የካህናት ሥልጠና ለቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ
ለውጥ ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው ተገለጠ
ምስካበ ቅዱሳን አቡነ ኪሮስ ቤተ ክርስቲያን
ካህናቱ በሥልጠና ላይ |
በሰሜን ሸዋ ሰላሌ ሀገረ ስብከት በሚገኘው በለገጣፎ ምስካበ ቅዱሳን አቡነ
ኪሮስ ቤተ ክርስቲያን የሚገኙ ካህናትና ዲያቆናት ለሁለት ቀናት የቆየ
ሥልጠና ተከታለዋል ፡፡ሥልጠናው መንፈሳዊ አገልግሎትና ትምህርተ ኖሎት ሲሆን የካህናት አገልግሎት መንፈሳዊ ከመሆኑ የተነሳ ሕዝበ ክርስቲያኑን በመንፈሳዊ ሕይወታቸው ከፍተኛ ለውጥ ማምጣት ይችሉ ዘንድ ስልጠናው አስፈላጊ መሆኑን ተጠቁሟል ፡፡ በተለይ ካህናት ከንስሓ ልጆቻቸው ጋር ያለው ግንኙነት እንዴትና በምን መልኩ መሆን እንዳለበትና ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት
መስጠት ይችሉ ዘንድ ትምህርተ ኖሎት መሰልጠን አስፈላጊ መሆኑ ተገልጦአል
ሥለጠናው የተዘጋጀው በደብሩ ስብከተ ወንጌል አስተባባሪነት ሲሆን ሰበካ ጉባኤውም ይሁንታውን መለገሱ ታውቆአል ፡፡ በሥልጠና
ላይ የተሳተፉት ካህናትና ዲያቆናት መምህራንም ሥልጠናው ወደፊትም ቢቀጥል ጥሩ ነው ካሉ በኋላ ሥልጠናው ከደብሩ አስተዳደር /ከላይ
መጀመር እንዳለበት አበክረው ጠቁመዋል የቤተ ክርስቲያን ትልቁ ችግር ከላይ በከፍተኛ አስተዳደር ላይ የተቀመጡ የደብሩም አስተዳደር ስልጠና እንደሚያስፈልገው በአጽንኦት ተናግረዋል አያይዘውም የደብሩን
ስብከተ ወንጌልን እናመሰግናለን ብለዋል ፡፡የደብሩ ስብከተ ወንጌል ወደፊትም ከካህናቱ ጋር በመሆን የንስሓ ልጆቻቸውን ለማስተማር ሁኔታዎችን እያመቻቸ መሆኑም ተገልጦአል ፡፡ ደብሩ እጅግ በጣም
ሰፊ መሬት ያለው ሲሆን ጠንካራ አስተዳደር ህዝብንና ካህናትን ያማከለ ዘመኑን የዋጀ አስተዳደር እንደሚያስፈልግም በተደጋጋሚ ተጠቁሞአል ዘመኑ ዝም ተብሎ የሚተኛበት ዘመን አይደለም ያሉት ካህናቱ ተደጋጋሚ ሥልጠናዎች
ያስፈልጉናል ብለዋል ፡፡ ጻድቁ አቡነ ኪሮስ ልጅ የሌላቸውን ልጅ ያገኙ ዘንድ የሚያስችል ቃልኪዳን የተሰጣቸው መሆኑ የሚታወቅ በመሆናቸው
ብዙ ምእመናን እየተሳሉ /ገድላቸውን በመሸከም በአዓመቱ ልጅ ተሸክመው እቦታው ድረስ ይሄዳሉ በዚህ ምክንያት በጣም ብዙ ሕዝብ የሚጎበኘው ታላቅ ቦታ በመሆኑ የተቀላጠፈ
ጠንካራ አስተዳደር የሰለጠኑ ካህናት ስለሚያስፈልግ ስልጠናው መዘጋጀቱን
የደብሩ ስብከተ ወንጌል ክፍሉ ገልጦአል ወደፊትም ተጠናክሮም ይቀጥላልም ተብሎአል::
የደብሩ ሰባክያነ ወንጌል ሊቀ ጠበብት ገረመው እና መምህር ቀለመወርቅ
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ