2013 ኖቬምበር 28, ሐሙስ

                                                      በጅማ ከተማ ሀገረ ስብከቱ እያስገነባ ያለው ሁለገቡ ሕንጻ
                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                    

ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ስለዕቅድ አፈጻጸሙ ግምገማ በማድረግ ላይ
                                                        






            የጅማ ሀገረ ስብከት የሦስት ወራት ዕቅድ                                                                                      
         አፈ ጻጸም ተገመገመ

በአዲስአበባሀገረስብከትየብፁዕወቅዱስፓትርያርክረዳትናየጅማዞንሀገረስብከትሊቀጳጳስብፁዕአቡነእስጢፋኖስበ14/3/2006 ዓ.ምበጅማሀገረስብከትበተደረገውአጠቃላይስብሰባየሦስትወራትዕቅድአፈጻጸምግምገማአድርገዋል ፡፡ የስብሰባውዋናዋናአጀንዳዎችሐምሌ  20እና21/2005 ዓ.ምበጎማወረዳአጋሮከተማበተደረገውየሀገረስብከቱጠቅላላጉባኤላይከታቀደውዕቅድመካከልበትናንትናውስብሰባላይየተነሳውበስብከተወንጌልእንቅስቃሴእናበጅማከተማሀገረስብከቱየሚያስገነባውንሁለገብሕንጻበተመለከተውይይትተደርገውባቸዋልበዚሁመሠረትየወረዳዎችናየጅማከተማአድባራትናገዳማትአፈጻጻምየተሻለመሆኑንየተገለጠሲሆንዝቅተኛውጤትላስመዘገቡትደግሞየማጠናከሪያተግሳፅደርሶአቸዋልበተለይበሕዝበክርስቲያኑከፍተኛርብርብእየተሰራእየተፈጸመየሚገኘውይህሕንጻ G+5 ሲሆንከትንሣኤበኋላይመረቃልተብሎይገመታልተብሎአልለዚሁማስፈጸሚ 4.500000/አራትሚሊዮንአምስትመቶሺህ ብር እስከመጋቢት ድረስለመሰብሰብመታቀዱንምተገልጦአልበከተማውየሚገኙማኅበረቅድሳንንጨምሮየሚገኙማኅበራትምከፍተኛርብርብእንዲያደርጉሊቀጳጳሱጥሪአቅርበዋልይህሁለገብሕንጻአገልግሎትየሚሰጠውበሀገረስብከቱየተዘጉትንአድባራትንማስከፈትናቀጠይልማትንምለማስቀጠልየሚችልመሆኑየታወቀሲሆንእስከአሁንእስከአራተኛፎቅድረስበመጠናቀቁእየተከራየይገኛል፡፡ <ዘመኑየውድድርነውመፍጠንይገባል>ያሉትሊቀጳጳሱበቀጣዩበከተማውመካከልበደጆችሽአይዘጉመንፈሳዊማህበርአማካይነትሊሰራየታቀደው G+4 ባለአራትፎቅሁለገብሕንጻበቀጣዩይጀመራልብለዋልይህሕንጻ ለ65 አድባራትናገዳማትመርጃይሆንዘንድመታሰቡንምጨምረውገልጠዋል፡፡ሁለገብሕንጻውንበተመለከተየውስጥዖዲተርእስከታሕሳስ 30 እንዲጠናቀቅመመሪያየሰጡሲሆንበመቀጠልምየውጪዖዲተርይመለከተዋልብለዋልሀገረስብከቱበልማትከተፋጠነስብከተወንግልበገጠሪቱሁሉይስፋፋልያሉትሊቀጳጳሱህገወጥሰባክያንናዘማርያንንበተመለከተበስብሰባውላይጥብቅመመሪያሰጥተዋልየሰባክያንንናዘማርያንንፎቶመለጠፍከቤተክርስትያናችንሥርዓትውጪነውያሉትሊቀጳጳሱይህንንበሚያደርጉአካላትላይእርምጃእንወስዳለንብለዋል፡፡
በተያያዘዜናጥር 18/ 2006 ዓ.ምብፁዕወቅዱስአቡነማትያስፓትርያርክዘኢትዮጵያበጅማሀገረስብከትውስጥየሚገኙትንየአበልቲ ቅ/ኪዳነምሕረትገዳምየአብነት ት/ቤትናበናትሪ ቅ/ገብርኤልቤተክርስቲያንለሚገነባውየካህናትናደቀመዛሙርትማሰልጠኛየመሠረትድንጋይለማስቀመጥእንደሚሄዱየተገለጠሲሆንለዚሁምከወዲሁዝግጅትእየተደረገመሆኑንታውቆአልበስብሰባውምላይየአድባራትናገዳማትአስተዳዳሪዎች ፤ሰበካጉባኤአባላት ፤ ካህናት፤ የማኅበራትተወካዮች፤ ሰባክያነወንጌልሌሎችምተገኝተዋል፡፡ሊቀጳጳሱከስብሰባውበኋላበሻሻአቡነገብረመንፈስቅዱስቤተክርስቲያንድረስበመሔድሕዝበክርስቲያኑንጎብኝተውናአጽናንተውተመልሰዋል፡፡በሻሻአቡነ ገ/መንፈስቅዱስቤተክርስቲያን በ1999 ዓ.ምካህናትናምእመናንየተሰየፉበትቦታመሆኑይታወሳል፡፡
                                                   

2013 ኖቬምበር 19, ማክሰኞ

                               

                                                           ከዲያቆን  ምትኩ አበራ


አንድ አላማ በሦስቱ መቅደሶች

November 20, 2013 at 2:35am
አጉራ ዘለል በመባል የሚታወቁትና ከጠቅላይ ቤተ ክህነታችን የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ ይሁንታ ውጪ ራሳቸውን ያሰማሩት  ህገ ወጥ "ሰባኪያን" በባሌ ሀገረ ስበከት ቅንጣት  ታህል ቦታ የላቸውም፡፡ ይህ ሊሆን የቻለው ደግሞ በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መምሪያው እያደረገ ያለው ጥብቅ ቁጥጥርና ክትትል እንዳለ ሆኖ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ ያለምንም ጣልቃ ገብነት ለሀገረ ስብከቱ የስብከተ ወንጌል ክፍል ኃላፊ በሰጡት ሙሉ ሥልጣንና ኃላፊነት መሠረት በሚደረገው እልህ አስጨራሽ ትንቅንቅ ነው፡፡ይህ ብቻ እንኳን በራሱ ህገ ወጦችን መከላከል ሲገባቸው ጭራሽኑ ያለ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ፈቃድ በማን አለብኝነት እየጋበዙ ሀገረ ስብከታቸውን የአጉራ ዘለል ሰባክያን መፈንጫ ለሚያደርጉ አንዳንድ የሀገረ ስብከት ጳጳሳትና ሥራ አስኪያጆች በቂ ማስተማርያ ነው፡፡
ውድ አንባቢያን የጽሑፌ መነሻ ማኅበሬ ማኅበረ ቅዱሳን ተጠይቆና በቁጥር 740/141/2006 በቀን 3/3/2006ዓ.ም. ተጽፎ በስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ ሓላፊ መልአከ ብርሐን ፍስሐ ጌታነህ ፊርማ ወጪ በሆነ ደብዳቤ ታዝዤ ለስብከተ ወንጌል አገልግሎት በባሌ ሀገረ ስብከት በጊኒር ወረዳ መገኘቴ ነበር፡፡ አብረውኝ በጠቅላይ ቤተ ክህነት የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ የሳንሱር ክፍል ኃላፊና የጉባኤው አስተባባሪና የልዑካኑ መሪ የሆኑት መምህር ናዖድ ኢያሱ፣ ዘማሪ ገብረ አምላክ ዘማሪና የዜማ መሣሪያ ባለሙያ የሆነው በኃይሉና ዘማሪት ቡርቱካን ነበሩ፡፡
ጉባዔው የሦስት ቀን ጉባዔ ሲሆን ከህዳር 6-8/2006ዓ.ም.የቆየ ነበር፡፡ ዓርብ ለሚጀምረው ጉባዔ ከአዲስ አበባ የተነሳነው ሐሙስ ሌሊት ነበር ምክንያቱ ደግሞ ጊኒር በአንድ ቀን ጉዞ ስለማይደረስ ነበር፡፡ ከአዲስ አበባ ባሌ ሮቤ 445ኪ.ሜ. ተጉዘን እዛው ሮቤ ካደርን በኋላ መንገዱ  ፒስታ በመሆኑ ብቻ 135ቱን ኪ.ሜትር 5 ሰዓት ተጉዘን ነበር ከሮቤ ጊኒር      የገባነው፡፡ በጊኒር ያየነው ነገር አስደንቆናል ሁሉም ነገር ሦስት ሲሆን ግን አንድ ነው፡፡ እዚያ ሦስት መቅደስ አለ ሰንበት ትምህርት ቤቱ ግን አንድ ነው፣በዋናነት ሦስት ማህበራት አሉ(ሰ/ት/ቤት፣ማኅበረ ቅዱሳን፣ስብከተ ወንጌሉን ለመደገፍ በአጥቢያው የተሰባሰቡ ወጣቶች) አላማቸውና አገልግሎታቸው ግን አንድ ነው፣ምን አለፋችሁ ቦታው ፍቅር የነገሠበት፣የጠቅላይ ቤተ ክህነታችን መዋቅር የሚከበርበት፣ ሀገረ ስብከቱ ከወረዳው፣ ወረዳው ከአጥቢያው፣አጥቢያው ከሰንበት ትምህርት ቤቱ፣ ሰንበት ትምህርት ቤቱ ከማኅበረ ቅዱሳን……..ወዘተ ተናበውና ተገናዝበው፣ተረዳድተውና ተዋደው የሚሠሩበት የሰላምና  የበረከት ቦታ ነው፡፡
 የዚህ ሁሉ አንድነት ምክንያቶች የሆኑት ሦስቱ መቅደሦች የሚገኙት በአንድ ቅጽር ነው፡፡ ቅጽሩ የሚገኘው ደግሞ ልከ እንደ ጊሸን ተራራ ባለው ጉብታ ነው፡፡ የእመቤታችን ቅድስት ማርያምና የሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ አብያተ ክርስቲያናት በመጠኑ ተራርቀው፤ሲገኙ የመድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ደግሞ በርቀት ታንጿል፡፡ እነዚህ ሁሉ ታዲያ ለምዕመኑ አንድ አጥቢያ  ሲሆኑ የሚተዳደሩት በአንድ ሰበካ ጉባዔ ሲሆን የሚገለገሉትም በአንድ ሰንበት ትምህርት ቤት ነው፡፡
የተሰጠው አገልግሎት ሦስት ዐይነት ነበር (ለምዕመናን በዓውደ ምሕረት ላይ፣ለስብከተ ወንጌል ማጠናከሪያ የበኩላቸውን ለማድረግ ለተሰባሰቡት ወጣቶች በማረፊያ ቦታችን፣ በማኅበረ ቅዱሳን የጊኒር ወረዳ ማዕከል አባላት በጽሕፈት ቤታቸው) ይሁን እንጂ አላማው ግን አንድ ነበር፡፡ ለማገልገል ወደ ቦታው የተጓዝነው ልዑካን የተውጣጣነው ከሦስት ቦታ  ነበር (ቅጠቅላይ ቤተ ክህነት፣ከማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማዕከል፣በግላቸው የሚያገለግሉ ዘማርያን ይሁን እንጂ አገልግሎቱ ግን በህብረት ነበር፡፡ መርሐ ግብሩን ሲያሳልጡ የነበሩ ባለ ድርሻ አካላት ሦስት ነበሩ(ስሙ እንዳይጠቀስ የተማጸነ የልዑካኑን ሙሉ ወጪ የቻለ አንድ ምዕመን፣እራሱ ፊት አውራሪ በመሆን ልዑካኑን ሲመራና ሲያስተባብር የነበረው የጠቅላይ ቤተ ክህነት ስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያና የባሌ ሀገረ ስብከት ከላይ እስከ ታች ባሉት መዋቅሮቹ)እነዚህ ሦስት አካላት ግን እንደ አንድ ልብ አስበው እንደ አንድ ቃል ተናግረዋል፡፡
በአጠቃላይ ይህ ታሪካዊና ታላቅ የሆነ የሦስት ቀን ጉባዔ፤ የጊኒር ከተማ ምዕመናን ነቅለው የወጡበት፣የማኅበረ ቅዱሳንና የጠቅላይ ቤተ ክህነትችን ጥምረት የታየበት፣ለስብከተ ወንጌሉ አገልግሎት ቀናዒያን የሆኑ ገንዘባቸውንና ጉልበታቸውን የማይሰስቱ ደጋግ ምዕመናን እናዳሉን ያየንበት፣መምሪያው አጉራ ዘለል ሰባክያንን ለማስታገስና ምዕመናንን ለመጠበቅ ያለውን ቁርጠኝነት ያሳየበት የተሣካ ጉባዔ ነበር ማለት ይቻላል፡፡
ውድ አንባቢዎቼ የተለመደ የፎቶ ግብዣዬን እነሆ፡፡ ታዲያ አንባችሁና አይታችሁ ስትጨርሱ የተሰማችሁን ሁሉ ብትጽፉልኝ ደስ ይለኛል፡፡
የልዑካኑ መሪ መ/ር ናዖድ ኢያሱ
የልዑካኑ መሪ መ/ር ናዖድ ኢያሱ
ሰበካ ጉባዔው ለሥራ እንጂ ለቢሮ አይጨነቅም
ሰበካ ጉባዔው ለሥራ እንጂ ለቢሮ አይጨነቅም
ትጉሃኑ የሰንበት ተማሪዎች ሊዘምሩ መጥተው ዘምረው አይሰወሩም ይማራሉ እንጂ
ትጉሃኑ የሰንበት ተማሪዎች ሊዘምሩ መጥተው ዘምረው አይሰወሩም ይማራሉ እንጂ
በመሰራት ላይ ያለው የቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን
በመሰራት ላይ ያለው የቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን
በመሠራት ላይ ላለችው ቅ/ማርያም ቤተ ክርስቲያን ስዕል እየሳለ የሚገኘው ሰዓሊ ሙሴ ከነ ስዕሉ
በመሠራት ላይ ላለችው ቅ/ማርያም ቤተ ክርስቲያን ስዕል እየሳለ የሚገኘው ሰዓሊ ሙሴ ከነ ስዕሉ
መ/ር ሰለሞን የወረዳው ሊቀ ካህን
መ/ር ሰለሞን የወረዳው ሊቀ ካህን
ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን
ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን
ሰዓሊው ከሚስላቸው ስእሎች አንዷ
ሰዓሊው ከሚስላቸው ስእሎች አንዷ
ዘማሪ ገብረ አምላክ
ወንጌል ናፋቂው ጊኒር ምዕመን
ወንጌል ናፋቂው ጊኒር ምዕመን
ወንጌል ናፋቂው ጊኒር ምዕመን
ወንጌል ናፋቂው ጊኒር ምዕመን
ወንጌል ናፋቂው ጊኒር ምዕመን
ወንጌል ናፋቂው ጊኒር ምዕመን
ወንጌል ናፋቂው ጊኒር ምዕመን
ወንጌል ናፋቂው ጊኒር ምዕመን
ወንጌል ናፋቂው ጊኒር ምዕመን
ወንጌል ናፋቂው ጊኒር ምዕመን
ትጉሃን ታዳሚዎች
ትጉሃን ታዳሚዎች
ልዑካኑ በከፊል የምንመገብባት ቦታ
ልዑካኑ በከፊል የምንመገብባት ቦታ
ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን
ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን
የጊኒር ከተማ በከፊል
የጊኒር ከተማ በከፊል
ልዑካኑ በከፊል
ልዑካኑ በከፊል
መ/ር ወጋየሁ የሀ/ስብከቱ ስ/ወ/ክ/ሓላፊ
ከተራራው ቁልቁል
ከተራራው ቁልቁል
የጊኒር ከተማ በከፊል
የጊኒር ከተማ በከፊል
ትጉሃኑ የሰንበት ተማሪዎች ሊዘምሩ መጥተው ዘምረው አይሰወሩም ይማራሉ እንጂ
ትጉሃኑ የሰንበት ተማሪዎች ሊዘምሩ መጥተው ዘምረው አይሰወሩም ይማራሉ እንጂ

                                                                                                                                                                                                                                                       

2013 ኖቬምበር 18, ሰኞ

                                                
                                             

በዲ/ን ታደሰ ወርቁ
                                                                                                                                                           Nationalization of <shame >in Ethiopia

November 16, 2013 at 11:48am
On the face of it, Ethiopia Government and we disagree about the political import of shame and humiliation to our beloved country. On the one hand, EPRDF uses the topic of <shame> to understand something else: how the Saudi Arabia mis/understand Ethiopia Economic success. On the other hand, we use the current Ethiopia nationalism to argue that the logic of humiliation itself needs to probe.
The EPRDF’s discourse marks that how national humiliation is used by the regime leaders to mobilize populations, but these populations are on opposite sides of the dispute: we consider nativity understanding of the Ethiopia self, while EPRDF examines a Saudi Arabia othering of western.
The complexity Suggested by this note demonstrates the Multi code nature of the word <shame> .To have shame is both a virtue and a problem along the lines of tension between having humility and humiliation. More to the point, both EPRDF and we agree that understand and humiliation is more complex than a simple political calculation of links between defeat, humiliation and revenge. Humiliation  thus is reframed from an irrational emotion that need to be cured, through (social) psychology ,to a social practice that needs to understood interims of political  and historical narratives .
Indeed, shame politics of EPRDF’S provide an interesting example how the self not only constructs the other as enemy, but how the other constructs the self-complex ways. Yet as #Dr.Tewoderos Adhanom’s ETV interview point out, shame discourse does not dominate Ethiopian images: shame is a product of ‎Saudi Arabia understanding of Ethiopian.
The contemporary Ethiopian nationalism is not just about celebrating the glories of Ethiopian civilization: it also commemorates Ethiopia’s weakness. This negative image comes our most directly in the discourse of Ethiopia’s decade of national humiliation.
To understand how Ethiopian nationalism works, we need to reverse #Paul Kennedy’s famous thesis about <the rise and fall of the great powers> to examine the < fall and rise >of Ethiopia: many of the titles of these books include the phrase <from humiliation to glory.> The discourse of national humiliation shows how Ethiopia’s insecurities are not just material, a matter of catching up to the the west militarily and economically, but symbolic. Indeed, one of the goals of Ethiopia foreign policy has been to  
 The brutal and inhuman crackdown on Ethiopian immigrants in Saudi Arabia context, international politics has been transformed from< conquer or be conquered> in to <humiliate or be humiliated.> Main stream commentators, thus have declared that history is<< strategic issue>>, especially as it informs the dynamic between nationalism and foreign policy.
Ethiopian nationalism is a huge field of inquiry. To gain purchase on this vast topic, it is helpful to take an oblique view of Ethiopian identity through an examination of the specialized field of EPRDF texts.
Finally, humiliation may still see like an odd place to look for nationalism: humiliation is something that you suffer, rather than promote. But as we have seen, in Ethiopia and in china, humiliation is not just about passive National humiliation discourse involves a very active notion of history and recovery.AS the ancient work #Liji tell us;<< the humiliation of a thing is sufficient to stimulate it: the humiliation of a country is sufficient to rejuvenate it.>> for me the day that happened  the brutal and inhuman crackdown on Ethiopian immigrants in Saudi Arabia and Ethiopian police crackdown on anti-Saudi Arabia protest following migrant worker attacks has been ,<official holiday> called National Humiliation Day./? However National humiliation is far from simply being an obscure historical curiosity. In other words, the narrative of national salvation depends upon national humiliation; the narrative of national security depends upon national insecurity. 

2013 ኖቬምበር 17, እሑድ


በደቡብ ጎንደር ሀ/ስብከት በሥራ አስኪያጁ ላይ የተላለፈውን የማሰናበት ውሳኔ የተቃወሙ መላው የጽ/ቤት ሠራተኞች ሥራ አቆሙ፤ ሀ/ስብከቱ ‹‹የመንበረ ጵጵስና ልዩ ጽ/ቤት›› እስከ ማቋቋም በደረሱ ሙሰኞች እና ጠንቋዮች እየታወከ ነው

  • የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት በሥራ አስኪያጁ ላይ የተላለፈውን የስንብት ውሳኔ ውድቅ በማድረግ ወደ ሓላፊነታቸው እንዲመለሱ ለሊቀ ጳጳሱ ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡ ይኹንና ትእዛዙ በሀ/ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ዘንድ ተቀባይነት አግኝቶ ተፈጻሚ ባለመኾኑ የሀ/ስብከቱን ሥራ በማቆም የተወሰደው የመላው ሠራተኛ ርምጃ፣ በአሜሪካ ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ጋራ በሐዋርያዊ ጉብኝት ላይ የሚገኙትን የብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ አቡነ ማቴዎስን መመለስ እየተጠባበቀ ነው፡፡
  • ራሳቸውን ‹‹የሊቀ ጳጳሱ የግል አማካሪ›› ብለው የሠየሙት ሙሰኞቹና ጠንቋዮቹ በሀ/ስብከቱና በሊቀ ጳጳሱ ስም ባስቀረፁት ማኅተምና ቲተር ጽ/ቤቱ የማያውቃቸውን ሕገ ወጥ ደብዳቤዎች ያዘጋጃሉ፡፡
  • ሥራ አስኪያጁ ከሓላፊነታቸው መሰናበታቸው የተገለጸው፣ ሊቀ ጳጳሱን የከበቡት ‹‹የሊቀ ጳጳሱ የግል አማካሪ›› ነን ባዮች በሐሰተኛ ማኅተምና ቲተር ባዘጋጁት ደብዳቤ ነው፡፡
  • በሀ/ስብከቱ በስምንት ዓመት ውስጥ 13 ሥራ አስኪያጆች ከሓላፊነታቸው መሰናበታቸው ሙሰኞች እና ጠንቋዮች በሊቀ ጳጳሱ ዙሪያ እየፈጠሩት ለሚገኙት ከፍተኛ ተጽዕኖ ማሳያ ኾኗል፡፡
Participants of the 32nd SGGA 02
አላግባብ ከሓላፊነታቸው የተሰናበቱት የደቡብ ጎንደር ሀ/ስብከት ሥራ አስኪያጅ አፈ መምህር አባ ገብረ ሥላሴ ጌትነት በመ/ፓ/አጠ/ሰ/መ/ጉባኤ ፴፪ኛው ዓመታዊ ስብሰባ ወቅት በተሳትፎ ላይ
  • ሥራ አስኪያጁ÷ መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ያልኾኑ ድርጅቶችን ድጋፍ በማስተባበር በሚያዘጇቸው የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎች፣ ከሌሎች አህጉረ ስብከት ጋራ በሚካሄዱ የልምድ ልውውጥ መርሐ ግብሮች፣ በወቅታዊ ግምገማዎችና በግምገማዎቹ ላይ በተመሠረቱ የማስተካከያ ርምጃዎች በሀ/ስብከቱና በዐሥራ ሁለቱም የወረዳ ቤተ ክህነት ጽ/ቤቶች የዘለቀ መልካም አስተዳደር በማስፈን፣ የቤተ ክርስቲያንን ይዞታዎች የባለቤትነት መብት በሕግ አግባብ በፍትሕ አካል በማስከበር ሞያዊ ጥረታቸው ሀ/ስብከቱን በመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ‹‹የአህጉረ ስብከት የሥራ ብቃት ዓመታዊ ውድድር›› ላይ ተሸላሚ በማድረግ ይታወቃሉ፡፡
  • በሕግ ዲፕሎማ ያላቸውና ለአንድ ዓመት ከዘጠኝ ወራት በሀ/ስብከቱ በሥራ አስኪያጅነት ሓላፊነት የቆዩት አፈ መምህር አባ ገብረ ሥላሴ ጌትነት፣ የመሬት ይዞታቸውን በሕገ ወጥ መንገድ የተነጠቁ የ12 አብያተ ክርስቲያንን የባለቤትነት መብቶች እንደጠበቃ በተለያዩ ፍ/ቤቶች በራሳቸው እየተሟገቱ አስመልሰዋል፡፡
  • ከእኒህም መካከል÷ በፎገራ ወረዳ መነጉዞር ኢየሱስ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ግንባታ የታቀደበትና በሀገር በቀል ደን የተሸፈነ አራት ሄክታር መሬት፣ በሊቦ ከምከም የዋሻ ተክለ ሃይማኖት አራት ሄክታር መሬት፣ በደብረ ታቦር ፀጉር ኢየሱስ 2.5 ሄ/ር መሬት፣ በፋርጣ ወረዳ የሞክሼ መርቆሬዎስ 2 ሄ/ር መሬት እና በስምና ጊዮርጊስ አንድ ሄክታር መሬት እንዲሁም በደብረ ታቦር እና ላይ ጋይንት ከተሞች ስፋታቸው 7012 ካሬ ሜትር የኾኑ የሕፃናት ማሳደጊያዎች የይዞታ መብቶች መረጋገጥ ይገኙበታል፡፡ የሀ/ስብከቱ የ፳፻፭ ዓ.ም. ዓመታዊ ሪፖርት እንደሚያሳየው 623 አብያተ ክርስቲያን የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡
  • በሥራ አስኪያጁ ላይ የተወሰደውን አላግባብ ከሓላፊነት የማሰናበት ርምጃ በመቃወም የሀ/ስብከቱ ጽ/ቤት ሠራተኞች ከኅዳር ፫ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም አንሥቶ ሥራ በማቆማቸው ሳቢያ ከፍተኛ የባለጉዳዮች መጉላላት እየታየ ነው፡፡ በሥራ እንቅሰቃሴው እና የሠራተኞች ቁጥጥሩ ቀናት ይፈጁ የነበሩ ሥራዎችን በሰዓታት ያሳጠረው ሀ/ስብከቱ በጽ/ቤት ደረጃ የቅሬታ ሰሚ ሠራተኛ በመመደቡ ክፍተት የሚታይባቸው አስተዳደራዊ ውሳኔዎችና አሠራሮች በቅሬታ መልክ በድጋሚ ቀርበው አፋጣኝ መፍትሔ ያገኛሉ፡፡
  • የጽ/ቤቱ ሠራተኞች ራሳቸውን ‹‹የሊቀ ጳጳሱ የግል አማካሪ›› ብለው በሠየሙና ለሥራ አስኪያጁ አላግባብ መታገድ ምክንያት ከኾኑ ግለሰቦች ውስጥ በሦስቱ ላይ ክሥ መሥርተዋል፡፡ ከእነርሱም መካከል በታች ጋይንት እና አዲስ ዘመን ከተሞች ሁለት ጊዜ በሥርዐተ ተክሊል ጋብቻ የፈጸመው የወረታ ወረዳ ቤተ ክህነት ስብከተ ወንጌል ሓላፊ መ/ር ዕንባቆም ዘርዐ ዳዊት ዋነኛው ሲኾን ካህናትንና ሊቃውንትን በመከፋፈልና በማጋጨት፣ የአጥቢያ ሰበካ ጉባኤያትን በጣልቃ ገብነት በመበጥበጥና ከሰንበት ት/ቤቶች ጋራ በማጋጨት በሚገባ ይታወቃል፡፡
  • ሌላው አዋኪ፣ በፎገራ ወረዳ የደራ ቅ/ጊዮርጊስ አስተዳዳሪው መልአከ ሰላም አፈ ወርቅ ወንድማገኝ የሚባሉ ሲኾን በመጋቢት ወር ፳፻፭ ዓ.ም. ጀምሮ በከፍተኛ የገንዘብ ማጭበርበር ተከሠው የታሰሩና ከሓላፊነታቸው የታገዱ ናቸው፡፡ መሪጌታ መፍቀሬ ሰብእ መኰንን እና መሪጌታ ኅሩይ ደመወዝ የተባሉት ግለሰቦች ደግሞ በደራ ወረዳ አንበሳሜ ከተማ እና በንፋስ መውጫ ቅድስት ሥላሴ በጥንቆላ ሥራ የሚተዳደሩ እንደኾኑ ተነግሯል፡፡
  • በሀ/ስብከቱ ሥራ አስኪያ ላይ የተላለፈው የማሰናበት ርምጃ አግባብነት የሌለው መኾኑን በመግለጽ ለሁለት ዓመታት ያህል ወደቆዩበት ሓላፊነታቸው እንዲመለሱ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ያስተላለፈውን ትእዛዝ ባለመቀበል ሁለተኛ የማሰናበት ደብዳቤ የጻፉት የሀ/ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ÷ በአማካሪ ነን ባይ ነገረ ሠሪዎች ላይ እንዲያውቁባቸውና ሀ/ስብከቱን ‹‹መቋጫ ከሌለው መካሠሥና ከፋ ብጥብጥ›› እንዲታደጉት የሀ/ስብከቱ አካላት በመምከር ላይ ናቸው፡
  • ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በአንድ መልእክታቸው፣ ‹‹ሐላፊነት፣ ሐቀኝነትና ተጠያቂነት የተሞላበት መልካም አስተዳደር ከአጥቢያ አብያተ ክርስቲያን እስከ መንበረ ፓትርያርክ ድረስ እንዲሰፍን ማድረግ ተገቢነቱ አያጠያይቅም፡፡ መልካም አስተዳደር ከሌለ ሁሉም ነገር ከንቱ እንደኾነ እናምናለን›› እንዳሉት፣ በሥራ አስኪያጅነት በሚመሩት ሀ/ስብከት የመልካም አስተዳደር አብነት እንደኾኑ የሚነገርላቸው እንደ አፈ መምህር አባ ገብረ ሥላሴ ጌትነት ያሉ ሓላፊዎች በተቋማዊ ለውጥ አመራራቸው ይጎለብቱ ዘንድ ዕድል ሊሰጣቸውና አስፈላጊው ድጋፍ ሊደረግላቸው ይገባል፡፡
  • ሀ/ስብከቱ÷ ባለፈው ዓመት መነሻቸውን አዲስ አበባ ባደረጉና ራሳቸውን ደቂቀ ኤልያስ በሚል ሲቀስጡ የተገኙ ሁለት ዲያቆናት ነን ባይ ግለሰቦችን ለፍትሕ አካል አቅርቦና እስከ ክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ድረስ ተከራክሮ በስድስት ወራት እስራት እንዳስቀጣው ሁሉ በቡድን ተደራጅተው አስተዳደሩንና መንፈሳዊ አገልግሎቱን በሚያውኩት ሙሰኞች እና ጠንቋዮች ላይም የሚወስደውን ርምጃ አጠናክሮ በመቀጠል ከመዋቅሩ ማጽዳት ይጠበቅበታል፡፡
  • የደቡብ ጎንደር ሀ/ስብከት የአራቱ የምስክር ጉባኤ ቤቶች መገኛ እንደመኾኑ መጠን የበርካታ ቋሚ መንፈሳዊ ት/ቤቶችና የአብነት ት/ቤቶች ምንጭ ነው፡፡ በዚህም መሠረት ብዛታቸው 7,167 የኾነ የንባብ፣ የቅዳሴ፣ የቅኔ፣ የዝማሬና መዋስዕት፣ የድጓ፣ አቋቋምና የመጻሕፍት መምህራን እንዲሁም ከ27,928 በላይ ደቀ መዛሙርት እንደሚገኙበት የሀ/ስብከቱ ሪፖርት ያስረዳል፡፡ እኒህን የአብነት መምህራንና ደቀ መዛሙርት ለመደጎም በገቢ ምንጭነት የሚያገለግል ባለአራት ፎቅ ሁለገብ ሕንፃ በደብረ ታቦር ከተማ ለመገንባት ዲዛየኑ አልቆ፣ የመሠረት ደንጊያው ተጥሎ ወደ ግንባታ ሥራው በመግባት ላይ ይገኛል፡፡ የድጓ ምስክር የሚገኝበት የቅድስት ቤተ ልሔም ጉባኤ ቤት እና ሙዝየም በብፁዕ ሊቀ ጳጳ አቡነ እንድርያስ የቅርብ ክትትልና በማኅበረ ቅዱሳን የቅዱሳት መካናት መርጃና ማቋቋሚያ ድጋፍ ለፍጻሜ መብቃቱ ይታወሳል፡፡

                                   በአውሮጳ   የካህናት አንድነት ማኅበር ሊቋቋም መሆኑ ታወቀ በ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከመላዋ አውሮጳ   የተውጣጡ ካህናት፡” የ...