ፈቃደ እግዚአብሔር
ምንድነው? እንዴት ማውቅ ይቻላል ?
ወለተ ማርያም /ከሮቤ ባሌ ጎባ
በ ኢሜል lemabesufekade@gmail.com
የተላከ
ፈቃደ እግዚአብሔርን እንዴት ማወቅ ይቻላል?» የሚለው የሰው ሁሉ ጥያቄ ነው። ብዙዎቻችን መመዘኛችን ሥጋዊ በመሆኑ ፈቃደ እግዚአብሔርን ለማወቅ፥ ለመቀበልም እንቸገራለን። የሚነገረው ሁሉ ለኅሊናችን መልስ ስለማይሆን አጥጋቢ መልስ አላገኘሁም እንላለን። ለምሳሌ፦ ከአይሁድ የተላኩ ካህናትና ሌዋውያን፦ መጥምቀ መለኰት ቅዱስ ዮሐንስን፦ «እንኪያስ አንተ ማነህ? አንተ ኤልያስ ነህን?» ባሉት ጊዜ፦ «አይደለሁም ፤» ብሏቸዋል። ዮሐ ፩፥፳፩። ነቢዩ ኤልያስ በእሳት ሠረገላ ወደ ሰማይ ቢያርግም በስሙ የተነገረ « እነሆ፥ ታላቋና የምታስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ሳትመጣ ቴስብያዊው ኤልያስን እልክላችኋለሁ።» የሚል ትንቢት አለ። ሚል ፬፥፭። ይኽንን ይዘው ነው፥ «ኤልያስ ነህን ?» ያሉት። ዮሐንስ «አዎን ነኝ፤» ማለት ይችል ነበር። ምክንያቱም ጌታችን ፦ «ልትቀበሉትስ ብትወዱ ፥ ይመጣ ዘንድ ያለው ኤልያስ ይህ ነው።» በማለት እንደመሰከረለት በሁሉ ኤልያስን ይመስለዋልና። ማቴ ፲፩፥፲፬። ነቢዩ ኤልያስ፦ ፀጉራም ፥ጸዋሚ ፥ተሐራሚ፥ ዝጉሐዊ፥ ባሕታዊ ፥ ድንግላዊ ነው። ቅዱስ ዮሐንስም ልብሱ የግመል ፀጉር ሆኖ፦ ጸዋሚ ፥ ተሐራሚ ፥ ዝጉሐዊ ፥ባሕታዊ ፥ ድንግላዊ ነው። ይሁን እንጂ «አይደለሁም፤» ያለው፦ «ነኝ፤» የሚለው እውነት ለአይሁድ ለኅሊናቸው መልስ ስለማይሆን ነው። ለእኛም ስለ ፈቃደ እግዚአብሔር የሚነገረው እውነት ሁሉ ለኅሊናችን መልስ አይደለም።
ፈቃደ እግዚአብሔርን ለማወቅ በሕግ በአምልኮ ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ያስፈልጋል። ቅዱስ ዳዊት፦ «ወደ እር ሱ ቅረቡ ፥