠራ በመኾኑ አሠራርዋ ከአድሏዊነትና ወገንተኝነት መጽዳት፣ ታማኝነትንና ፍትሐዊነትን መጎናጸፍ ይኖርበታል ብለዋል ፓትርያርኩ፡፡
ቤተ ክርስቲያን ሲባል ሕንፃ ቤተ መቅደሱ ብቻ ሳይኾን የካህናትና የምእመናን አንድነትም መኾኑን ያስረዱት አቡነ ማትያስ፣ በይበልጥም ቤተ ክርስቲያኒቷን በሓላፊነት ለመጠበቅ ጥሪው ያላቸው ካህናት በአበው ሥርዐት በተደነገገው መሠረት÷ ቀኖናዋንና ትውፊቷን መጠበቅና ማስጠበቅ፣ ምእመኖቿን በስብከተ ወንጌል ማርካትና በግብረ ገብነት እንዲታነፁ ማድረግ የዉሉደ ክህነት ሓላፊነት ነው፤ ከዚኽ አንጻር ዉሉደ ክህነት የቤተ ክርስቲያኒቱ ተልእኮ ፈሩን ሳይስት እንዲፈጸም የማድረግ መንፈሳዊ ግዴታ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
በዓለ ሢመቱ የአንድ መሪ ግለሰብ በዓል እንዳልኾነ ያስገነዘቡት ፓትርያርኩ፣ በዓሉ የቤተ ክርስቲያኒቱ ኹለንተናዊ ልዕልናና ክብር በፊት እንዴት እንደነበር፣ አኹን ምን ላይ እንዳለና በቀጣይ ሐዋርያዊ ተልእኮዋን በስኬት ለማከናወን ምን መደረግ እንዳለበት እየታሰበ እንደሚከበር አብራርተዋል፡፡ ከሥርዐተ ሢመታቸው ወዲህ ባለፈው የአንድ ዓመቱ ጉዞ ውስጥ ተከናውነዋል ያሏቸውን ተግባራት ፓትርያርኩ በንግግራቸው ዘርዝረዋል፡፡
‹‹የቤተ ክርስቲያኒቱ ሕግ እየተሻሻለ ነው፤ በመልካም አስተዳደር፣ በመሪ ዕቅድ እንድትመራ ጥረት እየተደረገ ነው፤›› በማለት ክንውኑን የጠቀሱት ፓትርያርኩ፣ ‹‹ችግሩ ለዘመናት የተከማቸና በአጭር ጊዜ ለውጥ ለማምጣት ስለሚያዳግት በትዕግሥት መጠባበቁ መልካም ይኾናል፤›› ብለዋል፡፡ በበዓለ ሢመታቸው ቀን የአስተዳደር መዋቅር ማሻሻያን አስመልክቶ ተናግረዋቸው የነበሩ ቃላት ኹሉ ‹‹እንደጸኑ ናቸው፤ አልተበረዙም፤ አልተከለሱም፤ እንዲያውም ከሲኖዶስ አባላት፣ ከሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና ከምእመናን ጋር በመኾን አጠናክራቸዋለኹ›› ያሉት አቡነ ማትያስ፣ ለመልካም አስተዳደር መረጋገጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ባለድርሻ አካላት ኹሉ መነሣት እንደሚኖርባቸው ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፤ ‹‹ይህ ግዴታ ነው›› ሲሉም አክለዋል፡፡
የቤተ ክርስቲያኒቱ የአስተዳደር መዋቅር እንዲሁም አደረጃጀትና አሠራር ከመሠረታዊ ክህነታዊና የስብከተ ወንጌል ተልእኮዋ ጋራ እንዲጣጣም፣ ሙስናና ብልሹ አሠራር እንዲወገድ የተደረጉ የሙከራ ትግበራዎችና በመደረግ ላይ ያሉ ጥረቶች፣ ‹‹ይኹንታ ካገኙበት የቅ/ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ውሳኔ በተፃራሪ ዕንቅፋት ገጥሟቸዋል፤›› የሚሉ የቅርብ ታዛቢዎች በበኩላቸው÷ ፓትርያርኩ ሙስናን በየአጋጣሚው በመቃወምና ስለመልካም አስተዳደር ደጋግሞ በመናገር ራሳቸውን አስተዋውቀው እንደኾነ እንጂ ያመጡት ተስፋ ሰጭ ውጤት የለም፤ እንዲያውም በደሉና ጥፋቱ መልኩን ለውጡ እየረቀቀና እየተባባሰ መምጣቱን በምሬት ይናገራሉ፡፡
በቤተ ክርስቲያኒቱ አስተዳደር ውስጥ ሥር ሰዷል ያሉት ጎሰኝነት ከቀድሞም ጀምሮ ስማቸው ሲጠቀስ በቆዩና በተለይ በፓትርያርኩ ጽ/ቤት ዙሪያ በተሰባሰቡ ግለሰቦች ተጽዕኖ እየገዘፈ መምጣቱን ታዛቢዎቹ ከማስረዳታቸውም በላይ፣ ፓትርያርኩ ‹‹እንደ ጸና ነው›› የሚሉት አቋማቸው በላቀ አመራርና የውሳኔ ሰጭነት አቅም ተፈትኖና በተግባር ተገልጦ ማየት እንደሚሹ ለሰንደቅ ገልጸዋል፡፡

                                   በአውሮጳ   የካህናት አንድነት ማኅበር ሊቋቋም መሆኑ ታወቀ በ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከመላዋ አውሮጳ   የተውጣጡ ካህናት፡” የ...