2014 ማርች 13, ሐሙስ

የቤተ ሰብእ መሪ

                                            አርባ ምንጭ መንበረ ጵጵስና

                                                                                                                                                              ከካቲት 28- 30 ድረስ ለመንፈሳዊ አገልግሎት ወደ አርባ ምንጭ  ከባልደረቦቼ መጋቤ ሐዲስ መንግስቱ አማረ ፤ ዲ. ተመስገን ዘገዬ እና ዘማሪት መሠረት ማሞ ጋር በመሆን ተጉዘን ነበር  አርባ ምንጭ እንደሚታወቀው ሁለቱን ሐይቆች አባያ እና ጫሞን ዓይን አድርጋ ውበትን የተላበሰች ቱሪስቶች ሁል ጊዜ የማይለይዋት ሞቃት ከተማ ናት ፡ አርባ ምንጭ  በከተማዋ ከላይና ከታች/ ከመግቢያዋና ከመወጫዋ ታላላቅ ዩኒቨርስቲዎች ይገኛሉ ፡፡ የሀገረ ስብከቱም ሊቀጳጳስ አቡነ ኤልያስም በቅርቡ አሰርተው በቅዱስ ፓትርያርኩ ያስመረቁትም ሁለገብ የሆነ መንበረ ጵጵስና ሁለቱን ሀይቆች በርቀት ይቆጣጠራል፡፡ እኛም የተጓዝንበትም አገልግሎት ውጤታማ ነበረ፡እሁድ ከቅዳሴ በኋላ በከተማዋ መሃል በሚገኘው ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ቅጥር ገቢ ወደ ሚገኘው የማኅበረ ቅዱሳን አርባ ምንጭ ማዕከል ብቅ አልን አባላቱ ውይይት ላይ ናቸው፡፡ የመወያያ አጀንዳው ‹‹የቤተ ሰብእ መሪ ›› የሚል ነበር  አባላቱ መንፈሳዊ አገልግሎትን  ለማጠናከር ሲሉ አሥር ያህል አባላት ያሉት ቡድን አዋቅረዋል  አንድ የቤተ ሰብእ መሪ አለው፡፡ ቤተ ሰብእ መሪው ስለመንፈሳዊ ሕይወታቸው አጠቃላይ ይከታተል ዘንድ ተመርጧል ለምሳሌ፤
                                ከንስሐ አባታቸው ጋር ያለቸውን   ግንኙነት
                                 በሰንበት ት/ቤት አገልግሎት
                                 በሰበካ ጉባኤ ያለቸውን ተሳትፎ
                                 በማህበራዊ ኑሮ
                                 ከሀገረ ስብከቱ እና አድባራት አገልጋዮች ያለቸውን መልካም ግንኙነት ይከታተላል የቤተ ሰብእ መሪው ፤ እኔም ይህ ተሞክሮ ለሌሎች የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮ ጥሩ ምሳሌ ስለሆነ ይበል እንላለን፡፡
                                           
2014 ማርች 5, ረቡዕ

ፓትርያርኩ የቤተ ክርስቲያኒቷን አስተዳደር የማሻሻል አቋሜ ‹‹አልተበረዘም፤ አልተከለሰም›› አሉ

  • ‹‹የፀረ ሙስና አቋማቸው ራሳቸውን ከማስተዋወቅ ያለፈ ውጤት አላመጣም›› /ተቺዎች/
(ሰንደቅ፤ የካቲት ፳፮ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም.)
Sendek front pageየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፍትሕ፣ ርትዕና እኩልነት የሞላባት፣ መልካም አስተዳደር የሰፈነባት ለማድረግ በዕለተ ሢመተ ፕትርክናቸው የተናገሩት ቃል ኹሉ እንደጸና መኾኑንና ከቅዱስ ሲኖዶስ አባላት፣ ከሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና ከምእመናን ጋር በመኾን እንደሚያጠናክሩት ፓትርያርኩ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ተናገሩ፡፡
የቤተ ክርስቲያኒቱ ስድስተኛ ፓትርያርክ ኾነው የተሾሙበት አንደኛ ዓመት ከትላንት በስቲያ በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በተከበረበት ወቅት ‹‹ሙስና ካልጠፋ ሕይወት አይኖርም›› ሲሉ የተናገሩት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚሰበሰበው ገንዘብ ከድኾች የተገኘ ሀብት ስለኾነ የድኾችን ገንዘብ በከንቱ የሚያማስነውን እግዚአብሔር እንደሚፈርድበት፣ በዚኽም እግዚአብሔርን ማታለልና በእግዚአብሔር ላይ መቀለድ እንደማይቻል አስጠንቅቀዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያን የእውነትና የሐቅ መገኛ ትኾን ዘንድ መንፈሳዊ ባሕርይዋ የሚያስገድዳትና አገልግሎትዋም በእግዚአብሔር ስም የሚሠራ በመኾኑ አሠራርዋ ከአድሏዊነትና ወገንተኝነት መጽዳት፣ ታማኝነትንና ፍትሐዊነትን መጎናጸፍ ይኖርበታል ብለዋል ፓትርያርኩ፡፡
ቤተ ክርስቲያን ሲባል ሕንፃ ቤተ መቅደሱ ብቻ ሳይኾን የካህናትና የምእመናን አንድነትም መኾኑን ያስረዱት አቡነ ማትያስ፣ በይበልጥም ቤተ ክርስቲያኒቷን በሓላፊነት ለመጠበቅ ጥሪው ያላቸው ካህናት በአበው ሥርዐት በተደነገገው መሠረት÷ ቀኖናዋንና ትውፊቷን መጠበቅና ማስጠበቅ፣ ምእመኖቿን በስብከተ ወንጌል ማርካትና በግብረ ገብነት እንዲታነፁ ማድረግ የዉሉደ ክህነት ሓላፊነት ነው፤ ከዚኽ አንጻር ዉሉደ ክህነት የቤተ ክርስቲያኒቱ ተልእኮ ፈሩን ሳይስት እንዲፈጸም የማድረግ መንፈሳዊ ግዴታ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
በዓለ ሢመቱ የአንድ መሪ ግለሰብ በዓል እንዳልኾነ ያስገነዘቡት ፓትርያርኩ፣ በዓሉ የቤተ ክርስቲያኒቱ ኹለንተናዊ ልዕልናና ክብር በፊት እንዴት እንደነበር፣ አኹን ምን ላይ እንዳለና በቀጣይ ሐዋርያዊ ተልእኮዋን በስኬት ለማከናወን ምን መደረግ እንዳለበት እየታሰበ እንደሚከበር አብራርተዋል፡፡ ከሥርዐተ ሢመታቸው ወዲህ ባለፈው የአንድ ዓመቱ ጉዞ ውስጥ ተከናውነዋል ያሏቸውን ተግባራት ፓትርያርኩ በንግግራቸው ዘርዝረዋል፡፡
‹‹የቤተ ክርስቲያኒቱ ሕግ እየተሻሻለ ነው፤ በመልካም አስተዳደር፣ በመሪ ዕቅድ እንድትመራ ጥረት እየተደረገ ነው፤›› በማለት ክንውኑን የጠቀሱት ፓትርያርኩ፣ ‹‹ችግሩ ለዘመናት የተከማቸና በአጭር ጊዜ ለውጥ ለማምጣት ስለሚያዳግት በትዕግሥት መጠባበቁ መልካም ይኾናል፤›› ብለዋል፡፡ በበዓለ ሢመታቸው ቀን የአስተዳደር መዋቅር ማሻሻያን አስመልክቶ ተናግረዋቸው የነበሩ ቃላት ኹሉ ‹‹እንደጸኑ ናቸው፤ አልተበረዙም፤ አልተከለሱም፤ እንዲያውም ከሲኖዶስ አባላት፣ ከሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና ከምእመናን ጋር በመኾን አጠናክራቸዋለኹ›› ያሉት አቡነ ማትያስ፣ ለመልካም አስተዳደር መረጋገጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ባለድርሻ አካላት ኹሉ መነሣት እንደሚኖርባቸው ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፤ ‹‹ይህ ግዴታ ነው›› ሲሉም አክለዋል፡፡
የቤተ ክርስቲያኒቱ የአስተዳደር መዋቅር እንዲሁም አደረጃጀትና አሠራር ከመሠረታዊ ክህነታዊና የስብከተ ወንጌል ተልእኮዋ ጋራ እንዲጣጣም፣ ሙስናና ብልሹ አሠራር እንዲወገድ የተደረጉ የሙከራ ትግበራዎችና በመደረግ ላይ ያሉ ጥረቶች፣ ‹‹ይኹንታ ካገኙበት የቅ/ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ውሳኔ በተፃራሪ ዕንቅፋት ገጥሟቸዋል፤›› የሚሉ የቅርብ ታዛቢዎች በበኩላቸው÷ ፓትርያርኩ ሙስናን በየአጋጣሚው በመቃወምና ስለመልካም አስተዳደር ደጋግሞ በመናገር ራሳቸውን አስተዋውቀው እንደኾነ እንጂ ያመጡት ተስፋ ሰጭ ውጤት የለም፤ እንዲያውም በደሉና ጥፋቱ መልኩን ለውጡ እየረቀቀና እየተባባሰ መምጣቱን በምሬት ይናገራሉ፡፡
በቤተ ክርስቲያኒቱ አስተዳደር ውስጥ ሥር ሰዷል ያሉት ጎሰኝነት ከቀድሞም ጀምሮ ስማቸው ሲጠቀስ በቆዩና በተለይ በፓትርያርኩ ጽ/ቤት ዙሪያ በተሰባሰቡ ግለሰቦች ተጽዕኖ እየገዘፈ መምጣቱን ታዛቢዎቹ ከማስረዳታቸውም በላይ፣ ፓትርያርኩ ‹‹እንደ ጸና ነው›› የሚሉት አቋማቸው በላቀ አመራርና የውሳኔ ሰጭነት አቅም ተፈትኖና በተግባር ተገልጦ ማየት እንደሚሹ ለሰንደቅ ገልጸዋል፡፡

2014 ማርች 4, ማክሰኞ

ፓትርያርኩ ከአማሳኞችና ጎሰኞች ጋራ ተዋርደው ከመምከር እንዲታቀቡና በዐደባባይ ቃል የገቡበትን ተቋማዊ ለውጥ በተግባር እንዲያስፈጽሙ ሊቃነ ጳጳሳቱ አሳሰቧቸው

His Grace Abune Elsa on 32 SGGA
ብፁዕ አቡነ አልሳዕ
  • ‹‹ቅዱስነትዎ÷ ይህን ታላቅ ሓላፊነት ሲቀበሉ ቅ/ሲኖዶስ አዲስ ዋና ጸሐፊ፣ አዲስ ዋና ሥራ አስኪያጅ አድርጎ ሰጥዎታል፤ መምከር ያለብዎ ከእነርሱ ጋራ ነው፤ ከዚያም ካለፈ ከቋሚ ሲኖዶሱ ነው፤ አስፈላጊ ከኾነም ጠቅላላው ጉባኤው ይሰበሰባል፡፡ እርስዎ ግን ወርደው ከማን ጋራ ነው እየተማከሩ ያሉት?››
  • ‹‹በአገራችን ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት እና ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በመላው ኢትዮጵያ ሲያገለግሉ ከየት መጣኽ አልተባባሉም፤ ከሥራ ወንድምችዎ ጋራ ከየት መጣኽ ሳንባባል በአንድነት እየተመካከርን ነው ማገልገል ያለብን፤ ከዚያ ወርደን መገኘት የለብንም፡፡››
  • ‹‹የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት በመጀመሪያ ቅዱስ ወንጌል ከዚያ የሐዋርያት፣ የሊቃውንት እያሉ ነው የሚቀጥሉት፤ እርስዎም ከብፁዕ ዋና ጸሐፊ፣ ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ ከቋሚ ሲኖዶስ፣ ከምልዓተ ጉባኤ ጋራ ነው፡፡ ከዚያ ሲወርድ ግን ከሊቃውንት መጽሐፍም ወርዶ ልቦለድ መጽሐፍ እንደ ማንበብ ነው!!›› /ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ፣ የሰሜን ጎንደር ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ/
His Grace gen sec of the patriarchate Abune Mathewos speaking on the enthronment anniv.
ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ አቡነ ማቴዎስ
  • ‹‹እግዚአብሔር ለሚወደው ሕዝብ ነቢይ ኾኖ ትንቢት የሚነግራቸውን፣ አስተዳዳሪ ኾኖ የሚመራቸውን፣ ኖላዊ ኾኖ የሚጠብቃቸውን አባት ያዘጋጅላቸዋል፤ የዛሬው ቀን ይህን እግዚአብሔር የሚወደውን ሕዝብ ለቅዱስነትዎ ያስረከበበት ቀን ነው፡፡››
  • ‹‹የዛሬው ቀን ለቤተ ክርስቲያን ችግሯን ፈቺ፣ ለዕድገቷ ፕላን አውጪ፣ ለአስተዳደሯ መመሪያ ሰጪ ለመኾን በዐደባባይ ቃል የገቡበት ቀን ስለኾነ በታላቅ አክብሮትና ደስታ እናስታውሰዋለን፡፡ ራስን ለሌላው አሳልፎ መስጠት በቀላል አይመጣም፤ የልብ መሻትና መሠበርን ይፈልጋል፤ ማዕርግ ከነክብሩ፣ ሥልጣን ከነእውነቱ፣ መስቀል ከነትዕግሥቱ ካልተሰጠ አይቻልም፡፡ /ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ/
His Holiness giving benediction on the day of His enthronment
ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ
  • ‹‹የዛሬ ዓመት የተናርኋቸው ቃላት ኹሉ እንደጸኑ ናቸው፤ አልተበረዙም፤ አልተከለሱም፤ እንዲያውም ከቅ/ሲኖዶስ አባላት፣ ከሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና ከምእመናን ጋራ በመኾን አጠናክራቸዋለኹ፡፡››
  • ‹‹የቤተ ክርስቲያን ጥሪ በምድር ላይ ለመከራ መስቀል እንጂ ለተድላ ሥጋ አይደለም፤ ተድላውና ደስታው የተዘጋጀው በላይኛው ዓለም ነው፤ የቤተ ክርስቲያን መሪ፣ አገልጋይና ተከታይ የኾነ ኹሉ በውል መገንዘብ ያለበት ይህን ነው፤ የተጠራነው ለሰማያዊ ሀብትና ሹመት እንጂ እንደ ሣር ቅጠል ለጊዜው ታይቶ ለሚጠፋ ምድራዊ ሀብትና ሥልጣን አይደለም፡፡››
  • ‹‹የቤተ ክርስቲያናችን አሠራር እንዳይቃና እየተጠላለፉና እየተመሰቃቀሉ ብዙ እንዳንራመድ የሚያደርጉን ምክንያቶች ከማንም ይኹን ከየት ምንጫቸው ከፍቅረ ንዋይና ከፍቅረ ሢመት ውጭ ናቸው የሚል ግንዛቤ የለም፤ ለእነዚኽ ደግሞ ቁልፍ መፍትሔያቸው ራስን ክዶ መስቀልን ለመሸከም በቁርጥ ከመነሣት በቀር ሌላ ሊኾን አይችልም፡፡ እኛ የቤተ ክርስቲያናችን ተጠሪዎች ሥራችን ሊቃና፣ ተደማጭነታችን ሊሰፋ፣ ተልእኳችን ሊሠምር፣ ሕዝባችን ሊያምነንና ሊከተለን የሚችለው የጌታችንን ቃል አክብረንና ራሳችንን ክደን ለእውነት የቆምን እንደኾን ብቻ ነው፡፡››
  • ‹‹ባሳለፍነው የአንድ ዓመት ጉዞ ቅ/ሲኖዶስ ቤተ ክርስቲያናችን በዕቅድ እንድትመራ፣ የቤተ ክርስቲያን ሀብትና ንብረት እንዳይባክን በዘመናዊ አያያዝ እንዲያዝ፣ መልካም አስተዳደር፣ ፍትሕና ርትዕ፣ እኩልነት፣ ግልጽነትና ተጠያቂነት እንዲሰፍን ከመወሰን ባሻገር ይህን በሕግ ማህቀፍ፣ በደንብና በመመሪያ አጠናክራ ለመሥራት በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና በዕውቅ ምሁራን አማካይነት ልዩ ልዩ ጥናቶችን እያካሔደች ትገኛለች፡፡ ይህ የተጀመረው የአሠራር ለውጥ ተፈጽሞ ሲታይ ኹሉን እንደሚያስደስት ጥርጥር የለውም፤ ቤተ ክርስቲያናችን በሕግና በሥርዐት ስትመራ፣ የቤተ ክርስቲያናችን ኢኮኖሚ ጠንካራ ይኾናል፤ መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎታችንም ለሕዝበ ክርስቲያን በአግባቡ ተደራሽ ይኾናል፡፡ እነዚኽን ዐበይት ጉዳዮች ከሥራ ላይ ለማዋል የኹሉም ቀና መንፈስና ትብብር ያስፈልጋል፤ ራስን መካድ ያስፈልጋል፡፡›› /ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ/
*                                  *                                  *
  • ለአንደኛ ዓመት በዓለ ሢመት አከባበር በእንግሊዝኛ የወጣው የመርሐ ግብሩ ዝርዝር የታየበት የአጻጻፍ ውስንነትና የእውነታ ስሕተት በታዳሚዎች ተተቸ – ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስን “the 1st patriarch of the Ethiopia Orthodox Tewahido Church” ያደርጋቸዋል፤  ‹‹Message from the Acting patriarch of EOTC” የሚል መርሐ ግብርም አለው! የሰዓት አገላለጹማ….
  • የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታይ የኾኑት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ባለቤ ለቤተ ክርስቲያን በማይገባ አለባበስ (በአጭር ቀሚስ) የበዓለ ሢመቱ እንግዳ መኾናቸው ቅሬታ ፈጥሯል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ይከታተሉ፡

2014 ማርች 3, ሰኞ

የፓትርያርኩ የለውጥ ተግዳሮትና ተስፋ – በአንደኛ ዓመት በዓለ ሢመት ዋዜማ

Abune Mathias 1st anniv. enthronment
  • የብልሹ አሠራርና ሙስናን ችግር በዐደባባይ የተናገሩ የመጀመሪያው ፓትርያርክ ናቸው
  • ጽኑ አቋም ስለሚጎድላቸው ለጣልቃ ገብነት የተመቹ ኾነዋል
  • ጣልቃ ገብነቶችን መቋቋምና የቅ/ሲኖዶሱን ልዕልና ማስከበር ይጠበቅባቸዋል
  • የተጠጓቸውን ‹አማካሪዎች› ማንነት መለየትና ዙሪያቸውን መፈተሽ አለባቸው
  • የተሟላና ብቃት ያለው የአማካሪ መዋቅር ያስፈልጋቸዋል
(አዲስ አድማስ፤ ቅጽ ፲፫ ቁጥር ፯፻፴፯፤ የካቲት ፳፪ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም.)
Admas logoየካቲት 21 ቀን 2005 ዓ.ም.፤ ለስድስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ምርጫ ከቀረቡት አምስት ዕጩዎች መካከል በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ማትያስ በከፍተኛ ድምፅ መመረጣቸው ተነገረ፡፡ ሊቀ ጳጳሱ በቤተ ክርስቲያኒቱ የፓትርያርኮች ምርጫ ታሪክ ከፍተኛውን የመራጮች ድምፅ በማግኘት አሸናፊ መኾናቸው በተገለጸበት ወቅት የብዙዎችን ትኩረት በሳበ ኹኔታ በመስቀላቸው ሲያማትቡ ታዩ፡፡
የወቅቱን ስሜታቸውን አስመልክቶ ‹‹ዜና ቤተ ክርስቲያን›› በተሰኘው መጽሔት ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ÷ ‹‹ፓትርያርክ እኾናለሁ የሚል መንፈስ በውስጤ ስላልነበረ ውጤቱ ሲገለጽ፣ እንዴት ነው ይህ የእግዚአብሔር ሥራ ምንድን ነው ከሚል ደነገጥኹኝ፤ በዚያው ቅጽበት የተሰማኝ፣ እግዚአብሔር ይህን ታላቅ ሓላፊነት እንዴት እችለዋለሁ? በል አንተ ታውቃለህ፤›› የሚል እንደነበር አስረድተዋል፡፡
ከምርጫው ሦስት ቀናት በኋላ የካቲት 24 ቀን 2005 ዓ.ም. በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በተከናወነው ሥርዐተ ሢመት÷ ለፓትርያርክነት መመረጣቸው የቤተ ክርስቲያኒቱ ጥሪ እንደኾነና ጥሪውን የተቀበሉት መኾኑን፣ መቀበላቸውም ለክብርና ለልዕልና ሳይኾን ለመሥዋዕት በመታዘዝ በመኾኑ የቅዱስ ሲኖዶሱን አባላት በመያዝ በጋራ እንደሚወጡት ያላቸውን እምነት ተናግረው ነበር፡፡
ፓትርያርኩ በዚያ ንግግራቸው ‹‹ቅዱስ ሲኖዶሱ በራሱ መተማመን አለበት›› ሲሉ በአጽንዖት የተናገሩ ሲኾን እንደ አንድ ልብ አሳቢ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ኾኖ በሥምረት ከሠራ፣ ችግር ይኖራል ብለው እንደማያምኑ ገልጸዋል፡፡ በቅ/ሲኖዶሱ ሊሠሩ ይገባል በሚል ካሳወቋቸው ተግባራት መካከልም ቤተ ክርስቲያኒቱ ፍትሕ ርትዕ እኩልነት የሞላባት፣ መልካም አስተዳደር የሰፈነባት የእውነትና የሐቅ መገኛ እንድትኾን በመንፈሳዊነት፣ ታማኝነትና ተጠያቂነት የተደገፈ መጠነ ሰፊ የሥራ እንቅስቃሴ ማድረግን ይጨምራል፡፡ ‹‹እምነትና ሐቅ በቤተ ክርስቲያን ካልተገኙ ከየት ይገኛሉ?›› ሲሉ የጠየቁት ፓትርያርኩ፣ ካህናትና ቤተ ክርስቲያኒቱን በሞያቸውና በልግሥናቸው አቅፈው ደግፈው የያዙ ምእመናን የድርሻቸውን ለመወጣት ብርቱ ጥረት ማድረግ አለባቸው ማለታቸውም ይታወሳል፡፡
ከፕትርክና ሢመቱም በኋላ ለብዙኃን መገናኛዎች በሰጧቸው ቃለ ምልልሶች÷ ሰው ሊመሰገንም ሊሾምም፣ ሊሻርም፣ ሊወቀስም የሚገባው በጠባዩ፣ በግብረ ገብነቱ፣ በትምህርቱ ብቻ እየተመዘነ እንጂ በዘሩ አንወደውም አንጠላውም በማለት በቤተ ክርስቲያኒቱ አስተዳደር ውስጥ ሥር የሰደደ የመጠቃቀሚያ መንገድ ነው የሚባለውን በጎሰኝነት መሳሳብን ተቃውመዋል፡፡
ቤተ ክርስቲያኒቷ ታላቅ መኾኗንና ለታላቅነቷ የሚመጥኑ ሰዎች መገኘት እንዳለባቸው በአጽንዖት የተናገሩት ፓትርያርኩ፣ ‹‹የተሟላና የተቃና ሥራ ለመሥራት ከኹሉ አስቀድሞ ብቃትና ጥራት ያለው ሥራ መሥራት ያስፈልጋል፡፡ ለዚኽ ደግሞ ሰው በሰው ላይ መደራረብ ሳይኾን ትምህርትና ችሎታ ያለው፣ ለተመደበበት የሥራ ደረጃ የሚመጥን ሰው መቀመጥ አለበት፤›› ብለዋል፡፡
የቤተ ክህነቱ አስተዳደር ከላይ እስከ ታች ተስተካክሎ የመልካም ሥራ አብነት ይኾን ዘንድ ‹‹ሙስና ይጥፋ፤ ተጠያቂነትና ሐቀኝነት ይስፋፋ›› የሚለውን ዐዋጅ ደጋግመው በማሰማት እየታወቁ የመጡት ፓትርያርኩ፣ ቅ/ሲኖዶስ የቤተ ክርስቲያኒቱን ስም ለመጠበቅና ክብርዋን ለመመለስ ሊወስዳቸው ይገባል ያሏቸውን የለውጥ ርምጃዎች በመዘርዝር በምልዓተ ጉባኤው በአጀንዳነት አስይዘው ዐቢይ ውሳኔ ለማስወሰን አስችለዋል፡፡
ፓትርያርኩ ሥር ነቀል ለውጥን የሚያመጡና ቆራጥ አቋምን የሚሹ ናቸው ያሏቸው እኒህ ዐበይት ርምጃዎች÷ ብልሹ አሠራር በፀረ ሙስና እንቅስቃሴ የሚታረምበትና የሚወገድበት፣ የአስተዳደር መዋቅሩና የሚሠራባቸው ደንቦችና ሕጎች ግልጽነትና ተጠያቂነት እንዲኖራቸው ተደርገው የሚሻሻሉበት፣ የቤተ ክርስቲያኒቱ ራእይና ተልእኮ በግልጽ የሚታይበት ስትራተጅያዊ የአመራር ሥርዐት የሚነደፍበት፣ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት እስከ አጥቢያ ላለው የገንዘብ ፍሰትና አያያዝ አንድ ወጥ የኾነ ሥርዐት የሚዘረጋበት እንደኾነ አመልክተዋል፡፡
His Holiness Abune Mathias with thier Graces the Archbishops
ቅዱስነታቸው ከብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ጋራ
አቡነ ማትያስ፣ አሳፋሪና አሳዛኝ ነው ያሉት የአሠራር ብልሽት ሳይታረም ቢቀጥል ቤተ ክርስቲያኒቱ ለሚገጥማት አስከፊ ችግር ፓትርያርኩ ራሳቸውን ከተወቃሾች ተርታ በመቁጠር ቤተ ክርስቲያኒቱን የሚታደግና ችግሮቿን የሚቀርፍ አጀንዳ በመያዝ በእግዚአብሔር፣ በታሪክና በመጪው ትውልድ ፊት የሚመዘን ችግር ፈቺ ውሳኔ እንዲወሰን የቅ/ሲኖዶሱን አባላት አነሣስተዋል፡፡
ፓትርያርኩ ከሹመታቸው በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በርእሰ መንበርነት የመሩትና በግንቦት ወር 2005 ዓ.ም. በተካሔደው የቅ/ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በይፋ ባስታወቁት በዚኽ መግለጫቸው ላይ በመወያየት ቤተ ክርስቲያኒቱ ማኅበራዊና መንፈሳዊ ሥራዎቿን በመሪ ዕቅድ በመምራት ሙስናንና የመልካም አስተዳደር ዕጦትን ከሥሩ ለመቅረፍ የሚያስችል ጥናት የሚያቀርብ ከሊቃነ ጳጳሳት፣ ከሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ ከቤተ ክህነቱ የሥራ ሓላፊዎችና ከምሁራን ምእመናን የተውጣጣ ዐቢይ ኮሚቴ ተሠይሟል፡፡
ይኸው የቅ/ሲኖዶሱ የምልዓተ ጉባኤ ስብሰባ፣ የቤተ ክርስቲያኒቱ የአደረጃጀትና አሠራር ጥናት የሁሉም አህጉረ ስብከት ማእከልና የመንበረ ፓትርያርኩ መቀመጫ በኾነው በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት እንዲደረግ መመሪያ ሰጥቷል፤ ሀ/ስብከቱም በመዋቅርና አደረጃጀት፣ በሰው ሀብት አስተዳደር፣ በሒሳብ አሠራርና ቁጥጥር የሚታይበትን የገዘፈና የተመሰቃቀለ ችግሩን ለመፍታት የባለሞያ ቡድን አቋቁሞ በፍጥነት ወደ ተግባር መግባቱ ተዘግቧል፡፡
በመንበረ ፓትርያርክም በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ደረጃም የተቋቋሙት ሁለቱም አካላት የጥናት ውጤታቸውን በጥቅምት ወር 2006 ዓ.ም. ለተካሔደው የቅ/ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ አቅርበው በማስገምገም የወሳኝ አካሉን ይኹንታ ከማግኘታቸውም በላይ ቀጣይ የአፈጻጸም አቅጣጫ ተሰጥቷቸዋል፤ የመሪ ዕቅድ ማህቀፉን ያስገመገመው ዐቢይ ኮሚቴ በቀጣይ ዕቅዱን በሥራ ለመተርጎም በሚያስችል አኳኋን በዝርዝር አዘጋጅቶ እንዲያቀርብ መመሪያ ተሰጥቶታል፡፡
የአዲስ አበባ ሀ/ስብከትን የአደረጃጀትና የአሠራር ለውጥ ጥናት የሠራው የባለሞያ ቡድንም ጥናቱን ወደ ታች አውርዶ በካህናት፣ በምእመናንና በሰንበት ት/ቤት ወጣቶች በውይይት ካዳበረ በኋላ ለቋሚ ሲኖዶስ እንዲያቀርብና በቋሚ ሲኖዶሱ እንዲጸድቅ በምልዓተ ጉባኤው በተሰጠው የአፈጻጸም አቅጣጫ መሠረት ተግባሩን አከናውኖ በውይይቱ የብዙኃኑን ካህናትና ምእመናን ተቀባይነት ያረጋገጠውን የጥናት ሰነድ በሀ/ስብከቱ አማካይነት ለቅ/ሲኖዶሱ አስረክቧል፡፡
ከነገ በስቲያ ሰኞ፣ የካቲት 24 ቀን 2006 ዓ.ም. በሚከበረው አንደኛ ዓመት የበዓለ ሢመት ዋዜማቸው ላይ የሚገኙት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ፣ በቀጣዩ የሥራ ዘመናቸው የተናገሯቸውንና ተጠንቶ የቀረቡላቸውን በተግባር ለመተርጎም የሚንቀሳቀሱበት እንደሚኾን አዲስ አድማስ ያነጋገራቸው የቤተ ክርስቲያኒቱ ሓላፊዎች፣ አገልጋይ ካህናትና ምእመናን ተስፋቸውን ገልጸዋል፡፡
ቤተ ክህነቱ ያለበትን መሠረታዊ ተልእኮውን የማያገለግል የተንዛዛ ቢሮክራሲ፣ ወገንተኝነትና ሙስና በፓትርያርክ ደረጃ አምነውና ተቀብለው በዐደባባይ ገልጠው ለመናገር አቡነ ማትያስ የመጀመሪያው እንደኾኑ የተናገሩ አንድ አገልጋይ÷ የፓትርያርኩ ተደጋጋሚ መግለጫዎች በየአጥቢያቸው ችግሩን የሚጋፈጡ ወገኖችን በልዩ ልዩ መንገድ ለተቋማዊ ለውጥና ለፀረ ሙስና ትግል እንዳነሣሣ፣ ይህም ቢያንስ ብልሹ አሠራሩን ለሕገ ወጥ ጥቅም ያዋሉ አማሳኞችን እንዳሸማቀቀ ይገልጻሉ፡፡
ለዓመታት የተከማቸው የቤተ ክርስቲያኒቱ ዘርፈ ብዙ ችግር በአንድ ዓመት ተጠንቶ ሊታወቅ ይችል እንደኾነ እንጂ መፍትሔ ያገኛል ተብሎ እንደማይጠበቅ የጠቀሱት አገልጋዩ፣ አንድ ዓመት የፓትርያርኩን ስኬት ለመገምገም በቂ አይደለም ይላሉ፡፡ ፓትርያርኩ በጵጵስና ከተሾሙበት ጊዜ ጀምሮ ለሠላሳ ዓመታት በውጭ የነበሩ እንደመኾናቸው ቤተ ክህነቱን በበላይነት የመምራት ልምድ ሊያንሳቸው እንደሚችል ጠቁመው፣ ይህን ክፍተት የሚጠቀሙ ከቀድሞም የነበሩና ዛሬም ያልታጠፉ የጥፋት እጆችን ተጽዕኖ በፓትርያርኩ ዙሪያ እንደሚያስተውሉ ገልጸዋል፡፡ ለዚህም ፓትርያርኩ የሚያስጠጓቸውን አማካሪዎች ማንነት በጥንቃቄ መለየት እንደሚኖርባቸው አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
ስለ ፓትርያርኩ የአንድ ዓመት ጉዞ የተጠየቁትና ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ከፍተኛ የሥራ ሓላፊ፣ ፓትርያርኩ ከተሾሙበት ዕለት አንሥቶ ያስተጋቧቸውን የተቋማዊ ለውጥ ዕሴቶችና መርሖዎች ተግባራዊ ለማድረግ ዙሪያቸውን መፈተሽ አለባቸው የሚለውን አስተያየት የሚጋሩት ሓላፊው፣ ‹‹ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ያለው ኹኔታ ብቃት ያላቸውን እውነተኛ ባለሞያዎች ከፓትርያርኩ የሚያሸሽ እንጂ የሚያቀርብ አይደለም፤›› ይላሉ፡፡
የአስተዳደራዊ መዋቅር ማሻሻያ ሒደት የራሱ ተግዳሮቶች እንዳሉት የሚናገሩት የሥራ ሓላፊው፣ የአመራር ብቃትና ብስለት ተግዳሮቶቹን ለበጎ ለውጦ በመጠቀም እንደሚረጋገጥ ያስረዳሉ፡፡ ፓትርያርኩ ሥር ነቀልና ቆራጥ ተግባራዊ ርምጃ እወስዳለኹ ብለው በጀመሩት እንቅስቃሴ ተቃውሞ ሲገጥማቸው፣ ተቃውሞውን የማዳመጥ አባታዊ ሓላፊነት ቢኖርባቸውም ዋናውን የቅ/ሲኖዶሱን ውሳኔ ሳይቀር እስከማመቻመች መድረሳቸው የፀረ ሙስና አቋማቸው ራሳቸውን ከሚያስተዋውቅ የሚዲያ ፍጆታና ከንግግር ያላለፈ፣ የሚናገሩትንም ያህል ጠንካራና ጽኑ አቋም የሚይዙ ውሳኔ ሰጭ ናቸው ብለው እንዳያምኑ እንዳደረጋቸው አስረድተዋል፡፡ ይህም በውጤቱ የተቋማዊ ለውጥ ተቃዋሚዎቹን በማፈርጠምና የለውጥ ተስፋውን በማመንመን ሒደቱ ዳግመኛ እንዳይነሣ አድርጎ አደጋ ውስጥ ሊከተውና የቤተ ክርስቲያኒቱን ችግር የበለጠ ሊያወሳስበው እንደሚችል ስጋታቸውን ገልጸዋል፡፡
‹‹ለፓትርያርኩ የአቋም ጽናት የሊቃነ ጳጳሳቱ የአቋም አንድነት አስፈላጊ ነው፤›› የሚሉት ሌላው አስተያየት ሰጪ፣ አቡነ ማትያስ ከምንጊዜውም በላይ በቤተ ክህነቱ ላይ ተባብሶ የሚታየውን የተቋማዊ ለውጡን ሒደት የሚያደናቅፉ አላስፈላጊ ጣልቃ ገብነቶችን መቋቋምና የቅዱስ ሲኖዶሱን የውሳኔ ልዕልና ማስከበር እንደሚጠበቅባቸው ያሳስባሉ፡፡
ፓትርያርኩ በተመረጡበት ቀን ‹‹እግዚአብሔር ይህን ታላቅ ሓላፊነት እንዴት እችለዋለሁ? በል አንተ ታውቃለህ፤›› ማለታቸው በርግጥም የሚገባ ነው ያሉት እኚኹ አስተያየት ሰጪ፣ ታላቋንና ጥንታዊቷን ቤተ ክርስቲያን ርእሰ አበው ኾኖ ለመምራት የውስጥ ችግሩና የውጭ ተግዳሮቱ የበዛ ቢኾንም ቤተ ክርስቲያኒቱን ወደ ዕድገትና ስሉጥነት የሚያደርሰው ጎዳና በአቡነ ማትያስ ዘመነ ፕትርክና መጠረግና መደልደል ይገባዋል ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል፡፡

2014 ፌብሩዋሪ 25, ማክሰኞ

አብይ ጾም (አንደኛ ሳምንት) ዘወረደ

Monday, February 24, 20141comments

ተቀነዩ ለእግዚአብሔር በፍርሃት:

 ወተሐሠዩ ሎቱ በረዓድ

አጽንዋ ለጥበብ ከመ ኢይትመዐዕ እግዚአብሔር።

ትርጉም፦ ለእግዚአብሔር በፍርሃት ተገዙ፥ 
በረዓድም ደስ ይበላችሁ
ጥበብን አጽኑአት ፤ እግዚአብሔር እንዳይቆጣ። (መዝ.፪፡፲፩-፲፪)

ጾም ማለት ከእህል እና ከውሃ እንዲሁም ከስጋ ፈቃድ ጾሙ እስኪፈጸም ድረስ መተው ማለት ነው።  ጾም ማለት በጾም ወቅት ስጋ ነክ ምግቦችን ሆነ ወተትን፤ ቅቤን የመሳሰሉትን የምግብ እና የመጠጥ አይነቶችን መለወጥ ብቻ ሳይሆን የምንወደውን የሥጋ ፍላጎት ስለ እግዚአብሔር ብለን መተው ነው።።
 ራስን መግዛት በክርስቲያናዊ ሕይወት ውስጥ ትልቅ ዋጋ እንዳለው ሁሉ አንድ ሰው የሥጋ ፍላጎቱን ወይም የዓለም ምኞቱን ትቶ እግዚአብሔርን እያሰበ የሚጾም ከሆነ በፈጣሪው ዘንድ ጾሙ ተቀባይነት አለው።  ጾም ለ እግዚአብሔር ያለንን ታዛዥነት የምንገልጽበት የፍቅር መገለጫ ነው ስለዚህ ይህን አብይ ጾም ስንጾም፤ አይናችን ትፁም (ክፉ ከማየት)፤ ጆሮም ትፁም (ክፉ ከመስማት ወይም ሰውን ከማማት እንታቀብ)፤ አፋችን ትጹም (ከመሳደብ ሆነ ክፉ ከማውራት)፤ እጅም ትፁም( ከመስረቅ ሆነ ሰውን ከመደብደብ) ፤ አግርም ትፁም (ከሃጢአት ቦታዎች ከመሄድ ምሳሌ ከጭፈራ ወይም ዳንኪራ ቤቶች)፤ ሁላችንም በተሰበረ ልብ ሆነን እንፁም። አሁን ያለንበት ወቅት አብይ ጾም ይባላል።  አብይ ማለት ታላቅ ማለት ነው። ይህ ጾም ታላቅ ጾም ያሰኘበት ምክንያት ለ55 ቀናት መጾሙ እና ከሌሎች አጽዋማት ጋር ሲነጻጸር በቁጥር መብለጡ ብቻ ሳይሆን ፍጥረታትን የፈጠረ አምላክ፤ ስለ ሰው ልጅ ፍቅር ሲል ከዙፋኑ ወርዶ ከእመቤታችን ተወልዶ፤ መጾም ሳይገባው ለእኛ አርአያ ለመሆን ሲል በገዳመ ቆሮንጦስ የጾመው ጾም ነው። የመጀመሪያው የአብይ ጾም ሳምንት ዘወረደ ይባላል።  ይህም ዘወረደ ማለት የወረደ» ማለት ነው፡፡ ይህም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅዱስ ፈቃዱ ሰው ሆኖ ከሰማየ ሰማያት ከባሕርይ ልዕልናው በትሕትና ወርዶ ከቅድስት ድንግል ማርያም መወለዱን የሚያመላክት፣ ይህም የሚታወስበት፣ የሚወሳበት የዐቢይ ጾም አንደኛው ሳምንት ነው፡፡ ዮሐ.3-13፡፡

ቀዳማዊው አዳም  የፈጣሪውን የእግዚአብሔር የጾም ትእዛዝ በማፍረሱ ምክንያት ገነትን ከመሰለ ቦታ እግዚአብሔርን ከመሰለ ቅዱስ አምላክ ጌታ ጋር ተለያየ።  ስለዚህም በጾም  ምክንያት የፈጣሪውን ሕግ አፍርሶ የጠፋውን ቀዳማዊውን አዳም ለማዳንና ወደ ቀደመ ክብሩ ለመመለስ ሲል የሰውን ልጅ ለመፈለግ የመጣው ዳግማዊው አዳም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የመጀመሪያ ሥራውን የጀመረው በጾም ነበር (ማቴ 4፥1-11)።
ዳግማዊው አዳም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፤ ሐጢአት የሌለበት፤ ንጹሐ ባሕርይ የሆነ፣ ፍጥረታትን በቃሉ የፈጠረ፤ ሁሉ በእጁ የሆነ፤ ድንቅ መካር ሃያል አምላክ ሲሆን ምንም እንደሌለው ተራበ፤ ይህም ለእኛ ምሳሌ ይሆነን ዘንድ ነው። የነቢያት አምላክ ነውና፤ ኦሪትንና ነቢያትን ሊፈጽም እንደ ነቢያቱ 40 ቀንና 40 ሌሊት በገዳም አደረ፤ በዲያቢሎስ ተፈተነ፤ ይህም ለእኛ ምሳሌ ይሆነን ዘንድ ነው። ከነቢያት መካከል እንደ እነ ሙሴ ጽላቱን ከፈጣሪው ዘንድ ከመቀበሉ በፊት እንዲሁ 40 ቀንና 40 ሌሊት ጾሟል፤ ምንጊዜም ቅዱሳን አባቶቻችን አገልግሎታቸውን ከመጀመራቸው በፊት
ቅድሚያ ይጾሙ ነበር። ሐዋርያትም ቢሆን መንፈሳዊ አገልግሎት ከመጀመራቸው በፊት በጾም ነበር ፈጣሪያቸውን የሚጠይቁት፤ ፈጣሪያቸውም የለመኑትንና የሚሹትን ይሰጣቸዋል።   የዚህ አይነቱ መንፈሳዊ ተጋድሎ ሐዋርያት በአገልግሎታቸው የጸኑና የበረቱ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል። ስለዚህ እኛም ዛሬ ጌታችንን፤ ቅዱሳን ነቢያትን፤ እንዲሁም ቅዱሳን ሐዋርያትን ምሳሌ አድርገን ራሳችንን ለፈጣሪ ሰጥተን እንጹም። በዚህ በመጀመሪያ ሳምንት እያንዳንዱ ክርስቲያን ለጾም ምን ያህል መዘጋጀት እንዳለበት ያውቃል ይረዳልም ስለዚህ ቅዱሳን አባቶቻችን ለፈጣሪያቸው ታምነው ጾሙን ከምግባር ጋር እንደጾሙት ሁሉ እኛም ልክ እንደ አባቶቻችን ይህን ታላቅ ጾም  ከምግባር ጋር ለመፈጸም እርሱ ፈጣሪያችን ይርዳን።  ለመጾም ቅድሚያ ሁኔታ ምን እንደሆን ሁላችንም እናውቃለን ነገር ግን የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነውና፤ ሰዎች ከታላቅ አክብሮት ጋር ስርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ጠብቀው እና ሕገ እግዚአብሔርን ፈጽመው እንዲሁም ደግሞ የቀደመውን እባብ ሰይጣን ዲያብሎስን በጾም ረትተው ወደ ዘለዓለማዊ ሕይወት ለመሸጋገር የሚያስችለውን ጎዳና የሚያዘጋጁበት ጊዜ ነው።  ጾሙ የበረከት ይሁንልን አሜን።

በዚህ በመጀመርያው ሳምንት ከመዝሙረ ዳዊት ላይ የሚሰበከው ምስባክ፦

በግዕዝ፦

ተቀነዩ ለእግዚአብሔር በፍርሐት
ወተሐሰዩ ሎቱ በረአድ
አጽንዕዋ ለጥበብ ከመ ኢይትመአዕ እግዚአብሔር

በአማርኛ፦

ለእግዚአብሔር በፍርሃት ተገዙ፥
በረዓድም ደስ ይበላችሁ
ተግሣጹን ተቀበሉ ጌታ እንዳይቈጣ። (መዝ.፪፡፲፩-፲፪)

በዚህ በመጀመርያው ሳምንት የሚነበበው የወንጌል ክፍል፦

ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው። አንተ የእስራኤል መምህር ስትሆን
ይህን አታውቅምን? እውነት እውነት እልሃለሁ፥ የምናውቀውን እንናገራለን ያየነውንም
እንመሰክራለን፥ ምስክራችንንም አትቀበሉትም። ስለ ምድራዊ ነገር በነገርኋችሁ ጊዜ
ካላመናችሁ፥ ስለ ሰማያዊ ነገር ብነግራችሁ እንዴት ታምናላችሁ? ከሰማይም ከወረደ በቀር
ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም፥ እርሱም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው። ሙሴም
በምድረ በዳ እባብን እንደ ሰቀለ እንዲሁ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት
እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ የሰው ልጅ ይሰቀል ይገባዋል። በእርሱ የሚያምን ሁሉ
የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ
ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና። ዓለም በልጁ እንዲድን ነው እንጂ፥ በዓለም እንዲፈርድ
እግዚአብሔር ወደ ዓለም አልላከውምና። በእርሱ በሚያምን አይፈረድበትም፤ በማያምን ግን
በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታል። ብርሃንም ወደ ዓለም ስለ
መጣ ሰዎችም ሥራቸው ክፉ ነበርና ከብርሃን ይልቅ ጨለማን ስለ ወደዱ ፍርዱ ይህ ነው።
ክፉ የሚያደርግ ሁሉ ብርሃንን ይጠላልና፥ ሥራውም እንዳይገለጥ ወደ ብርሃን አይመጣም፤
እውነትን የሚያደርግ ግን ሥራው በእግዚአብሔር ተደርጎ እንደ ሆነ ይገለጥ ዘንድ ወደ
ብርሃን ይመጣል። ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ ይሁዳ አገር መጣ፥
በዚያም ከእነርሱ ጋር ተቀምጦ ያጠምቅ ነበር። ዮሐንስም ደግሞ በሳሌም አቅራቢያ በሄኖን
በዚያ ብዙ ውኃ ነበርና ያጠምቅ ነበር፥ እየመጡም ይጠመቁ ነበር ዮሐንስ ገና ወደ ወኅኒ
አልተጨመረም ነበርና። ስለዚህም በዮሐንስ ደቀ መዛሙርትና በአይሁድ መካከል ስለ ማንጻት
ክርክር ሆነ። ዮሐ.፫፡፲-፳፭

2014 ፌብሩዋሪ 20, ሐሙስ

ል ረገድ ከፍተኛ ተስፋ የተጣለባቸውና በቋሚ ሲኖዶሱ ላይ ርክክብ የተካሔደባቸው የመዋቅር የአደረጃጀት የአሠራር ጥናት ሰነዶች ብዛት ዐሥራ ሦስት ሲኾን ከአንድ ሺሕ ገጽ ያላነሰ ጠቅላላ ብዛት ያላቸው እንደኾኑ ከቋሚ ሲኖዶሱ ርክክብ አንድ ቀን አስቀድሞ በሀ/ስብከቱ ጽ/ቤት በተካሔደ መርሐ ግብር ላይ ተገልጧል፡፡ His Grace Abune Estifanos with the 12 documentsየጥናት ሰነዶቹም የአደረጃጀትና የመዋቅር ጥናትና መመሪያ፣ የአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ደረጃ መስፈርት ጥናትና መመሪያ፣ የአገልግሎት መደቦች የሥራ ዝርዝር ሰነድ፣ የተፈላጊ ችሎታ መመሪያና የሰው ኃይል ትመና ሰነድ፣ የደመወዝ ስኬል ጥናት ሰነድ፣ የአገልጋዮች ማስተዳደርያ፣ የፋይናንስ፣ የልማት ሥራዎች፣ የግዥ፣ ሽያጭና ንብረት አስተዳደር፣ የዕቅድ ዝግጅት፣ ሪፖርትና ግምገማ፣ የኦዲትና ኢንስፔክሽን ፖሊሲዎችና ዝርዝር የአፈጻጸም መመሪያዎች እንዲኹም የሥልጠና ማእከልና የአረጋውያንና የሕፃናት መርጃ ማእከል ፕሮጀክት ጥናት ሰነድ እንደኾኑ ተዝርዝሯል፡፡ የጥቅምት ቅ/ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ለጥናቱ በሰጠው ይኹንታና በሰጠው አቅጣጫ መሠረት የጥናት ሰነዱ ለርክክብ ከመቅረቡ አስቀድሞ÷ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የመምሪያና ድርጅት ሓላፊዎችን ጨምሮ የሀገረ ስብከቱ የዋና ክፍል ሓላፊዎች፣ የክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጆች፣ የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪዎች፣ የሀገረ ስብከቱ ማኅበረ ካህናት፣ ማኅበረ ምእመናንና የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች እንደተወያዩበት ተገልጦአል፡፡ በውይይት የተነሡት ሐሳቦች በአግባቡ ተመዝግበውና ተገምግመው በእያንዳንዱ የመዋቅርና የአሠራር መመሪያ ውስጥ እንዲካተቱ መደረጉን የባለሞያ ቡድኑ ሰብሳቢ አቶ ታደሰ አሰፋ ያስረዱ ሲኾን ለ14 ቀናት በጥናቱ ላይ በተካሔደው ውይይት 96 በመቶ ተቀባይነት እንዳገኘ ማረጋገጣቸውን ተናግረዋል፡፡ ‹‹ጥናቱን እንድናደርግ የተሰጠን ዕድል ታሪካዊ ነው፤›› ያሉት አቶ ታደሰ፣ ችግር ፈቺ እንደኾነ ለሚያምኑበት የጥናት ሰነድ ዝግጅት መሳካት አስተዋፅኦ አድርገዋል ያሏቸውን ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ የሀገረ ስብከቱን ሓላፊዎችና አገልጋዮች እንዲኹም የለውጥ እንቅስቃሴውን ያስጀመሩትንና ከጅምሩ እስከ ፍጻሜው በኹሉ ነገር አልተለዩም ያሏቸውን ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስን አመስግነዋል፤ የቤተ ክርስቲያኒቱ የበላይ አካል የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ እንደወሰነውም በካህናት፣ ምእመናንና የሰንበት ት/ቤቶች ወጣቶች አስተያየት ዳብሮ የቀረበው የጥናት ሰነዱ በቋሚ ሲኖዶሱ ጸድቆ ወደ ተግባር ይገባ ዘንድ አደራ ብለዋል፡፡ በተያያዘ ዜና፣ በትውፊታዊውና ጥንታዊው የቤተ ክርስቲያኒቱ የትምህርት ማእከላት በኾኑት አብያተ ጉባኤያት ወንበር ተክለው የሚያስተምሩ የአብነት መምህራን ዋነኛ የጤና ችግር ከዐይን እክል ጋር የተያያዘ መኾኑን ሰንደቅ የደረሰው መረጃ ጠቁሟል፡፡ An Accomplished Scholars of the Ethiopain Orthodox Tewahido Church Traditional Schools አባ ሰረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል የውስጥና የውጭ ተባባሪዎቻቸውን አሰልፈው በፓትርያርኩ ደብዳቤ ያሳገዱት የሦስተኛው ዙር ሀገር አቀፍ የአብነት መምህራን ጉባኤ ተሳታፊ የምስክር ሊቃውንት በማኅበረ ቅዱሳን የዋናው ማእከል ጽ/ቤት በራፍ ማኅበረ ቅዱሳን ለሦስተኛ ጊዜ ባዘጋጀውና በፓትርያርኩ ደብዳቤ እንደታገደ በተገለጸው የአብነት መምህራን ሀገር አቀፍ ጉባኤ ላይ ለመገኘት ከኹሉም አህጉረ ስብከት ተውጣጥተው ወደ አዲስ አበባ ከመጡት 202 የምስክር መምህራን መካከል ለ170ዎቹ ተሳታፊዎች የጤና ምርመራ መደረጉን መረጃው ያመለክታል፡፡ W.ro Alemtsehay Meseret, Deputy Board Chair of Kidusat Mekanat Limat ena Mahiberawi Agelgilot ወ/ሮ ዓለም ፀሐይ መሠረት የማኅበረ ቅዱሳን ቅዱሳት መካናት ልማትና ማኅበራዊ አገልግሎት ዋና ክፍል ምክትል የቦርድ ሰብሳቢ የንዋያተ ቅድሳት ምርት ከቤተ ክርስቲያናችን የገቢ ማስገኛ ዘዴዎች በአማራጭነት ሊካተት ይችላል፡፡ ንዋያተ ቅድሳት በቅድስት ቤተ ክርስቲያን በቅዳሴና በልዩ ልዩ መንፈሳዊ አገልግሎቶች የምትጠቀምባቸውን ግብአቶች ያጠቃልላል፡፡ እነዚህ ግብዓቶች ቤተ ክርስቲያን ካላት መንፈሳዊ አገልግሎት÷ ቅዳሴ፣ ክርስትና፣ ተክሊልና ፍትሐት ስፋት እንዲኹም የምእመናኑና የአብያተ ክርስቲያኑ ብዛት ከግምት ስናስገባው ከፍተኛ ምርትንና ሽያጭን ይጠይቃል፡፡ ምርቱና ሽያጩ ለቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች የገቢ ምንጭ ለመፍጠር ብቻ ሳይኾን የአመራረቱን ትውፊትና ሥርዐት ለመጠበቅ፣ ከከተማ ውጭ ያሉትን ገዳማትና አድባራት የንዋያተ ቅድሳት እጥረት ለመቀነስ በከፍተኛ ኹኔታ ያግዛል፡፡ ለዚኽ ገለጻ ተብሎ በተሰበሰበው መረጃ መሠረት፣ በአኹኑ ሰዓት ንዋያተ ቅድሳት በገበያ ላይ ለሽያጭ የሚቀርቡት 95% ከቤተ ክርስቲያን ጋራ ምንም ግንኙነት በሌላቸው ለትርፍ በተቋቋሙ ወይም በሚሠሩ የግል አቅራቢዎች ወይም አምራቾች ነው፡፡ ለምሳሌ ያህል፡- 95 በመቶ የጧፍ ምርት በአብዛኛው ከመርካቶ የግል አቅራቢዎች የሚቀርብ ነው፡፡ ምእመናን በአነስተኛ ግምት በዓመት ወደ 93 ሚልዮን ብር ለጧፍ ግዥ ያወጣሉ፡፡ ከ93 ሚልዮን ብር ሽያጭ 20 ሚልዮን ብር ትርፍ ይገኛል ተብሎ ሊሰላ ይችላል፡፡ ይህ ትውፊቱን ጠብቆ በቤተ ክርስቲያን ካህናት ተመርቶ ቢኾን ኖሮ የካህናቱም ገቢ በዚኹ መጠን ያድግ ነበር፡፡ የጧፍ ምርት፡- የሰው ኃይል፣ የፈትል ክር፣ ሰም ወይም ዋክስ በአካባቢ በሚሠራ ቴክኖሎጂ በመጠነኛ ዋጋ የሚዘጋጅ ነገር ግን ኹሌም ገበያ ያለው ምርት ነው፡፡ የተለየም ሞያ የማይጠይቅ ሥራ ነው፡፡ በመቶ ሺሕ የሚቆጠሩ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ካህናት፣ የካህናት ሚስቶች በቀላሉ ሥልጠና ቢሰጣቸው ኑሯቸውን ሊያሻሽሉ ይችላሉ፡፡ ጧፍ በቤተ ክርስቲያን ካለመመረቱ የተነሣ በአኹኑ ሰዓት አምራቾች የሚጠቀሙበት የሰም ዋጋ ውድ ከመኾኑ ጋራ ተያይዞ ትውፊቱን ለመጠበቅ የሚያስችል ምክንያት ስለሌላቸው በአብዛኛው ሻማና ሞራ እንዲኹም ልዩ ልዩ ኬሚካሎች በመጠቀም ጣፉን በማምረት ላይ ናቸው፡፡ ይህም ከጧፉ ጢስ ጋራ በተያያዘ ካህናትን ለጤና ችግር እየዳረጋቸው ይገኛል፡፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ማኅበረ ቅዱሳን የልማት ተቋማት የጧፍ ማምረቻ ማሽን ፈብርኮ በየዓመቱም 250‚000 ጧፍ ከሰም ያመርታል፡፡ ምርቱን ለማምረት ለሚፈልጉ አብያተ ክርስቲያናት የማሽን ሥራና ሥልጠና ይሰጣል፡፡ /የምጣኔ ሀብትና የሕዝብ ጤና አጠባበቅ ባለሞያዋ ወ/ሮ ዓለም ፀሐይ በ፴፪ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ዓመታዊ ስብሰባ ላይ ‹‹በቤተ ክርስቲያን ልዩ ልዩ አነስተኛ የገቢ ማስገኛ ዘዴዎችን ተግባራዊ ስለማድረግ›› በሚል ርእስ ካቀረቡት ጥናታዊ ጽሑፍ የተወሰደ/

2014 ፌብሩዋሪ 18, ማክሰኞ

ተጠቃሚው ማነው?

ማኅበረ ቅዱሳን ለሦስተኛ ጊዜ ያዘጋጀው የአብነት መምህራን ጉባኤ መታገዱን መግለጫዎችና ዜናዎች እያሳወቁን ነው፡፡ የአብነት መምህራን በቤተ ክህነቱ ‹ለአበል የተረሱ፣ ለሹመት የሚታወሱ› ሆነዋል፡፡ ስብሰባ፣ ዐውደ ጥናት፣ ሥልጠና፣ ጉዞ፣ ሲሆን እነርሱን የሚያስታውስ የለም፡፡ የጵጵስና ሹመት ሲመጣ ግን ‹ከእገሌ ይህንን ከእገሌም ያንን ተማርኩ› የሚለው ይበዛል፡፡ የቤተ ክርስቲያኒቱም ሆነ የሀገሪቱ ሀገራዊ ዕውቀት ማዕከል መሆናቸው ተረስቶ ይህንን ያህል ዘመን ሲኖሩ ‹ቤት ልሥራላቸው፣ ዘር ልዝራላቸው› ያለ ቤተ ክህነት አልገጠመንም፡፡ እንዲያውም እነ መምሬ በዕውቀቱን እነ አያ ብሩ እየቀደሟቸው ቦታ ቦታውን ይዘውታል፡፡
ማኅበረ ቅዱሳን ለውጥ አምጭ ሥራ ከሠራባቸው ዘርፎች አንዱ የአብነት ትምህርት ቤቶች መሆናቸውን እስላም ከክርስቲያኑ የሚመሰክረው ነው፡፡ ለአብነት መምህራን ደመወዝ ከመክፈል ቤት እስከ መሥራት፣ ትምህርት ቤቶቻቸውን ከመገንባት ለተማሪዎቹ ቁሳቁስ እስከ ማቅረብ፣ የጤና መርሐ ግብሮችን ከማከናወን እስከ ካሪኩለም ቀረጻ ሰፊ ሥራዎች ተሠርተዋል፡፡
ለአንድ ሊቅ ከቁሳዊ ነገር በላይ መንፈሳዊ ነገሩ ይበልጥበታል፡፡ ጽድቁ፣ ክብሩ፣ ስሙ፣ መዓርጉ፣ ታሪኩ ታላቅ ነገሮች ናቸው፡፡ ከቁሳዊው ድጋፍም ሞራላዊው ድጋፍ ታላቅ ነው፡፡ እነዚህ የአብነት መምህራን ቦታና ዐቅም ወስኗቸው፣ እድሜና አሠራር ገድቧቸው እንዳይቀሩ፤ እርስ በርስ ተገናኝተው እንዲመክሩ፤ አሠራራቸውን እንዲያዘምኑ፣ ዕውቀት እንዲከፋፈሉ፣ ልምድ እንዲለዋወጡ፣ ህልውናቸውን እንዲተዋወቁ፣ ወጥ አሠራር እንዲዘረጉ መደረጉ የሚያስመርቅ እንጂ የሚያስረግም አልነበረም፡፡

በርግጥ ይህንን መሰል ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸውን ሥራዎች ለመሥራት ተገቢ የሆኑ ቢሮክራሲያዊ መንገዶችን አሟጦ መጓዝ፤ ማወቅ ያለበት እንዲያውቅ፣ መስማት ያለበትም እንዲሰማ ማደረግ፣ ማሳመንና ማግባባት፣ በአሠራሩና በዓላማው ላይ ቀደም ብሎ ከሚመለከታቸው ጋር መወያየት ያስፈልጋል፡፡ አንድን ታላቅ መኪና የአንዲት ብሎን መላላትና መውለቅ እንደምታስቆመው ሁሉ የጥቂት ቤተ ክህነታዊ አሠራሮች አለመጠበቅ ታላቁን ዓላማ ሊያደናቅፈው እንደሚችል ማወቅ ተገቢ ነው፡፡ ትናንት እንዲህ ስለሠራን ነው ማለቱ ብዙም አያዋጣም፡፡ ሁልጊዜ ፋሲካ የለምና፡፡
በዚያም ሆነ በዚህ ግን የአብነት መምህራኑ መሰባሰብና በሞያቸውና አገልግሎታቸው ዙሪያ መምከር የሚጠቅመው ማንን እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ሲሆን ቤተ ክህነቱ ራሱ አስቦ መሥራት ነበረበት፤ ካልሆነም ደግሞ የሚሠሩትን ማትጋትና ማገዝ ይገባው ነበር፡፡ ሁለቱም ግን አልሆኑም፡፡ ማኅበሩ በቤተ ክህነቱ አሠራር ያላከናወናቸው ነገሮች አሉ ከተባለ እንዲያከናውን ማድረግ እንጂ አገር አቋርጠው ወንበር አጥፈው የመጡትን ሊቃውንት ማንገላታት የሚገባ አልነበረም፡፡ ጉባኤው ተስተካክሎ በመካሄዱ የምትጠቀመው ቤተ ክርስቲያን ናት ባለ መደረጉ ግን ከሰይጣን በቀር ተጠቃሚው ማነው
በሌላ በኩልም ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና የፓትርያርኩ ጽ/ቤት በጉዳዩ አፈታት ላይ የሄዱበት መንገድም አስገራሚ፣ አስተዛዛቢም ነው፡፡ የማኅበሩ ጽ/ቤት ከቤተ ክህነቱ በ50 ሜትር ርቀት ላይ መኖሩ እየታወቀ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁም ሆኑ ፓትርያርኩ ያንን ሁሉ የደብዳቤ ውርጅብኝ ማዝነብ ለምን አስፈለጋቸው? ደግሞስ ጉዳዩ የውስጥ ጉዳይ ነው፤ ለእነዚያ ሁሉ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የመጻፉ ዓላማው ምንድን ነው? አስፈላጊ ከሆነ ልጆቹን ጠርቶ ‹ጉባኤውን አቁሙ› ማለት ይቻል የለም እንዴ? ደግሞስ መጀመሪያውኑ ሳያጣሩ መጻፍ፣ ከዚያ ደግሞ የመሻሪያ ደብዳቤ መጻፍ፣ አከታትሎ ደግሞ የመሻሪያ መሻሪያ መጻፍ የቤተ ክህነቱን ተቋማዊ ኪሣራ ከማሳየት በቀር ሌላ ምን ያሳያል?
የዛሬን አያድርገውና የፓትርያርክ ደብዳቤኮ የእምነት መግለጫ፣ የሚጠቀስ፣ በክብር የሚቀመጥ፣ በሃይማኖተ አበው መጽሐፍ ላይ የሚሠፍር ነበር፡፡ እንዲህ ጊዜ በሰጠ ቁጥር መዥለጥ እየተደረገ የሚጻፍ አልነበረም፡፡ ደግሞስ አንድ አባት ልጆቹን ጠርቶ መምከር እየቻለ ‹‹ልጆቼ እንዲህ ያሉ ናቸው›› ብሎ ለዓለም መንገር ከየት ያመጣነው ሥርዓት ነው? ዓለም ችግሯን ለቤተ ክርስቲያን ታቀርባለች እንጂ ቤተ ክርስቲያን ችግሯን እንዴት ለዓለም አቤት ትላለች?
የሊቃውንቱ መሰባሰብና መወያየት ለቤተ ክርስቲያኒቱ የወንጌል ሥምሪት ወሳኝ ነው፡፡ እንዲያውም ከሲኖዶሱ ጉባኤ በፊት ሊደረግ የሚገባው ነገር ቢኖር የሊቃውንቱ ጉባኤ ነበር፡፡ በቤተ ክርስቲያኒቱ የትምህርተ ሃይማኖት፣ የሥርዓትና የትውፊት ጉዳዮች ላይ መክረው የውሳኔ ሃሳቦችን ማቅረብ የነበረባቸው ሊቃውንቱ ናቸው፡፡ ይህ ባለመሆኑም ይመስላል የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ አጀንዳዎች ሃይማኖታዊ ከመሆን ይልቅ አስተዳደራዊና ቢሮክራሲያዊ የሆኑት፡፡ ስንትና ስንት የምእመናን ጥያቄዎች እያሉ የሹመትና የበጀት ጥያቄዎች ዋነኛ መነጋገሪያዎች የሚሆኑት፡፡
የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንኮ የራስዋን ጳጳሳት እንድትሾም የተሟገቱት ከመላዋ ሀገሪቱ የተሰባሰቡ ሊቃውንት ነበሩ፡፡ ምነው መሠረቱ ተዘነጋ፡፡
አሁንም ሊቃውንቱን ተዋቸው፣ ቤተ ክርስቲያን እንደነርሱ ላሉት ናትና፡፡ በጉባኤያቸው ተገኝቶ መወያየት፣ የጉባኤውን አጀንዳ አብሮ መቅረጽ፣ ጉባኤውን መምራት፣ አሠራሩን ማሳየት ይገባል፣ የአባትም ነው፡፡ የገዛ ሊቃውንቶቻችንን ግን አትሰብሰቡ፣ አትመካከሩ፣ አትወያዩ፣ ችግር አትፍቱ ብሎ ማገድ፣ እምቢ ካላችሁ ‹ለመንግሥት እነግርባችኋለሁ›› ብሎ መንግሥትን ማስፈራሪያ ማድረግ ሃይማኖታዊ አይደለም፡፡ ምነው በጎንደሩ የጥምቀት ኤግዚቢሽ የመንግሥት አካላት ሊቃውንቱን ሲያከብሩ ባየን፤ ይህቺ ቤተ ክርስቲያንኮ ያለ ኢትዮጵያውያን ጳጳሳት ኖራ ታውቃለች፣ ያለ ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ግን የኖረችበት ዘመን የለም፣ አይኖርምም፡፡
አሁንም እጠይቃለሁ፤ የሊቃውንቱን ጉባኤ ማገድ ጥቅሙ ለማን ነው? ባሏን ጎዳሁ ብላ..... እንደተባለው ካልሆነ በቀር፡፡ ሊቃውንቱንም አስተምረው ለወግ ለመዓርግ ባበቋቸው ልጆቻቸው ሲታገዱ ማየት የስምንተኛውን ሺ መግባት ከማሳየት በቀር ሌላ ምን ያሳያል፡፡

                                   በአውሮጳ   የካህናት አንድነት ማኅበር ሊቋቋም መሆኑ ታወቀ በ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከመላዋ አውሮጳ   የተውጣጡ ካህናት፡” የ...