ማክሰኞ 21 ኤፕሪል 2015

ታላቁ ሊቅ ሊቀ ጉባዔ ቀለመወርቅ ገብረ ዮሐንስ አረፉ



ሊቀ ጉባዔ ቀለመወርቅ   በ1927 ዓ.ም ነሐሴ 5 ቀን  በቀድሞው ጎንደር ከ/ሀገር  እስቴ ወረደ  ከአባተቸው  ገብረ ዮሐንስና ከእናታቸው ወ/ሮ ጠጅቱ  ተወለዱ ፡፡ዕድሜያቸው ለትምህርት እንደደረሱ በአካባቢያቸው  ከሚገኙ መምህራን  ዳዊት ፤ ውዳሴማርያም  አጠቃላይ ንባብ በሚገባ ተምረዋል ፡፡ በመቀጠልም ወደ ደብረ ታቦር ሄደው ዲቁናን  ከብፁዕ አቡነ ሚካኤል ዘግሸን ተቀብለዋል ፡፡ ወደጎጃም በመጓዝ  ቅኔን ከነ አገባቡ በሚገባ ተምረዋል  በ1946 ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ ሄደው  ጽርሐ አርያም ቅ. ሩፋኤል  ተመድበው አገልግለዋል  ፡፡በ1951 ዓ.ም መጋቤ ብሉይ ቶማስ ደብረ ጽጌ ቅ/ ማርያም ተመድበው ሲሄዱ አብረው በመሄድ  በዚሁ ገዳም እንደገና ቅኔ ፤ መጻሕፍተ ብሉያት ፤ባሕረ ሓሳብ  ከየኔታ አምሳሉ ክብረ በዓል የተማሩ ሲሆን የኔታ አምሳሉ ሲልቁ ከየኔታ ቀለመወርቅ አቋቋም፣ ክበረ በዓል እና መዝሙር በሚገባ ተምረዋል ፡፡ ከ1956 ዓ.ም ከሰዋስወ ብርሃን ቅ/ ጳውሎስ ማሰልጠኛ በመጡ በአባ ገ/ሚካኤልና በመምህር ገ/ወልድ(የአሁኑ አቡነ ኤርምያስ) የስብከት ዘዴ እና የመሳሰሉትን ስልጠናዎች ሰልጥነዋል(በቦታው)፤ አያይዘውም በ1978 ዓ.ም ወደ ዘዋይ ገዳም ገብተው ለ3 ወራት ያህል የስብከት ዘዴ እና የመሳሰሉትን ተጨማሪ ሥልጠናን ወስደዋል ::  
 ፡ በ1959 ዓ.ም ወደ ደብረ ጽጌ ገዳም ተመልሰው  በሊቀ  ጉባዔነት ፤ በንባብ መምህርነት ፡ የገዳሟ አስጎብኚ በመሆን ሃይማኖተ አበውን በማስነበብ ፤ በሰባኬ ወንጌልነት፤ አገልግለዋል ፡፡ በተለይ የጻድቁ አቡነ ሀብተማርያምን ገድል            ለ28  ዓመታት/ ለ4 ሱባኤያት) በመተርጎም  የጻድቁን ታሪክ ለህዝቡ በማስተዋወቅ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ናቸው፡፡ በአጠቃላይ በደብረ ጽጌ ገዳም ብቻ ለ56 ዓመታት ያህል ቤተ ክርስቲያንን አገልግለዋል  ሊቀ ጉባዔ  ቀለመወርቅ ፤ቅን ፤ሰው ወዳጅ፤ ዘመኑን የዋጁ ሰባኬ ወንጌል የማንኛውን ጥያቄ መላሽና  የሚጠቀሱ መጽሐፍ ነበሩ፡፡ ባደረባቸው ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዱ ቆይተው ሚያዝያ 11  ቀን በ80 ዓመታቸው  አርፈው  ሥርዓተ ቀብራቸው  በተለያየ ቦታ የሚገኙ ሊቃውንት  ልጆቻቸው  ወዳጅ ዘመዶቻቸው  በተገኙበት  ሚያዝያ 12  /2007 ዓ.ም  በደብረ ሊባኖስ ገዳም  ተፈጽሟል ፡፡ሊቀ ጉባዔ ባለትዳርና  የሦስት ወንዶችና  ሦስት ሴቶች ልጆች አባት ናቸው ፡፡ የአባታችንን ነፍስ  ከቅዱሳን ዕቅፍ ያኑርልን፡፡

1 አስተያየት:

  1. በቅድሚያ መምህር ለማ በእግዚአብሔር ስም እያመሰገንን የታዩትን ጥቃቅን ስህተቶች ልናርም እንወዳለን ታሪክ ነውና፡፡
    ………፡በ1951 ዓ.ም መጋቤ ብሉይ ቶማስ ደብረ ጽጌ ቅ/ ማርያም ተመድበው ሲሄዱ አብረው በመሄድ በዚሁ ገዳም እንደገና ቅኔ ፤ መጻሕፍተ ብሉያት ፤ባሕረ ሓሳብ ከየኔታ አምሳሉ ክብረ በዓል የተማሩ ሲሆን የኔታ አምሳሉ ሲልቁ ከየኔታ ቀለመወርቅ አቋቋም፣ ክበረ በዓል እና መዝሙር በሚገባ ተምረዋል ፡፡ ከ1956 ዓ.ም ከሰዋስወ ብርሃን ቅ/ ጳውሎስ ማሰልጠኛ በመጡ በአባ ገ/ሚካኤልና በመምህር ገ/ወልድ(የአሁኑ አቡነ ኤርምያስ) የስብከት ዘዴ እና የመሳሰሉትን ስልጠናዎች ሰልጥነዋል(በቦታው)፤ አያይዘውም በ1978 ዓ.ም ወደ ዘዋይ ገዳም ገብተው ለ3 ወራት ያህል የስብከት ዘዴ እና የመሳሰሉትን ተጨማሪ ሥልጠናን ወስደዋል ፡፡ ከ1959 ዓ.ም ጀምሮ በደብረ ጽጌ ገዳም ውስጥ በሊቀ ጉባዔነት ፤ በንባብ መምህርነት ፡ የገዳሟ አስጎብኚ በመሆን ሃይማኖተ አበውን በማስነበብ ፤ በሰባኬ ወንጌልነት፤ አገልግለዋል ፡፡ በተለይ የጻድቁ አቡነ ሀብተማርያምን ገድል ለ28(ለ4 ሱባኤያት) ዓመታት በመተርጎም የጻድቁን ታሪክ ለህዝቡ በማስተዋወቅ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ናቸው፡፡ በአጠቃላይ በደብረ ጽጌ ገዳም ብቻ ለ56 ዓመታት ያህል ቤተ ክርስቲያንን አገልግለዋል ሊቀ ጉባዔ ቀለመወርቅ ፤ቅን ፤ሰው ወዳጅ፤ ዘመኑን የዋጁ ሰባኬ ወንጌል የማንኛውን ጥያቄ መላሽና የሚጠቀሱ መጽሐፍ ነበሩ፡፡ ባደረባቸው ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዱ ቆይተው ሚያዝያ 11 ቀን በ80 ዓመታቸው አርፈው ሥርዓተ ቀብራቸው በተለያየ ቦታ የሚገኙ ሊቃውንት ልጆቻቸው ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት ሚያዝያ 12 /2007 ዓ.ም በደብረ ሊባኖስ ገዳም ተፈጽሟል ፡፡ ሊቀ ጉባዔ ቀለመወርቅ ባለትዳርና የሦስት ወንዶችና ሦስት ሴቶች ልጆች አባት ናቸው ፡፡ የአባታችንን ነፍስ ከቅዱሳን ዕቅፍ ያኑርልን፡፡

    ምላሽ ይስጡሰርዝ

                                   በአውሮጳ   የካህናት አንድነት ማኅበር ሊቋቋም መሆኑ ታወቀ በ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከመላዋ አውሮጳ   የተውጣጡ ካህናት፡” የ...