በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ መሠረት የሚቀርቡ መንፈሳዊ ትምህርቶች ፤መረጃዎች እና የመሳሰሉት የሚስተናገዱበት ገጽ ነው
ማክሰኞ 10 ጁን 2014
ሰኞ 9 ጁን 2014
ቅዳሜ 31 ሜይ 2014
‹‹የዓመቱ በጎ ሰው›› የመጨረሻዎቹ ዕጩዎች
የ2006 ዓም ‹‹የዓመቱ
በጎ ሰው›› ሽልማት በሰባት ዘርፎች የመጨረሻዎቹ ዕጩዎች ታውቀዋል፡፡ በልዩ ልዩ ዘርፎች ዕውቀትና ተሞክሮ ያላቸው፣
በሞያው ለረዥም ዘመን ያገለገሉ ምሁራን፣ ጋዜጠኞች፣ ታዋቂ ሰዎች፣ ደራስያን፣ የዜማ ሰዎች፣ ሳይንቲስቶች፣ የባሕል ባለሞያዎች፣
የሚገኙበት 21 ዳኞች የመጨረሻዎቹን ሰባት ተሸላሚዎች ለመለየት ድምፅ እየሰጡ ነው፡፡ ዳኞቹ እርስ በርሳቸው የማይተዋወቁ ሲሆን
በዘርፋቸው የራሳቸውን ድምፅ ብቻ ይሰጣሉ፡፡ የመጨረሻዎቹ ዕጩዎች የሚታወቁት በሚቀጥለው ሳምንት ውስጥ ነው፡፡
ቅዳሜ 24 ሜይ 2014
የአቶ ዓለማየሁ አቶምሳ ፹ ቀን የቅ/ሲኖዶስ አባላት በተገኙበት ይዘከራል
***
- የቀድሞው የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዝዳንት አቶ ዓለማየሁ አቶምሳ ወስመ ጥምቀቱ ገብረ እግዚአብሔር የ፹ ቀን መታሰቢያ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት በዛሬው ዕለት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይከናወናል፡፡
- በፀረ ሙስና አቋማቸው የሚታወቁት አቶ ዓለማየሁ አቶምሳ ወስመ ጥምቀቱ ገብረ እግዚአብሔር፣ በአንዳንድ የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች እንደተናፈሰው፣ የፕሮቴስታንት ቤተ እምነት ተከታይ አልነበሩም፡፡
- በኦሮሚያ ፀረ ሙስና ኮሚሽን የሕግ ባለሞያና በምዕራብ ወለጋ ሀ/ስብከት ግምቢ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ቤት አባልና የአገልግሎቱ ፍሬ የኾኑት ባለቤታቸው ወ/ሮ ፀሐይ በንቲ እንዲሁም ቤተሰዎቻቸው ብፁዕ አቡነ ኄኖክ ኖላዊ ኄር ኾነው የሚመክሯቸው፣ በቅዱሳን ወዳጅነታቸውና በጽኑ ኦርቶዶክሳዊ ሥነ ምግባራቸው የሚታወቁ ናቸው፡፡
- የዐደባባይ ሰዎችንና የፖሊቲካ ባለሥልጣናትን ፕሮቴስታንታዊ በማድረግና ፕሮቴስታንታዊ ናቸው በሚል ፕሮቴስታንታዊነት ማስፋፋት፣ በኵላዊቷ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ላይ በፈጠራ ታሪክ የሚገፋ ጎሳዊ ጥላቻን በማጠናከር ሀገራዊ አንድነትን ለአደጋ ለማጋለጥ አድርባይ ፖሊቲከኞችና ጎጠኞች በስፋት የተያያዙት የብተና ፕሮጀክት ነው፡፡
- ከነፍስ ኄር አቶ ዓለማየሁ የፖሊቲካ አቋም ጋራ ፍቅር ባይኖረንም በዚህ መንፈስ በሐዋርያዊቷ ቤተ ክርስቲያናችን ላይ የሚሰነዘረውን የአድርባዮችና ጎጠኞች ሤራና ስልት ማጋለጥ ግን ኦርቶዶክሳዊነታችን ግድ ይለናል፡፡
- በሐራዊ ምንጮች እንደተረጋገጠው፣ ነፍስ ኄር አቶ ዓለማየሁ አቶምሳ በሓላፊነት በሠሩባቸው አካባቢዎች ኹሉ በአጥቢያቸው በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ሰበካ ጉባኤያት በአባልነት ተመዝግበው አስተዋፅኦ በማድረግ የምእመንነት ግዴታቸውን የተወጡ ኦርቶዶክሳዊ ነበሩ፡፡
- በአዲስ አበባ የመካኒሳ ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ አባል የነበሩት የቅዱሳን ወዳጅ አቶ ዓለማየሁ፣ በስፋት ከሚነገረው መመረዝ ጋራ በተያያዘ በታመሙበት ወቅት በጥያቄአቸው መሠረት የደብረ ሊባኖስ ገዳም አበው መነኰሳት በመኖርያ ቤታቸው እየተገኙ ጸሎት ያደርጉላቸው፣ ጠበልም ያጠምቋቸው ነበር፡፡
- ሥርዓተ ቀብራቸው በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል መከናወኑ መንግሥታዊ የቀብር ሥርዓትን ለማሳመር ሳይሆን በሃይማኖታቸው ኦርቶዶክሳዊ የቤተ ክርስቲያን ልጅ ስለኾኑ ነው!!
ሐሙስ 22 ሜይ 2014
ግንቦት 12 ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
>+"+ እንኩዋን ለዓለም ሁሉ መምሕር ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅና ለኢትዮዽያውያኑ ቅዱሳን ተክለ ሃይማኖት ወክርስቶስ ሠምራ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ +"+
=>ለቤተ ክርስቲያን የብርሃን ምሰሶ ስለሆነላት ስለ ታላቁ ሐዋርያዊ ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ምን እላለሁ? ምንስ እናገራለሁ? እንደ እኔ ያለ ኃጥእ: ለባሴ ሥጋና ገባሬ ንስሃ ስለሱ ሊናገር አይቻለውምና:: አባቶቻችን እንደ ነገሩን ስለ አፈ ወርቅ ለመናገር አፈ ወርቅ መሆን ያስፈልጋል:: እስኪ በቅዱሱ አባት ምልጃ ጥቂት ልሞክር::
+ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ማን ነው?
=>ነገዱ ከሶርያ: የተወለደው በ347 ዓ/ም በእስክንድርያ ሲሆን አባቱ አስፋኒዶስ እናቱ ደግሞ አትናስያ ይባላሉ:: እነርሱ ደግ ቢሆኑ ይህንን እንቁ ልጅ እግዚአብሔር ሰጣቸው:: ዮሐንስ ለክርስቲያን እንደሚገባ በትምሕርትና በጥበብ አደገ:: ገና በሕጻንነቱ ወደ ግሪክ ሔዶ የዘመኑን ሳይንስ (ፍልስፍና) ከአፉ እስከ ገደፉ ተምሮ ተመልሷል::
=>ለቤተ ክርስቲያን የብርሃን ምሰሶ ስለሆነላት ስለ ታላቁ ሐዋርያዊ ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ምን እላለሁ? ምንስ እናገራለሁ? እንደ እኔ ያለ ኃጥእ: ለባሴ ሥጋና ገባሬ ንስሃ ስለሱ ሊናገር አይቻለውምና:: አባቶቻችን እንደ ነገሩን ስለ አፈ ወርቅ ለመናገር አፈ ወርቅ መሆን ያስፈልጋል:: እስኪ በቅዱሱ አባት ምልጃ ጥቂት ልሞክር::
+ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ማን ነው?
=>ነገዱ ከሶርያ: የተወለደው በ347 ዓ/ም በእስክንድርያ ሲሆን አባቱ አስፋኒዶስ እናቱ ደግሞ አትናስያ ይባላሉ:: እነርሱ ደግ ቢሆኑ ይህንን እንቁ ልጅ እግዚአብሔር ሰጣቸው:: ዮሐንስ ለክርስቲያን እንደሚገባ በትምሕርትና በጥበብ አደገ:: ገና በሕጻንነቱ ወደ ግሪክ ሔዶ የዘመኑን ሳይንስ (ፍልስፍና) ከአፉ እስከ ገደፉ ተምሮ ተመልሷል::
ሰኞ 19 ሜይ 2014
ግንቦት 11 ቅዱስ ያሬድ ካህን
በ ዲ.ዮርዳኖስ አበበ
"+ እንኩዋን ለታላቁ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ ዓመታዊ የዕረፍት (የመሰወር) በዓል በሰላም አደረሳችሁ +"+
=>ቅዱስ ያሬድ:- ከእግዚአብሔር ያገኘነው አባታችን: ክብራችን: ሞገሳችን ነውና በምን እንመስለዋለን? አንደበቱ ጣፋጭ (ጥዑም): ልቡናው የቅድስና ማሕደር: ሕሊናው የምሥጢራት ሠረገላ ነው:: እስከ አርያም ተነጥቆ የማይፈጸም ምሥጢርን የተመገበ ማን እንደርሱ!
+ሊቀ ሊቃውንት እዝራ ሐዲስ እንደሚሉት:- "ቅዱስ ያሬድ ለኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከራስ ጸጉሯ እስከ እግር ጥፍሯ: ሙሉ አካሏ ነው"
=>የሊቁ ዜና ሕይወት በጥቂቱ:-
+ቅዱስ ያሬድ የተወለደው በ505 ዓ/ም አክሱም አካባቢ ሲሆን እናቱ ክርስቲና (ታኡክልያ) አባቱ ደግሞ ይስሐቅ (አብድዩ) ይባላሉ:: ሊቁ በሕጻንነቱ ምሥጢር (ትምሕርት) አልገባው ብሎ ይቸገር ነበር:: ትምሕርት እንቢ ያለው ሰነፍ ስለ ነበር አይደለም:: በጥበበ እግዚአብሔር እንጂ::
-ምን ትምሕርት ባይገባው ጾምና ጸሎትን ያዘወትር ነበር:: ልቡናው ደግሞ በእመቤታችንና በልጇ ፍቅር የታሠረ ነበር:: አንድ ቀን ግን መምሕሩ የነገሩት ቀለም አልያዝሕ አለው:: ሲፈትኑትም ባለመመለሱ ተገረፈ:: ዱላው በጣም ስለተሰማው ቅዱሱ ከመምሕሩ ኮብልሎ ማይ ኪራሕ አካባቢ ሲደርስ ደክሞት አርፎ እግዚአብሔር ትጋትንና ተስፋ አለመቁረጥን ከትል አስተማረው:: ትሏ 6 ጊዜ ወድቃ በ7ኛው ፍሬዋን ስትበላት ተመልክቷልና:: ከዚህ በሁዋላ ቅዱስ ያሬድ ወደ መምሕሩ ተመልሶ: ይቅርታ ጠይቆ ትምሕርት ጀመረ::
-ሊቁም ትጋትንና ጸሎትን ከሰጊድ ጋር አበዛ:: እግዚአብሔር ደግሞ በድንግል እናቱ አማካኝነት የምሥጢር ጽዋን አጠጣው:: ካህኑ ያሬድ እንዲያ አልገባህ ያለው ምስጢር ተገልጦለት በጥቂት ጊዜ ብሉይ ከሐዲስ ወሰነ::በምሥጢር ባሕርም ይዋኝ ጀመር::
-ያን ጊዜ ሰማያዊ ዜማ አልተገለጠም ነበርና በጸሎት ላይ ሳለ ተደሞ መጣበት:: 3 መላእክት በወፎች አምሳል መጥተው አነጋገሩት:: ድንገትም ነጥቀው ወደ ሰማያት: ወደ ልዑላኑ መላእክት ዘንድ አደረሱት:: ሊቁ በሰማያት ልዩ ምሥጢር: ልዩ ምስጋናና ልዩ ዜማን አዳመጠ:: ይሕንን ምስጋና ብዙ ቅዱሳን ቢሰሙትም ቅዱስ ያሬድ ግን ይዞት እንዲወርድ ተፈቀደለት::
-ሊቁ ወደ ምድር ተመልሶ በታላቅ ተመስጦ አክሱም ጽዮን ውስጥ በሃሌታ አመሰገነ:: ሕዝቡና ንጉሡም ከጣዕሙ የተነሳ አደነቁ:: ቅዱስ ያሬድ ለተወሰነ ጊዜ በአክሱምና ደብረ ዳሞ ሲያገለግል ቆይቶ: ከመሬት ክንድ ከስንዝር ከፍ ብሎ ለእመቤታችን አንቀጸ ብርሃንን ደርሶላት ከሃገሩ ወጣ::
-ቅዱስ ያሬድ በቀሪ የሕይወቱ ዘመናት:-
1."5" ያሕል መጻሕፍትን ጽፏል
2.በጣና ቂርቆስ: በዙር አባና በሌሎችም ቦታዎች ወንበር ዘርግቶ ብዙ ደቀ መዛሙርትን አፍርቷል
3.በሰሜን ተራሮች አካባቢ በትጋሃ መላእክትና በተባሕትዎ ኑሯል
-በ576 ዓ/ም በተወለደ በ71 ዓመቱ በዚህች ቀን ተሰውሯል::
-አባቶቻችን:-
-ጥዑመ ልሳን
-ንሕብ
-ሊቀ ሊቃውንት
-የሱራፌል አምሳያ
-የቤተ ክርስቲያን እንዚራ
-ካህነ ስብሐት
-መዘምር ዘበድርሳን
-ማኅሌታይ
-ልዑለ ስብከት
እያሉ ይጠሩታል::
=>የቅዱሱ ጸሎትና በረከት ሃገራችንን ከክፉው ሁሉ ይጠብቅልን::
=>ግንቦት 11 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ያሬድ ካህን ወማኅሌታይ
2.አቡነ ሐራ ድንግል ጻድቅ
3.ክርስቲናና ይስሐቅ (የቅዱስ ያሬድ ወላጆች)
4.ቅድስት ታውክልያ እናታችን (ንግሥናን ንቃ ሰማዕት የሆነች)
5.ቅድስት ኤፎምያ ሰማዕት
6.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት
7.ቅድስት አናሲማ ገዳማዊት
8.አባ በፍኑትዮስ ገዳማዊ
9.አባ አሴር ሰማዕት (ኢትዮዽያዊ)
10.አባ በኪሞስ ጻድቅ
=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ገላውዴዎስ ሰማዕት
2.ቅዱስ ፋሲለደስ ሰማዕት
3.ብፁዐን ኢያቄም እና ሐና
=>+"+ እንዲህ ያለው ሰው ከአሥራ አራት ዓመት በፊት እስከ ሦስተኛው ሰማይ ድረስ ተነጠቀ:: እንዲህ ያለውንም ሰው አውቃለሁ:: በሥጋ እንደ ሆነ ወይም ያለ ሥጋ እንደሆነ አላውቅም:: እግዚአብሔር ያውቃል:: ወደ ገነት ተነጠቀ:: ሰውም ሊናገር የማይገባውን: የማይነገረውን ቃል ሰማ:: +"+ (2ቆሮ. 12:2-5)
<ወስብሐት ለእግዚአብሔር>
ዓርብ 16 ሜይ 2014
ምንኩስና
(ክፍል አንድ) በዲያቆን ኤርምያስ ነቢዩ
መነኮሰ ማለት ከዓለም የራቀ፤ መናኝ ማለት ሲሆን
የተጀመረውም የአዳም ሰባተኛ ትውልድ በሆነ በሔኖክ ነው። ይኸውም
ይታወቅ ዘንድ የሔኖክ አባት ያሬድ ውሉደ እግዚአብሔር የተባሉት የሴት ልጆች በሰይጣን ወጥመድ ተይዘው፤
ከእግዚአብሔር ፈቃድ ወጥተው
ከደብር ቅዱ ሲወርዱ እንደ ተነሱ በሰማ ጊዜ አስጠርቶ እንዲህ ያለውን ክፉ ሥራ እንዳይሰሩ ተቆጥቷቸው እንደ ነበር
የቤተ ክርስቲያን
መጻሕፍት ይነግሩናል። እናንተ የሴት ልጆች፤ ወዮላችሁ፤ ተው፤ የአባታችሁን
መሃላ አታፍርሱ። የ እግዚአብሔርን ት ዕዛዝ የተወ፤ ያባቱን መሐላ
ያፈረሰ፤ ከደብር ቅዱስ የወረደ፤ ከአዋልደ ቃየን ጋርም ኃጢአት የሠራ ተመልሶ ወደ ደብር ቅዱስ አይገባም ብሎ
መክሯቸው ነበር። እነርሱ ግን ምክሩን አቃልለው ከደብር ቅዱስ ወርደው ከቃየን ልጆች ጋር ዝሙት
እየፈጸሙ ይዘፍኑ ይሳለቁ ጀመር።
ሔኖክ በዚህ እያዘነ ከኖረ በኋላ ከተወለደ ጀምሮ
ሦስት መቶ ስድሳ አምስት ዓመት ሲሆነው ከዓለም ተለይቶ በጾም ጸሎት ጸንቶ ወደ አንጻረ ገነት ሄዶ በግብረ ምንኩስና ኖሯል። በዚያም ለስድስት ዓመታት ከተጋደለ በኋላ በፈቃደ እግዚአብሔር ወደ ብሔረ
ሕያዋን አርጓል። ዘፍ 5፤24 ዕብ 11፤5። ኤልያስም ሔኖክን አብነት አድርጎ በጾም በትኅርምትና በድንግልና ከኖረ በኋላ
በሠረገላ እሳት ወደ ሰማይ አርጓል። 2ኛ ነገ 2፤11 በዚህም መዓስባንና ደናግላን በሥር ዓተ ምንኩስና ጸንተው ንጹሐን የመንፈስ
ቅዱስ አርጋብ ሆነው ወደ መንግሥተ ሰማይ ማረጋቸው ከሔኖክና ከኤልያስ ምሳሌነት እንረዳለን። ሔኖክና ኤልያስ መነኮስ ማለት ከዓለም
የራቀ በመሆኑ ከዓለም ርቀው የሰሩት የብቸኝነት ሥራቸው መነኮሳት ያሰኛቸዋል።
በተጨማሪም የእግዚአብሔር አገልጋይ (ካህን) ሆኖ
ጠጉሩን ሳይላጭ ፤ ጥፍሩን ሳይቆረጥ፤ ጠጅ ሳይጠጣ፤ በስንዴና በወይን እያስታኮተ የኖረው ርዕሰ ባህታዊ መልከ ጼዴቅም ለመነኮሳት
አብነታቸው ነው። ዘፍ 14፤ 8-23 ዕብ 7፤1-5። ለመዓስባን ሥርዓተ
ምንኩስናን የጀመረላቸው ሔኖክ ለደናግላን ደግሞ ኤልያስ ነው። ይኸውም
ለአዲስ ኪዳን ምንኩስና መሰረት ነው ማለታችን ነው። ጌታችን ሐዋርያትንና
አርድዕትን የመረጠው ከመዓስባንም ከደናግላንም ነው። ለሁሉም እክል
ሥልጣን በመስጠትም ተካክለው መንግሥተ ሰማያትን እንዲወርሱ አድርጓል።
ዮሐንስ መጥምቅም ሔኖክንና ኤልያስን አብነት በማድረግ በገዳም ተወስኖ የግመል ጸጉር ለብሶ፤ ወገቡን በጠፍር መታጠቂያ
ታጥቆ፤ የማርና የወይን ጠጅ ሳይጠጣ በግብረ ምንኩስና ጸንቶ ኖሯል።
ማቴ 3፤4 ሉቃ 1፤15
መናፍቃን እንደሚሉት
ምንኩስና “ሰው ሰራሽ ጽድቅ” ሳይሆን የ እግዚአብሔር ሰዎች ገንዘብ ያደረጉት
የ እግዚአብሔር ጸጋ ነው። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
ቤቱን፤ ወንድሙንና እህቱን፤ አባቱንና እናቱን፤ ሚስቱንና ልጆቹን እርሻውንም ሁሉ ትቶ በስሜ አምኖ የተከተለኝ መቶ እጥፍ ይቀበላል።
የዘለዓለም ድኅነትም ያገኛል ብሎ ስለ መ ዓረገ ምንኩስና ደገኛነት የተናገረውን ቃል በመዝለል “ምንኩስና ከአምላክ ሕግ የተለየ
ከንቱ ሰው ሰራሽ ጽድቅ ነው እያሉ መሣለቅ ከወንጌል ጎዳና መውጣትን ያመለክታል። ማቴ 19፤29
ቀጥሎም በሉቃስ ወንጌል “አንድ ሰው አቤቱ ልከተልህ
እወዳለሁ” ነገር ግን አስቀድሜ የቤቴን ሰዎች እሠራ ዘንድ ፍቀድልኝ ቢለው፦ “ማንም በእጅ ዕርፍን ይዞ እያረሰ ወደ ኋላው የሚመለከት
ለ እግዚአብሔር መንግስት የተዘጋጀ አይደለም” ብሎ የመለሰለት ቃል የምንኩስናን ሥር ዓት ለመሥራት መሆኑ የሚታበል አይደለም። ሉቃ
9፤28
የሰው ሃብቱ ልዩ ልዩ ስለሆነ የተቻለው በድንግልና
መንኩሶ እንደ ኤልያስ እግዚአብሔርን ያገለግላል። ያልተቻለው ደግሞ
እንደ ሔኖክ ቤት ሠርቶ ሚስት አግብቶ ሕጻናትን ወልዶ ቀጥቶ አሳድጎ በዚህ ዓለም ከኖረ በኋላ ይመነኩሳል። ይህም ሐዋርያትን አብነት አድርጎ ቤቱን፤ ንብረቱን፤ ሚስቱንና ልጆቹን ትቶ
የምናኔን ሥራ ይሠራል ማለት ነው። በዚህ ዓለም እየኖሩ እግዚአብሄርን
ከምንም በላይ ደስ ያሰኙ ሰዎች አሉ። ነገር ግን ልብ ሳይከፈል በመላ
ኃይል እግዚአብሄርን ለማገልገል ምንኩስና መልካም ነው። ቅዱስ ጳውሎስ
“እኔ ኃዘን እንድትኖሩ እወዳለሁ፤ ሚስት ያላገባ ሰው በሚያስደስተው
ገንዘብ እግዚአብንሔርን ያስበዋልና። ሚስት ያገባ ግን ሚስቱን በሚያስደስታት
ገንዘብ የዚህን ዓለም ንብረት ያስባል። እንዲህ ከሆነ ደግሞ የ እግዚአብሔርና የሰው ፈቃድ ይለያያል። ያለው ለዚህ ነው።
1ኛ ቆሮ 7፤32-34
ከዚህ በላይ ስለ ምንኩስና መዘርዘራችን የ እግዚአብሔር
ጸጋ መሆኑን ለማመልከት እንጂ ጥንት አዳምና ሔዋን ወንድና ሴት ሆነው መፈጠራቸውን ፤ በሐዲስ ኪዳንም ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ “ወንድ አባቱንና እናቱንትቶ ከሚስቱ ጋር ይከተላል፤ ባልና
ሚስት አንድ አካል ይሆናሉ። እንዲህም ከሆነ አንድ አካል እንጂ ሁለት
አካል አይባሉም። እግዚአብሄር አንድ ያደረጋቸውን ሰው አይለያቸውም። ከዚህስ አስቀድሞ በኦሪት የተጻፈውን አልተመለከታችሁምን?” ብሎ ማስተማሩን
በመዘንጋት አይደለም። ዘፍ 3፤24 ማቴ 19፤4-6
ይቆየን...........
ደንበኛ ይሁኑ ለ፡
ልጥፎች (Atom)
በአውሮጳ የካህናት አንድነት ማኅበር ሊቋቋም መሆኑ ታወቀ በ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከመላዋ አውሮጳ የተውጣጡ ካህናት፡” የ...
-
June 1, 2015 ከሐራ ዘተዋሕዶ በሐዋርያዊት፣ ጥንታዊት እና ብሔራዊት ቤተ ክርስቲያናችን ህልውና እና ዕድገት ፊት ከተጋረጡትና አፋጣኝ እልባት ከ...
-
‹‹…ወንድማችንን እናውቃቸዋለን፤ በእውነቱ ለፌ ወለፌ የማይሉ ደረቅ ሊቅ ናቸው፤ በሃይማኖቱ ዘርፍ ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን፣ ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን አንዲቱም ነጥብ እንዳትዛባ...