ማክሰኞ 19 ኖቬምበር 2013

                               

                                                           ከዲያቆን  ምትኩ አበራ


አንድ አላማ በሦስቱ መቅደሶች

November 20, 2013 at 2:35am
አጉራ ዘለል በመባል የሚታወቁትና ከጠቅላይ ቤተ ክህነታችን የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ ይሁንታ ውጪ ራሳቸውን ያሰማሩት  ህገ ወጥ "ሰባኪያን" በባሌ ሀገረ ስበከት ቅንጣት  ታህል ቦታ የላቸውም፡፡ ይህ ሊሆን የቻለው ደግሞ በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መምሪያው እያደረገ ያለው ጥብቅ ቁጥጥርና ክትትል እንዳለ ሆኖ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ ያለምንም ጣልቃ ገብነት ለሀገረ ስብከቱ የስብከተ ወንጌል ክፍል ኃላፊ በሰጡት ሙሉ ሥልጣንና ኃላፊነት መሠረት በሚደረገው እልህ አስጨራሽ ትንቅንቅ ነው፡፡ይህ ብቻ እንኳን በራሱ ህገ ወጦችን መከላከል ሲገባቸው ጭራሽኑ ያለ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ፈቃድ በማን አለብኝነት እየጋበዙ ሀገረ ስብከታቸውን የአጉራ ዘለል ሰባክያን መፈንጫ ለሚያደርጉ አንዳንድ የሀገረ ስብከት ጳጳሳትና ሥራ አስኪያጆች በቂ ማስተማርያ ነው፡፡
ውድ አንባቢያን የጽሑፌ መነሻ ማኅበሬ ማኅበረ ቅዱሳን ተጠይቆና በቁጥር 740/141/2006 በቀን 3/3/2006ዓ.ም. ተጽፎ በስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ ሓላፊ መልአከ ብርሐን ፍስሐ ጌታነህ ፊርማ ወጪ በሆነ ደብዳቤ ታዝዤ ለስብከተ ወንጌል አገልግሎት በባሌ ሀገረ ስብከት በጊኒር ወረዳ መገኘቴ ነበር፡፡ አብረውኝ በጠቅላይ ቤተ ክህነት የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ የሳንሱር ክፍል ኃላፊና የጉባኤው አስተባባሪና የልዑካኑ መሪ የሆኑት መምህር ናዖድ ኢያሱ፣ ዘማሪ ገብረ አምላክ ዘማሪና የዜማ መሣሪያ ባለሙያ የሆነው በኃይሉና ዘማሪት ቡርቱካን ነበሩ፡፡
ጉባዔው የሦስት ቀን ጉባዔ ሲሆን ከህዳር 6-8/2006ዓ.ም.የቆየ ነበር፡፡ ዓርብ ለሚጀምረው ጉባዔ ከአዲስ አበባ የተነሳነው ሐሙስ ሌሊት ነበር ምክንያቱ ደግሞ ጊኒር በአንድ ቀን ጉዞ ስለማይደረስ ነበር፡፡ ከአዲስ አበባ ባሌ ሮቤ 445ኪ.ሜ. ተጉዘን እዛው ሮቤ ካደርን በኋላ መንገዱ  ፒስታ በመሆኑ ብቻ 135ቱን ኪ.ሜትር 5 ሰዓት ተጉዘን ነበር ከሮቤ ጊኒር      የገባነው፡፡ በጊኒር ያየነው ነገር አስደንቆናል ሁሉም ነገር ሦስት ሲሆን ግን አንድ ነው፡፡ እዚያ ሦስት መቅደስ አለ ሰንበት ትምህርት ቤቱ ግን አንድ ነው፣በዋናነት ሦስት ማህበራት አሉ(ሰ/ት/ቤት፣ማኅበረ ቅዱሳን፣ስብከተ ወንጌሉን ለመደገፍ በአጥቢያው የተሰባሰቡ ወጣቶች) አላማቸውና አገልግሎታቸው ግን አንድ ነው፣ምን አለፋችሁ ቦታው ፍቅር የነገሠበት፣የጠቅላይ ቤተ ክህነታችን መዋቅር የሚከበርበት፣ ሀገረ ስብከቱ ከወረዳው፣ ወረዳው ከአጥቢያው፣አጥቢያው ከሰንበት ትምህርት ቤቱ፣ ሰንበት ትምህርት ቤቱ ከማኅበረ ቅዱሳን……..ወዘተ ተናበውና ተገናዝበው፣ተረዳድተውና ተዋደው የሚሠሩበት የሰላምና  የበረከት ቦታ ነው፡፡
 የዚህ ሁሉ አንድነት ምክንያቶች የሆኑት ሦስቱ መቅደሦች የሚገኙት በአንድ ቅጽር ነው፡፡ ቅጽሩ የሚገኘው ደግሞ ልከ እንደ ጊሸን ተራራ ባለው ጉብታ ነው፡፡ የእመቤታችን ቅድስት ማርያምና የሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ አብያተ ክርስቲያናት በመጠኑ ተራርቀው፤ሲገኙ የመድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ደግሞ በርቀት ታንጿል፡፡ እነዚህ ሁሉ ታዲያ ለምዕመኑ አንድ አጥቢያ  ሲሆኑ የሚተዳደሩት በአንድ ሰበካ ጉባዔ ሲሆን የሚገለገሉትም በአንድ ሰንበት ትምህርት ቤት ነው፡፡
የተሰጠው አገልግሎት ሦስት ዐይነት ነበር (ለምዕመናን በዓውደ ምሕረት ላይ፣ለስብከተ ወንጌል ማጠናከሪያ የበኩላቸውን ለማድረግ ለተሰባሰቡት ወጣቶች በማረፊያ ቦታችን፣ በማኅበረ ቅዱሳን የጊኒር ወረዳ ማዕከል አባላት በጽሕፈት ቤታቸው) ይሁን እንጂ አላማው ግን አንድ ነበር፡፡ ለማገልገል ወደ ቦታው የተጓዝነው ልዑካን የተውጣጣነው ከሦስት ቦታ  ነበር (ቅጠቅላይ ቤተ ክህነት፣ከማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማዕከል፣በግላቸው የሚያገለግሉ ዘማርያን ይሁን እንጂ አገልግሎቱ ግን በህብረት ነበር፡፡ መርሐ ግብሩን ሲያሳልጡ የነበሩ ባለ ድርሻ አካላት ሦስት ነበሩ(ስሙ እንዳይጠቀስ የተማጸነ የልዑካኑን ሙሉ ወጪ የቻለ አንድ ምዕመን፣እራሱ ፊት አውራሪ በመሆን ልዑካኑን ሲመራና ሲያስተባብር የነበረው የጠቅላይ ቤተ ክህነት ስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያና የባሌ ሀገረ ስብከት ከላይ እስከ ታች ባሉት መዋቅሮቹ)እነዚህ ሦስት አካላት ግን እንደ አንድ ልብ አስበው እንደ አንድ ቃል ተናግረዋል፡፡
በአጠቃላይ ይህ ታሪካዊና ታላቅ የሆነ የሦስት ቀን ጉባዔ፤ የጊኒር ከተማ ምዕመናን ነቅለው የወጡበት፣የማኅበረ ቅዱሳንና የጠቅላይ ቤተ ክህነትችን ጥምረት የታየበት፣ለስብከተ ወንጌሉ አገልግሎት ቀናዒያን የሆኑ ገንዘባቸውንና ጉልበታቸውን የማይሰስቱ ደጋግ ምዕመናን እናዳሉን ያየንበት፣መምሪያው አጉራ ዘለል ሰባክያንን ለማስታገስና ምዕመናንን ለመጠበቅ ያለውን ቁርጠኝነት ያሳየበት የተሣካ ጉባዔ ነበር ማለት ይቻላል፡፡
ውድ አንባቢዎቼ የተለመደ የፎቶ ግብዣዬን እነሆ፡፡ ታዲያ አንባችሁና አይታችሁ ስትጨርሱ የተሰማችሁን ሁሉ ብትጽፉልኝ ደስ ይለኛል፡፡
የልዑካኑ መሪ መ/ር ናዖድ ኢያሱ
የልዑካኑ መሪ መ/ር ናዖድ ኢያሱ
ሰበካ ጉባዔው ለሥራ እንጂ ለቢሮ አይጨነቅም
ሰበካ ጉባዔው ለሥራ እንጂ ለቢሮ አይጨነቅም
ትጉሃኑ የሰንበት ተማሪዎች ሊዘምሩ መጥተው ዘምረው አይሰወሩም ይማራሉ እንጂ
ትጉሃኑ የሰንበት ተማሪዎች ሊዘምሩ መጥተው ዘምረው አይሰወሩም ይማራሉ እንጂ
በመሰራት ላይ ያለው የቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን
በመሰራት ላይ ያለው የቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን
በመሠራት ላይ ላለችው ቅ/ማርያም ቤተ ክርስቲያን ስዕል እየሳለ የሚገኘው ሰዓሊ ሙሴ ከነ ስዕሉ
በመሠራት ላይ ላለችው ቅ/ማርያም ቤተ ክርስቲያን ስዕል እየሳለ የሚገኘው ሰዓሊ ሙሴ ከነ ስዕሉ
መ/ር ሰለሞን የወረዳው ሊቀ ካህን
መ/ር ሰለሞን የወረዳው ሊቀ ካህን
ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን
ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን
ሰዓሊው ከሚስላቸው ስእሎች አንዷ
ሰዓሊው ከሚስላቸው ስእሎች አንዷ
ዘማሪ ገብረ አምላክ
ወንጌል ናፋቂው ጊኒር ምዕመን
ወንጌል ናፋቂው ጊኒር ምዕመን
ወንጌል ናፋቂው ጊኒር ምዕመን
ወንጌል ናፋቂው ጊኒር ምዕመን
ወንጌል ናፋቂው ጊኒር ምዕመን
ወንጌል ናፋቂው ጊኒር ምዕመን
ወንጌል ናፋቂው ጊኒር ምዕመን
ወንጌል ናፋቂው ጊኒር ምዕመን
ወንጌል ናፋቂው ጊኒር ምዕመን
ወንጌል ናፋቂው ጊኒር ምዕመን
ትጉሃን ታዳሚዎች
ትጉሃን ታዳሚዎች
ልዑካኑ በከፊል የምንመገብባት ቦታ
ልዑካኑ በከፊል የምንመገብባት ቦታ
ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን
ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን
የጊኒር ከተማ በከፊል
የጊኒር ከተማ በከፊል
ልዑካኑ በከፊል
ልዑካኑ በከፊል
መ/ር ወጋየሁ የሀ/ስብከቱ ስ/ወ/ክ/ሓላፊ
ከተራራው ቁልቁል
ከተራራው ቁልቁል
የጊኒር ከተማ በከፊል
የጊኒር ከተማ በከፊል
ትጉሃኑ የሰንበት ተማሪዎች ሊዘምሩ መጥተው ዘምረው አይሰወሩም ይማራሉ እንጂ
ትጉሃኑ የሰንበት ተማሪዎች ሊዘምሩ መጥተው ዘምረው አይሰወሩም ይማራሉ እንጂ

                                                                                                                                                                                                                                                       

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

                                   በአውሮጳ   የካህናት አንድነት ማኅበር ሊቋቋም መሆኑ ታወቀ በ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከመላዋ አውሮጳ   የተውጣጡ ካህናት፡” የ...