- ቅዱስ ሲኖዶስ በሊቢያ በግፍ የተሠው ክርስቲያኖች፣ ሃይማኖታችንን አንክድም በማለት የሃይማኖት ሰማዕትነትን የተቀበሉየሃይማኖት መስተጋድላን መኾናቸውን አረጋገጠ፤ ‹‹የልጆቻችን ሰማዕትነት በእግዚአብሔር መንግሥት ታላቅ ዋጋ ስላላቸው በዚኽ ከሐዘናችኹ እንድትጽናኑ ቤተ ክርስቲያን ታሳስባለች፡፡››
- ነገ ወቅዱስ ፓትርያርኩ እና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ መላው የአዲስ አበባ ገዳማት እና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ሊቃውንት፣ ካህናት የሰንበት ት/ቤቶች ወጣቶች እንዲኹም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያው ሓላፊዎች እና ልዩ ልዩ ሠራተኞች በተገኙበት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ጸሎተ ፍትሐት እና ጸሎተ ወንጌል ይከናወናል
- ሥነ ሥርዐቱ በደቡብ አፍሪቃ በግፍ የተገደሉ ንጹሐን ኢትዮጵያውያንንም ይጨምራል
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ