የደቡብ ትግራይ ማይጨው እና የደቡብ ምሥራቅ ትግራይ አህጉረ ስብከት ሊቀጳጳስ
ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ ሐምሌ 29 2006 ዓ.ም ከማይጨው ከተማ እና ዙሪያው አድባራትና ገዳማት ለተውጣጡ ከ70 በላይ የሚሆኑ ካህናትን ለ15 ቀናት ያህል ሰልጥነው በተመረቁ ዕለት ሊቀጳጳሱ እንደተናገሩት ዘመኑ የተወሳሰበ ከመሆኑ የተነሳ ዘመኑን የዋጁ በተለያዩ ጊዜያት በሥልጠና የታገዙ ካህናት ያስፈልጋሉ ሲሉ በምርቃቱ ላይ ተናገሩ፡፡ ስልጠናው የተዘጋጀው በነገረ መለኮት
ምሩቃን መንፈሳዊ ማኅበር እና በደቡብ ትግራይ ማይጨው ሀገረ ስብከት ጋር በጋራ በመሆን ነው፡፡ ሥልጠናው ትምህርተ ኖሎት፤ ሥርዓተ
ቤተክርስቲያን፤ የስብከት ዘዴ እና ሌሎችንም ያካተተ መሆኑ ታውቆአል
፡፡ደፊትም በዚሁ ምልኩ ሥልጠናዎች ለካህናቱ እንደሚሰጥ ሊቀጳጳሱ አስታውሰዋል፡፡
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ መሠረት የሚቀርቡ መንፈሳዊ ትምህርቶች ፤መረጃዎች እና የመሳሰሉት የሚስተናገዱበት ገጽ ነው
ማክሰኞ 12 ኦገስት 2014
ሰኞ 11 ኦገስት 2014
ኦ ፍና/ቆፍና ቅዱስ አማኑኤል ቤተክርስቲያን
ከአዲስ አበባ 185 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በመርሐቤቴ
ወረዳ በዓላም ከተማ የሚገኝ በ4ኛው ክፍለ ዘመን በአባ ሰላማ ካሣቴ ብርሃን አማካይነት በአብርሃ ውአጽብሃ
ነገሥታት እንደታነጸ ይነገራል፡፡
ነገሩ እንዲህ ነው በ4ኛው ክ/ዘ ነገስታቱ አብርሃ
ወአጽብሃ ከጳጳሱ አባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን ጋር በመሆን አብያተ ክርስቲናትን በማሳነጽ በማስፋፋት ላይ በነበሩበት ጊዜ በመርሐቤቴ ሲያልፉ አሁን ቤተክርስቲያኑ የታነጸበት ቦታ ጳጳሱ አባ ሰላማ አረፍ አሉ፡ እዚያው እያሉ ጌታችን የተወለደባትን ቤተልሔምን በራእይ
አሳያቸው ከቦታውም ጋር አመሳስሎ ካሳያቸው በኋዋላ ቤተ
ክርስቲን መስራት እንዳለባቸው ተገነዘቡ፡፡ ይህ መንገድ በጣም ድንቅ ነው ሲሉ ኦ ፍና ብለው ጠሩት /ቆፍና ማለት፡ ቆፍ ብሂል
ቅሩበ እግዚአብሔር ማለት ነውና እገዚአብሔር የቀረበው ቦታ ነው ሲሉ
እንዲህ ሰይመውታል፡፡ከዚያ ተነሳ በእውነት እግዚአብሔር ከኛ ጋር
ነው በማለት የቅዱስ አማኑኤል ቤተክርስቲያን እንዲታነጽ ወሰኑ፡፡አማኑኤል
ማለት እገዚአብሔር ከኛ ጋር ነው ማለት ነውና፡፡ይህ ጥንታዊ ቤተ ክርስቲያን እጅግ በጣም የቆዩ ቅርሳቅርስ የሚገኙበት ታርካዊ ጥንታዊ ነው ፡፡ ባሁኑ ሰዓት በቦታው የሚገኙትን ቅርሶች ለጎብኚዎች በሚመች መልኩ ላስቀመጥና ለጉብኝት ዝግጁ ላማድረግ የደብሩ ሰበካ ጉባዔ
ከሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች ጋር በጋራ በመስራት ላይ መሆናቸውን የደብሩ አስተዳዳሪ ሊቀ ትጉሃን ጳውሎስ ገልጸዋል፡፡ ኦ ፍና
ቅዱስ አማኑኤል በአሁኑ ሰዓት ኦ ፍና አምሳለ ቤተልሔም ቅዱስ አማኑኤል ቤተ ክርስቲያን በሚል በብፁዕ አቡነ ኤፍሬም የሀገረ ስብከቱ
ሊቀ ጳጳስ ተሰይሞአል፡፡ ይህ ጥንታዊ ደብር ከርእሰ አድባራት ተድባበ ማርያም ቤተ ክርስቲያን ቀጥሎ መሠራቱ
ይታውቃል፡፡ቦታውን ከፍ አድርጎ ትራራ ላይ ለመሥራት ታስቦ በውቅቱ የነበሩት ምእመናን ከተለያ
ቦታዎች አፈር አምጥተው ስለደለደሉት አራት አይነት አፈር በቦታው ይገኛል፡፡ ደብሩም በግራኝ አህመድ ጊዜ በመቃጠሉ ብዙ ቅርሶች
የወደሙ ሲሆን በየጊዜው የተነሱ ነገሥታት መልሰው አሳንጸውታል፡፡
ምእመናን! ወደ ቦታው በመሄደ እንድትጎበኙ የደብሩ ሰበካ ጉባኤ ጥሪውን
ያስተላልፋል፡፡
ዓርብ 8 ኦገስት 2014
ልጆችም ወላጆችም የሚተባበሩበት የፍልሰታ ለማርያም መታሰቢያ ጾምና በዓል
August 8, 2014
Leave a comment
(አለቃ አያሌው ታምሩ)- በኢትዮጵያ እመቤታችንን መውደድ በልማድ እንደ ተረት በማይታይ ዓይነት ኹኔታ ተስፋፍቶ የኖረ አይደለም፡፡ ወንድም ሴትም ቢኾኑ እንዳላቸው የእምነት መጠን በእመቤታችን ስም ጸሎት ጸልየው፣ ስእለት ተስለው፣ ምጽዋት አድርገው፣ ዝክርዋን ዘክረው፣ ስምዋን ጠርተው፣ በአማላጅነትዋ ተማፅነው ዐሳባቸው እየተፈጸመላቸው፣ የጎደለው እየሞላላቸው፣ የጠመመው እየተቃናላቸው፣ ድውያን ፈውስ በማግኘት፣ ሠራተኞች ለሥራቸው የተቃና መንገድ በማግኘት፣ መምህራን በሚያስተምሩበት፣ ቅዱሳን ገድላቸውን በሚፈጽሙበት ጊዜና ምክንያት ኹሉ የእመቤታችንን ረድኤት እያገኙ ስለሔዱና ዛሬም ያው ያልተቋረጠ ስለኾነ ነው፡፡
- ከቀደሙ ሰዎች ታሪክ ከእስራኤል መሳፍንት አንዱ
ለኾነው የዮፍታሔ ልጅ መታሰቢያ ልጆች ወይም ደናግል በየዓመቱ በዓል ሲያከብሩ እንደነበረ ተነግሯል፡፡ (መጽ.
መሳ.፲፩፥፵፡፡) እንዲህ ከኾነ ዘንድ ኢትዮጵያውያት ቆነጃጅትና ሕፃናት፥ ኢትዮጵያውያን ጎልማሶች የእናታችንን፥
የእመቤታችንን የቅድስት ድንግል ማርያምን መታሰቢያ በየዓመቱ ሲያከብሩ የበለጠ ነገር ፈጽመዋል ማለት ነው፡፡
* * *
- ‹‹ተንሥአ እግዚኦ ውስተ ዕረፍትከ አንተ ወታቦተ መቅደስከ፡፡›› ‹‹አቤቱ ወደ ዕረፍትህ
ተነሥ፤ አንተና የመቅደስህ ታቦት፡፡›› (መዝ.፻፴፩፥፰)
- ‹‹ተንሥኢ ወንዒ ቅርብትየ እንቲአየ ሠናይት ርግብየ ውስተ ጽላሎት ኰኵሕ ቅሩበ
ጥቅም፡፡›› ‹‹አቅራቢያዬ መልካማ ርግቤ ተነሽ ነዪ በግንቡ አጠገብ ወዳለው ወደ ዋሻው
ጥላ፡፡›› (መኃ.፪፥፲-፲፬)
በኢትዮጵያ ከፍ ብሎ የሚታየው በብዛት ልጆች ተሳትፎ የሚያደርጉበት የፍልሰታ ጾምና በዓል ነው፡፡ ፍልሰታ የሚለው ቃል የእመቤታችን ሥጋ ከጌቴሴማኒ ወደ ገነት መፍለሱን፣ ኋላም በገነት በዕፀ ሕይወት ሥር ከነበረበት መነሣቱን ለማመልከት የሚነገር ቃል ነው፡፡
ታሪኩ እንደሚገልጸው፣ እመቤታችን ካረፈች በኋላ ቅዱሳን ሐዋርያት በኀዘን ላይ እንዳሉ ለጊዜው በኢየሩሳሌም ያልተገኘውና በሀገረ ስብከቱ የነበረው ቅዱስ ቆማስ ከሀገረ ስብከቱ ወደ ኢየሩሳሌም ሲመጣ ቅዱሳን መላእክት ሥጋዋን ወደ ገነት ሲያፈልሱ አይቶና ደርሶ ነገሩንም ከመላእክት ተረድቶ ለወንድሞቹ ለሐዋርያት ነግሯቸው ነበር፡፡
ሐዋርያትም ከእመቤታችን በመለያየታቸው እያዘኑ ምስጢሩን ለማወቅ ይጓጉ ስለነበር ጌታ ተገልጾላቸው፤ ‹‹እናቴን አሳያችኋለሁ፤›› የሚል ተስፋ ሰጥቷቸው ነበር፡፡ በዚህ ተስፋ ላይ ሳሉም ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ፣ ‹‹ከነሐሴ ፩ ቀን ጀምረን በጾም እመቤታችንን እንዲያሳየን ፈጣሪያችንን እንጠይቀው፤›› አላቸው፡፡ እነርሱም ዐሳቡን ተቀብለው ከነሐሴ ፩ ቀን ጀምሮ ኹለት ሱባዔ ከጾሙ በኋላ ነሐሴ ፲፮ ቀን ጌታ መላውን ሐዋርያት ወደ ገነት አውጥቶ በገነት በዕፀ ሕይወት ሥር ከነበረው መቃብር እመቤታችንን ነፍስዋን ከሥጋዋ አዋሕዶ አንሥቶ ትንሣኤዋንና ዕርገትዋን አሳይቶ ለዓለም ይህንኑ እንዲያስተምሩ አዘዛቸው ይላል፡፡
መሠረቱ ግን ቀደም ሲል የገለጥነው በመዝሙር ፻፴፩፥፰ ላይ፤ ‹‹አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ፤›› የሚለው ነውና እንግዳ ነገር ሊኾን አይችልም፡፡ በዚኹ መሠረት ኢትዮጵያ ይህን ጽሑፍ ካገኘችበት ጊዜ ጀምሮ፣ ‹‹ለሐሴቦን ንጉሥ ልጅ ኹሉ ክብርዋ ነው፤ በወርቀ ዘቦ ልብስ ተሸልማለች፤ በኋላዋም ለንጉሥ ደናግልን ይወስዳሉ፤ ባልንጀሮችዋንም ይወስዱልኻል፡፡ በአባቶች ፈንታ ልጆች ተወለዱልሽ፤ ወንዶች ልጆችሽን በዕቅፋቸው፥ ሴቶች ልጆችሽንም በትከሻቸው ያመጡልሻል፤›› ተብሎ በተነገረው የነቢያት ቃል መሠረት ልጆችም ወላጆችም በመተባበር የእመቤታችንን የፍልሰታ ጾምና በዓል ሲጠብቁ ይኖራሉ፡፡
ከቀደሙ ሰዎች ታሪክ ከእስራኤል መሳፍንት አንዱ ለኾነው የዮፍታሔ ልጅ መታሰቢያ ልጆች ወይም ደናግል በየዓመቱ በዓል ሲያከብሩ እንደነበረ ተነግሯል፡፡ (መጽ. መሳ.፲፩፥፵፡፡) እንዲህ ከኾነ ዘንድ ኢትዮጵያውያት ቆነጃጅትና ሕፃናት፥ ኢትዮጵያውያን ጎልማሶች የእናታችንን፥ የእመቤታችንን የቅድስት ድንግል ማርያምን መታሰቢያ በየዓመቱ ሲያከብሩ የበለጠ ነገር ፈጽመዋል ማለት ነው፡፡
የጾመ ፍልሰታን መታሰቢያ ለመፈጸም ልጆችም ወላጆችም ይተባበራሉ፤ ጾሙ በፍትሕ ነገሥት በአንቀጽ ፲፭ ከተዘረዘሩት አጽዋም አንዱ ነው፡፡ ጾሙ ከፍቅር ጋራ የሚፈጸም ስለሆነ ልጆችም ወላጆችም የሚጾሙት በጉጉት ነው፡፡ ወላጆችም ከባድ ምክንያት ካላጋጠማቸው በስተቀር ከአልጋው ወርደው፣ ከመሬት ላይ ተኝተው ወይም ከቤታቸው ወጥተው በቤተ እግዚአብሔር ዙሪያ ማረፊያ አሰናድተው ከነሐሴ ፩ – ፲፮ ድረስ ውዳሴ ማርያም፣ ቅዳሴ ማርያም በመስማት፣ በምጽዋት፣ ቅዳሴ በማስቀደስ በከፍተኛ ሥነ ሥርዓት ይጾሙታል፡፡
ልጆችም ረኀብ ሳይሰማቸው፣ ውኃ ጥም ሳያሸንፋቸው ከሰባት ዓመት ዕድሜ ጀምሮ ያሉ ወንዶችና ሴቶች ሕፃናት እየጾሙ ይቆርባሉ፤ በመጨረሻም ነሐሴ ፲፮ ቀን ወላጆች በዓሉን በሥነ ሥርዓት ሲያከብሩ ልጆችም በልዩ ሥነ ሥርዓት ያከብሩታል፡፡
‹‹አሸንዳ›› የሚባል ሣር ዓይነት ቅጠል አለ፤ ኹኔታው ቀጭን ቢኾንም ቁመቱ ረዘም ያለ ኾኖ ቅርፁ ፊላ ዓይነት ነው፤ ሲነቅሉት ሥሩ ነጭ ነው፡፡ ዛጎል ይመስላል፡፡ በልዩ አሠራር ሠርተው በቀሚሳቸው ላይ ይታጠቁታል፤ እንደ ዘርፍ ኾኖ ወደ ታች ይወርዳል፤ በሚጫወቱበት ጊዜ ዙሪያውን ሲነሣ ክንፍ ይመስላል፡፡ በዚኽ ዓይነት ሥርዓት በዓሉን ሲያከብሩ ይውላሉ፤ በተለይ በገጠር ላሉ ሴቶች ሕፃናት ቆነጃጅት ልዩ በዓላቸው ነው፡፡
አሸንዳ ከሚባለው ሣር ዓይነት ቅጠል በልዩ አሠራር ሠርተው የሚታጠቁትና ሲጫወቱ ዙሪያውን የመነሣቱ ኹኔታም መላእክት እመቤታችንን ክንፍ ለክንፍ ገጥመው እያመሰገኑ ማሳረጋቸውን ያሳስባል፡፡ ነቢዩ ኢሳይያስ በትንቢቱ ምዕራፍ ፮ ላይ ባየው ራእይ÷ ሱራፊ መልአክ በኹለት ክንፍ ፊቱን፣ በኹለት ክንፍ እግሩን ሲሸፍን፣ ኹለት ክንፉን በግራ በቀኝ ዘርግቶ ረብቦ ይታያል የሚለውን ያመለክታል፤ በዓሉንም የአሸንድዬ በዓል ይሉታል፡፡ በእውነት፤ ‹‹ደናግልን ለንጉሥ በኋላዋ ይወስዳሉ፤›› ሲል ቅዱስ ዳዊት የተናገረው ቃል ልጆች በእመቤታችን ፍቅር እየተኮተኮቱ አድገው ለእግዚአብሔር ቤተሰብ መኾናቸውን ያሳያል፡፡ በዚህ ሥርዓት ያደጉ ልጆችን እስከ ሕይወታቸው ፍጻሜ ከእመቤታችን ፍቅር የሚለያቸው የለም፡፡
በኢትዮጵያ እመቤታችንን መውደድ በልማድ እንደ ተረት በማይታይ ዓይነት ኹኔታ ተስፋፍቶ የኖረ አይደለም፡፡ ወንድም ሴትም ቢኾኑ እንዳላቸው የእምነት መጠን በእመቤታችን ስም ጸሎት ጸልየው፣ ስእለት ተስለው፣ ምጽዋት አድርገው፣ ዝክርዋን ዘክረው፣ ስምዋን ጠርተው፣ በአማላጅነትዋ ተማፅነው ዐሳባቸው እየተፈጸመላቸው፣ የጎደለው እየሞላላቸው፣ የጠመመው እየተቃናላቸው፣ ድውያን ፈውስ በማግኘት፣ ሠራተኞች ለሥራቸው የተቃና መንገድ በማግኘት፣ መምህራን በሚያስተምሩበት፣ ቅዱሳን ገድላቸውን በሚፈጽሙበት ጊዜና ምክንያት ኹሉ የእመቤታችንን ረድኤት እያገኙ ስለሔዱና ዛሬም ያው ያልተቋረጠ ስለኾነ ነው፡፡
በረድኤት ከሚያገኙት ተስፋ ሌላ በራሳቸውም ኾነ በሌላ ሰው በኩል በራእይ፣ በሕልም፣ በገሃድ እየተገለጸች የምታደርግላቸው ማጽናናት ልባቸውን የፍቅርዋ ምርኮኛ፣ የረድኤትዋ እስረኛ አድርጎት ይኖራል፡፡ ይህም ለአባቶቻችን ብቻ የተደረገ አይደለም፡፡ ስለ እውነት ምስክርነት ሲባል ይህ ለኹላችንም እንኳ የደረሰ ተስፋ መኾኑን ላረጋግጥላችኹ እወዳለኹ፡፡ ስለዚህ ነው ኢትዮጵያውያት ቆነጃጅትና ኢትዮጵያውያን ጎልማሶች ለእመቤታችን በየዓመቱ ከነሐሴ ፩ – ፲፮ ቀን የሚያደርጉትን ጾምና በዓል የበለጠ ያደርገዋል ያልኹት፡፡
በዮሐንስ ራእይ ምዕ. ፲፱ ፥ ፯-፰ ላይ፤ ‹‹የበጉ ሠርግ ደርሷልና ደስ ይበለን፤ ሴቲቱም ተዘጋጅታለች፤ እንድትለብስም ንጹሕ የብርሃን ልብስ ተሰጣት፤ ይኸውም ልብስ የቅዱሳን ክብር ነው፡፡ መጽሐፍ ወደ በጉ ሠርግ የተጠሩ ብፁዓን ናቸው፤ ይህ የእውነት ቃል የእግዚአብሔር ነውና አለኝ፤›› የሚል ተጽፏል፡፡
ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ተሰሎንቄ በላከው መልእክቱ ምዕ. ፬ ፥ ፲፯ ላይ፤ ‹‹ጌታን ለመቀበል በደመና ወደ አየር እንነጠቃለን፤ ከእንግዲህ ወዲህም ከጌታ ጋራ ለዘለዓለም እንኖራለን፤›› በማለት የገለጠው ተስፋ ለቅዱሳን በመታደሉ ዮሐንስ በራእዩ ምዕ.፳ ፥ ፱-፲፪ የገለጠው የሰው ኹሉ ትንሣኤ ከመድረሱ አስቀድሞ ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም የቅድስናን ክብር እንድትጎናጸፍ ልጅዋ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ፈቀደ በእናትነትዋ በመንፈስ ቅዱስ መቀደስን በቅድሚያ እንዳገኘች፤ ዛሬም÷ ኋላም ሞቶ ተነሥቶ በዐዲስ ሕይወት ከጌታ ጋራ መኖርን አግኝታለችና ይህን የሚያምን ልብ ሕያውነትዋን፣ በሕይወት መኖርዋን አምኖ፤ ‹‹በእግዚአብሔር ዘንድ ሞገስ ያገኘሽ እናታችን፣ እመቤታችን ወላዲተ አምላክ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ! ከልጅሽ ለምኚልኝ፤ አማልጂኝ፤ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ መንበር ፊት በምታቀርቢው ጸሎትሽ፣ አማላጅነትሽ አስቢኝ፤›› እያለ ሊጸልይ ይገባዋል፡፡
ምንጭ፡- ወላዲተ አምላክ በኢትዮጵያ፤ ፲፱፻፸፱ ዓ.ም.
እሑድ 3 ኦገስት 2014
አቡነ ጴጥሮስ ሰማዕት
አቡነ ዼጥሮስ ምንም እንኩዋ ለሃገራቸውና ሃይማኖታቸው የከፈሉት ዋጋ ትልቅ ቢሆንም ትውልዱም: መንግስቱም: ራሷ ቤተክርስቲያናችንም ተገቢውን ክብር ሰጥተው እያሰቧቸው አይደለም
ታሪካቸውም ባጭሩ........................
በ1875 ዓ.ም. በሰሜን ሸዋ አገረ ስብከት ሰላሌ አውራጃ ፍቼ ከተማ ተወለዱ። ወላጆቻቸው ዕድሜያቸው ገና በወግ ለትምህርት ሳይደርስ ወደ ደብረ ሊባኖስ ገዳም በመውሰድ ባሕታዊ ተድላ ለተባሉ መምህር አደራ ሰጧቸው። በዚያው ገዳም የንባብ ቤቱንና የዜማውን የትምህርት ደረጃዎች በሚያስገርም ሁኔታ በአጭር ጊዜ አቀላጥፈው በመጨረስ ገና በልጅነት የዕድሜ ደረጃቸው ሦስተኛውን የቅኔ ትምህርት ጀምረው በአጭር ጊዜ ሙሉ ቤት ተቀኙ። ይህንኑ የቅኔ ትምህርት ለማስፋፋት በምዕራብ ጎጃም አገረ ስብከት ወደሚገኘው የቅኔ ትምህርት ማዕከል ዋሸራ ተሻግረው ለመምህርነት የሚያበቃውን ትምህርት ፈጽመው አስመሰከሩ።
ከዚያም ከቅኔው ዐውድማ ጎጃም ወደ ዜማው አዝመራ ጎንደር ተሻገሩ። በዚያም እንደ ቅኔው ሁሉ እስከ ማስመስከር ባይደርሱም የዜማውን ትምህርት በአጥጋቢ ሁኔታ ቀጸሉ። ከጎንደርም በወቅቱ ወሎ ቦሩ ሜዳ ከተባለው ቦታ ላይ ወንበር ዘርግተው የመጻሕፍትን ምሥጢር በየዓይነቱ ሲመግቡ ወደ ነበሩት ስመ ጥሩው መምህር አካለ ወልድ ዘንድ በመሔድ ዋና ዋናዎቹን የመጻሕፍት ትርጓሜ ትምህርቶች ማለትም ብሉያትን፣ ሐዲሳትንና ሊቃውንትን በብቃት አሔዱ።
ከዚህ በኋላ ልክ በ1900 ዓ.ም. እዚያው ወሎ አማራ ሳይንት በተባለው ቦታ ወደሚገኘው ምስካበ ቅዱሳን ገዳም በመሔድ ወንበር ዘረጉ። በዚያው ቦታ ለዘጠኝ ዓመታት ያህል ቅኔንና መጻሕፍትን አስተማሩ።
በዚህ ዓይነት በመማርና በማስተማር ራሳቸውን በእግዚአብሔር ቃል በሚገባ ከጐሰሙ በኋላ በ1909 ዓ.ም. ወደ ደብረ ሊባኖስ ገዳም በመሔድ ሥርዓተ ምንኩስናን ፈጸሙ። ብዙም ሳይቆዩ ማዕረገ ቅስናን ተቀብለው ከወንበሩ አገልግሎት ጋር የቤተ መቅደሱን ተልእኮም ደርበው ያዙ።
በ1910 ዓ.ም. መምህር ኃይለ ማርያም ተብለው በወላይታ ሶዶ በሚገኘው ደብረ መንክራት ምሁር ኢየሱስ ገዳም ተሾሙ። በ1916 ዓ.ም. እንደገና በዝዋይ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም በመምህርነት ተሾሙ። በ1919 ዓ.ም. ወደ አዲስ አበባ በመምጣት የመንበረ መንግሥት ቅዱስ ማርቆስ መምህርና በቤተ መንግሥት የግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ አበ ንስሐ ሆኑ።
የግብፅ ቤተ ክርስቲያን ከአንድ ሺ ስድስት መቶ ዓመታት በኋላ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዕውቀት መንፈሳዊ ከእርሷ ተወልደው በእቅፏ ውስጥ ባደጉ ኢትዮጵያውያን ጳጳሳት እንድትመራ ፈቃዷን ስትገልጽ ከተመረጡት አባቶች አንዱ በመሆን ግንቦት 18 ቀን 1921 ዓ.ም. በእስክንድርያው መንበረ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን ማዕረገ ጵጵስናን ተቀበሉ። ከዓመት በኋላም “አቡነ ጴጥሮስ ጳጳስ ዘምሥራቅ ኢትዮጵያ ተላዌ አሠሩ ለአቡነ ኢየሱስ ሞዓ” ተብለው በያኔው መንዝና ወሎ አገረ ስብከት ተሾሙ።
ሐምሌ 22 ቀን 1928 ስምንት ወታደሮች በስተጀርባቸው ሃያ እርምጃ ርቀው ተንበርክከው በተንጠቀቅ ቆሙ። ወዲያው አዛዡ «ተኩስ» በማለት ትእዛዝ ሲሰጥ ስምንቱም ተኩሰው መቷቸው። ግን በስምንት ጥይት ሳይሞቱ ቀሩ። መሞታቸውንና አለመሞታቸውን ለማረጋገጥ ዶክተር ተጠራ። ዶክተሩም እንዳልሞቱ አረጋገጠ። ከዚያም ሌላ ወታደር በሦስት የሽጉጥ ጥይት ራስ ቅላቸውን መትቶ ገደላቸው።
« እኔ ግን ኢትዮጵየዊ ነኝ፡፡ ሓላፊነትም ያለብኝ የቤተክርስቲያን አባት ነኝ፡፡ ስለዚህ ስለ ሀገሬና ስለ ቤተ ክርስቲያኔ እቆረቆራለሁ፡፡. . . እኔን ለመግደል እንደወሰናችሁ አውቃለሁ፡፡ ስለዚህ በእኔ ላይ የፈለጋችሁትን አድርጉ፡፡ ግን ተከታዮቼን አትንኩ» ሰማዕተ ጽድቅ በሆነ ደማቸው አተሙ፡፡ አኩሪ በሆነ አባታዊ ሓላፊነታቸው ለአገር፣ ለቤተክርስቲያን፣ ለወገን ሁሉ አለኝታነታቸው አረጋግጠው ሐምሌ 22 ቀን 1928 ዓ.ም. በሰማዕትነት አለፉ፡፡
"ብፁዕነታቸው በፍርድ ችሎት ላይ እንዳሉ ሕዝቡ ሁሉ ስለእርሳቸው እያዘነ ሳለ መስቀላቸውን አውጥተው እየጸለዩ ሕዝቡን ባረኩ። ወዲያው የሞታቸው ሰዓት መድረሱን ዐውቀው ሰዓታቸውን ከኪሳቸው አውጥተው ተመለከቱ። በዚህ ጊዜ ሁሉ ምንም ፍርሃት አይታይባቸውም ነበር። የሞታቸውን ፍርድ ያነብ የነበረው ኢጣልያዊ ዳኛ ግን ይንቀጠቀጥ ነበር። ታላቅ ፍርሃትም በፊቱ ይታይ ነበር።"
የኢጣሊያ ፋሺስት በ1928 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ላይ የግፍ ጦርነትን ባነሣ ጊዜ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ከጦር ስፍራ ለመለየት ስላልሆነላቸው፣ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን ተከትለው ወደ ሰሜን ጦር ግንባር ዘምተዋል፡፡ ፋሺስቱ በማይጨው የመርዝ ጦርነት ከማድረጉ የተነሣ፣ የኢትዮጵያ ሠራዊት ሲበታተንም ከንጉሠ ነገሥቱ ጋር የተመለሱት አቡነ ጴጥሮስ ወደ ደብረ ሊባኖስ ሄደው ለአገርና ለነፃነት መሞት ቅዱስ ተግባር መሆኑን ለሥላሴ አርበኞች በመስበክም ይታወቃሉ፡፡
አርበኞች አዲስ አበባን በሁለት አቅጣጫዎች ከሰሜናዊ ምዕራብ እና በደቡባዊ ምሥራቅ አቅጣጫ ለመቆጣጠር ውጊያ በከፈቱበት ጊዜ የተማረኩት አቡነ ጴጥሮስ፣ ለፋሺሽት እንዲገዙ የኢጣሊያ መንግሥት ገዢነትንም አምነው አሜን ብለው እንዲቀበሉ ግፊት ቢያደርጉባቸውም፤ እምቢኝ ለሀገሬና ለሃይማኖቴ ብለው ለሰማዕትነት ያበቃቸውን የሞት ጽዋ ተቀብለዋል፡፡
ቅዱስ ጳውሎስ ደቀ መዝሙሩ የሆነው ጢሞቴዎስን የተሰጠውን አደራ በመጠበቅ ሓላፊነቱንና ግዴታውን መወጣት እንደ ሚገባው ሲገልጽ «እቀብ ማህጸንተከ፤ አደራህን ጠብቅ» በማለት ነው፡፡ 1ኛጢሞ.6 .2፡፡ ጢሞቴዎስ በመምህሩ የተጣለበትን አደራ ለመወጣት የዚህ ዓለም ፈቃድ ሳያሸንፈው ተወጥቷል፡፡ የዓላውያን ነገሥታት ማዋከብ፣ ድብደባ አደራውን እንዳይወጣ አላደረገውም፡፡ የአቡነ ጴጥሮስ የሰማዕትነትም ጉዞ መነሻውም መድረሻውም የእነዚህ አባቶች አርአያ ፍኖት ነው፡፡
ለሀገራቸውና ለወገናቸው እስከ መጨረሻዋ ሰዓት ድረስ እውነቱን ከሐሰት በመለየት ለሕዝባቸው የሰጡት ምስክርነት የተጣለባቸውን አደራ ከመወጣት ነው፡፡ አለቃ ተጠምቀ የተባሉ ቅድስናን ከሊቅነት ጋራ አስተባብረው የያዙ የቅኔ መምህራቸው አንድ ቀን ብፁዕነታቸውን ጠርተው የሚከተለውን የአደራ ቃል ያስተላልፋሉ፡፡ «ኀይለማርያም አንተ ወደፊት ጳጳስ ትሆናለህ፤ በወቅቱም አረመኔ በዚህች ሀገር ይሠለጥናል፡፡ ታዲያ ያኔ አንተ ለነፍስህ ሳትሳቀቅ በሰማዕትነት እለፍ፤ ሰማዕትነት ክፍልህ ነው፡፡ አደራ፡፡» /መርሻ አለኸኝ /ዲያቆን/፣ 1986 ዓ.ም፣ ዜና ጳጳሳት ኢትዮጵያውያን፣ ገጽ.80/
ሐዋርያው ቅዱስ ጢሞቴዎስ የመምህሩን የአደራ ቃል በመያዝ እስከ መጨረሻው እንደጸናው ብፁዕነታቸውም የመምህራቸውን የአደራ ቃል በሰማዕትነት አትመው ጠበቁ፡፡ አንዲትም ቀንና ሰዓት ከሞት ሳይሸሹ እና ሳይደበቁ ለአገራቸው ፣ለቤተ ክርስቲያናቸው እና ለሕዝባቸው ሲሉ ሞትን ተጋፈጡ፡፡ የሰማዕትነትን ጽዋ ተጎነጩ፡፡ የዚህ ምንጩ አደራ ነው፡፡ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ቤተክርስቲያን በአደራ የሰጠቻቸውን ሓላፊነት ለመወጣት ሕዝበ ክርስቲያኑን በጸሎታቸው እየደገፉ፣ በትምህርታቸው እያበረቱ አስተዳድረዋል፡፡
ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ሕዝብ ቀስቅሰዋል፤ ራስዎም አምጸዋል፣ ሌሎችንም እንዲያምጹ አድርገዋል በሚል የወንጀል ክስ ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡ ችሎቱ ተሰይሞ ሲቀርቡ ዳኛው «ካህናቱም ሆኑ የቤተክህነት ባለሥልጣናት ጳጳሱ አቡነ ቄርሎስም የጣሊያንን መንግሥት ገዥነት አምነው አሜን ብለው ሲቀበሉ እርስዎ ለምን ዐመፁ) ለምን ብቻዎን አፈንጋጭ ሆኑ)» ሲል ጠየቃቸው፡፡ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ በቆራጥነት «አቡነ ቄርሎስ ግብጻዊ ናቸው፤ ስለ ኢትዮጵያና ስለ ኢትዮጵያውያን የሚገዳቸው ነገር የለም፡፡ እኔ ግን ኢትዮጵየዊ ነኝ፡፡ ሓላፊነትም ያለብኝ የቤተክርስቲያን አባት ነኝ፡፡ ስለዚህ ስለ ሀገሬና ስለ ቤተ ክርስቲያኔ እቆረቆራለሁ፡፡. . . እኔን ለመግደል እንደወሰናችሁ አውቃለሁ፡፡ ስለዚህ በእኔ ላይ የፈለጋችሁትን አድርጉ፡፡ ግን ተከታዮቼን አትንኩ» በማለት ሕያው በሆነ ቃላቸው መለሱ፡፡ ሰማዕተ ጽድቅ በሆነ ደማቸው አተሙ፡፡ አኩሪ በሆነ አባታዊ ሓላፊነታቸው ለአገር፣ ለቤተክርስቲያን፣ ለወገን ሁሉ አለኝታነታቸው አረጋግጠው በሰማዕትነት አለፉ፡፡ / መርሻ አለኸኝ/ዲያቆን/፣ 1996ዓ.ም፣ዜና ጳጳሳት ኢትዮጵያውያን፣ገጽ.77/
ፋሺስት ጣሊያን የእርሱ አቋም የራሳቸው አቋም፤ የእርሱ የጭቆና አገዛዝ የእርሳቸው አገዛዝ፣ የእርሱ ተራ ፕሮፓጋንዳ የእርሳቸው እውነት አድርገው እንዲቀበሉ መደለያ /ገንዘብ፣ መኪና በዘመኑ ዘመናዊ የሚባል ቤት/ ልስጦት ሳይላቸው ቀርቶ ነውን) ለሕዝባቸው፣ ለሀገራቸውና ለቤተክርስቲያናቸው ሰማዕት የሆኑት) እርሳቸው ግን መንኖ ጥሪትን ገንዘብ ያደረጉ አባት በመሆናቸው ሌሎቹ የቤተ ክህነቱ ባለሥልጣናት ለፋሺስት ጣሊያን ሲያድሩ መደለያው ሳያንበረክካቸው በመንፈሳዊ ወኔ ሰማዕት ሆነዋል፡፡
የፋሺስት ኢጣሊያ ወራሪ ኃይል በሐምሌ 22 ቀን 1928 ዓ.ም. ሰማዕቱን ገድሎ አስክሬናቸው አደባባይ ላይ ጥሎ ከዋለ በኋላ፣ ቀብራቸው በምስጢር መፈጸሙ መዛግብት እንደሚያስረዱ እና የእኚህን ታላቅ አባት ቀብር በምስጢር የተፈጸመበት ቦታ ለማግኘት የተለያዩ ምሁራን በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ ያሉ የታሪክ ሰነዶችን ሲመረምሩ ቢቆዩም፣ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ “ከአዲስ አበባ በስተደቡብ በምስጢር ቀበሯቸው” ከሚል ጠቅላላ ፍንጭ ያለፈ ምንም ዓይነት የተረጋገጠ ማስረጃ ሳይገኝ ቆይቶ ነበር ፡፡
ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን ከአዲስ አበባ ከተማ መስፋፋት ጋር ተያይዞ “ለቡ” ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ የሰፈሩ ምዕመናን በአካባቢው ተወልደው ካደጉ አረጋውያን ጋር ባደረጉት ማኅበራዊ ግንኙነት ሰማዕቱ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ፋሽስቶች በመኖርያነትና በእስር ቤትነት ይጠቀሙበት በነበረው “ሙኒሳ ጉብታ” ላይ መቀበራቸውን ከወላጆቻቸው ሲሰሙ እንዳደጉ በእርግጠኝነት አስረድተዋቸዋል፡፡
በዚህም በፋሺስት ኢጣሊያ ከ76 ዓመት በፊት ሰማዕት የሆኑት አቡነ ጴጥሮስ የተቀበሩበት ቦታ በአዲስ አበባ በስተደቡብ በለቡ አካባቢ መገኘቱን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አረጋግጣለች፡፡

ከሰማዕቱ በረከት ረድኤት ምልጃ አምላክ ያሳትፈን::
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ::

ሐሙስ 24 ጁላይ 2014
ፈቃደ እግዚአብሔርን ለማወቅ ምን ማድረግ ያስፈልጋል?
ባለፈው ጽሁፋችን ፈቃደ እግዚአብሔርን እንዳናውቅ ያደረጉንን ነገሮች ምን ምን እንደሆኑ ለማየት ሞክረናል ከዚህ ቀጥለን
ደግሞ ፈቃደ እግዚአብሔርን ማወቅ እንድንችል ምን ማድረግ እንዳለብን እንመለከታለን፡፡
1.
በሃይማኖት ትምህርት መብሰል
የሰው ልጅ በተፈጥሮ የተሰጠውን የማሰብ የማገናዘብ ፀጋውን በእውቀት የማዳበር የማስፋፋት የማጣጣም ሓላፊነት አለበት ይህ ካልሆነ በሁሉ ነገር ጥሬ ይሆንና በነፍሱ እና በሥጋውም ሲቸገር ይኖራል እንኳዋን ከእግዚአብሔር ጋር ይቅርና
ከሰው ጋርም መኖር ይቸገራል፡፡ በሃይማኖት ትምህርት የበሰለ ሰው ደግሞ እግዚአብሔር የሚወደውን ሁሉ ለመረዳት አቅም ይኖረዋል፡፡ የእግዚአብሔር ፈቃድ እንዴት እንደሚገለጥ መረዳት ይችላል :: ጥበብ ወደ ልብህ
ትገባለችና ዕውቀትም ነፍስህን ደስ ታሰኛለች ምሳ 2፤ 10 የብዙ ሰው ችግር ሆኖ የሚታየው በአብዛኛው የሃይማኖት ትምህርት እውቀት ማጣት ነው ፡፡ እንደሚታወቀው ሕዝበ ክርስቲያኑ መሠረታዊ የሃይማኖት ትምህርትን
እንደ አስኮላው ትምህርት በየአጥቢያቸው መርሃግብር ወጥቶ
መማር እስካሁን አልተለመደም ይሁን እንጂ አሁን ዘመኑ የግድ ይህንን ማድረግ እንደሚገባ ያስገድዳል፡፡ ሁሉም ሰው ስለሃማኖቱ ጠንቅቆ ማውቅ ሲችል ነው እግዚብሔር
የሚወደውን ማውቅና ማሳወቅ የሚችለው ይህ ካልሆነ ግን ወደ ስህተት
መንገድ ተያይዞ መጥፋቱ አይቀሬ ነው፡፡ለዚህ ነው ነቢዩ ፤ ሕዝቤ
እውቀት ከማጣቱ የተነሳ ጠፍቶአልአንተም እውቀትን ጠልተሃልና…. በማለት የተናገረው፡፡ ሆሴ 4፤ 6
ይህ ዘመናችን እጅግ በጣም የተወሳሰበ ከመሆኑ የተነሳ ተአምራት ሚመስሉ ግን ያልሆኑ እውነት የሚመስሉ ሐሰት የሆኑ
በሃይማኖት ትምህርት በስለናል አውቀናል የሚሉትን እንኳን ሳይቀር የማረኩ ነገሮች የሚታዩበት ዘመን ነው እንዲህ ያለውን ዘመን ደግሞ በሃማኖት ትምህርት የበሰለ ሰው ካልሆነ በስተቀር
ሊቋቋመው አይችልም :: ሥር ሰዳችሁ በእርሱ ታነጹ እንደተማራችሁም በሃይማኖት ጽኑ፡፡ ተብሎ እንደተጻፋ ቆላስይስ 2፤7
2.ሊቃውንተ
ቤተ ክርስቲያንን ማማከር
ሌላው እጅግ በጣም ሊተኮርበት የሚገባ ነገር ግን እስካሁን በአብዛኛው ኢየተዘነጋ የመጣው ነገር በቤተ ክርስቲያን የሚታወቁ ሊቃውንትን የማማከር ተግባር ሊተኮርበት ይገባል፡፡ ምክንያቱም ብዙ ጊዜ ምእመናን
መንፈሳዊ ሕይወታቸውን በዘፈቀደ ሲመሩት ይስተዋላል ወደ ተለያዩ ገዳማትም ሲገጓዙ ከጉዞው በፊት ማማከርን መልመድ ያስፈልጋል፡፡ ጻድቁ ኢዮብ ፤ የቀደመውን ትውልድ ጠይቅ አባቶቻቸውም ለመረመሩት ነገር ትጋ ፡፡ ኢዮ 8፤8 በማለት የተናገረው
ለዚሁ ነው፡፡ አባትህን ጠይቅ ያስታውቅህማል ሽማግሌዎችን ጠይቅ ይነግሩህማል ዘዳ 32፤7
አንድ በሓላፊነት ላይ ያለ ሰው የሚሰራው ስራ ውጤታማ እንዲሆን የግድ አማካሪ እንደሚያስፈልገው ሁሉ በመንፈሳዊ ሕይወቱም
ውጤታማ ሊሆን የሚፈልግ ሰውም አማካሪ ያስፈልገዋል፡፡ ነገር ግን ከፉ ምክርም እንዳለ መጠንቀቅ እንደሚገባ መዘንጋት የለበትም እውነተኞቹ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ብዙ ጊዜ በየ ካፍቴርያውና በመሳሉት ቦታም ስለማይገኙ
ምእመናን መቀላሉ ስለማያገኗቸው ለክፉ መካሪዎች እንዳይጋለጡ መጠንቀቅ
ያስፈልጋል ፡፡
3.ከኃጢአት
መንጻት
ኃጢአት ሰው መልካም ሆነውን ነገር ተግባራዊ እንዳያደርግ የሚያደርግ የሰው
ልጆች የመንፈሳዊ ሕይወት ማነቆ ነው፡፡ የሚጠጋውም ርኩስ መንፈስ ብቻ ነው ከዚህ የተነሳ መንፈሳዊ ነገር ማሰብም ሆነ መሥራት አይችልም
፡፡መልካም ባታደርግ
ግን ኃጢአት በደጅ ታደባለች ፈቃድዋም ወደ አንተ ነው፡ ዘፍ 4፤7 / ሰው በኃጢአት
በኖረ ቁጥር መልካም አስተሳሰቡ ቀናነቱ ሌሎችም መንፈሳዊ ተግባራትና ሐሳብ እየመነመኑ ይሄዳሉ ብሎም ይጠፋሉ ለዚህ ሁሉ መነሻው
ኃጢአት ነው፡፡የኃጢአተኛ መብራት ይጠፋል፡ የእሳቱም ነበልባል ብልጭ
አይልም፡ኢዮ 18፤5 / ተብሎ እንደተጻፈው ፡፡ ስለዚህ ሰው ከኃጢአት ሳይነጻ ፈቃደ እግዚብሔርን ማውቅ መረዳት አይችልም፡፡
እግዚአብሔር በሰው በጎ ሥራ ከተደሰተ ለሰው ሁሉ የሚያስፈልገውን የሚያውቅ አምላክ ነውና በጊዜውና በሰዓቱ ሁሉንም ያከናውናል፡፡ እግዚአብሔር የሚያደርገው ሁሉ በጎ ነውና፡፡
“መላእክት ሁሉ ረቂቃን አይደሉምን የዘላለም ሕይወትን ይወርሱ ዘንድ ላላቸው ለአገልግሎት ይላኩ የለምን” ዕብ.1፡14
ደንበኛ ይሁኑ ለ፡
ልጥፎች (Atom)
በአውሮጳ የካህናት አንድነት ማኅበር ሊቋቋም መሆኑ ታወቀ በ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከመላዋ አውሮጳ የተውጣጡ ካህናት፡” የ...
-
June 1, 2015 ከሐራ ዘተዋሕዶ በሐዋርያዊት፣ ጥንታዊት እና ብሔራዊት ቤተ ክርስቲያናችን ህልውና እና ዕድገት ፊት ከተጋረጡትና አፋጣኝ እልባት ከ...
-
‹‹…ወንድማችንን እናውቃቸዋለን፤ በእውነቱ ለፌ ወለፌ የማይሉ ደረቅ ሊቅ ናቸው፤ በሃይማኖቱ ዘርፍ ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን፣ ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን አንዲቱም ነጥብ እንዳትዛባ...