ደብረ ሊባኖስ ገዳም ሲነሳ አብረው የሚታወሱ ለረጅም ዘመናት
ድጓ በማስተማር በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንን የፈሩ በምናኔያቸው ፤በማስተማር ብቃታቸው፡ በመኅሌት ቁመት ድካም
የማያውቃቸው አለቃ መርዓዊ ዛሬ ግንቦት 7 /2007 ዓ.ም ማረፋችው ተሰማ፡፤ ይህ ዜና እንደተሰማ በተለይ በ አዲስ አበባ አድባራትና
ገዳማት በማገልገል ላዪ የሚገኙ ሊቃውንት ልጆቻቸው ዛሬ ከሰዓት በኋላ ወደ ደብረ ሊባኖስ ገዳም ኢየተመሙ ይገኛሉ፡፡አለቃ መርዓዊ
ከገዳሙ ህልውና ቀጥሎ በስስት ዓይን የሚታዩ ትሁት ፤መናኝ፤ ፤ ማኅሌታዊ፤ መምህር ነበሩ ፡፡
ማሳሰቢያ
ይህን አሳዛኘ ዜና የሰማሁት ለአገልግሎት ኮቦልቻ እንደደረስኩ ነውና ሙሉ ዝርዝር መረጃዎችን አጠናክረን እናደርሳለን፡፡
የሊቁ አባታችንን ነፍስ ከቅዱሳን ሊቃውንት አጠገብ ያኑርልን፡፡
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ