“ይቅርታ አድርጉልን ?” :- የቤተ ክህነቱ ተቋማዊ ድቀት ምስክሮች ስልተ ነገር(በጽጌ ማርያም)
December 10, 2013 at 10:16am
በቅርቡ የበጋሻው ደሳለኝ እና የያሬድ አደመ ቀኖናዊ ያልሆነ የ
“ይቅርታ አድርጉልን ?”እግረ ጉዞ ለብዙዎች የመነጋገሪያ ጉዳይ ሆኗል፡፡የ
“ይቅርታ አድርጉልን ?”ሒደትም
የመጀመሪያ እንጂ የመጨረሻ እንደማይሆንም በራሳቸው “ይቅርታ አድርጉልን ?”በሚሉት እና ከቤተ ክርስቲያን አውጥተው
“እምነ ጽዮን ”የስደተኞች ማኀበር በሚል በፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ መስመርነት በሐዋሳ ከአደራጆት ቡድናቸው ጋር
መከፋፈላቸውም ገላጭ እሆነ ነው፡፡ይህ ቀኖናዊ አግባቦችን አላሟላም የሚባለው የ
“ይቅርታ አድርጉልን ?”እግረ ጉዞ
ያስከተለው
መለስተኛ ውዝግብ በልጆቹ ብቻ አልተወሰነም፡፡ደዌው ተዛምቶ እውነተኛ የቤተ ክርስቲያን ልጆችንም አምሶ
ነበር፡፡አሁንም ቢሆን ( በመሠረቱ )የጉዳዬን ማዕከላዊ ጭብጥ እና መነሻ አድበስብሶ የሚያልፍ ከመሆን የታደገው
ያገኘ አይመስልም፡፡
በ
“ይቅርታ አድርጉልን ?”እግረ ጉዞ ላይ የሚነሡትን
ክርክሮች ወይም አሳቦች በሁለት ከፍሎ ማየት ይቻላል፡፡አንደኛው በይቅርታ በራሱ ተፈጥሯዊ ምንነትና ትርጉም ላይ
ያነጣጠረ ነው፡፡ይቅርታ ምንድ ነው? ውግዘት ምንድ ነው? በቤተ ክርስቲያን ትምህርት፣በቀኖና ድንጋጌዎችና ትውፊትስ
ያለው ቦታ ምንድ ነው? የማዉገዝ ምክንያቶች ምንድ ናቸው? መናፍቃን የሚወገዙት እንዴት ነው? እንዴትስ
ይመለሳሉ?የሚሉትን ጥቄዎች በመመለስ ላይ የሚሽከረከሩ ናቸው፡፡ይህ ክርክር ዕውቀት ሰጪነቱ እንደተጠበቀ ሆኖ በግልብ
ምሁራዊነት(pseudo intellectualism)የተጣበበ መሆኑንም መደበቅ አይቻልም፡፡በዚህም ምክንያት ከስልት
አኳያ ዕውቀት ሰጪነቱ ጎጂ ባይሆንም በቀጥታ“ይቅርታ አድርጉልን ?”የሚሉትን ልጆች ወይም የሐዋሳውን አፈንጋጭ
ስብስብ በአድራሻ ገላጭ አይደለም፡፡ሁለተኛው በ”ይቅርታ አድርጉልን”ባዬቹ ትእምርታዊ(symbolic) ትርጉም ላይ
ያነጣጠረ ነው፡፡ይህ ምልክታ በአብዛኛው ‹ውጫዊ› በተለይም ፖለትካዊ፣ ክልላዊነትና ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ዘውጌነት
የሚጫነው ነው፡፡የ”ይቅርታ አድርጉልን”ን ውዝግብ ከጥቅስ እና ከቀኖና ክርክር ለጥጦ በመመልክት አገራዊ እና ምዕመን
ዐቀፍ ገጽታ ለመስጠት