ቅዳሜ ታኅሳስ 26
2006 ዓ.ም በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ በተዘጋጀው መርሃ ግብር ላይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ
ዘኢትዮጵያ እንደተናገሩት የመስቀል ደመራ በዓል በአለም ቅርስነት በመመዝገቡ እንኩዋን ደስ አለችሁ ካሉ በኋላ በቀጣይም የጥምቀት
በዓል ፤ የቅዱስ ያሬድ ዜማ ፤ ቅኔ፤ እና የ መጻሕፍት ትርጓሜ በአለም
ቅርስነት እነዲመዘገቡ ማስተዋወቅ ና በትጋትና በጥራት መስራት አለብን ብለዋል ቅዱስ ፓትርያርኩ ለዚህ ታላቅ ውጤት ለመብቃት በባሕልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የቅርስና ጥበቃ ባለስልጣናት
ቢሮን ተወካይ፤ የአዲስ አበባን አድባራትና ገዳማትን አመስግነዋል በተዘጋጀው የእንኩን ደስ አላችሁ በዓል ላይ ብፁዐን ሊቃነ ጳጳሳት
የአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች ፤ካህናት ምእመናን ተገኙ ሲሆን የገነተ ጽጌ ቅዱስ ዑራኤል ደብር ሊቃውንት ወረብ
አቅርበዋል፡፡ በተቸማሪም ደብሩ ለተገኙት ተሳታፊዎች የቁርስ መስተንግዶ አቅርቦአል፡፡
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ መሠረት የሚቀርቡ መንፈሳዊ ትምህርቶች ፤መረጃዎች እና የመሳሰሉት የሚስተናገዱበት ገጽ ነው
ቅዳሜ 4 ጃንዋሪ 2014
ዓርብ 3 ጃንዋሪ 2014
የገና ዛፍ የነጮች የባዕድ አምልኮ መገለጫ መሆኑን ያውቃሉ? የገና ዛፍ ታሪክና አመጣጡ
የገናን ዛፍ የት መጣውን /ምንጩን/ ስናጤነው ቅዱሳት መጻሕፍት እንዲህ ይነግሩናል። በዞራስተርን የሁለት አማልክት ዕምነት የሚያምኑት ምዕራባውያን አዲሱን ዓመታቸውን /2014/ ከተቀበሉ ዛሬ ሦስተኛ ቀናቸውን ይዘዋል። በዞራስተርን የሁለት አማልክት ዕምነት መሠረት ክፉውና ደጉ የተባሉ ሁለት አማልክቶች አሉ። እንደ ዕምነቱ አስተሳሰብ ከሆነ እዚህ ምድር ላይ የሆነው እየሆነው ያለውና የሚሆነውም ማንኛውም ነገር በሙሉ የሚከናወነው በእነዚህ በሁለቱ አማልክቶች ፉክክር ነው። ክፉው አምላክ ከሰለጠነ /የበላይ ከሆነ/ በምድር ላይ ክፉ የሆኑ ብዙ ነገሮች ይከሰታሉ። በተቃራኒው ደግሞ ደጉ አምላክ ከሰለጠነ በጎ ነገሮች ይከሰታሉ ማለት ነው። ምዕራባውያኑ ታዲያ ደጉን አምላካቸውን ማለትም ጣዖታቸውን ሳተርን ብለው ይጠሩታል።
በምዕራቡ ዓለም የክረምቱ ወቅት በጣም አስቸጋሪ ነው። ዛፎች ሁሉ ቅጠሎቻቸው ይረግፋሉ። ልምላሜ አይታይባቸውም። ፅድ ግን በተፈጥሮው ይህን አስቸጋሪ ወቅት ተቋቁሞ የማለፍ ኃይል አለው። በመሆኑም ፅድ ክፉውን ዘመን /ክረምቱን/ ተቋቁሞ መልካሙ ዘመናቸው እስኪመጣላቸው ድረስ በልምላሜ ይቆይላቸዋል። ይህም ሳተርን /ደጉ አምላካቸው/ ከክፉው አምላክ ለመሸሸግ በፅድ ውስጥ ተደብቆ ይኖራል ብለው ያመናሉ ምዕራባውያኑ። እናም ብራ ሲሆን /በእኛ መስከረም ጠባ እንደምንለው ነው/ የደጉን አምላክ ‹‹የእንኳን ደህና መጣህ›› በዓልን በድምቀት ያከብራሉ።
ሐሙስ 2 ጃንዋሪ 2014
ኢትዮጵያዊው ብርሃን
አቡነ ተክለ ሃይማኖት በሰሜን ሸዋ ቡልጋ ጽላልሽ ወይም ዞረሬ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የሰበካ ክልል ከአባታቸው ከካህኑ ቅዱስ ጸጋ ዘአብና ከእናታቸው ቅድስት እግዚእ ኃረያ መጋቢት ፳፬ ቀን ተፀንሰው፤ በ፲፩፻፺፯ ዓ.ም ታሕሣሥ ፳፬ቀን ተወለዱ፡፡በተወለዱ በሦስት ቀናቸው ከእናታቸው እቅፍ ወርደው «አሐዱ አብ ቅዱስ፣አሐዱ ወልድ ቅዱስ፣ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ» ብለው ሥላሴን አመስግነዋል፡፡ ወላጆቻቸውም ፍስሐ ጽዮን አሏቸው፡፡ ትርጓሜውም የጽዮን ተድላዋ ወይም ደስታዋ ማለት ነው፡፡ አባታቸውየቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ሲያስተምሯቸው አካባበቢያቸው ደግሞ በዘመኑ የነበሩ ልጆች ይማሩ የነበረውን ፈረስ መጋለብን፣ ቀስት መወርወርን፣ እርሻን እና አደንን አስተምረዋቸዋል፡፡
ደብረሊባኖስገዳም
ረቡዕ 1 ጃንዋሪ 2014
ሊያዩት የሚገባ የቴሌቬዥን መርሐግብር ፡ ታህሳሥ 27 2006 ዓ.ም
- አቡነ ተክለ ሃይማኖት ወይን ተክለው ለ12 ዓመታት በቦታው በመቀመጥ ሲጸልዩበት የነበሩበትና በርካታ ተዓምራትን ያከናወኑበት ቦታ ያዩበታል፡፡
- ጻድቁ አቡነ ህጻኑ ሞአ የተወለዱበትና እንደ በሬ ተጠምደው በማረስ ገድላቸውን የፈጸሙበት ታላቅ ስፍራን ይመለከቱበታል፡፡
- የቦታውን የቀደመ ታሪኩን ያውቁበታል ፤ ዛሬን ያዩበታል ፤ ነገን ያሳስብዎታል፡፡
(አንድ አድርገን ታህሳሥ 23 2006 ዓ.ም)፡- አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከኢትዮጵያውያን
አበው መካከል በእግዚአብሔር ቸርነት ተነሥተው ከሐዋርያ ማዕረግ የደረሱ
የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያንን ተስፋ ያደሱ ታላቅ አባት ሲሆኑ በሃያ ዓመት ዕድሜያቸው ጨለማ የሰለጠነባትን ክፍል ብርሃን እንድትሆን
‹‹አዲስ ሐዋርያ አድርጌ ሾሜሃለሁ›› ሲል ያከበራቸውና ለሾማቸው ‹‹ተክለ ሃይማኖት›› ብሎ ስም ለሠየማቸው ለፈጣሪያቸው ሕይወታቸውን አሳልፈው ከሰጡበት ጊዜ ጀምሮ ያለ ጽልሁት ያለ ሐኬት በርዳታ በማስተማር
በሰማዕትነት ፤ በድንግልና ፤ በምንኩስና ፤ በተባሕትዎና በልዩ ልዩ ተጋድሎ ሰማንያ ዘመን ሃይማኖቸውን ጠብቀው ፤ ፈጣሪያቸውን
አገልግለው ፤ ገድላቸውን ካጠናቀቁ በኋላ በመቶ ዘመን ዕድሜያቸው በደብረ ሊባኖስ ገዳም አርፈዋል፡፡
ረቡዕ 11 ዲሴምበር 2013
“ይቅርታ አድርጉልን ?” :- የቤተ ክህነቱ ተቋማዊ ድቀት ምስክሮች ስልተ ነገር(በጽጌ ማርያም)
December 10, 2013 at 10:16am
በቅርቡ የበጋሻው ደሳለኝ እና የያሬድ አደመ ቀኖናዊ ያልሆነ የ“ይቅርታ አድርጉልን ?”እግረ ጉዞ ለብዙዎች የመነጋገሪያ ጉዳይ ሆኗል፡፡የ“ይቅርታ አድርጉልን ?”ሒደትም
የመጀመሪያ እንጂ የመጨረሻ እንደማይሆንም በራሳቸው “ይቅርታ አድርጉልን ?”በሚሉት እና ከቤተ ክርስቲያን አውጥተው
“እምነ ጽዮን ”የስደተኞች ማኀበር በሚል በፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ መስመርነት በሐዋሳ ከአደራጆት ቡድናቸው ጋር
መከፋፈላቸውም ገላጭ እሆነ ነው፡፡ይህ ቀኖናዊ አግባቦችን አላሟላም የሚባለው የ“ይቅርታ አድርጉልን ?”እግረ ጉዞ ያስከተለው
መለስተኛ ውዝግብ በልጆቹ ብቻ አልተወሰነም፡፡ደዌው ተዛምቶ እውነተኛ የቤተ ክርስቲያን ልጆችንም አምሶ
ነበር፡፡አሁንም ቢሆን ( በመሠረቱ )የጉዳዬን ማዕከላዊ ጭብጥ እና መነሻ አድበስብሶ የሚያልፍ ከመሆን የታደገው
ያገኘ አይመስልም፡፡በ“ይቅርታ አድርጉልን ?”እግረ ጉዞ ላይ የሚነሡትን ክርክሮች ወይም አሳቦች በሁለት ከፍሎ ማየት ይቻላል፡፡አንደኛው በይቅርታ በራሱ ተፈጥሯዊ ምንነትና ትርጉም ላይ ያነጣጠረ ነው፡፡ይቅርታ ምንድ ነው? ውግዘት ምንድ ነው? በቤተ ክርስቲያን ትምህርት፣በቀኖና ድንጋጌዎችና ትውፊትስ ያለው ቦታ ምንድ ነው? የማዉገዝ ምክንያቶች ምንድ ናቸው? መናፍቃን የሚወገዙት እንዴት ነው? እንዴትስ ይመለሳሉ?የሚሉትን ጥቄዎች በመመለስ ላይ የሚሽከረከሩ ናቸው፡፡ይህ ክርክር ዕውቀት ሰጪነቱ እንደተጠበቀ ሆኖ በግልብ ምሁራዊነት(pseudo intellectualism)የተጣበበ መሆኑንም መደበቅ አይቻልም፡፡በዚህም ምክንያት ከስልት አኳያ ዕውቀት ሰጪነቱ ጎጂ ባይሆንም በቀጥታ“ይቅርታ አድርጉልን ?”የሚሉትን ልጆች ወይም የሐዋሳውን አፈንጋጭ ስብስብ በአድራሻ ገላጭ አይደለም፡፡ሁለተኛው በ”ይቅርታ አድርጉልን”ባዬቹ ትእምርታዊ(symbolic) ትርጉም ላይ ያነጣጠረ ነው፡፡ይህ ምልክታ በአብዛኛው ‹ውጫዊ› በተለይም ፖለትካዊ፣ ክልላዊነትና ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ዘውጌነት የሚጫነው ነው፡፡የ”ይቅርታ አድርጉልን”ን ውዝግብ ከጥቅስ እና ከቀኖና ክርክር ለጥጦ በመመልክት አገራዊ እና ምዕመን ዐቀፍ ገጽታ ለመስጠት
ሰኞ 9 ዲሴምበር 2013
የካህናት ሥልጠና ለቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ
ለውጥ ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው ተገለጠ
ምስካበ ቅዱሳን አቡነ ኪሮስ ቤተ ክርስቲያን
ካህናቱ በሥልጠና ላይ |
በሰሜን ሸዋ ሰላሌ ሀገረ ስብከት በሚገኘው በለገጣፎ ምስካበ ቅዱሳን አቡነ
ኪሮስ ቤተ ክርስቲያን የሚገኙ ካህናትና ዲያቆናት ለሁለት ቀናት የቆየ
ሥልጠና ተከታለዋል ፡፡ሥልጠናው መንፈሳዊ አገልግሎትና ትምህርተ ኖሎት ሲሆን የካህናት አገልግሎት መንፈሳዊ ከመሆኑ የተነሳ ሕዝበ ክርስቲያኑን በመንፈሳዊ ሕይወታቸው ከፍተኛ ለውጥ ማምጣት ይችሉ ዘንድ ስልጠናው አስፈላጊ መሆኑን ተጠቁሟል ፡፡ በተለይ ካህናት ከንስሓ ልጆቻቸው ጋር ያለው ግንኙነት እንዴትና በምን መልኩ መሆን እንዳለበትና ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት
መስጠት ይችሉ ዘንድ ትምህርተ ኖሎት መሰልጠን አስፈላጊ መሆኑ ተገልጦአል
ሥለጠናው የተዘጋጀው በደብሩ ስብከተ ወንጌል አስተባባሪነት ሲሆን ሰበካ ጉባኤውም ይሁንታውን መለገሱ ታውቆአል ፡፡ በሥልጠና
ላይ የተሳተፉት ካህናትና ዲያቆናት መምህራንም ሥልጠናው ወደፊትም ቢቀጥል ጥሩ ነው ካሉ በኋላ ሥልጠናው ከደብሩ አስተዳደር /ከላይ
መጀመር እንዳለበት አበክረው ጠቁመዋል የቤተ ክርስቲያን ትልቁ ችግር ከላይ በከፍተኛ አስተዳደር ላይ የተቀመጡ የደብሩም አስተዳደር ስልጠና እንደሚያስፈልገው በአጽንኦት ተናግረዋል አያይዘውም የደብሩን
ስብከተ ወንጌልን እናመሰግናለን ብለዋል ፡፡የደብሩ ስብከተ ወንጌል ወደፊትም ከካህናቱ ጋር በመሆን የንስሓ ልጆቻቸውን ለማስተማር ሁኔታዎችን እያመቻቸ መሆኑም ተገልጦአል ፡፡ ደብሩ እጅግ በጣም
ሰፊ መሬት ያለው ሲሆን ጠንካራ አስተዳደር ህዝብንና ካህናትን ያማከለ ዘመኑን የዋጀ አስተዳደር እንደሚያስፈልግም በተደጋጋሚ ተጠቁሞአል ዘመኑ ዝም ተብሎ የሚተኛበት ዘመን አይደለም ያሉት ካህናቱ ተደጋጋሚ ሥልጠናዎች
ያስፈልጉናል ብለዋል ፡፡ ጻድቁ አቡነ ኪሮስ ልጅ የሌላቸውን ልጅ ያገኙ ዘንድ የሚያስችል ቃልኪዳን የተሰጣቸው መሆኑ የሚታወቅ በመሆናቸው
ብዙ ምእመናን እየተሳሉ /ገድላቸውን በመሸከም በአዓመቱ ልጅ ተሸክመው እቦታው ድረስ ይሄዳሉ በዚህ ምክንያት በጣም ብዙ ሕዝብ የሚጎበኘው ታላቅ ቦታ በመሆኑ የተቀላጠፈ
ጠንካራ አስተዳደር የሰለጠኑ ካህናት ስለሚያስፈልግ ስልጠናው መዘጋጀቱን
የደብሩ ስብከተ ወንጌል ክፍሉ ገልጦአል ወደፊትም ተጠናክሮም ይቀጥላልም ተብሎአል::
የደብሩ ሰባክያነ ወንጌል ሊቀ ጠበብት ገረመው እና መምህር ቀለመወርቅ
ሐሙስ 5 ዲሴምበር 2013
ሰበር ዜና – የመስቀል ደመራ ክብረ በዓል የመጀመሪያው የኢትዮጵያ የዓለም መንፈሳዊ ቅርስ ኾኖ በዩኔስኮ ተመዘገበ
December 5, 2013
1 Comment
(ሪፖርተር፤ ኅዳር ፳፮ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም.)
ኄኖክ ያሬድ
የኢትዮጵያው
የመስቀል ክብረ በዓል በዓለም ቅርስነት መመዝገቡን ዩኔስኮ አስታወቀ፡፡ ዩኔስኮ የመስቀል ክብረ በዓልን
(Commemoration feast of the finding of the True Holy Cross of Christ)
በዓለም ቅርስነት መመዝገቡን ኅዳር 25 ቀን ይፋ ያደረገው፣ በኢንታንጀብል (መንፈሳዊ) ባህላዊ ቅርሶች ጥበቃና ክብካቤ ላይ የሚሠራው ኮሚቴው ስምንተኛውን ጉባኤ እያካሄደባት ካለው የአዘርባጃኗ ባኩ ከተማ ነው፡፡ስለ ቅርሱ የመረመረው ኮሚቴ ባቀረበው ውሳኔ ሐሳብ ላይ እንደተመለከተው፣የመስቀል ክብረ በዓል የኢትዮጵያን ሃይማኖታዊና ባህላዊ ትውፊቶችን የያዘ፣ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ መምጣቱና በአገሪቱ ማኅበራዊ አንድነትንና የርስ በርስ ትስስርን፣ ብዝኃነትንም የሚያንጸባርቅ፣ በበርካታ ብሔረሰቦች ባህሎች መካከል ትስስርን የፈጠረ በመኾኑ ዓለም አቀፍ መስፈርቱን አሟልቷል ብሎታል፡፡
ደንበኛ ይሁኑ ለ፡
ልጥፎች (Atom)
በአውሮጳ የካህናት አንድነት ማኅበር ሊቋቋም መሆኑ ታወቀ በ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከመላዋ አውሮጳ የተውጣጡ ካህናት፡” የ...
-
June 1, 2015 ከሐራ ዘተዋሕዶ በሐዋርያዊት፣ ጥንታዊት እና ብሔራዊት ቤተ ክርስቲያናችን ህልውና እና ዕድገት ፊት ከተጋረጡትና አፋጣኝ እልባት ከ...
-
‹‹…ወንድማችንን እናውቃቸዋለን፤ በእውነቱ ለፌ ወለፌ የማይሉ ደረቅ ሊቅ ናቸው፤ በሃይማኖቱ ዘርፍ ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን፣ ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን አንዲቱም ነጥብ እንዳትዛባ...